ዜና: በአፍዴራ በአውሎ ንፋስ ምክንያት 26,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ፤ የጎርፍ አደጋ ስጋት ተፈጥሯል
በአፋር ክልል ሰሜን ዞን አፍዴራ ወረዳ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተውን አውሎ ነፋስ ተከትሎ 26,000 የሚጠጉ ሰዎች ሲፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለ ምግብ፣ መጠለያ እና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ መቅረታቸውንና ከ2,500 በላይ ቤቶች መውደማቸውን ኬር ኢትዮጵያ አስታወቀ።
በደናክል ዝቅተኛ ስፍራ የምትገኘው አፍዴራ ከተማ በመሠረተ ልማቶቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን፤ በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉም ተመላክቷል። ኬር ኢትዮጵያ አደጋው የአየር ንብረት ለውጥ እንዴት ራቅ ያሉና ተጋላጭ የሆኑ ማኅበረሰቦችን ተመጣጣኝ ባልሆነ መንገድ እየጎዳ እንዳለ አመላካች ነው ብሏል።
የስድስት ልጆች እናት የሆነችውና ቤቷ በአደጋው የወደመባት አሲያ ማሙዳ፣ “የምንበላው ምንም ነገር የለም፤ የምንተኛበትም ቦታ የለም” ስትል ስለ ሁኔታው አስረድታለች።
በዩኤስኤድ የሚደገፈው የረሀብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሲስተምስ ኔትዎርክ (FEWS NET) በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሠረት በአየር ሁኔታ መዛባት፣ በክረምት ዝናብ መቋረጥ እና ከግጭት ጋር በተያያዙ ችግሮች ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ ከባድ የምግብ ዋስትና እጦት አሁንም በስፋት ተንሰራፍቶ ይገኛል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8757

Addis standard
በአፍዴራ በአውሎ ንፋስ ምክንያት 26,000 ሰዎች ተፈናቅለዋል ተባለ፤ የጎርፍ አደጋ ስጋት ተፈጥሯል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30/ 2017 ዓ/ም፦ በአፋር ክልል ሰሜን ዞን አፍዴራ ወረዳ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም የተከሰተውን አውሎ ነፋስ ተከትሎ 26,000 የሚጠጉ ሰዎች ሲፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ያለ ምግብ፣ መጠለያ እና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ መቅረታቸውንና ከ2,500 በላይ ቤቶች መውደማቸውን ኬር ኢትዮጵያ አስታወቀ። በደናክል ዝቅተኛ ስፍራ የምትገኘው አፍዴራ ከተማ በመሠረተ ልማቶቿ ላይ ከፍተኛ ጉዳት…
ከ #ናይሮቢ - #አዲስ_አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ መባሉ "ከእውቅናው ውጭ" መሆኑን ሚኒስቴሩ ገለፀ
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፤ "ከናይሮቢ - አዲስ አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት ተጀመረ" በሚል የተሰራጨው ዘገባ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ "እውቅና ውጪ ነው" ሲል ገለፀ።
'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን በትናንትናው ዕለት ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ሚካኤል ገለጻ አቢሲኒያ ሌግዠሪ በየቀኑ ወደ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ መካከል የሕዝብ ማመላለስ ሥራዎችን ይሠራል።
ይሁን እንጂ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው ዓጭር መግለጫ፤ ቢቢሲ አማርኛ በድረገጹ "አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታወቀ" ሲል ዘግቦ ይህንን መረጃ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህጋዊነቱን ሳያረጋግጡ ሌሎችም ሚዲያዎች አሰራጭተዋል ብሏል።
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02Qj7LQn6VTi2SXDU2tJ7dAu4PumdFLeJfxbohfaBAuh1VPXFnou2LEuVsYanyjLtUl

ዜና፡ በቆላ ተንቤን ድርቅ ከ20 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ፤ ክስተቱ በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ መባባስ አመላካች ነው ተብሏል
ማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተንቤን ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የ22 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ27,000 በላይ እንስሳት መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
