Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የ #ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከሰላም ልዑክ ጋር ያደረጉት ውይይት
ፕሬዝዳንቱ ከኢትዮጵያ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና የንግድ ማህበረሰብን ያካተተ የሰላም ልዑክ ባደረጉት ውይይት በትግራይ “የጦርነት ዝግጅት የለም" ብለዋል። አክለውም "ትግራይ በሰላም የማይፈታ ጉዳይ በፍጹም የላትም” ሲሉም ገልጸዋል።

ዜና፡ በ #ኦሮሚያ ክልል የአንድ አመት ከስምንት ወር ህፃን "በፀጥታ ኃይሎች" መገደሉ ተገለጸ፤ የአካባቢው ባለስልጣን ህፃኑ የተገደለው 'በተኩስ ልውውጥ ነው' ብለዋል
በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባ ቦር ዞን ኖጳ ወረዳ፤ የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን "በፀጥታ ኃይሎች" በተቶከሰ ጥይት መገደሉን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ዛራ ሀሰን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። በአሁኑ ወቅትም በፀጥታ ችግር ምክንያት ከቀዬቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን ገልጸዋል።
የህፃኑ እናት ወ/ሮ ዛራ ሀሰን፤ “ልጇ የተገደለው የአባቱ እቅፍ ውስጥ እያለ” መሆኑን ገልጸዋል። “በሰዓቱ ሁላችንም ቤት ውስጥ ተቀምጠን ነበር። ልጃችንም በአባቱ እቅፍ ውስጥ ነበር፤ ከዛም በተተኮሰው ጥይት ተመታ። ልጁ ከሞተ በኋላ አባቱ አስከሬኑን ትቶ እራሱን ለማትረፍ ሮጦ አመለጠ” ብለዋል።
የኖጳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደጀኔ ከበደ የህፃኑን ሞት አረጋግጠው፤ ነገር ግን ህጽኑ የተገደለው "በመንግስት ኃይሎች እና በሸኔ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ በመሆኑ በየትኛው ወገን ጥይት እንደተመታ አልተለየም" ብለዋል። “ታጣቂዎቹ ከዚህ ክስተት በፊት ለብዙ ቀናት የሰዎቹን ቤት እንደ መደበቂያ ሲጠቀሙበት ነበር” ሲሉም ተናግረዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8698

Addis standard
በኦሮሚያ ክልል የአንድ አመት ከስምንት ወር ህፃን "በፀጥታ ኃይሎች" መገደሉ ተገለጸ፤ የአካባቢው ባለስልጣን ህፃኑ የተገደለው 'በተኩስ ልውውጥ ነው' ብለዋል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24/ 2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ኢሉ አባ ቦር ዞን ኖጳ ወረዳ፤ የአንድ አመት ከስምንት ወር ህጻን “በፀጥታ ኃይሎች” በተቶከሰ ጥይት መገደሉን ወላጅ እናቱ ወ/ሮ ዛራ ሀሰን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። በአሁኑ ወቅትም በፀጥታ ችግር ምክንያት ከቀዬቸው ለመፈናቀል መገደዳቸውን ገልጸዋል። የአካባቢው ባለስልጣናት የህፃኑን ሞት አረጋግጠው፤ ነገር ግን ህጽኑ የተገደለው “በመንግስት…
ዜና፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማርያም "በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራርያ" ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ
ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያሬድ ሀይለማርያም "ከፀጥታ አካላት በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራርያ" ከሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሀላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡
አቶ ያሬድ “ከአንድ አመት ወዲህ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በሚገኙ ሚዲያዎች ላይ እየቀረብኩ አገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የምሰጠቸው መግለጫዎችና ማብራሪያዎች፣ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ዜጎችን ስለ መብታቸው እንዲያውቁና በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በማስመልከት የማካፍላቸው ሃሳቦችና የምሰነዝራቸው የሰሉ ትችቶች በአገዛዝ ሥርአቱ ዘንድ በጥሩ ሁኔታ አልታዩም” ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ከዚህ የተነሳ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ አይነት ጫናዎችን ሳስተናግድ ቆይቻለሁ ብለዋል።
“የተለያዩ ዛቻዎች፣ ማስፈራሪያዎችና ትንኮሳዎችን በጸጥታ አካላት በኩል ሲፈጸሙ እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ስልኮቼ ያልተለመዱ ጥሪዎችን ሳስተናግድ ያለውን ግልፅ ስጋት ችላ በማለት በሥራዬ ላይ አተኩሬ ቆይቻለሁ” ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8709

