Addis Standard Amharic
17.6K subscribers
4.02K photos
101 videos
3 files
3.24K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና: #ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት #አረብ ኤምሬት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከ #ዱባይ ፖሊስ የዘመናዊ ሞተር ሳይክሎች ድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከዱባይ ፖሊስ ለቪአይፒ ጥበቃና እጀባ እንዲሁም ለፈጣን መንገድ (Highway) ትራፊክ ቁጥጥር የሚያገለግሉ ዘመናዊ ሞተር ሳይክሎችን በድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ድጋፉን አስመልክተው ዛሬ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ "ከሪፎርም ወዲህ በብዙ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ እየዘመነ የመጣ ተቋም መሆኑን" ገልፀዋል።

አክለውም ተቋሙ በቅርቡ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም ለሰርቪላንስና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ድሮኖችን መታጠቁን ጠቅሰው አሁን ላይ ደግሞ ለእጀበና ለፈጣን መንገድ ትራፊክ ቁጥጥር የሚያገለግሉ ዘመናዊ የሞተር ሳይክሎችን በድጋፍ ማግኘቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶች የማስተናገድ አቅሟ እያደገ መምጣቱን ያነሱት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ በቀጣይ ወራቶች በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሀገራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲከወኑ ለማስቻል በድጋፍ የተገኙትን እና ሌሎች ዘመናዊ የሎጂስቲክ አቅሞችን በመጠቀም እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

https://www.facebook.com/share/1CKN2qKg6N/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በ #አዲስ_አበባ መካሄድ ጀመረ

#ኢትዮጵያ እና ጣልያን በጋር ያዘጋጁት 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ፣ የዓለምአቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዝዳንት አልቫሮ ላሪዮ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሐፊና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን ጨምሮ በርካታ ሚኒስትሮችና ባለድርሻ አካላት የጉባኤው ተሳታፊ ናቸው።

የምግብ ሥርዓት ጉባኤው አጀንዳዎች በዓለም የምግብ ሥርዓት ላይ በተገኙ ለውጦችና ተግዳሮቶች ላይ እንደሚሆን ተገልጿል። ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን ያገኟቸውን ስኬቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች ላይ ሪፖርት ያቀርባሉ፤ በሮሙ ጉባኤ የገቧቸው ቃሎች የደረሱበትን ደረጃ ይገመግማል እንዲሁም አቅጣጫዎችንም ያሰቀምጣል ተብሏል።

ለምግብ ስርዓት ሽግግር ስራዎች በአነስተኛ ወለድ የፋይናንስ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ፣ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀም እና ሀገር በቀል የፋይናንስ መሰብሰብ አቅምን ማጎልበት ላይ ምክክሮች እንደሚደረግ ኢፕድ ዘግቧል።

ከጉባኤው ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብሮች፣ የሁለትዮሽ ውይይቶችና ጉብኝቶች ይደረጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ዕለታዊ ዜና፡ በ #አዳማ ከተማ የ #ህንድ ዜጋ አስክሬን ተገኘ፤ ፖሊስ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

በአዳማ ከተማ ባሳለፍነው ቅዳሜ አስክሬኑ የተገኘው የህንድ ዜጋ አሟሟትን በተመለከተ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ።

ኤን ቪ ሱባ ራኦ የተባለው የህንድ ዜጋ ለካልፓታሩ ፕሮጀክት የሚሰራ የፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ሰራተኛ ሲሆን አስክሬኑ ያለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 19፣ 2017 ዓ/ም በአዳማ ከተማ በፖሊስ መገኘቱን በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ሸዋዬ ዳቻሳ የውጭ ሀገር ዜጋው ህይወት ማለፉን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠው፤ የክስተቱን መንስኤና ሁኔታ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8664
#አልሸባብ#ኢትዮጵያ ጦር ያስለቀቀውን ከተማ ከሶማሊያ ሠራዊት መልሶ ተቆጣጠረ

የሶማሊያው ታጣቂ ቡድን አልሸባብ ከ11 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ጦር እንዲለቅ የተደረገውን እና በሶማሊያ መንግሥት ሠራዊት ስር የነበረችውን ማሃስ ከተማ ዳግም በቁጥጥሩ ስር ማስገባቱ ተሰማ።

በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ክልል ውስጥ የምትገኘው ማሃስ ትናንት እሁድ ከባድ ውጊያ መካሄዱን ቢቢሲ ሶማሊኛ ዛሬ ማለዳ ባወጣው ዘገባ አመላክቷል።

በከተማዋ በመንግሥት ወታደሮች እና ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው በሚነገርለት በአልሸባብ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደው ከባድ ውጊያ በርካቶች መሞታቸው ተሰምቷል።

