Addis Standard Amharic
17.6K subscribers
4.02K photos
101 videos
3 files
3.24K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ከ100 ሺህ ቶን በላይ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋለ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

#አዲስ_አበባ በዓመት ከመነጨው 100 ሺህ 585 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።

በከተማዋ 325 የመልሶ መጠቀም ማህበራት የተቋቋሙ ሲሆን በዓመት ከተመረተው 983ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ 100 ሺህ 585 ቶኑን መልሰው ጥቅም ላይ ማዋላቸውን አስታውቀዋል።

አምስት ሺህ 460 ቶን ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ስራ ማዋል ተችሏል ብለዋል።

በጽዳት ዘመቻ 675 ሺህ 384 ነዋሪዎችና ሁለት ሺህ 540 ተቋማት በሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳትፈዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ በተሰራው የጽዳት ስራ በከተማዋ የሚከሰቱ የወረርሽኝ ምጣኔዎችን መቀነስ፣ ወንዟችና አካባቢን ከብክለት መታደግ፣ ቆሻሻን ወደሀብት መቀየር እና ከተማዋን ውብና ጽዱ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

ቆሻሻን ከመሰብሰብ ባለፈ በአግባቡ የማስተዳደርና መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

(ኢፕድ)
በ354 የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርገዋል በተባሉ 354 ተጠርጣሪ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ገለፀ።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዲበራ ፉፋ፤ ማደያ ውስጥ ነዳጅ እያለ የለሚ ብለዋል በተባሉ እና ከማደያ ለተሽከርካሪዎች መሸጥ ሲገባቸው በጀሪካንና በበርሜል ሲሸጡ የተገኙ ተጠርጣሪዎቹ ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከታሪፍ ማሻሻያ ፍላጎት ጋር በተያያዘ በወራት መጨረሻ ላይ በማደያዎች አካባቢ የሚታዩትን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሕግ ማስከበር ስራዎች በስፋት እየተሰሩ እንደሚገኝ አንስተዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተደረጉ ጠንካራ የቁጥጥር ስራዎችም በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በወራት መጨረሻ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ የተሸከርካሪ ሰልፎችን መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

ከነዳጅ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች በኢትዮ ቴሎኮም በኩል የለማውን ጂፒኤስ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አቶ ዲበራ ጠቁመዋል፡፡
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid05Wj5xPeFaPdaprrd2TYJLghp9WTLNPiFYjNWjD7oAFjeJ5z5BcZ9mLszEipnb96Rl
ዜና፡ የ #ቤላሩስ ፕሬዚዳንት የ #ኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ከደገፉ በኋላ ከአዲስ አበባ ጋር ያላቸው የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብር መጠናከሩን አመላከቱ

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ። በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት ጠንካራ “ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት” እንዳላቸውም ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ለእኛ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት በጣም አስፈላጊ አገሮች መካከል አንዷ ናት” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ቤላሩስ የቴክኖሎጂ፣ የግብርና እና የምህንድስና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቤላሩስ ለኢትዮጵያ የግብር ማሽነሪዎችን ድጋፍ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል።

በጥቅምት ወር የቤላሩሱ መሪ ኢትዮጵያ የባህር መዳረሻ ለማግኘት ያላትን ፍላጎት በብርቱ ደግፈዋል። የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው፤ ሉካሼንኮ የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎትን የሚቃወሙ “ፍጹም ሞኞች" ናቸው ብለዋል። አክለውም "በጦርነት ወይም በድርድር ኢትዮጵያ ወደ ባህር በር ትደርሳለች። በእርግጥም በሰላማዊ መንገድ ቢሆን የተሻለ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

መሉ ዘገባ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8680
ዜና: የ #ኢትዮጵያ እና #ጂቡቲ 11ኛው የጋራ መከላከያ ኮሚቴ ስብሰባ ትኩረቱን የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርን ማሳደግ ላይ አድርጎ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ የጋራ መከላከያ ኮሚቴ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ማካሄድ ጀመረ።

ስብሰባው እየተካሔደ ያለው በመከላከያ ውጪ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹና በጂቡቲ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ ኮሎኔል ማጆር (ሜጄር ጄነራል) አብዱረህማን አብዲ በተመራ ወታደራዊ ልዑካን መካከል ነው።

እንዲሁም በጂቡቲ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አታሼ ሜጄር ጄነራል ተስፋዬ ወልደማርያም በመድረኩ ላይ የተገኙ ሲሆን ከሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ሀላፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