የሞት መጠኑ ከፍ ማለቱ በክልሉ እየተፈጠረ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ አመላካች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የሚደረገው እርዳታ አነስተኛ መሆኑ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል።
የያቄር ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጎይቶም ገብረሃዋርያ፤ "ሰዎች እየሞቱ ነው፣ አስቸኳይ ድጋፍ ካልተሰጠን ምንም ማድረግ አንችልም" ሲሉ ስለ ሁኔታው ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል። አክለውም ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ አስከፊ እየሆነ በመምጣቱ ሰዎች ምግብና ውሃ እያለቀባቸው መጥቷል ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደ ሲሆን በክልሉ እየተከሰተ ስላለው ቀውስ ተወያይቶ የአስቸኳይ እርዳታ አስፈላጊነት ላይ ተስማምቷል።
ይሁን እንጂ የአካባቢው ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው አካላት ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን ምንም አይነት አስቸኳይ እርዳታ ወደ ቆላ ተንቤን እንዳልደረሰ ተናግረዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8764

በቆላ ተንቤን ድርቅ ከ20 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ፤ ክስተቱ በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ መባባስ አመላካች ነው ተብሏል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 1/ 2017 ዓ/ም፦ በማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተንቤን ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት የ22 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ27,000 በላይ እንስሳት መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። የሞት መጠኑ ከፍ ማለቱ በክልሉ እየተፈጠረ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ አመላካች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የሚደረገው እርዳታ አነስተኛ መሆኑ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል። የያቄር ቀበሌ አስተዳዳሪ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የባንክ ስርዓትን የማይጠቀሙ የንግድ ማህበረሰብ አካላት ላይ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ከድርጊታቸው ካልታቀቡ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።
አቶ ማሞ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እንቅስቃሴን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፤ የባንክ ስርዓትን የማይጠቀሙ የንግድ ማህበረሰብ አካላት በአፋጣኝ በባንክ ስርዓት እንዲገለገሉ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ተማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።
በተለይ በቅርብ ቀናት በ #ዱባይ ከገበያ ሁኔታ ያፈነገጠ የትይዩ ገበያውን የሚያስፋፉ ህገወጥ ድርጊቶች እንዳሉ መረዳቱን ገልጾ የገለጸው ባንኩ፤ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።

የ #ቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል በከፍተኛ ውሽንፍር አዘል ዝናብ ሳቢያ ተጎዳ
ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በዘነበው ውሽንፍር አዘል ዝናብ ሳቢያ በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሥር የሚገኘው የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።
ኢንስቲትዩቱ በዛሬው እለት እንደገለጸው፤ በደረሰው ጉዳት በተለይም በእንስሳትና በሰብል ምርምር ፕሮግራሞች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት ደርሷል።
ለሙከራ እየተደረጉ የነበሩ የምርምር ሥራዎች ሙሉ በሙሉ እንደተበላሹም ገልጿል።
ከንብረት ውድመት በተጨማሪም ህንጻዎች የፈረሱ ሲሆን፣ ትልልቅ ዛፎች ተነቅለው በምርምርና በቢሮ ሕንፃዎች ላይ በመውደቅ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና፡ "ህዳሴ ግድቡ ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ እክል ለመፍጠር እየተሯሯጠች ነው"_ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ
"ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ እክል ለመፍጠር እየተሯሯጠች ነው" ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ ተናገሩ። "የሚቀየር ነገር የለም፤ ያለቀ እና የሞተ ጉዳይ ተደርጎ ነው መወሰድ ያለበት" ብለዋል።
