#የአፍሪካ_ህብረት ተልዕኮ ከ50 በላይ #አል-ሸባብ ታጣቂዎች በደቡባዊ #ሶማሊያ መገደላቸውን አረጋገጠ
የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) በሶማሊያ የመንግስት ኃይሎች የሚደገፉት ወታደሮቹ ባሳለፍነው አርብ በደቡባዊ ሶማሊያ በባሪሬ ከተማ በተካሄደ ከባድ ውጊያ ከ50 በላይ የአል-ሸባብ አባላትን መግደላቸውን አስረጋገጠ።
አውሶም ከሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሰጠው መግለጫ፤ “በባሪሬ በተልዕኮው ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል” የሚሉ የሚዲያ ዘገባዎችን አስተባብሏል።
"አውሶም ኃይሎቹ ከሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ኃይሎች (SNAF) ጋር በመተባበር የባሪሬ ከተማን መልሶ ለመቆጣጠር ሐምሌ 25 ቀን ጥቃት መጀመሩን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል" ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) ገልጿል። አውሶም ይህን ያለው፤ አል-ሸባብ በባሪሬ በተካሄደው ከባድ ውጊያ የአፍሪካ ህብረት ንብረት የሆኑ የታጠቁ ሰዎች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን እና የአውሶም ወታደሮች ማፈግፈጋቸውን መግለጹን አስመልክቶ በገዳዩ ላይ ምላሽ ሲሰጥ ነው።
“የጋራ ወታደራዊ ዘመቻው ለአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል፣ ከ50 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ሲል የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) ማስታወቁን ዥንዋ ዘግቧል።
ከሞቃዲሾ በስተደቡብ ምዕራብ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ባሪሬ ከተማ፤ በሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ከሚገኙ ስትራቴጂካዊ አካባቢዎች አንዷ ነች።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ታጣቂዎችን እና መንግስትን ጭምሮ ለተለያዩ አካላት ያቀረቡት ጥሪዎች
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰኔ 2016 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ባለ152 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
ኮሚሽነሩ ሪፖርቱን አስመልኮቶ ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ፤ በ #አማራ እና በ #ኦሮሚያ ክልሎች በትጥቅ ትግል ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እና የሰብዓዊነት ህጎች እና ድንጋጌዎችን እንዲያከብሩ ጠይቀዋል። በተጨማሪም መንግስትን ጨምሮ ሁሉም የግጭት ተሳታፊዎች ኃይሎች አለመግባባትን በቁርጠኝነት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በነሀሴ ወር በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ዝናብ እንደሚኖር ተገለፀ
በነሀሴ ወር በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የ #ኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።
ኢኒስቲትዩቱ በነሃሴ ወር በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ጠቁሟል።
በተጨማሪም በፀሐይ ሀይል ታግዘዉ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በመነሳትም በረዶ የቀላቀለ እና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል አስገንዝቧል።
በሌላ በኩል በአንዳንድ ቦታዎች ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ የእርጥበት መብዛት ጋር ተያይዞ በረባዳማ አካባቢዎች የውሃ በሰብል ላይ መተኛት፣ የመሬት አቀማመጡ ከፍታ ባላቸውና ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የመሬት መንሸራተትና በጎርፍ መጠቃት ሊያጋጥም እንደሚችልም ተገልጿል።
እንዲሁም እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሰብል በሽታ እና የአረም መስፋፋት ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት ሰብሎች በጎርፍ እንዳይጠቁ እና በማሳ ላይ ውሃ እንዳይተኛ የጎርፍ መቀልበሻዎችንና ከማሳ ውሰጥ ውሃን ማንጣፈፊያ ቦዮችን ማዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል ብሏል።
ኢኒስቲትዩቱ፤ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ አልፎ አልፎ በሚኖረው ተደጋጋሚ ከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ የማስከተል እድል ይኖረዋል ሲል ለኢፕድ ገልጿል።

ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ከ118 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 118 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ለ #ኬንያ፣ #ጅቡቲ፣ #ሱዳንና #ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል እየሸጠች እንደምትገኝ የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ተናግረዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 25 ሺህ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት ታቅዶ 29 ሺህ በላይ ጊጋ ዋት ሰዓት ማመንጨት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
ከተመረተው ኃይል ውስጥም ለኬንያ 85 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ለማከናወን ታቅዶ 86 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም ለጅቡቲና ሱዳን ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ በቅደም ተከተል 30 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር እና 900 ሺህ ዶላር መገኘቱን ለኤፍ ኤም ሲ ገልጸዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ከሶስቱ ሀገራት በተጨማሪ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ በሙከራ ደረጃ መጀመሩን ነው የገለጹት፡፡
ለጎረቤት ሀገራቱ ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሽያጭም በአጠቃላይ 118 ነጥብ 1ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ ካመረተው ሃይል ውስጥ 7 በመቶውን ወደ ውጪ በመላክ ከተቋሙ አጠቃላይ ገቢ 20 በመቶ የሚሆነውን መሸፈን መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ዜና፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በቀጠሉት ግጭቶች በህይወት የመኖር መሰረታዊ መብት "አሳሳቢ" ደረጃ ላይ መድረሱን ኢሰመኮ አመለከተ
በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በቀጠሉት በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች ምክንያት በህይወት የመኖር መሰረታዊ መብት "አሳሳቢ" ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳዩ በርካታ ክስተቶች መስተዋላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በአማራ ክልል በአዛኛው አከባቢዎች በመንግስት ሀይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች [ፋኖ] መካከል እየተካሄደ ባለው የትጥቅ ግጭት በግጭቱ ላይ ተሳታፊ ያልነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን አስታውቋል።
ግጭቶች ሲካሄዱባቸው በነበሩ አከባቢዎች የመንግስት ሀይሎች በሚቆጣጠሩበት ወቅት "ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ትቀልባላችሁ" ያሏቸው ሰዎች ላይ ግድያና መኖሪያ ቤቶችን በእሳት ማቃጠል ጥቃቶች መፈጸማቸውን አመላክቷል።
በሌላ በኩል በክልሉ የሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች [ፋኖ] "ለመከላከያ ሰራዊት መንገድ አሳይታችሗል፤ ሰዎችን ጠቁማችሁ አስይዛችሗል" በሚል እና የመንግሥት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው እንዳይገቡ በማስፈራራት እና በገቡት ላይ ግድያ እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች ላይ ዘረፋ እና ውድመት መፈጸማቸውን በምርመራ መረጋገጡን በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ሀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች መካከል በሚደረገው በትጥቅ የታገዘ ግጭት ሳቢያ በሁለቱም አካላት በንጹሃን ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ኢሰመኮ አስታውቋል።"የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ በሰዎች ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ እገታ እና የንብረት ውድመት ደርሷል” ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8737

Addis standard
በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በቀጠሉት ግጭቶች በህይወት የመኖር መሰረታዊ መብት "አሳሳቢ" ደረጃ ላይ መድረሱን ኢሰመኮ አመለከተ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28/ 2017 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ በተለያዩ አከባቢዎች በቀጠሉት በትጥቅ የታገዙ ግጭቶች ምክንያት በህይወት የመኖር መሰረታዊ መብት “አሳሳቢ” ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳዩ በርካታ ክስተቶች መስተዋላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። ኮሚሽኑ ከሰኔ 2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን የተመለከተ…
ዜና: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸውን ባጡ #ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለጸ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ገለጸ፡፡
የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ እንደሚገኝ የገለጸው ሚኒስቴሩ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ለሕልፈት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡
መንግሥት ዜጎች በተለያዩ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ ተንቀሳቅሰው መሥራት እንዲችሉ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን በማከናወን በርካታ ዜጎችን የዕድሉ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም አመልክቷል፡፡
ሚኒስቴሩ አክሎም ዜጎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ የውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ከሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በየመን የባህር ዳርቻ ላይ ሰጥማ ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ትናንት እሁድ ማለዳ ላይ ከሰጠመችው ጀልባ የነበሩት ተሳፋሪዎች "በሙሉ የኢትዮጵያ ዜጎች እንደነበሩ" የተገለጸ ሲሆን በየመን አብያን ግዛት የባህር ዳርቻ ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ አስከሬኖች መገኘቱ ተገልጿል፡፡