ስብሰባው አሁን ያለውን የጸጥታ ትብብር ስራዎች አፈፃፀም በመገምገም ለወደፊት በሚሰሩ ስራዎች ላይም አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም በ10ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ስምምነት የተደረገባቸውን የሰላም እና ጸጥታ ስራዎች አፈጻጸም በመገምገም ላይ ትኩረት እንደሚያደረግ የተጠቀሰ ሲሆን፤ “የሁለትዮሽ ወታደራዊ ትብብርን ለማሳደግ እና ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ” ያለመ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ ላይ “ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያላቸው ሀገሮች መሆናቸውን” የገለፁት ሜጄር ጄነራል ተሾመ ገመቹ፤ ለልዑካን ቡድኑ “ሁለተኛ ሀገራችሁ ወደሆነችው ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁ” ብለዋል።

https://www.facebook.com/100076048904470/posts/763368192874804/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ዩናይትድ ኪንግደም #እስራኤል ቅድመ ሁኔታዎችን ካላሟላች ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና እንደምትሰጥ አስታወቀች

ዩናይትድ ኪንግደም እስራኤል "በጋዛ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለማስቆም ተጨባጭ እርምጃዎችን" ካልወሰደች በመስከረም ወር ለፍልስጤም እውቅና እንደምትሰጥ ጠቅላይ ሚኒስተር ኪር ስታርመር ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነትን ማድረግ፣ የሁለት አገር መፍትሄ የሚያመጣ ዘላቂ ሰላም ማስፈን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ አቅርቦቱን እንደገና እንዲጀምር መፍቀድን ጨምሮ፣ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አለባት፤ አለዚያ እንግሊዝ እርምጃውን በመስከረሙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ትወስዳለች ብለዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እርምጃው "ለሐማስ አስከፊ አሸባሪነት ሽልማት ነው" ብለዋል።

የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ከዚህ ቀደም ለፍልስጤም እውቅና መስጠት እንደ የሰላም ሂደት አካል ከፍተኛ ተጽዕኖ በሚያሳድርበት ጊዜ ሊደረግ ይገባል ሲል ተናግሯል።

ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍጥነት እርምጃ እንዲወስዱ ከራሳቸው የፓርላማ አባላት ጭምር ጫና እየደረሰባቸው ነው።

አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ኪር፣ እቅዱን አሁን እያስታወቁ ያሉት በጋዛ ስላለው "ትዕግሥት የሚፈትን ሁኔታ" እና "የሁለት መንግሥታት የመፍትሄ ዕድሉ እየቀነሰ ነው" የሚል ስጋት ስላደረባቸው ነው።

ባለፈው ሳምንት ፈረንሳይ በመስከረም ወር ለፍልስጤም መንግሥት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cx29n51xq1do
ዜና: በሩሲያ የባህር ዳርቻ የተከሰተውን እጅግ ከፍተኛ የተባለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በፓሲፊክ ውቅያኖስ ዙሪያ ሱናሚ ይከሰታል በሚል ማስጠንቀቂያዎች እየተሰጡ ነው

ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ላይ በሩሲያ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ የተከሰተውን 8.8 ማግኒቲዩድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በሰሜናዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ውስጥ በርካታ ሱናሚዎች ይከሰታሉ በሚል ከሃዋይ እስከ ኒውዚላንድ ያሉ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያዎችን አውጥተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በጎርጎሮሳውያኑ 2011 በጃፓን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ላይ የደረሰውን ፍንዳታ ካስከተለው የመሬት መንቀጥቀጥ ወዲህ በዓለም ላይ ከተመዘገቡት የመሬት መንቀጥቀጦች ሁሉ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

የፓሲፊክ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማዕከል የመሬት መንቀጥቀጡ በሁሉም የሃዋይ ደሴቶች የባህር ዳርቻዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ሱናሚ አስነስቷል ብሏል።

የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎች ከተላለፉባቸው ሀገራት መካከል ራሽያ፣ ጃፓን፣ ታይዋን፣ ቻይና፣ ሃዋይ፣ ጉአሜ፣ ቶንጋ፣ ካሊፎርኒያ፣ አላስካ፣ ኦሪገን፣ ዋሽንግተን፣ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ፣ ሜክሲኮ፣ ፔሩ እና ኢኳዶር ተጠቃሽ ናቸው።

የፊሊፒንስ ባለስልጣናት በአርኪፔላጎ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ግዛቶች እና ከተሞች ከአንድ ሜትር ያነሱ የሱናሚ ሞገዶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፤ ሰዎችም ከባህር ዳርቻ አካባቢዎች እንዲርቁ መምከራቸውን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ፍራንስ 24 ዘግቧል።

======
የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ በ #ማዕከላዊጎንደር ዞን በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ ከ1200 በላይ እንስሳት ሞቱ፤ በ #ደቡብ_ጎንደርም ከ175ሺህ በላይ ሰዎች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል

በማዕከላዊ ጎንደር "የቡና ቁርስ የምትሆን አንዲት ዳቦ ተቃምሰው የሚያድሩ አሳዛኝ እናቶች አሉ"_ነዋሪ


#አማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ ወረዳ በሚገኙ ስድስት ቀበሌዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ 32 ሺህ ሰዎች በምግብ እጥረት ሲጎዱ፤ ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ዋሲሁን ከፍያለው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