በተጨማሪም ኢ/ር አሸብር ባልቻ የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ በበጀት አመቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሀገር ውስጥ [93 በመቶ] እና ለውጪ [7 በመቶ] ካቀረበው የኃይል ሽያጭ 75.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።
"የሀገር ውስጥ ፍላጎት ተሟልቶ ነው ወይ ሀይል ለውጭ ሀገራት እንዲቀርብ የተደረገው" በሚል አዲስ ስታንዳርድ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ላነሳው ጥያቄ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አንዷለም ሲአ (ኢ/ር) "የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሳናሟላ የተሸጠ የለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ለማህበረሰቡ ተደራሽ በሆኑ እና መሬት ላይ ባሉ የሀይል ማስተላለፊያዎች ሁሉ አቅርቦት መኖሩን የገለጹት ኢንጂነር አንዷለም፤ ነገር ግን የሀይል ፍላጎት የለም ማለት አይደለም የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ባልተዘረጋባቸው አከባቢዎች የሀይል አቅርቦት እጥረት አለ ብለዋል።
ሙሉውን ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8768

"ህዳሴ ግድቡ ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ እክል ለመፍጠር እየተሯሯጠች ነው"_ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1/ 2017 ዓ/ም፦ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ይመረቃል መባሉን ተከትሎ ግብፅ እክል ለመፍጠር እየተሯሯጠች ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ ተናገሩ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2018 ዓ.ም እቅድን አስመልክቶ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢ/ር አሸብር ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2017 ዓ.ም…
ሰባት #ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በረሃብና በውሃ ጥም በባህር ላይ መሞታቸው ተገለጸ
ከ #ሶማሊያ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞች መካከል ሰባት ኢትዮጵያውያን በረሃብና በውሃ ጥም መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
ድርጅቱ፤ 82 ህጻናትን ጨምሮ 250 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ፣ ማክሰኞ ዕለት ደቡብ የመን በሚገኘው አርቃህ አካባቢ ደርሳለች ብሏል። ይሁን እንጂ “ሰባት ስደተኞች በመንገድ ላይ በረሃብና በጥም ሞተዋል” ሲል አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅቱ ትናንት ረዕብ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በየመን የሚገኙ ቡድኖቹ “ከቦሳሶ ሶማሊያ በመነሳት ከሰባት ቀናት አስከፊ ጉዞ የተረፉ ሰዎችን ህይወት አድን እርዳታ” ማድረጋቸውን ገልጿል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
ከፈረንጆቹ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ በምስራቁ መስመር ከ350 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን እና ያሉበት አለመገኘቱን ገልጿል።
ከዚህ አደጋ ቀደም ብሎ እሁድ እለት 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ሰጥማ 68 ሰዎች ህይወት አልፏል። 74 የሚሆኑት ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል። ======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ከ #ሶማሊያ ወደ #የመን በመጓዝ ላይ ከነበሩ ስደተኞች መካከል ሰባት ኢትዮጵያውያን በረሃብና በውሃ ጥም መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታወቀ።
ድርጅቱ፤ 82 ህጻናትን ጨምሮ 250 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነችው ጀልባ፣ ማክሰኞ ዕለት ደቡብ የመን በሚገኘው አርቃህ አካባቢ ደርሳለች ብሏል። ይሁን እንጂ “ሰባት ስደተኞች በመንገድ ላይ በረሃብና በጥም ሞተዋል” ሲል አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅቱ ትናንት ረዕብ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ በየመን የሚገኙ ቡድኖቹ “ከቦሳሶ ሶማሊያ በመነሳት ከሰባት ቀናት አስከፊ ጉዞ የተረፉ ሰዎችን ህይወት አድን እርዳታ” ማድረጋቸውን ገልጿል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።
ከፈረንጆቹ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ በምስራቁ መስመር ከ350 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን እና ያሉበት አለመገኘቱን ገልጿል።