ደንብ ማስከበር አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት ላይ የድብደባ ወንጀል የፈጸሙ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ/ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ጀሞ መስታወት ፋብሪካ አካባቢ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
የወንጀል ድርጊቱን ከፈጸሙት ተጠርጣሪዎች መካከል ዮሀንስ ከበደ፣ ሠዒድ ሠይፉ፣ እስማኤል ሱልጣን፣ ሃይረዲን ሽፋ፣ ፈጅሩ ሱልጣን፣ ባህሩ ራህመቶ፣ ሚነወር ሀይሉ፣ ሀይልዬ ጀማልና አስማረ አለሙ የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ሁለት ተጠርጣሪዎች አለመያዛቸውም ተመላክቷል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በእግረኛ መንገድ ላይ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድ በማከናወን ላይ ሳሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አባላት የሆኑት ማቱሳላ ማዶሬና አቡሽ ሽጉጤ ድርጊቱን ለመከላከል ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት በድንጋይና በእርግጫ ተረባርበው አባላቱ ላይ የድብደባ ወንጀል ፈጸመዋል ብሏል።
ግለሰቦቹ ድርጊቱን ፈጽመው ቢሰወሩም በክ/ከተማው ፖሊስ በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ፖሊስ ገልጾ በፈጸሙት የወንጀል ድርጊትም ተገቢውን ምርመራ የማጣራትና ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረቱን መቀጠሉንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄደ ጀመረ
አራተኛው ሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሰላም ኮንፍረንስ በሁለተኛ ቀን ውሎው በሐረር ኢማም አህመድ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ኮንፍረንሱ "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነትና ለአብሮነት'' በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች እና ተወካዮች፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ታድመዋል።
እንዲሁም የየክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሃይማኖት ተቋማትና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኮንፍረንሱ ህዝቡ ሰላሙን እንዲጠብቅና የሰላም ባለቤት ሆኖ እንዲሰራ፣ ሰላም በሀገሪቱ በዘላቂነት ፀንቶ እንዲቀጥል የሃይማኖት አባቶችና ምዕምናን ይበልጥ እንዲሰሩ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ በሰላም በአንድነትና በአብሮነት ፀንታ እንድትቆም ህብረተሰቡን ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
በኮንፍረንሱ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂዎች የሰላም መልዕክትና ጥሪ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሰላም ኮንፍረንሱን የኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ ተመልክቷል።
ከዚህ ቀደም የሰላም ኮንፍረንሱ በድሬ ዳዋ፣ ጅማ እና ባህርዳር ከተሞች መካሄዱ ይታወቃል።

ዜና፡ የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ለ #ሩሲያ ለማከራይት ስምምነት ላይ ደርሷል መባሉን "ፍጹም ሀሰት" ሲል አስተባበለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ #አሜሪካ እና በ #አውሮፓ ማዕቀብ ምክንያት የአቪዬሽን ችግር ለገጠመው ለሩሲያ አየር መንገድ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን እና የመለዋወጫ ዕቃዎችን በኪራይ ለማቅረብ ውይይት እያደረገ ነው መባሉን "ፍጹም ሀሰት ነው" ሲል አስተባብሏል።
የአየር መንገዱ ዋና አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ አየር መንገዱ በሁለት ምክንያቶች ለሩሲያ አየር መንገድ ለማከራየት ሀሳብ እንደሌለው ገልጸዋል። "እኛ አውሮፕላን የሚያስፈልገን ሰዓት ነው እንኳን ልናከራይ” ፤ በተጨማሪም "በየሀገሩ ስንበር የየሀገሩን ህግ ስለምናከብር እና ከአሜሪካ ጋር ቁርኝት ስላለን የአሜሪካን ህግ እናከብራለን" ብለዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ #ኤርትራ አየረ መንገድ የተያዘበት ገንዘብ ግን አሁንም አለመለቀቁን ገልጸው ነገር ግን “በፍርድ ቤት ሄደን ለማስለቀቅ ሙከራ አድርገን ነበረ ግን አልተቻለም ስለዚህ የፖለቲካ ውሳኔ ይኖርበታል” ብለዋል። አክለውም አየር መንገዱ በኤርትራ አየር ክልል እየበረረ መሆኑን ገልጸዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው ሲናገሩም አየር መንገዱ በበጀት ዓመቱ ከ19 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መንገደኞችን በማጓጓዝ 7.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን አስታውቀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8741