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ሀይለማርያም "በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራርያ" ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24/ 2017 ዓ/ም፦ ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ያሬድ ሀይለማርያም “ከፀጥታ አካላት በሚደርስባቸው ዛቻ እና ማስፈራርያ” ከሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከሀላፊነት መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡ አቶ ያሬድ “ከአንድ አመት ወዲህ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ በሚገኙ ሚዲያዎች ላይ እየቀረብኩ አገሪቱ…
የ #ወሎ_ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የወሎ ኮምቦልቻ የመንገደኞች አውሮፕላን ማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ። ማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና የኢትዮጵያ አየር መንግድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በተገኙበት በዛሬው ዕለት ሐምሌ 24/ 2017 ተመርቋል።
ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ በመርኃግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁ ለክልሉም ይሁን ለሀገራዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ የበርካታ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን አንስተው ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ይደረጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፤ የአየር ትራንስፖርቱን በማዘመንና ተደራሽነቱን በማስፋት የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በውጭና በሀገር ውስጥ መዳረሻውን እያሰፋ እና እየዘመነ መምጣቱን አንስተው፤ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የወሎ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ህንጻ በአንድ ጊዜ 320 መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ ስድስት አዳዲስ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን በተያዘላቸው ጊዜና በጥራት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዜና: #ግብፅ እና #አሜሪካ በውሃ ደህንነት እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ መከሩ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ከግብጹ አቻቸው ባድር አብደላቲ ጋር በግብጽ የውሃ ደህንነት ዙርያ እንዲሁም በመካከላኛው ምስራቅ ሰላማን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች እና ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት አስታወቀ።
ሚኒስትሮቹ ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ ላይ ሩቢዮ፤ “ግብፅ በሐማስ ተይዘው የነበሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ላሳየችው ጽኑ ድጋፍ” ለአብደላቲ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስነብቧል።
በተጨማሪም በሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር ስለሚደረገው ሽግግር አስፈላጊነትም ተወያይተዋል ሲል መስሪያ ቤቱ አክሎ ገልጿል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባድር አብደላቲ ስብሰባውን አስመልክቶ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ ከአሜሪካ አቻቸው ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነትን በማጠናከር፣ ቁልፍ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች እና በግብፅ የውሃ ደህንነት ዙርያ መምከራቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይቱን ያካሄዱት በጋዛ ስላለው ረሃብ አስመልክቶ ከሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች በኩል የሚደረጉ ጥሪዎች እየተበራከቱ በመጡበት በአሁኑ ወቅት ነው።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: #ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከጠቅላላው የወጪ ንግዷ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ከጠቅላላው የወጪ ንግዷ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በበጀት ዓመቱ ከጠቅላላው የወጪ ንግድ ገቢ 5.145 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 8.3 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘት መቻሉን ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል፡፡
ይህም በ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው 3.71 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶለር ጋር ሲነፃፀር የ4.59 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም 123.78 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡
እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን በ2016 ዓ.ም. ከነበረበት 1066 ወደ 1,300 ለማሳደግ ታቅዶ 501 አዳዲስ ገበያዎች በመክፈት 1,567 ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ከ8.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የጥራት መንደር ተገንብቶ 5 ጥራት አስጠባቂ ተቋማትን በአንድ ቦታ በመያዝና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ቀጠናዊ ውህደት እና ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትን ከማጎለበት አንጻር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ተግባራዊነት ብሔራዊ የትግበራ ኮሚቴ በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ሚኒስትሩ፤ አያይዘውም በ2018 በጀት ዓመት ስኬቶችን ለማስቀጠል እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡

ዜና: #ኢሰመጉ በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው “ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እና የሚዲያ ዘመቻዎች” እጅግ እንዳሳሰበው ገለጸ
የ #ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው “ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እና የሚዲያ ዘመቻዎች” እጅግ እንዳሳሰበው ገለፀ።
ኢሰመጉ፤ የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ ሙሉ በሙሉ የማስፈታት፤ የመበተንና የማቋቋም (DDR) ሂደት መጓተት፣ የ #ኤርትራን ጨምሮ እና ሌሎች ኃይሎች ከ #ትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ አለመውጣት፣ እንዲሁም በሚሊዮን የሚቆጠሩ የውስጥ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው በሰላምና በክብር አለመመለሳቸው የሰላሙን ሂደት አደጋ ላይ ጥሎታል ብሏል።
"የፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ከሁለት ዓመታት በኋላ ቁልፍ የሆኑ አንቀጾች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመሆናቸው የተነሳ ሰላምም ጦርነትም የሌለበት ሁኔታ መፈጠሩንም" የገለጸው ድርጅቱ፤ ይህም "የእርስ በርስ አለመተማመን እና የዳግም ግጭት ስጋት እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል" ሲል ገልጿል።
ኢሰመጉ፤ "የትግራይ ጊዜያዊ እስተዳደርና በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ሀይሎች አለመግባባቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ፣ ተገቢውን ጥረት እንዲያደርጉ እና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ እና የአካባቢውን ማሀበረሰብ ስጋት ውስጥ ከሚከቱ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ" ጥሪ አቅርቧል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8717

ኢሰመጉ በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው "ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እና የሚዲያ ዘመቻዎች" እጅግ እንዳሳሰበው ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25/ 2017 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በተለያዩ አካላት የሚደረጉ ወታደራዊ ይዘት ያላቸው “ዝግጅቶች፣ ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች እና የሚዲያ ዘመቻዎች” እጅግ እንዳሳሰበው ገለፀ። ኢሰመጉ ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና በትግራይ የታጠቁ ኃይሎች መካከል ከ2013-2015 ዓ.ም በዘለቀው…
ዜና ትንታኔ፡ አዲሱ የ #ሶማሌ ክልል መዋቅር በክልሉ፣ #አፋር እና #ኦሮሚያ ክልሎች ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሰላ ቀቃወሞ ገጠመው
የሶማሌ ክልል መንግስት አዲስ 14 ወረዳዎችን፣ ሁለት የዞን አስተዳደሮችን እና 25 ማዘጋጃ ቤቶችን ማዋቀሩን ተከትሎ በአፋር፣ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ቀቃወሙ።
የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሞሃመድ አደም፤ ለውጦቹ የተደረጉት “ሙሉ በሙሉ በክልሉ ውስጥ” መሆናቸውንና “ምንም አይነት የወሰን አስተዳደር ማሻሻያ እንደማያካትቱ” ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ይሁን እንጁ አዲሱ መዋቅር በሶማሌ ክልል ከሚንቀሳቀሰው፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)፣ ከኦሮሚያ ክልል፤ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስ ፓርቲ( ኦፌኮ) እና ታጣቂው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እንዲሁም ከአፋር ክልል፤ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ተቃውሞ ገጥሞታል።