ከዚህ አደጋ ቀደም ብሎ እሁድ እለት 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ሰጥማ 68 ሰዎች ህይወት አልፏል። 74 የሚሆኑት ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል። ======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: #አዲስ_አበባ በዓለም ላይ “ከፍተኛ” የአየር ብክለት ካለባቸው ከተሞች ውስጥ አንዷ ናት ተባለ
በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የአየር ብክለት መጠን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የስዊዘርላንድ የአየር ጥራት ተቋም የሆነው አይኪውኤይር (IQAir) አስታወቀ።
ድርጅቱ በተያዘው ሳምንት ባወጣው ሪፖርት፤ ሐምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. በተደረገ ምዘና በዓለም ላይ ከፍተኛ የአየር ብክለት ካለባቸው ከተሞች መካካል 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ገልጿል።
የከተማዋ የአየር ሁኔታ የዓለም ጤና ድርጅት ካስቀመጠው ገደብ በከፍተኛ ደረጃ ማለፉን የገለጸው ሪፖርቱ፤ “ጤናማ ያልሆነ” በሚል ምድብ ውስጥ መካተቷን አመላክቷል።
በዕለቱ በተደረገው ምዘና፣ የአዲስ አበባ የአየር ጥራት መረጃ ጠቋሚ (AQI) 147 ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም በተለይ እንደ የመተንፈሻ አካላት ችግር ወይም የልብ ህመም ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የጤና ስጋት መሆኑ ተጠቁሟል።
ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ ጭስ፣ በባዮማስ ማቃጠል፣ ከግንባታ እና ከጠጠር መንገዶች የሚነሳ አቧራ እንዲሁም ቆሻሻን ማቃጠል የከተማዋ የአየር ብክለት ዋነኛ መንሰኤዎች ናቸው ተብሏል።
በሪፖርቱ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መዲና ኪንሻሳ በአየር ብክለት እስከ ዛሬ ባለው ሪፖርት ቀዳሚውን ደረጃ የያዘች ሲሆን አዲስ አበባ በዛሬው ዕለት ከ 4ኛ ደረጃ ወደ 26 ዝቅ ብላለች።
======================

ዜና: የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ #ጋዛን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የቀረበውን ዕቅድ አፀደቀ
የእስራኤል የደህንነት ካቢኔ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የቀረበውን እና የጋዛ ከተማን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ዕቅድ አፀደቀ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ “የእስራኤል መከላከያ የጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር በዝግጅት ላይ ነው። በተመሳሳይ ከውጊያ ቀጠና ውጪ ለሚገኙ ሰላማዊ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ይሰጣል” ብሏል።
ሁለት የእስራኤል መንግሥት ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በሀገሪቱ የደህንነት ካቢኔ የተላለፈ ማንኛውም ውሳኔ በሀገሪቱ የመንግሥት ካቢኔ መጽደቅ ይኖርበታል፤ ስብሰባው እስከ ፊታችን እሁድ ድረስ ላይደረግ ይችላል ተብሏል።
የጋዛ ከተማን መያዝ እስራኤል በፍልስጤም ግዛት ላይ እያካሄደች ያለችውን ጦርነት በእጅጉ ያባብሳል የተባለ ሲሆን፤ እስራኤል ሰብዓዊ እርዳታ ወደ አከባቢው እንዳይገባ ማገዷን በቀጠለችበት ሁኔታ በረሃብ የሚሰቃዩና የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዲፈናቀሉ ያስገድዳል።
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር በበኩላቸው እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርገውን ከበባ ለማጠናከር ያላትን እቅድ “ስህተት ነው” ሲሉ ኮንነዋል።
አክለውም “ይህ እቅድ ግጭቱን ለማስቆም ወይም ታጋቾችን ለማስለቀቅ አያግዝም፤ ይልቁኑ ብዙ ደም መፋሰስ ብቻ ነው የሚያስከትለው” ብለዋል።
የሀገሪቱ የደህንነት ካቢኔ ዛሬ ካካሄደው ስብሰባ ቀደም ብሎ ትናንት ሐሙስ የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል “የጋዛ ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሯ ስር ታደርጋለች” ብለው ነበረ።
https://www.facebook.com/share/1F6CJRcoBf/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ዋሺንግተን ዲ.ሲ ከአንዳንድ የ #ኢትዮጵያ አካባቢዎች የበለጠ ወንጀል የተበረከተባት ከተማ ናት_ የፕሬዚዳንት ትራምፕ አማካሪ ስቴፈን ሚለር
የፕሬዚዳንት ትራምፕ አማካሪ ስቴፈን ሚለር የ #አሜሪካ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲን የወንጀል ደረጃ ከባህዳግ እና ከአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የከፋ መሆኑን ገለፁ።