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ለሩሲያ ለማከራይት ስምምነት ላይ ደርሷል መባሉን "ፍጹም ሀሰት" ሲል አስተባበለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29/ 2017 ዓ/ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች እና የመለዋወጫ ዕቃዎች ለሩሲያ አየር መንገድ ለማከራይት ስምምነት ላይ ደርሷል መባሉን “ፍጹም ሀሰት” ሲል አስተባበለ። የአየር መንገዱ ዋና አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በ2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድን የስራ አፈጻጸም አስመልክተው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል:: በዚህ…
ጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ 3 ሺህ 210 ቶን ዓሣ ተመረተ
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ በፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ 3 ሺህ 210 ቶን የዓሣ ምርት ተገኘ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አስፋው ጮራሞ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በዞኑ ከኩሬ እና ከተለያዩ ውሃ አካላት 4 ሺህ 200 ቶን የዓሣ ስጋ ለማምረት ታቅዶ 4 ሺህ 111 ነጥብ 6 ቶን ዓሳ ተመርቷል።
ከዚህ ውስጥ 3 ሺህ 210 ቶን ምርት የተገኘው የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ ከፈጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ ነው ብለዋል።
በሐይቁ ላይ 160 ወጣቶች በተለያዩ ማህበራት ተደራጅተው በዓሣ ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ለወጣቶቹ ምርታማነታቸው እንዲጨምር የሚያስችል ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ጠቅሰው የምርት ማከማቻና መሸጫ ሼድ ግንባታ፣ የምርት ማቆያ ፍሪጆች እና ሐይቅ ላይ የምርት ማጓጓዣ የሞተር ጀልባ እንዲያገኙ ተደርጓል ነው ያሉት።
እንዲሁም ምርትን ወደ ተለያዩ የአካባቢ ገበያዎች አጓጉዘው የሚሸጡበት ፍሪጅ የተገጠመለት መኪና እና ሌሎች ድጋፍ መደረጋቸውን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ በቀን እስከ አንድ ቶን የሚደርስ ዓሣ እያመረቱ መሆናቸውን ገልጸው ከአካባቢ ገበያ ጀምሮ እስከ ማዕከላዊ ገበያ ድረስ ምርት እያቀረቡ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድብ 1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማመንጨት ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጥሎ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ሲሆን÷ ግድቡን ተከትሎ የተገነባው የሀላላ ሎጅም ለአካባቢው የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የገቢ ምንጭ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
(ኤፍ ኤም ሲ)

ዜና፡ #ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት ገደማ የዲፕሎማሲያዊ መሻከር በኋላ በሶማሊያ አዲስ አምባሳደር ሾመች
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የነበራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተቀዛቀዘ ከአስር ወራት በኋላ አዲስ አምባሳደር ሾመች።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት አብዲሰላም አብዲ አሊ በሞቃዲሾ በሚገኘው የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ትናንት ሰኞ እለት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን የሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል።
ሚኒስትሩ አዲስ የተሾሙትን አምባሳደር በመቀበል በሁለቱ ጎረቤት ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር እና ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በሶማሊያ አዲሱ የኢትዮጵያ አምባሳደር የተሾሙት፤ በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ሶማሊያ አንድ ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማትን “ከዲፕሎማሲያዊ ሚናቸው ጋር በማይጣጣም መልኩ” ተሰማርተዋል ስትል ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሻከረ በኋላ ነው።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8745

ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት ገደማ የዲፕሎማሲያዊ መሻከር በኋላ በሶማሊያ አዲስ አምባሳደር ሾመች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29/ 2017 ዓ/ም፦ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር የነበራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተቀዛቀዘ ከአስር ወራት በኋላ አዲስ አምባሳደር ሾመች። የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር የሆኑት አብዲሰላም አብዲ አሊ በሞቃዲሾ በሚገኘው የሚኒስቴሩ መስሪያ ቤት ትናንት ሰኞ እለት በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን የሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤ ተቀብለዋል። ሚኒስትሩ…
ዜና: በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ 2,400 ሄክታር ሰብል ወደመ
በ #ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ እና ሰበታ ሃዋስ ወረዳዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ አዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,400 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
የኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ተስፋዬ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ባሳለፈነው ቅዳሜ ምሽት አዋሽ ወንዝ በአራት አቅጣጫዎች ሞልቶ በመፍሰሱ ወሬርሶ ቀሊና እና ሙሉ ሳተዩ በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገድዷል።
ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብል እና እንደ ዶሮ፣ ፍየል እና በግ ያሉ እንስሳት በጎርፉ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የጠፉት አጠቃላይ የእንስሳት ብዛት አሁንም በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
የሰበታ ሀዋስ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አሸናፊ ንጉሴ በበኩላቸው የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ወደ አዋሽ ባሎ ቀበሌ በመግባቱ 240 አባወራዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውንና በሰብል እንዲሁም በእንስሳት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል። አያይዘውም የአከባቢው ነዋሪዎች ጎርፉን ይባባሳል በሚል በስጋት ላይ መውደቃቸውን ጠቁመዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8750