የዝናብ እጥረቱ በምዕራብ በለሳ ወረዳ ከሚገኙ 32 ቀበሌዎች ቆላማ በሆኑ አከባቢዎች መከሰቱን የገለጹት አቶ ዋሲሁን ችግሩ በይበልጥ በስድስት ቀበሌዎች ማለትም በሳሚ፣ ላቫ ማርያም፣ አሳውጋሪ፣ ጃንዳብ፣ ላየ እና ሴራ በተባሉ ቀበሌዎች አስከፊ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ በምዕራብ በለሳ ወረዳ አርባያ ከተማ ዙርያ አርሶአደር፤ “መንግስት በሁለት ወር የሚሰጠን ማሽላ አለች በሷ ነው እንግዲህ እንዳይሞትም እንዳይዳንም ሆነን የምንኖረው። የሚለበስ የለም ራቁት ነው። ዞሮ ዞሮ ግን መቼም መኖር ከተባለ እስኪሞቱ ድረስ የበላም ኑሮ ነው ያልበላም ኑሮ ነው" ሲሉ በአከባቢው ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ ደቡብ ጎንደር ዞን 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች 175ሺህ በላይ ወገኖች ለድርቅ መጋለጣቸውን የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8686
#ኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የኤርትራን መንግሥት በትጥቅ ለመታገል በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ

የኤርትራን መንግሥት ለመጣል ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የገለፀው "የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ" ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የትጥቅ ትግል ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ አባል እና ቃል ዐቀባይ አሊ መሐመድ ዑመር፤ "የኢትዮጵያ መንግሥት የመንቀሳቀስ እና የመናገር ዕድል ሰጥቶናል" ሲሉ ገልጸው፤ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ጽ/ቤት መክፈታቸውንና አዲስ አበባ ላይም ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

ቃል ዐቀባዩ፤ ባለፈው ሳምንት በዋናነት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና ጅቡቲ የሚገኙ አፋሮችን በሚመለከት እና በአካባቢው ቀጣናዊ ኹኔታዎች ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ መደረጉንና ድርጅታቸውም መሳተፉን ገልፀዋል።

"የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ" ከ11 ዓመታት በፊት እ.አ.አ በ 2014 ስዊድን ውስጥ ተመሥርቶ ለዓለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት ኤርትራ ውስጥ ስላለው "ፈታኝ" ያሉት ኹኔታ ሲያስገነዝብ፣ ሲሰባሰቡም መቆቱን የገለፁት አሊ መሐመድ ፤ አሁን ወደዚህ የመጡበት ምክንያት ምን እንደሆነም አስረድተዋል።

https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0AuHYyfLLQjC7srpHtKtP658DsDzoEbseKbLLbySvyzrNpKR5XpcD1WD93GoNE3jkl
ዜና: ሂዩማን ራይትስ ዎች የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅ ውድቅ እንዲደረግ አሳሰበ፤ የ #ኢትዮጵያ አጋሮችም ረቂቅ ህጉን እንዲያወግዙት ጥሪ አቅርቧል

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማሻሻያ ረቂቅን ውድቅ እንዲያደርግ አሳሰበ።

የመብት ተሟጋች ድርጅቱ ማሻሻያው "ለፌደራል መንግስት ሰፊ ስልጣን የሚሰጥ እና የሲቪክ ምህዳርን በእጅጉ የሚገድብ ነው" ሲልም አስጠንቅቋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋሮች ረቂቁን እንዲያወግዙ እና ማንኛውም የህግ ማሻሻያ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ደረጃዎች ጋር መጣጣም እንዳለበት እንዲያሳስቡ ጥሪ አቅርቧል።

የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ላቲሺያ ባደር፤ “በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበራት ሕግ ላይ የቀረቡት ማሻሻያዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት የመጡትን ለውጦች የሚያፈርስ እና ወደ ኋላ የሚመልስ ነው” ብለዋል።

አክለውም ረቂቅ ህጉ ለሲቪል ማህበራት ተሳትፎ እና ለመብቶች ተሟጋች ድርጅቶች ከባድ ስጋት እንደሚፈጥርም አስጠንቅቀዋል። “እነዚህን ማሻሻያዎች መቀበል የሲቪክ ምህዳርን የሚጎዳ ይሆናል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሙሉ ዘገባ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8689
በፎቶ፡ የአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የ2017 የአርንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን "5 ነጥብ 5 ቢሊየን" ችግኞች መተከላቸውን" ብሔራዊ አረንጓዴ አሻራ ቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ ተገልጿል።

በተከላው በመርሃ-ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን ሰዎች ተሳታፊ መሆናቸውም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመህርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ቢሊየን ገደማ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን፤ ይህም ባለፉት ሰባት ዓመታት የተተከሉ ችግኞችን መጠን 48 ቢሊየን ማድረስ የሚያስችል ነው” ብለዋል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ ዕቅዳችን 50 ቢሊየን ችግኝ መትከል ነው ሲሉም በመህርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።