ትናንት ሃሙስ ከኒውስኔሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት ስቴፈን፤ ዋሺንግተን ዲሲ ያለው “ወንጀል ከባግዳድ የከፋ ነው፣ ከአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ከዓለም አደገኛ ስፍራዎች የከፋ ነው” ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ከተማዋ “ለሁሉም አሜሪካውያን ደህንነቷ የተጠበቀ መሆኗን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋሉ” ሲሉ ገልጸዋል።

ዜና: ገዥው ፓርቲ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስ ሴራ ሸርበዋል ሲል ከሰሰ
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስና የተቀናጀ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ከሰሰ። ገዢው ፓርቲ እነዚህ ኃይሎች ሀገሪቱ የጀመረችውን የሰላምና የብልጽግና ጎዳና ለማደናቀፍ “የመጨረሻ ሙከራ” እያደረጉ ነው ብሏል።
ፖርቲው ይህን ያለው ከሐምሌ 30 ቀን እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ያካሄደን መደበኛ ስብሰባ ማጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው።
“ከጥቂት ዓመታት በፊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የገጠመንን ጦርነት በአሸናፊነት ተወጥተናል” ያለው መግለጫው፤ “ወታደራዊ ድላችንን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቋጭተናል። ዳሩ ግን ይፈልጉት የነበረው የተራዘመ ጦርነት በስምምነቱ የተጨናገፈባቸው ጠላቶቻችን ሌሎች ስልቶችን ወደ መሞከር ገብተዋል” ብሏል። በመሆኑም “ሁከት በመቀስቀስና መንግስትን በማዳከም” ላይ ያተኮሩ አማራጭ ስልቶችን መጠቀም ጀምረዋል ሲል መግለጫው ከሷል።
እነዚሁ አካላት “ኢትዮጵያን ከመንገዷ ለማስቀረት የመጨረሻውን ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛሉ” ያለው የፓርቲው መግለጫ፤ በዚህ የመጨረሻ ሙከራቸው “ስድስት ስልቶችን” እንደሚጠቀሙ በግምገማ መረጋገጡን ጠቁሟል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8770

ገዥው ፓርቲ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስ ሴራ ተሸርቧል ነው ሲል ከሰሰ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2/ 2017 ዓ/ም፦ ገዢው ብልጽግና ፓርቲ “ታሪካዊ ጠላቶች” እና “የውስጥ ባንዳዎች” ሲል የጠራቸው አካላት ኢትዮጵያን ለማተራመስ አዲስና የተቀናጀ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲል ከሰሰ። ገዢው ፓርቲ እነዚህ ኃይሎች ሀገሪቱ የጀመረችውን የሰላምና የብልጽግና ጎዳና ለማደናቀፍ “የመጨረሻ ሙከራ” እያደረጉ ነው ብሏል። ፖርቲው ይህን ያለው ከሐምሌ 30 ቀን እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2017 ዓ.ም…
ርዕሰ አንቀፅ፡ ወጣቶች ከኢትዮጵያ ለመውጣት እየሞቱ ነው፤ የማስመሰል ብልጽግናን ለማቆም እና እውነታውን ለመጋፈጥ ጊዜው አሁን ነው!
ባሳለፍነው እሁድ ሐምሌ 27 ቀን፤ 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ሌላኛዋ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ሰምጣለች። ቢያንስ 68 ሰዎች (አብዛኞቹ ወጣቶች የሆኑ) መከላከል በሚቻል አሳዛኝ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። ህይወታቸውን ያጡት ዜጎች ሲሹ የነበሩት ሀብትን ሳይሆን መፃዒ ተስፋን ነበር። ይህ ጽሑፍ እስከታተመበት ድረስ አደጋው የደረሰባቸው 78 ሰዎች አልተገኙም።
ከሊቢያ የግድያ ቦታዎች አንስቶ በሻርክ እስከተሞሉት የየመን ባህር ድረስ፣ ገንዘብ ከሚቀሙትና የሰውነት አካላትን ከሚያወጡ ከህገወጥ አዘዋዋሪዎች አንስቶ የሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች በጅምላ ተኩስ እስከሚከፍቱበት ድንበር ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ወጣቶች እየሞቱ ይገኛሉ። ወጣቶቹ ሀገራቸውን ለቀው የሚሰደዱት ሀሴት ፈላጊዎች ስለሆኑ አይደለም፤ በርካታ ሀብት የማካበት ፍላጎት ስላላቸውም አይደለም፤ ነገር ግን ሌላ አማራጭ ስላልታያቸው ነው።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ድንበርን ያለጥበቃ ያቋርጣሉ፣ በአዘዋዋሪዎች እጅም ይወድቃሉ። እናም ለስቃይ፣ ለፆታዊ ጥቃት፣ ለግዳጅ ስራ ወይም ለሞት ይዳረጋሉ። ወደ ሀገራቸው የመመለስ እድል የገጠማቸው ጥቂቶችም የሚመለሱት አካል ጉዳት ደርሶባቸው እና ከስነልቦና ጉዳት ጋር ነው።
ሆኖም መንግሥት ዝምታን መርጧል። የሚያብረቀርቅ መሠረተ ልማትን፣ አረንጓዴ አሻራን ዘመቻዎችን እና የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ማደግን ያወድሳል። ክልብ ለማዘንም ጊዜው አሁን ነው። ቆራጥ እርምጃ ለመውሰድም ጭምር ጊዜው አሁን ነው።
ሙሉውን ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8777