አልሸባብ በከተማዋ ላይ ጥቃት የፈጸመው ተቀጣጣይ ፈንጂ በጫኑ መኮኖች በመታገዝ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሶማሊኛ ተናግረዋል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር በአካባቢው ስላለው ግጭት ባወጣው አጭር መግለጫ የአካባቢ እና የመንግሥት ኃይሎች በርካታ የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደላቸውን ገልጿል።

ነገር ግን ሚኒስቴሩ ምን ያህል ታጣቂዎች እንደተገደሉ የገለፀው ነገር የለም። የአከካባቢው ነዋሪዎች በአልሸባብ እና በመንግሥት ወታደሮች መካከል በነበረው ውጊያ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/c8e1l4874epo
ከ50 በላይ አባላትን ያካተተ የሰላም ልዑክ #መቐለ መግባቱ ተገለፀ

#ኢትዮጵያ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና ነጋዴዎችን ያካተተ የሰላም ልዑክ መቐለ ገባ።

ልዑካን ቡድኑ መቀለ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በ #ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል አሰፋ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት ልዑኩ ከፕሬዝዳንት ታደሰ እና ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር መገናኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በተጨማሪም ልዑኩ ክፍፍሎችን ለማጥበብ እና ሰላምን ለማጠናከር ከፖለቲካ፣ ከሃይማኖት እና ከሲቪክ መሪዎች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል።

ይህ ጉዞ በዚህ ወር ወደ ትግራይ የተደረገው ሁለተኛው የሰላም ልዑክ ጥረት ነው። በቅርቡ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተመራ ልዑክ ወደ መቀለ በማምራት ከትግራይ ክልል መሪዎች ጋር ተወያይቷል።

የሃይማኖት አባቶቹ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከፌደራል እና ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02LFHz4aGLxMzsBN48j3pqdFxc35JxizNcB9RLrfEi5sRdaAMvLu8coNeD7WkNikKdl
ዜና: በእስራኤል የሚገኙ ሁለት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች "#እስራኤል#ጋዛ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመች ነው" አሉ

በእስራኤል የሚገኙ ሁለት አንጋፋ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሆኑት በትሴለም (B’Tselem) እና 'ፒዚሽያንስ ፎር ሂውመን ራይትስ' እስራኤል በጋዛ በሚገኙ ፍልስጤማውያን ላይ "የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀመች ነው" ሲሉ አስታወቁ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶቹ ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጡት ሪፖርት እስራኤል ባለፉት ሁለት ዓመታት በተካሄደው ጦርነት መካከል በጋዛ የሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ፍልስጤማዊ በመሆናቸው ብቻ የጥቃት ኢላማ አድርጋቸዋለች ሲሉ ከሰዋል።

በዚህም በፍልስጤማውያን ላይ ከፍተኛ እና በአንዳንድ ሁኔታዎችም የማይጠገን ጉዳት ደርሷል ያሉት የመብት ተሟጋች ድርጅቶቹ፤ አያይዘውም የእስራኤል የምዕራባውያን አጋሮች ይህንን ድርጊት የማስቆም "ህጋዊና ሞራላዊ ግዴታ አለባቸው" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ከተፈጸሙት ወንጀሎች መካከልም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋውያን መገደላቸው፣ የግዳጅ መፈናቀልና የምግብ እጥረት፣ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶች እና የሲቪል መሠረተ ልማቶች መውደማቸው ፍልስጤማውያንን ከጤና አገልግሎት፣ ከትምህርት እና ከሌሎች መሰረታዊ መብቶች እንዲገፈፉ መንሰዔ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

የበትሴለም ዳይሬክተር የሆኑት ዩሊ ኖቫክ "እየተመለከትን ያለነው አንድን ቡድን ለማጥፋት ታስቦ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸም ግልጽና ዓላማ ያለው ጥቃት ነው" ሲሉ ገልጸው፤ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርበዋል።

https://www.facebook.com/share/1VaQBu1Wsm/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ዜና፡ “በመንግስት ላይ ተገቢውን ጫና ለመፍጠር ለምናደርገው ትግል መራጩ ህዝብ ከጎናችን እንድትቆሙ” ሲል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኮክሰ ጠየቀ

#ኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ፤ በአገራችን ያንዣበበው አደጋ ለመቀልበስ ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍንና መጪው ምርጫ ነጻ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ ይሆን ዘንድ “በገዢው ፓርቲ/መንግስት/ ላይ ተገቢውን ጫና ለመፍጠር ለምናደርገው ትግል መራጩ ህዝብ የምናቀርበውን ጥሪ እንድትከታተሉና ከጎናችን እንድትቆሙ” ሲል ጠየቀ።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (አፌኮ)፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲን (ኢሕአፓ) ጨምሮ ስምንት ፓርቲዎችን ያካተተው ኮክሱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ "ጥያቄዎቻችን ከፖለቲካ ጥያቄ ባሻገር የአገር-አድን ፣የህዝብ መድህንነት አጀንዳ ናቸውና፤ የሲቪል ማኅበረሰብ አባላት በሁሉም መድረኮች፣ በሙሉ አቅማችው ከፓርቲዎቹ ጎን እንዲሰለፉ” በማለት ጥሪ አቅቧል።

