በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ በተደረገው የ7.7 ቢሊዮን የዘረፋ ሙከራን በተመለከተ በሰራነው ዘገባ ላይ የተሰጠ ማብራሪያ
ሐምሌ 15/ 2017 ዓ/ም “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ አጭበርብረውኛል በባላቸው 14 ግለሰቦች ላይ ክስ መሰረተ፤ ሁለቱ የደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ናቸው” በሚል ርዕስ ለአንባብያን ያደረስነው ዘገባ ላይ ክሱ የተመሰረተው በባንኩ አለመሆኑን በመገንዘብ በዘገባው ላይ ማስተካካያ አድርገናል።
ዘገባውን በተመለከተ ባንኩ በዕለቱ ለአዲስ ስታንዳርድ መደረግ ያለባቸውን ማስተካከያዎችን ጠቁሟል። በጥቆማውም መሰረት በዕለቱ ከሱ የተመሰረተው የፌ/ዐ/ሕግ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት መሆኑን በመግለጽ ማስተካከያ ተደርጓል።
ባንኩ በዛሬው ዕለት ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ደብዳቤ “ዘገባው ለተወሰኑ ሰዓታት አየር ላይ ከቆየ በኋላ እዚያው ላይ የማጭበርበር ሙከራ መሆኑንና ክሱንም ያቀረበው የፌ/ዐ/ሕግ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት መሆኑን በሚገልፅ መልኩ ማስተካከላችሁን እንደ በጎ እርምጃ ወስደነዋል” ሲል ገልጿል።
ይሁን እንጂ ቀደም ብሎ የነበረው ዘገባ ስህተት ያለበት መሆኑንና በባንኩ ጥቆማ መሰረት እርማት ማድረጋችን በግልፅ ባለማሳወቃችን ኣንባብያን የዘገባዉን ማሻሻያ ልብ ያላሉት መሆኑን በመግለጽ በግልጽ ማስተካካያ መደረጉን እንድናሳውቅ ጠይቋል።
በዚህም መሰረት 1ኛ በተጠርጣረዎች ላይ ክስ የመሰረተው ባንኩ ሳይሆን በፌ/ዐ/ሕግ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት በመሆኑን በይፋ ልናሳውቅ እንወዳለን።
2ኛ በዘገባው ባንኩ ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ “አጭበርብረውኛል አለ" በሚል የተጠቀሰውን “የማጭበርበር ሙከራ” በሚል እንዲስተካከልለት በጠየቀው መስረት ማስተካከያ አድርገናል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ግብጽ ኢትዮጵያን ለማደናቀፍ እና ውሃና አፈሩን ለብቻዋ ለመጠቀም የማታደርገው እንቅስቃሴ የለም” _ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ግድቡ ያደረጉትን ንግግርና የግብፅ ተጽዕኖን በተመለከተ ያደረጉት ገለጻ።

ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ገለፀ
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው ዛሬ በሰጡት ማብራሪያ በተገኘው ገቢ የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ73 በመቶ እድገት ማሳየቱን የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በዚህም ተጨማሪ 68 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የቴሌ ብር ደንበኞች ቁጥር 54 ነጥብ 8 ሚሊየን መድረሱና በበጀት ዓመቱ በቴሌ ብር 2 ነጥብ 3 ትሪሊየን የገንዝብ ዝውውር መደረጉም ተገልጿል። አሁን ላይ የቴሌ ብር የገንዘብ ዝውውር 4 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር ደርሷል ብለዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 512 ከተሞች የ4 ጂ እንዲሁም 16 ከተሞች ደግሞ የ5ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት ማግኘታቸውን አብራርተዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡
ፍሬሕይወት ታምሩ 462 ሺህ የሳይበር ጥቃት ሙከራ መደረጉን ጠቅሰው በተገነባው የሳይበር ሴክዩሪቲ አሰራርም ሙከራዎችን ማክሸፍ ተችሏል ብለዋል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላለፈ
ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ጠበቆች ከመጋረጃ ጀርባ ምስክር እንዳይሰማ የይግባኝ አቤቱታውን ያቀረቡት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን ጠበቃው ተናግረዋል።
በወቅቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለሐምሌ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ያስታወሱት ጠበቃው፤ ይሁን እንጂ እስከ ሐምሌ 29 የሚቆይ ከሆነ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከመጋረጃ በስተጀርባ ያለውን ምስክር ለመስማት ለትናንት ሐምሌ 16 ቀጠሮ በመያዙ በተከሳሽ ላይ "የማይተካ ጉዳት ያደርሳል" በሚል ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በድጋሚ ደብዳቤ አቤቱታ ማቅረባቸውን አመልክተዋል።
በዚህም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አስታውሰው ይህንኑ የእግድ ትዕዛዝ ይዘን ትናንት ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ችሎት ላይ ምስክር ከመሰማቱ አስቀድሞ አቀረብን ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8653

