ዜና፡ የ #ደላንታ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ 'ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች' በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ
በ #አማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደላንታ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አያሌ ብሩ 'ማንነታቸው ባልታወቀ' የታጠቁ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ተገለጸ።
የጽ/ቤት ኃላፊው ሀምሌ 12/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:20 ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ግቢ ወጥቶ በግምት 50 ሜትር ርቀት ላይ እንደደረሰ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል ሲል የደላንታ ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ትናንት ሐምሌ 13 ቀን በሰጠው የሀዘን መግለጫ አስታውቋል።
በተያዘው አመት መጋቢት ወር መጀመሪያ በደቡብ ወሎ ዞን የወረባቦ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ፈንታው ከበደን ጨምሮ ሶስት ሰዎች በታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ይታወሳል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8572

Addis standard
የደላንታ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ 'ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች' በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14/ 2017 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የደላንታ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አያሌ ብሩ ‘ማንነታቸው ባልታወቀ’ የታጠቁ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ተገለጸ። የጽ/ቤት ኃላፊው ሀምሌ 12/2017 ዓ.ም ከጥዋቱ 12:20 ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ግቢ ወጥቶ በግምት 50 ሜትር ርቀት ላይ እንደደረሰ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ…
ዜና፡ ኦፌኮ በ #ኦሮሚያና #አማራ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ቁጥጥር ስር እንዲቆሙና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ
የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ፣ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ቁጥጥር ስር እንዲቆሙና ከሁሉም የታጠቁና የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ፤ “በታሪካዊ ዴሞክራሲያዊ መደላድል ተስፋ የተጀመሩት ያለፉት ሰባት ዓመታት፣ ‘የባከነ ተስፋ’ ዜና መዋዕል ሆነው ተጠናቀዋል” ብሏል። ዛሬ ኦሮሚያ እና መላው ኢትዮጵያ አንዱ ሌላውን በሚያባብስ አውዳሚ አዙሪት ውስጥ በወደቁ የፖለቲካ፣ የጸጥታ፣ የኢኮኖሚና የሰብዓዊ ቀውሶች ተወጥረዋል ሲልም ገልጿል።
በተጨምሪም “መንግሥት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታን በዘዴ አፍርሷል” ሲል የከሰሰው ኦፌኮ ይህ ጥቃት ስፍር ቁጥር የሌላቸው ጋዜጠኞችን፤ማህበራዊ አንቂዎችን እና የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችን ማሰር፣ በግዳጅ መሰወር እና መግደልን እንደሚያጠቃልል አስታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8576

ኦፌኮ በኦሮሚያና አማራ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ቁጥጥር ስር እንዲቆሙና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14/ 2017 ዓ/ም፦ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በኦሮሚያና በአማራ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ፣ በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ቁጥጥር ስር እንዲቆሙና ከሁሉም የታጠቁና የፖለቲካ ቡድኖች ጋር ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ። ማዕከላዊ ኮሚቴው ሐምሌ 12 እና 13/ 2017 ዓ.ም. በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ባወጣው መግለጫ፤…
ዜና: ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ትግራይን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው - #ምርጫ ቦርድ
ቀጣዩን ሰባተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ሜላተወርቅ ኃይሉ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ተሻሽሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው "የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ" ዙርያ ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ከነባሩ አዋጅ ውስጥ 26ቱ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ያስታወቁት ሰብሳቢዋ፤ አያይዘውም በሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ተግባራዊ ለማድረግ እና የወጣቶች እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎን በሚያረጋግጥ መልኩ መሻሻሉን ጠቁመዋል።
ችግሮች ሲፈጠሩም የፓርቲዎች፣ የምርጫ ቦርድ እና የገዢው ፓርቲ አባላት የሚገኙበት የሶስትዮሽ ኮሚቴ ተቋቁሞ በውይይት እንዲፈታ በመደረግ ላይ መሆኑንም አክለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8581

ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ትግራይን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተከናወኑ ነው - ምርጫ ቦርድ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14/ 2017 ዓ/ም፦ ቀጣዩን ሰባተኛው ዙር ሀገር አቀፍ ምርጫ ትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ አከባቢዎች ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ሜላተወርቅ ኃይሉ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ተሻሽሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ…
ልዩ ዘገባ፡ የማዕድን እሰጥአገባ፣ #የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ
- ሺንግሹ የወርቅ ፕሮጀክቱን አለመሸጡን አስተባብሏ፤ ግዢ የፈጸመው የአውስትራሊያው አስካሪ ዝምታን መርጧል
#በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ዢንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ (Hong Kong Xingxu Mining International Investment Co. Ltd) ፈቃዶቹ እንዲሰረዙ መጠየቁ ተገለጸ።
ባለስልጣኑ ለማዕድን ሚኒስቴር ሐምሌ ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ኩባንያ የፌደራል እና የክልሉን መንግስት አዋጆች ባለማክበር፣ ስራውን ባግባቡ ባለማከናወን እና የአካሄድ ጥሰቶችን በመፈጸም “የገባውን ውል አላከበረምል” ሲል በመግለጽ የተሰጠው የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠይቋል።
ባለስለጣኑ በተጨማሪም “በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ያገኘውን የታደሰ የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ “እውቅና እንደማይሰጠው” አስታውቋል።
አስካሪ ሜታልስ የነጆ ወርቅ ፕሮጀክትን ሙሉ በሙሉ ጠቀለለው በሚል የቀረበውን መረጃ በተመለከተ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የሆንግኮንጉ ኩባንያ ሺንግሹ ማዕድን የሀገር ውስጥ ስራ አስኪያጅ ሱራፌል ወንድማገኝ የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።
በአውስትራልያው አስካሪ ሜታልስ እና በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ መካከል የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ እና አንድምታውን በተሻለ ለመረዳት አዲስ ስታንዳርድ ለአስካሪ ሜታልስ በይፋዊው የኢሜይል አድራሻ እንዲሁም በቀጥታ ለአስካሪ ሜታልስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጂኖ ዲአና ጥያቄ ቢልክም ምላሽ አላገኘም። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8557

የማዕድን እሰጥአገባ፣ የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ - Addis standard
ሺንግሹ የወርቅ ፕሮጀክቱን አለመሸጡን አስተባብሏ፤ ግዢ የፈጸመው የአውስትራሊያው አስካሪ ዝምታን መርጧል በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12/ 2017 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል…
የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ ባለቤቱን ጨምሮ ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ
በቀድሞው የ #ባህር_ዳር ከተማ እና የ #ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ባለቤቱን ጨምሮ ጥፋተኛ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ16 እና 15 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡
የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የአለልኝ አዘነ ባለቤት ወ/ሮ አደይ ጌታቸው እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል የሆነው ሉንጎ ሉቃስ መጋቢት 17/ 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 እስከ 8 ሰዓት ገደማ ባለው ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ልማት ሰፈር በተቀነባበረ ሁኔታ የ26 አመቱን ወጣት አለልኝ አዘነን በመግደል ራሱን ያጠፋ እንዲመስል በማድረግ የግድያ ወንጀል መፈፀማቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በመረጋገጡ ጥፋተኛ ውሳኔን ማሳለፉን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
ፍርድ ቤቱ በቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ግድያ ጥፋተኛ በተባሉት 1ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አደይ ጌታቸው (የአለልኝ አዘነ ባለቤት) ላይ የ16 አመት እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽ ሉንጎ ሉቃስ (የወ/ሮ አደይ ጌታቸው እህት ባል) ላይ 15 አመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
የእግርኳስ ህይወቱን በአርባምንጭ ከተማ ክለብ የጀመረው አለልኝ በባህርዳር ከተማ ለሁለት ዓመታት ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በመሆንም በዓለም አቀፋፍ ውድድሮች ላይ ድንቅ ችሎታውን ማሳየቱ ይታወቃል።