ፓርቲዎቹ፤ ከመጪው ምርጫ በፊት የቦርዱ “ሀጋዊ የአሰራርና ተቋማዊ ችግር እስካልተፈታ ድረስ ለምርጫ መዘጋጀት የሚለው ሀሳብ ትርጉም አልባ ይሆናል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በእነዚህ ሁኔታዎቸ “ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ሊኖር አይችልም” ያለው መግለጫው፤ “እውነተኛ ሪፎርም ከሌለ በኢትዮጵያ ተኣማኒ፣ አካታች፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሊኖር አይችልም” ብሏል።

ሙሉ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8667
ዜና: የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነጻ የህክምና አገልግሎት መስጠት ጀመረ

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክረምት ነጻ የበጎ ፈቃድ የጤና ምርመራ እና የሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

ከሐምሌ 21 እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባሉት ሰባት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው አገልግሎት ከፍለው መታከም የማይችሉ ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በአገልግሎቱ ማስጀመርያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ፤ ኮሌጁ ማሕበረሰቡን በዚህ መንገድ በተጠናከረ መንገድ ለማገልገል ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

አክለውም የክረምት ነጻ በጎፈቃድ ምርምራ እና የሕክምና አገልግሎት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ጀማል ሺፋ በበኩላቸው፥ 50,000 የሚደርሱ ዜጎችን በሰሞኑ የጤና አገልግሎት ነጻ ሕክምና እንዲያገኙ እቅድ መያዙን ገልጸው፤ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው የጤና ምርመራ ማንኛውም ሰው አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ለቀዶ ሕክምና ለማግኘት ይጠባበቁ ከነበሩት መካከል በቁጥር 200 የሚደርሱት በዚህ ሳምንት አገልግሎቱን እንዲያገኙ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

======
የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: በአዲስ አበባ በአልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን #ፖሊስ አስታወቀ

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ “በተደረገ ፍተሻ”፣ “አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች” ጋር መያዙን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤  “ኦፕሬሽኑ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ የሚደረገው ጥረት አካል ነው” ያሉ ሲሆን፣  “የመዲናዋን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ እና የተጠና ፍተሻና አሰሳ እንደሚደረግ” ገልጸዋል።

የጦር መሳሪያዎቹ “መኝታ ቤቶችን በሚያከራዩ ቤቶች ውስጥ የተያዙ” ሲሆን፣ እነዚህ ቤቶች “ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ያለባቸው  እና ውስን ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሆናቸውን” የከተማዋ ፖሊስ አመልክቷል።

ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ነበሩ ያላቸው ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ተገቢው ምርመራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባብ ለማስጠየቅ እንደሚሰራ ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: https://addisstandard.com/Amharic/?p=8674&amp=1
ዜና: #ኢትዮጵያ እና #ቤላሩስ የግብርና ማሽነሪዎችን በጋራ ለመገጣጠም የሚያስችሉ ጥረቶች ላይ እየመከሩ መሆናቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ የእርሻ ማሽነሪዎችን በጋራ ለመገጣጠም የሚያስችሉ የሽርክና ስምምነቶችን ለማቋቋም እየተነጋገሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከቤላሩሱ ፕሬዝዳንት ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።

በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ሀገሮች የቤላሩስ የእርሻ ማሽነሪዎችን በቤላሩስ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ በጋራ ለመገጣጠም የሚያስችሉ የሽርክና ሥራዎችን ለማቋቋም በዝርዝር ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ አክለውም "በሀገራችን ተገጣጥመው የተሰሩ ማሽነሪዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለገበያ እንደሚቀርቡ ተስፋ እናደርጋለን" ያሉ ሲሆን "በዚህ ረገድ የሚደረጉ ድርድሮች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃሉ ብዬ እጠብቃለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

የቤላሩስ ማሽነሪዎች በኢትዮጵያ መልካም ስም እንዳላቸው የጠቆሙት ሚኒስትሩ አያይዘውም “እነዚህ መሳሪያዎች በጣም አስተማማኝ፣ ዘላቂ እና ለአጠቃቀም ቀላል ናቸው። የእኛ አርሶአደሮችም ለማሽነሪዎቹ ጥሩ አስታየት ነው ያላቸው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትብብሩ ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያላቸውን ግንኙነት በማጠናከር ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ ከቤላሩስ ጋር በሚኖራት ግንኙነት የግብርና ዘርፏን ለማዘመን ፍላጎት እንዳላት የቤላሩስ የመንግስት የዜና ወኪል ቤልታ ዘግቧል።