Addis standard
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ አስተላለፈ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17/ 2017 ዓ/ም፦ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ ሊደረግ የነበረው የምስክር አሰማም ሂደት እንዲታገድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን የተከሳሾች ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የሚገኙበት የክስ መዝገብ…
ዜና፡ “በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ በሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱ ሰዎች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል” - #ፌደራል ፖሊስ
የፌደራል ፖሊስ በውጭና በሀገር ውስጥ ሆነው በማህበራዊ ሚዲያ ሀገሪቱን የብጥብጥና የሁከት ማዕከል ለማድረግ የሚዲያ ዘመቻ በሚያካሄዱት ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተጠናከረ ኦፕሬሸን ይካሄዳል ሲል አስታወቀ።
ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ሙከራ የሚያደርጉ ግለሰቦች እና ቡድኖችን ለሕግ የማቅረብ ሥራን አጠናክሬ እቀጥላለሁም ብሏል።
“በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያ እንዲሁም በሁሉም መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ አሰሳና ፍተሻ እንደሚካሄድ ገልጿል፤ ዋነኛ ትኩረቴ “በፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይ” ነው ሲል አስታውቋል።
ፌደራል ፖሊስ ይህንን ያስታወቀው በቀጣይ ሦስት ወራት (ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም) በኢትዮጵያ የሚካሄዱ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በተዘጋጀ የፀጥታ ዕቅድ ላይ በተደረገ ውይይት መሆኑን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትም ከመከላከያ ሠራዊት፣ #ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሪፐብሊካን ጋርድ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተውጣጡ ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሮች መሆናቸውን ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ውይይቱን በመሩበት ወቅት በቀጣይ ሀገራችን ከሐምሌ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም የምታስተናግዳቸውን ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ሁነቶች በሰላም እንዲከናወኑ ከእንግዳ አቀባበል ጀምሮ ስምሪቱን በተደራጀ መልኩ መምራትና ማስተባበር እንደሚያስፈልግ መናገራቸውንም መረጃው አካቷል።

#ፈረንሳይ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና እንደምትሰጥ ፕሬዚዳንት ማክሮን ገለጹ
ፈረንሳይ በመጪው መስከረም ፍልስጤምን በአገርነት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ገለጹ። ፈረንሳይ ለፍልስጤም በአገርነት ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያ የቡድን ሰባት አባላት አገር ያደርጋታል።
ማክሮን "ፈረንሳይ ለመካከለኛው ምስራቅ ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ባላት ታሪካዊ ቁርጠኝነት፤ ፍልስጤምን በአገርነት እውቅና ለመስጠት ወስኛለሁ" ሲሉ ትናንት ሐሙስ ዕለት በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።
ፍልስጤምን በአገርነት በይፋ እውቅና የመስጠት እወጃው የሚደረገው በኒውዮርክ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ እንደሆነም አስፍረዋል።
"በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ አስፈላጊው ነገር የጋዛ ጦርነት አክትሞ የሲቪሎችን ህይወት መታደግ ነው። ሰላም ይቻላል። አስቸኳይ የተኩስ አቁም፣ መላው ታጋቾች መለቀቀ እና ለጋዛ ህዝብ ከፍተኛ ሰብዓዊ እርዳታ መሰረታዊ ነገሮች ናቸው" ሲሉም በተጨማሪ በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣናት የማክሮንን እርምጃ በበጎነት ሲቀበሉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃማስ መስከረም መጨረሻ በእስራኤል ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ውሳኔያቸው "ሽብርን የሚሸልም ነው" ሲሉ ተችተውታል።
አሜሪካ የማክሮንን እርምጃ "በጽኑ እንደምትቃወመው" በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ማርኮ ሩቢዮ በኩል ያስታወቀች ሲሆን፤ ውሳኔውን "ግድየለሽ" ሲሉ ተችተውታል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/cjelezpp3lyo