የአፋር ህዝብ ፓርቲ ትናንት ሐምሌ 24 ቀን ባወጣው መግልጫ፤ የሱማሌ ክልል ወቅርን አውግዞ፤ ውሳኔውን እንዲሽርና ለሠላም ግንባታ ህጋዊ መንገድ ብቻ እንድከተል አሳስቧል። የፌዴራሉ መንግስትና የፀጥታ አካላት ይህ ጉዳይ ከቁጥጥር ሳይወጣና ሌላ “ደም አፋሳሽ ጦርነት” ሳይቀሰቀስ በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን እንዲያፀና አሳስቧል።
በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግርስ (ኦፌኮ)፤ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገውንና ሞያሌ ከተማን የሚመለከቱ ለውጦችን ያካተተውን የአስተዳደር መልሶ ማዋቀር እቅድን “ከፋፋይ” ሲል ጠርቶ በጽኑ እንደሚያወግዝ አስታውቋል።
ይሁን እንጂ በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሱ አምስት ፓርቲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግርስን (ኦፌኮ) መግለጫ ተዋውመዋል። ፓርቲዎቹ ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ያወጣው መግለጫ “በውጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ የገባ ነው” በማለት “በጽኑ እንደሚያወግዙት” አስታወቀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8714

አዲሱ የሶማሌ ክልል መዋቅር በክልሉ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የሰላ ቀቃወሞ ገጠመው - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25/ 2017 ዓ/ም፦ የሶማሌ ክልል መንግስት አዲስ 14 ወረዳዎችን፣ ሁለት የዞን አስተዳደሮችን እና 25 ማዘጋጃ ቤቶችን ማዋቀሩን ተከትሎ በአፋር፣ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀቃወሙ። አዲሱ አስተዳደራዊ መዋቅር የጸደቀው ሐምሌ 19/ 2017 ዓ/ም የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 4ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው። የሶማሌ ክልል ኮሙዩኒኬሽን…
ዜና፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ስምረት ፓርቲ በድንበር ላይ በተፈጸመ ጥቃት እርስ በእርሳቸው ተወነጃጀሉ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን በአፋር ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ምላዛት አከባቢ የትግራይ ጸጥታ ኃይል ላይ "በአቶ ጌታቸው ረዳ በሚመራው ስምረት ፓርቲ አነሳሽነት ተፈጸመ" ባለው ጥቃት የአንድ የትግራይ የጸጥታ ኃይል አባል ህይወት ማለፉን አስታወቀ።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ጥቃቱ የተፈጸመው ረቡዕ ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ ሀይሉ አንዳይ ክንደያ የተባሉ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች አባል ተገድለዋል ብሏል። መግለጫው አያይዞም ጥቃቱ “በስምረት ፓርቲ አባላት የተቀነባበረ” ነው ሲል ከሷል።
ቢሮው አክሎም ስምረት ፓርቲ "ራሱን እንደ መፍትሄ አምጪ እያሳየ የሽብር ድርጊቶችን መፈጸም መጀመሩን" እና "ነጻ መሬት የሚል ሽፋን በመጠቀም በውጭ ኃይሎች የሚደገፍ አጀንዳ እያስፈጸመ" ነው ሲል ገልጿል።
የስምረት ፓርቲ በበኩሉ፤ የቀረበበትን ክስ “መሰረተ ቢስ” ሲል አስተባብሎ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ “በሙስናና በክልሉ አለመረጋጋትን በመፍጠር” ከሷል።
ተጨማሪ ለመመልከት፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8731

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ስምረት ፓርቲ በድንበር ላይ በተፈጸመ ጥቃት እርስ በእርሳቸው ተወነጃጀሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25/ 2017 ዓ/ም፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ በትግራይ ክልል ደቡብ ምስራቃዊ ዞን በአፋር ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ምላዛት አከባቢ የትግራይ ጸጥታ ኃይል ላይ “በአቶ ጌታቸው ረዳ በሚመራው ስምረት ፓርቲ አነሳሽነት ተፈጸመ” ባለው ጥቃት የአንድ የትግራይ የጸጥታ ኃይል አባል ህይወት ማለፉን አስታወቀ። የስምረት ፓርቲ በበኩሉ፤ የቀረበበትን ክስ “መሰረተ ቢስ” ሲል አስተባብሎ፤…
ዜና: #ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየቱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኮሚሽነሮች ልዑክ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን አስታወቀ፡፡
ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በተለያዩ መድረኮች ላይ ስለኮሚሽኑ የእስካሁን የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም በትግራይ ክልል ምክክር በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ ገለፃ አድርገዋል ተብሏል፡፡