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ 2,400 ሄክታር ሰብል ወደመ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30/ 2017 ዓ/ም፡– በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ኢሉ እና ሰበታ ሃዋስ ወረዳዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ አዋሽ ወንዝ በመሙላቱ ከ5,000 በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,400 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። የኢሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ተስፋዬ…
ከ #ናይሮቢ - #አዲስ_አበባ በአውቶብስ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ
ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት አስታወቀ።
ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን 'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ እንደሚያስከፍል የተናገሩት ዳይሬክተሩ ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (16 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ገደማ) መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ አቶ ሚካኤል ገለጻ አቢሲኒያ ሌግዠሪ በየቀኑ ወደ በናይሮቢ እና በአዲስ አበባ መካከል የሕዝብ ማመላለስ ሥራዎችን ይሠራል።
ባለፈው ዕሁድ ሥራውን በይፋ ሲጀምር ሰባት ተሳፋሪዎች ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ትኬት ቆርጠው ነበር።
"እሁድ የሙከራ ጉዞ ነበር፤ነገር ግን በደንብ ማስታወቂያ ስላልተሠራ ቀጥታ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች አልተገኙም" የሚሉት አቶ ሚካኤል "ባሱ 46 ሰዎች የመያዝ አቅም ቢኖረውም ቀጥታ አዲስ አበባ የሚሄዱት ሰባት ሰዎች ብቻ ነበሩ" ብለዋል።
'አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች' ዳይሬክተር አቶ ሚካኤል አውቶብሶቹ አስተናጋጆች፣ ራሳቸውን የቻሉ የሴቶችን እና የወንዶች መጸዳጃ፣ በውስጣቸው የኢንተርኔት እና 'ስክሪንን' ጨምሮ የመዝናኛ አግልግሎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c4ge2z4pyjgo

ዜና: የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል በፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሁለት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በፈፀሙት ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ በጽኑ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈ።
አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የምዝገባና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታምሩ ግንበቶ እና 2ኛ ተከሳሽ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የውጪ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጅላሉ በድሩ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 9(1) (ሀ) መተላለፋቸው ተመላክቷል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሙስና ጉዳዮች ችሎትም ተከሳሾቹ ጥፋተኝነታቸዉ በሰዉ እና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ 1ኛ ተከሳሽ ታምሩ ግንበቶ በ8 አመት ፅኑ እስራት እና 1 ሺህ ብር፤ 2ኛ ተከሳሽ ጅላሉ በድሩ ደግሞ በ4 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8754

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል በፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30/ 2017 ዓ/ም፦ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ችሎት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሁለት የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች በፈፀሙት ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል ጥፋተኛ ሆነዉ በመገኘታቸዉ በጽኑ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተላለፈ። አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የምዝገባና ቁጥጥር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር…
#ኢትዮጵያና #ተርኪሚኒስታን “ኢ-ፍትሃዊ የሆኑ የባህር በር ተግዳሮቶችን” በጋራ ለመፍታት መስማማታቸው ተገለጸ
ኢትዮጵያና ተርኪሚኒስታን በባህር በር ምክንያት የሚከሰቱ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት እንዲሁም ቀጣናዊ ውህደትንና ንግድን ለማጠናከር ከስምምነት ላይ መደረሳቸው ተገለጸ።
ሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት ባህር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ጉባኤ (UNLLDC3) "በአጋርነት ለውጥ ማምጣት" በሚል መሪ ሀሳብ በተርኪሚኒስታን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከተርኪሚኒስታኑ የንግድና የውጭ ኢኮኖሚ ግንኙነት ሚኒስትር ናዛር ሃልናዛሮቪች አጋሃኖቭ ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሀገራት ኢ-ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ተግዳሮት በጋራ ለመፍታት የመከሩ ሲሆን፤ ለንግድና ኢኮኖሚ እድገት መፋጠን አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ቀልጣፋና አነስተኛ ወጪ ያላቸውን የትራንስፖርት መፍትሄዎች ለመፍጠር ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል ሲል ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።
ሚኒስትሮቹ ከፍተኛ የትራንስፖርት ወጪ፣ በጎረቤት ሀገራት ወደቦች ላይ ሙሉ ጥገኝነት እና የንግድ መስመሮችን የሚያውኩ የጂኦ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ስጋቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተግዳሮቶችን አንስተዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0QPtZ56XDfE3AzubxfRLuCamLn43KG3zqh5sv2ZmUVYZtVi2YUgCV9kQE4owpu2NYl