በ #አዲስ_አበባ 247 ቦታዎች ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተጋላጭ መሆናቸው ተገለፀ
በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ 247 ቦታዎች መለየታቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
ዋና ስራ አስኪያጅ በከተማዋ የተሰራውን የጎርፍ መከላከል ስራ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመው መጠነኛ ጎርፍ ከሚቲዎሮሎጂ ትንብያ አንጻር የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
ግዮን አካባቢ የተከሰተው የጎርፍ ክስተት ለጎርፍ መከላከል የተሰራውን ድጋፍ ጥሶ ወጥቶ መሆኑንም ገልጸዋል። አክለውም በቤተል አካባቢ የተከሰተውም ለውሃ መፍሰሻ የተሰሩት መሰረተ ልማቶች በበረዶ በመዘጋታቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በረዶውን በማጽዳት ፈጣን ምላሽ ተሰጥቷል ብለዋል።
በተከሰተው ጉዳትም በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰና በንብረት ላይም የደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑን አስታውቀዋል አጠቃላይ ጎርፉ ባስከተለው የጉዳት መጠን ላይ ዳሰሳ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል።
በከተማዋ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ፤ በወንዝ ዳር ፕሮጀክት የለሙትን ሳይጨምር 64 ቦታዎች የጎርፍ መከላካያ ግንቦች መሰራታቸውንም አስታውቀዋል። ጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችንም በጊዜያዊነት የማንሳት ስራ ተሰርቷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
======
የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
በአዲስ አበባ ከተማ ለጎርፍና ተያያዥ አደጋዎች ተጋላጭ የሆኑ 247 ቦታዎች መለየታቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
ዋና ስራ አስኪያጅ በከተማዋ የተሰራውን የጎርፍ መከላከል ስራ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ሰሞኑን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመው መጠነኛ ጎርፍ ከሚቲዎሮሎጂ ትንብያ አንጻር የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
ግዮን አካባቢ የተከሰተው የጎርፍ ክስተት ለጎርፍ መከላከል የተሰራውን ድጋፍ ጥሶ ወጥቶ መሆኑንም ገልጸዋል። አክለውም በቤተል አካባቢ የተከሰተውም ለውሃ መፍሰሻ የተሰሩት መሰረተ ልማቶች በበረዶ በመዘጋታቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በረዶውን በማጽዳት ፈጣን ምላሽ ተሰጥቷል ብለዋል።
በተከሰተው ጉዳትም በሰው ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰና በንብረት ላይም የደረሰው ጉዳት መጠነኛ መሆኑን አስታውቀዋል አጠቃላይ ጎርፉ ባስከተለው የጉዳት መጠን ላይ ዳሰሳ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ብለዋል።
በከተማዋ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር ወንድሙ፤ በወንዝ ዳር ፕሮጀክት የለሙትን ሳይጨምር 64 ቦታዎች የጎርፍ መከላካያ ግንቦች መሰራታቸውንም አስታውቀዋል። ጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎችንም በጊዜያዊነት የማንሳት ስራ ተሰርቷል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
======
የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይቀላቀሉ
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ75 ቀናት ኋላ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ
#በትግራይ ክልል መቀለ አቅራቢያ የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከ75 ቀናት በኋላ ስሚንቶ ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።
መስቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በግብአት ማውጫ ሳይት (ኳሪ ሳይት) ላይ አጋጥሞት በነበረው ችግር ምክንያት ላለፉት 75 ቀናት ምንም አይነት ምርት እያመረተ እንዳልነበር ጠቁሞ አሁን ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ስምምነት ላይ በመደረሱ ወደ ምርት መመለሱን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ለምርት ማቆሙ ዋነኛ ምክንያቴ ለስሚንቶ ምርት የምጠቀምባቸው የተለያዩ ጥሬ እቃዎች በተለያዩ ምክንያቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማግኘት ስላልቻልኩ ነው ሲል መግለጹን ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ ባቀረብነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል።
ፋብሪካው የጥሬ እቃ በማወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በጊዜያዊነት እና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው መንግታዊ እና ማህበረሰባዊ አካላት ጋር በመመካከር ለመፍታት ጥረት ባደርግም እስካሁን መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም ማለቱም በዘገባው ተካቷል።
ነገር ግን ጥሬ እቃ በሚያወጣባቸው አከባቢዎች እያጋጠሙት ስላሉ ችግሮች በይፋ የገለጸው ነገር አልነበረም።