ወጣቶች ከኢትዮጵያ ለመውጣት እየሞቱ ነው፤ የማስመሰል ብልጽግናን ለማቆም እና እውነታውን ለመጋፈጥ ጊዜው አሁን ነው! - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2/ 2017 ዓ/ም፦ ባሳለፍነው እሁድ ሐምሌ 27 ቀን፤ 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ሌላኛዋ ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ሰምጣለች። ቢያንስ 68 ሰዎች (አብዛኞቹ ወጣቶች የሆኑ) መከላከል በሚቻል አሳዛኝ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል። ህይወታቸውን ያጡት ዜጎች ሲሹ የነበሩት ሀብትን ሳይሆን መፃዒ ተስፋን ነበር። ይህ ጽሑፍ እስከታተመበት ድረስ አደጋው የደረሰባቸው 78 ሰዎች…
"በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል" ተግባር የተሰማሩ 138 ተጠሪጣሪዎች ባንክ ሒሳብ ታገደ
"ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ መታገዱን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ገለፀ፡፡
የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑ በህገ ወጥ መጠቀም የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ አሳስቧል፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱን አገልግሎቱ ለኢዜአ ገልጿል፡፡
በዚህ መሠረትም ክትትል ተደርጎ የተደረሰባቸው እና በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያለው፡፡
ይህ የተገለፀው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን ተከትሎ ነው።
አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ተማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።
በተለይ በቅርብ ቀናት በ #ዱባይ ከገበያ ሁኔታ ያፈነገጠ የትይዩ ገበያውን የሚያስፋፉ ህገወጥ ድርጊቶች እንዳሉ መረዳቱን ገልጾ የገለጸው ባንኩ፤ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
"ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓትን ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች" የባንክ ሒሳብ መታገዱን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ገለፀ፡፡
የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑ በህገ ወጥ መጠቀም የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት እንደሚያሰቀጣ አሳስቧል፡፡
ይሁን እንጂ አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው መቆየቱን አገልግሎቱ ለኢዜአ ገልጿል፡፡
በዚህ መሠረትም ክትትል ተደርጎ የተደረሰባቸው እና በሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ነው ያለው፡፡
ይህ የተገለፀው የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን የሚጠቀሙ የንግዱ ማህበረሰብ ገንዘባቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ መግለፃቸውን ተከትሎ ነው።
አቶ ማሞ ብሔራዊ ባንክ ምርመራ እያከናወነ መሆኑን ገልጸው “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ስርዓት ተማኝነትን ሆነ ብሎ ለመሸርሸር እና የገበያ ዋጋን ለማዛባት በማለም መቀመጫቸውን በውጭ ሀገር ያደረጉ ህገ ወጥ የገንዝብ ዝውውር አስተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚቀጥል” ገልጸዋል።
በተለይ በቅርብ ቀናት በ #ዱባይ ከገበያ ሁኔታ ያፈነገጠ የትይዩ ገበያውን የሚያስፋፉ ህገወጥ ድርጊቶች እንዳሉ መረዳቱን ገልጾ የገለጸው ባንኩ፤ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል።
ዜና: #ኮሚሽኑ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን ገለፀ
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለፁ።
የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራው በአዉሮፓ፣እስያ እና አፍሪካ በበይነ መረብ አማካኝነት እንዲሁም አንዳንድ ሀገራት ላይ በአካል በመሄድ እንደሚከናወን ገልጸዋል።
በተጨማሪም አምስት ኮሚሽነሮች የተካተቱበት ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በአካል ተገኝቶ አጀንዳ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቆ ከነገ ነሀሴ 3 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን እንደሚጀምር ገልጸው፤ አጀንዳ የማሰባሰቡ ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ አጀንዳዎችን አንጥሮ በማውጣት ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እንደሚያዘጋጁም ጠቅሰዋል።