በማንኛውም ሁኔታ መነጋገርና መመካከር እንደሚገባ የገለጹት ኮሚሽነሮቹ አክለውም "እንደ አንድ ሀገር ልጆች በመቀራረብ በትግራይም ሆነ እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች ለመፍታት መረባረብ እንደሚያስፈልግ" ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ የፓርቲ አመራሮች በበኩላቸው ደግሞ ኮሚሽኑ ፈታኝ ሁኔታዎችን በመቋቋም በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱን ለመጀመር ወደ ተግባር መግባቱ ተስፋ ሰጪ ጅማሮ እንደሆነ ጠቅሰው የምክክር ሂደቱ በፍጥነት ሊጀመር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
በተለይ በትግራይ የሚታዩ ውጥረቶች ተባብሰው ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመው በክልሉ ያለውን አውድ የሚያንጸባርቅ የምክክር ሥነ ዘዴ ተቀርጾ ሁሉንም ወገን አካታችና አሳታፊ የሆነ ምክክር እንዲካሄድ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመድረኮቹ ላይ ፓርቲዎቹ በትግራይ ክልል የምክክር ሂደቱ እንዲጀመር አስቻይ ሁኔታ በመፍጠርና በንቃት በመሳተፍ ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበት እንዲሰሩ ጥሪ መቅረቡን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት ነበር የተባለ 27.75 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር ዋለ
የጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት ነበር ያለው 27.75 ኪ.ግ የማመዝን ጥፍጥፍ ወርቅ በ #አዲስ_አበባ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ።
ወርቁን በተሽከርከሪ አካል ውስጥ ደብቀው በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች እና ሁለት ተሽከርካሪዎች በቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ በቱሉዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተይዘዋል ተብሏል፡፡
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር የዋለው ጥፍጥፍ ወርቅ ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት የቆየ እና በጉምሩክ የኢንተለጀንስ ባለሙያዎች የተያዘ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ ለቃሊቲ ጉምሩክ ባለሙያዎች ፣ አመራሮች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ አይደለም ተብሏል። በመሆኑም ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጠይቋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት ነበር ያለው 27.75 ኪ.ግ የማመዝን ጥፍጥፍ ወርቅ በ #አዲስ_አበባ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ።
ወርቁን በተሽከርከሪ አካል ውስጥ ደብቀው በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች እና ሁለት ተሽከርካሪዎች በቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ በቱሉዲምቱ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተይዘዋል ተብሏል፡፡
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር የዋለው ጥፍጥፍ ወርቅ ከአንድ ወር በላይ ክትትል ሲደረግበት የቆየ እና በጉምሩክ የኢንተለጀንስ ባለሙያዎች የተያዘ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ ለቃሊቲ ጉምሩክ ባለሙያዎች ፣ አመራሮች እና የፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ አይደለም ተብሏል። በመሆኑም ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጠይቋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: በትግራይ ክልል ቆላ ተንቤን በተከሰተ ድርቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች ሞቱ
በማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተንቤን ወረዳ በዚህ ሳምንት በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተገለፀ። በድርቁ በያከር አካባቢ ብቻ ከ18,000 በላይ የቤት እንስሳት ሲሞቱ፤ በመቶዎች የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት ደግሞ ወድሟል።
ይህም አሁን ላይ ከጦርነት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባላገገመው ክልሉ ውስጥ ረሀብ ሊመለስ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጎይቶም ገብረሐዋሪያ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ዝናብ ባለመኖሩ እና በመኖ እጥረት ምክንያት 184 ከብቶች፣ 900 አህዮች፣ ከ4,500 በላይ በጎች፣ ከ13,000 በላይ ፍየሎች ሞተዋል። አያይዘውም "እስከዛሬ ድረስ ዝናብ በአካባቢው አልጣለም"ሲሉ ገልጸው "ንቦችም ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል" ሲሉ አክለዋል።