ዜና: በ #ጋምቤላ ከተማ ትናንት ሌሊት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ50 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደረሰ
በጋምቤላ ከተማ ትናንት ሐምሌ 17 ሌሊት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ50 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ፡፡
አቶ ዱቦል ያንግ የተባሉ ነዋሪ ዝናቡ ሌሉትን ሲዘንብ ማደሩን ገልጸው በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ በኒውላንድ አከባቢ ከ50 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
በሰዎች ላይ እስከ አሁን ስለደረሰ ጉዳት አለመስማታቸውን የገለጹት ነዋሪው አክለውም ቤታቸው በጎርፍ ጉዳት የደረሰበት አባወራዎች በአሁኑ ሰዓት ቦታውን ለቀው መሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት በነበሩ የክረምት ወራቶች ተመሣሣይ ክስተቶች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ዱቦል ያንግ የአሁኑ ግን "የተለየ እና ከባድ" ሲሉ ገልጸውታል፡፡
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ሳይመን ሙን በበኩላቸው ሌሊት 10 ሰዓት ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ በተለይ ረግርጋማ በሆኑና በውኃ መውረጃ አካባቢዎች በተሰሩ ቤቶች በተለይም 05 እና 01 ቀበሌ ላይ ጉዳት ማድረሱን ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
"አንዳንዴ ጠባብ የሆኑ የውሃ ቦዮች አሉ" ያሉት ከንቲባው በሌላ በኩል ደግሞ የውሀ ማስወገጃ ቦዮች በሚጣሉ ዕቃዎች በመዘጋታቸው የተነሳ ለጎርፍ መጥለቅለቁ ከፍተኛ መንሰኤ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/760168129861477/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

በ #አዲስ_አበባ በጳጉሜን ወር በሚካሄደው ሁለተኛው የ #አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የ45 የሀገራት መሪዎች ይታደማሉ ተባለ
በአዲስ አበባ ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የ45 የሀገራት መሪዎች እንደሚታደሙ ተገለጸ።
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በሚካሄደው ሁለተኛ የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአፍሪካ እና የአለም መሪዎች በጋራ ተገናኝተው ወደ ተግባር የሚለወጭ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ እንዲመክሩ ከማስቻሉም ባለፈ የተረጋገጡ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ለማሳየት የሚያስችል መድረክ ይፈጥራል ተብሏል።
ኢትዮጵያ በየክረምቶ በቢሊየኖች የሚቆጠር ችግኞች እየተተከሉ እንደሚገኝ በመጠቆም ከጳጉሜን 3 እስከ 5 ቀን በሚካሄደው ጉባኤው የአረንጓዴ አሻራ ትሩፋቶቿን ለማስተዋወቅ ትጠቀምበታለች ሲል የኬንያው ስታር ጋዜጣ በዘገባው ጠቁሟል።
በናይሮቢ ኬንያ ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም ጳጉሜን ወር ላይ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባኤ ላይ ሀገራት “የናይሮቢ ዲክላሬሽን” ስምምነትን ተቀብለው ማጽደቃቸው ይታወሳል።
"ይህ ስምምነት በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ንግግር ለአፍሪካ የጋራ አቋም መሠረት ሆኖ ያገለግላል" ሲል የስምምነት ሰነዱ ያትታል።
የአፍሪካ ሀገራት “በሙሉ ድምጽ እና ድጋፍ” ተቀብለውታል የተባለው ይህ ስምምነት የአህጉሪቱ አቋም ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እና ኮንፈረንሶች ላይ የሚቀርብ ነው መባሉም በወቅቱ ተዘግቧል፡፡
ስምምነቱ የአየር ንብረትን ለመከላከል እና ለመቋቋም የአፍሪካ ሀገራት የሚተገብሯቸውን የፖሊሲ ማሻሻያዎች የያዘ እንዲሁም በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሊወስዷቸው የሚገቡ እርምጃዎችን ያስቀመጠ ነው፡፡