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለ ምንም አይነት ውጫዊ እና ውስጣዊ አካል ተፅዕኖ እንደሚከናወን ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ዜጎች ራሳቸዉ እንዲወስኑ መደረጋቸው እና በጋራ የሚወያዩበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
አክለውም በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለእቅዱ መሳካት በጋራ መስራት እንዳለባቸው እና ጉባኤዉ በቀጣይ ዓመት እንደሚጀመር መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ መጀመሩን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለፁ።
የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራው በአዉሮፓ፣እስያ እና አፍሪካ በበይነ መረብ አማካኝነት እንዲሁም አንዳንድ ሀገራት ላይ በአካል በመሄድ እንደሚከናወን ገልጸዋል።
በተጨማሪም አምስት ኮሚሽነሮች የተካተቱበት ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በአካል ተገኝቶ አጀንዳ ለመሰብሰብ ዝግጅቱን አጠናቆ ከነገ ነሀሴ 3 2017 ዓ.ም ጀምሮ ስራውን እንደሚጀምር ገልጸው፤ አጀንዳ የማሰባሰቡ ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ አጀንዳዎችን አንጥሮ በማውጣት ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እንደሚያዘጋጁም ጠቅሰዋል።
የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ያለ ምንም አይነት ውጫዊ እና ውስጣዊ አካል ተፅዕኖ እንደሚከናወን ያነሱት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ዜጎች ራሳቸዉ እንዲወስኑ መደረጋቸው እና በጋራ የሚወያዩበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
አክለውም በሀገር ውስጥም በውጭም ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለእቅዱ መሳካት በጋራ መስራት እንዳለባቸው እና ጉባኤዉ በቀጣይ ዓመት እንደሚጀመር መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
======================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በ #ኢትዮጵያ 'ደህንነትና በፋይናንስ ስርዓት' ላይ ስጋት መጣሉን ሚኒስቴሩ ገለፀ፤ ማህበራዊ ሚዲያ 'ስደተኞችን ለማሳመን' ጥቅም ላይ መዋሉንም ገልጿል
በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ፤ በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች የግለሰቦችን ህይወት በቻ ሳይሆን “በአገር ደህንነትና በፋይናንስ ስርአቱ ላይ የተደቀነው ስጋት እየጨመረ መምጣቱን” ገልጸዋል።
በ #ቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው የብሔራዊ ትብብር ጥምረት የፌደራልና የክልል የህግ ማስከበር የስራ ቡድን አመታዊ ሪፖርት ግምገማ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ተስፋዬ፤ “መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከአገር ለመውጣት በሚደረገው ሂደት ውስጥ ዜጎቻችን በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ሰለባ ከመሆናቸው በተጨማሪ በአገር ደህንነትና በፋይናንስ ስርአቱ ላይ የተደቀነውን ስጋት እየጨመረ መጥቷል” ብለዋል።
በተጨማሪም የወንጀል ቡድኖች ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በርቀት ሆነው ለዜጎች “ተጨባጭ ያልሆነ ተስፋ በመስጠት፣በማታለልና በማስገደድ” በወንጀል ተግባር ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ “ለከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ቁሳዊ ኪሳራ እየዳረጓቸው እንደሚገኙ” መግለጻቸውን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሙሉ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8790

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር "በኢትዮጵያ ደህንነትና በፋይናንስ ስርዓት" ላይ ስጋት መጣሉን ሚኒስቴሩ ገለፀ፤ ማህበራዊ ሚዲያ ስደተኞችን ለማሳመን ጥቅም ላይ መዋሉንም ገልጿል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3/ 2017 ዓ/ም፡- በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ፤ በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎች የግለሰቦችን ህይወት በቻ ሳይሆን “በአገር ደህንነትና በፋይናንስ ስርአቱ ላይ የተደቀነው ስጋት እየጨመረ መምጣቱን” ገልጸዋል። በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ባለው የብሔራዊ ትብብር ጥምረት የፌደራልና የክልል የህግ ማስከበር…