እንደ እሳቸው ገለጻ በህፃናትና በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ የተመጣጠነ የምግብ እጥረት ምልክቶች፣ እንደ እብጠት ያሉ እና ሌሎችም ከረሃብ ጋር የተያያዙ ምልክቶች እየታዩ ነው።
በድርቁ ምክንያት 650 ሄክታር የእርሻ መሬት ሳይዘራ የቀረ ሲሆን 50 ሄክታር ሰሊጥ ደግሞ መብቀል አለመቻሉን ጠቁመዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8733

በትግራይ ክልል ቆላ ተንቤን በተከሰተ ድርቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶች ሞቱ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26/2817 ዓ/ም:- በማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተንቤን ወረዳ በዚህ ሳምንት በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተገለፀ። በድርቁ በያከር አካባቢ ብቻ ከ18,000 በላይ የቤት እንስሳት ሲሞቱ፤ በመቶዎች የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬት ደግሞ ወድሟል። ይህም አሁን ላይ ከጦርነት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባላገገመው ክልሉ ውስጥ ረሀብ ሊመለስ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል። የወረዳው የኢኮኖሚ…
ዜና: በየመን የባህር ዳርቻ የስደተኞች ጀልባ ተገልብጣ ከ60 በላይ #ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (IOM) ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በየመን የባህር ላይ ሰጥማ ከ60 በላይ ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን አስታወቀ።
ትናንት እሁድ ማለዳ ላይ ከሰጠመችው ጀልባ ውስጥ ከነበሩት 154 ስደተኞች መካከል 68ቱ ሲሞቱ፣ 74 የሚሆኑት ደግሞ እስካሁን ያሉበት አለመታወቁን የተመድ የስደተኞች ድርጅትን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
"በጀልባዋ ላይ የነበሩት ተሳፋሪዎች በሙሉ የኢትዮጵያ ዜጎች እንደነበሩ" የተገለጸ ሲሆን በየመን አብያን ግዛት የባህር ዳርቻ ላይ በደርዘን የሚቆጠሩ አስከሬኖች መገኘቱ በዘገባው ተመላክቷል።
በየመን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት ተወካይ የሆኑት አቤዱሳቶር ኢሶቭ በበኩላቸው 'ካንፋር ' በተባለ አካባቢ የ54 ስደተኞች አስክሬን በውቅያኖስ ዳር የተለያየ ቦታ ወድቆ መገኘቱን በሌላ ቦታ የተገኘ 14 አስክሬን ወደ ሆስፒታል መላኩን ተናግረዋል።
12 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፋቸው የተገለጸ ሲሆን የአከባቢው ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት በአሰሳ እና የማዳን ስራ ላይ መሰማራታቸው ተመላክቷል።
ጀልባዋ ስደተኞቹን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ወደ የመን ሲሆን ሀገሪቱ እንደ ሳዑዲ ዓረቢያ ባሉ የባህረ ሰላጤው አገሮች ለመድረስ ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መሸጋገሪያ ነች። የተመድ የስደተኞች ድርጅት እንዳስታወቀው፣ የመን በእርስ በርስ ጦርነት ብትታመስም የአፍሪካ ስደተኞችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያስተናገደች ይገኛል።

በሰው መነገድ ወንጀል ላይ የተሳተፉ 5 ሰዎች ሞት ተፈረደባቸው
በሰው መነገድ ወንጀል ላይ በተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወሰን መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና የብዙ የሰዎች ህይወት እየቀጠፈ ያለ ወንጀል ነው፡፡
በወንጀሉ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ወንጀለኞች በአዋጅ ቁጥር አንድ ሺህ 178 መሰረት የሞት ቅጣት፣ የዕድሜ ልክ እስራትና እስከ 25 ዓመት እስራት ያስቀጣል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በሂደቱ የተሳተፉ 5 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ እንዲወስን መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በሰው የመነገድ ወንጀል ለመከከላከልና ለመቆጣጠርም የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በክልሎች መካከል ቅንጅትና ትብብር የሚፈጥሩ ስራዎችና መመሪያ የማጽደቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም በህገወጥ ድርጊቱ በስፋት ተጠቂ ለሆኑት ወጣቶች በሀገር ወስጥ የስራ እድል ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ሰው የመነገድና በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልም ድንበር ተሻጋሪ የተደራጀ ወንጀል መሆኑን አንስተው፤ ይህንንም ለመቆጣጠር ከጅቡቲ፣ ኬንያና ማላዊ ጋር ዓለም አቀፍ ትብበር ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ባለፈው በጀት ዓመት የተወሰደው የህግ እርምጃ እንደሀገር የተሰጠውን ትኩረት ማሳያ ነው፡፡
በቀጣይም የተሻለ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
(ኢፕድ)