ዜና: #ኢሕአፓ "መንግስት ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ወታደራዊ ምላሽ መስጠትን ያቁም" ሲል አሳሰበ
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) "መንግስት ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ወታደራዊ ምለሽ መስጠትን እና ንጹሃንን የጦርነት ዒላማ ማድረግን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቆም" አሳሰበ።
አሕአፓ፣ "ለሁሉም በሚታይ መልኩ ዓላማቸው የገዢውን ስልጣን መጠበቅ ብቻ የሆኑ ጦርነቶች እና አለመረጋጋቶች በሁሉም ክልሎች ላለፉት ሰባት አመታት ቀጥለዋል" ሲል 11ኛ ጉባኤውን ማጠናቀቁን ተከትሎ ባወጣው ገልጿል።
መንግሥት "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚገፉ የውጭ ፖሊሲዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በመቀበሉ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በእጅጉ እንዲያሽቆለቁል አድርጓል" ሲል የወቀሰው ፓርቲው፤ "ከዚህ ቀደም መካከለኛ ገቢ የነበራቸው ዜጎች አሁን በልተው ማደር የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አድርጓል" ሲል ከሷል።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8655

ኢሕአፓ "መንግስት ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ወታደራዊ ምላሽ መስጠትን ያቁም" ሲል አሳሰበ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18/ 20017 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) “መንግስት ለፖለቲካዊ ጥያቄዎች ወታደራዊ ምለሽ መስጠትን እና ንጹሃንን የጦርነት ዒላማ ማድረግን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቆም” አሳሰበ። ኢሕአፓ ይህን ያለው “ጽናት እስከ ድል” በሚል መሪ ቃል ከሃምሌ 14 እስከ ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ ሲያካሄድ የቆየውን 11ኛ ጠቅላላ…
የ #አፋር_ፖሊስ በቀድሞ ሠራተኛው "ቁጥጥር ስር ይገኛል" ያለውን የፌስቡክ ገፅ መልሶ መቆጣጠር አለመቻሉንና አዲስ ገፅ መክፈቱን ገለፀ
የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን ፌስቡክ ገፅ "በቀድሞ ሠራተኛው ቁጥጥር ስር መግባቱን" ተከትሎ አዲስ የፌስቡክ ገፅ መክፈቱን አስታወቀ። በቀደሞ ገፁ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን የማይወክሉ እና ሀሰተኛ የሆኑ መረጃዎች አየተሰራጩበት ይገኛልም በሏል።
የአፋር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቢልኤ አህመድ ትናነት ለኢቢሲ እንደተናገሩት፤ ከዚህ ቀደም በአፋር ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ የኮሙኒኬሽን ምክትል ዳይሬክተር የነበረው ጃምእ አደም በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ በወንጀል የሚፈለግ ተጠርጣሪ ነው።
ተጠርጣሪው የተሰጠውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው የፌስቡክ ገፁ ላይ የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን የማይወክሉ እና ሀሰተኛ የሆኑ መረጃዎችን እያወጣ እንደሆነ ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
ይህ የተከሰተው ሐምሌ 16 በአፋር ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ የፌስቡክ ገጽ ላይ ከተለጠፉ ቀስቃሽ መግለጫ በኋላ።
የመጀመሪያው ልጥፍ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ "የአፋር ህዝብ ግዛትን ለኢሳ አሳልፎ ለመስጠት ተስማምቷል” ሲል ከሷል። የአፋርን ግዛት "ለወታደራዊ ዓላማ ለመጠቀም የተደረጉ ሙከራዎችንም" አውግዟል። በተጨማሪም የፌደራል መንግስት "የክልሉን ሃብት በመበዝበዝ፣ የጎሳ ግጭትን በማባባስ እና ለአፋር ጥቅም ጠላት የሆኑ ቡድኖችን በመደገፍ" ተችቷል። እነዚህን ክሶች የክልሉ ፖሊስ ውድቅ አድርጓል እንዲሁም ገጹ አሁንም በኮበለለ የቀድሞ ሰራተኛ ቁጥጥር ስር እንደሆነም አረጋግጧል።
https://www.facebook.com/share/p/1BkvA2QXCq/

በ #ሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በተቋቋመ ጊዜያዊ ችሎት አንድ ግለሰብ በ3 ዓመት እስራት ተቀጣ
በሀዋሳ ከተማ አየተከበረ ባለው ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በተቋቋመ ጊዜያዊ ችሎት አንድ ግለሰብ በሦስት ዓመት እስራት ተቀጣ።
ግለሰቡ ዛሬ ማለዳ ስልክ ነጥቆ ሊያመልጥ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሽመልስ ብሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ከንግስ በዓል ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የጸጥታና ህገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና ህግን ለማስከበር ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ጊዜያዊ የምድብ ችሎት ተቋቁሞ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በዚህም የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት ግለሰቡ የፈጸመውን ወንጀል አጣርቶ የሦስት ዓመት እስራት እንደተፈረደበት ማወቅ ተችሏል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ፌደራል ፖሊስ እና የክልል ፖሊስ በጋራ በመሆን ከአንድ ማዕከል በተሰጠ አቅጣጫ የፀጥታ ማስከበር ስራውን እየሰሩ መሆናቸውን ኢንስፔክተር ሽመልስ አስረድተዋል።
ጊዜያዊ ችሎቱም ከሌሎች አካባቢዎች የመጡ እንግዶችን ታሳቢ አድርጎ ፍትህን ለማፋጠን የተቋቋመ ስለመሆኑም ተገልጿል።
(ኤፍ ኤም ሲ)

ዜና: #ኢትዮጵያ እና #ፓኪስታን የፓርላማ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ኢትዮጵያና ፓኪስታን የፓርላማ ትብብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታኑ ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር ሰይድ ዩሱፍ ራዛ ጊላኒ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድርገዋል።
በውይያታቸውም ሁለቱ ወገኖች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአቬሽን ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማሳደግ መስማማታቸውን ዘ ኔሽን ጋዜጣ ዘግቧል።
ሁለቱ አገራት ለአለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነት ስለሚኖራቸው የባለብዙ ወገን ትብብር ሰፋ ያለ ውይይት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ኢስላማባድ ለአለም አቀፉ ሰላም እና ደህንነት እየተጫወተች ያለውን ሚና አወድሰዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላት ገልጸው፤ ይህም በ 'ግሪን ሌጋሲ' ዕቅዶች ስር በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን የአካባቢ ጥበቃ ትብብር አጉልቶ ያሳያል ብለዋል።
የፖኪስታን ብሔራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር ሰይድ ዩሱፍ ራዛ ጊላኒ በበኩላቸው ደግሞ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን ማኅበረሰብ ጋር የአካባቢ ጥበቃን ጨምሮ በልዩ ልዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
https://www.facebook.com/share/14FgNAif3ne/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

የ #ኢትዮጵያ እና የ #ሳዑዲአረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙርያ ተወያዩ
የሳዑዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጋር ትናንት አርብ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በስልክ መወያየታቸውን የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስትሮቹ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ዙርያ ወይይት ያደረጉ ሲሆን፤ በቀጠናው ያሉትን ተግዳሮቶች ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ጨምሮ፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን አስታየት ተለዋውጠዋል ተብሏል።