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የህዳሴ ግድቡ ግንባታ በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበረው በመንግስት እና በህዝብ ድጋፍ የተሰራ ፕሮጀክት ነው ሲል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ገለፀ።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ሲሉ መናገራቸውን ተከትሎ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥቷል።
የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር ዛሬ በሰጡት መግለጫ "ማንም አካል ተነስቶ እኔ ነኝ የሰራሁት ቢል ያለምንም ማስረጃ ምንም ማድረግ አይችልም" ብለዋል።
"ምክንያቱም ምንም አይነት፣ ቅንጣት ያክል ገንዘብ ከውጭ ብድርና እርዳታ እንደሌለ ላለፉት 14 ዓመታት መንግስትም ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል። እኛም ለሚድያዎች ስንገልጽ ቆይተናል። ሚዲያውም በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ቆይተዋል" ሲሉ የትራምፕን ንግግር ወድቅ አድርገዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩት የተባለውን ነገር መንግስት በአርቆ አሳቢነት በጥልቅ ዲፕሎማሲያዊ አሰራር ነው መልስ መሰጠት ያለበት ሲሉም አክለዋል።
ምክንያቱም ማንም ሰው እየተነሳ ስለ ሀገር ጉዳይ የራሱን እና የግሉን አስተያየት መስጠት አይቻልም ያሉት ወ/ሮ ፍቅርተ እንደ መንግስት ግልጽ እና የተብራራ መረጃ ወደፊት ሊሰጥ እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
"እውነት እና እውነታው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰራ መሆን መግለጽ ብቻ ነው፤እኛ ይህንን ነው ልናስረዳ የምንችለው ማለትም የሚገባን። የፍራትም አይደለም የማሽቆጥቆጥም አይደለም። ዲፕሎማሲ የመንግስት አሰራር አለው መንግስት በራሱ ጊዜ እና በሚፈልገው አይነት መልስ ይሰጣል" ሲሉ ገልፀዋል።

ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ብድር አልወሰደም- አቶ አሕመድ ሽዴ
ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ብድር አልወሰደም ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናገሩ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እና በገንዘብ ሚኒስቴር አስተባባሪነት የኢትዮጵያ የፋይናንስ ጉባኤ የግሉ ዘርፍ መድረክ ዛሬ መካሄድ ተጀምሯል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በመድረኩ፥ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ምንም ዓይነት ብድር እንዳልወሰደ አንስተው፤ ከወጪ ንግድ 8.3 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን ተናግረዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው፥ ወደ ትግበራ ከገባ ዓመት ሊሞላው ቀናት በቀሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን ገልፀዋል።
ከማሻሻያው በኋላ ከሁሉም ምንጮች የ32.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው፤ ከማሻሻያው በፊት በ2016 የነበረው አፈፃፀም ግን 24.7 ቢሊዮን ዶላር እንደነበረ አስታውሰዋል።
(ኢቢሲ)

ዜና፡ #የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ የማጭበርበር ሙከራ አድረገዋል በተባሉ 14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ሁለቱ የደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ናቸው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሰባት ቢሊየን 735 ሚሊየን ብር የማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል በተባሉ 14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ። ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች መሆናቸው ታውቋል።
አድራሻቸው አዲስ አበባ መሆኑ የተገለጹ የደህንነት ተቋሙ ሰራተኞች ንጉሴ እምሩ ጉሪኖ እና መሀመድ ነጋሽ ገሰሰ (ቅፅል ስም ዋለልኝ) የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ላይ ተጠቅሷል።
አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት የቀረበው የክስ ዝርዝር እንደሚያሳየው ለተመሰረተው ክስ 20 የሰው እና 24 የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበዋል። ከ14ቱ ተከሳሾች ውስ) 13 በእስር ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
የክሱ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተካሳሾቹ “በዋና ወንጀል አድራጊነት እና ስልጣንን አለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል” ነው የተመሰረተባቸው።
በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ መገናኛ ብዙሃን “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በሚል ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ዘገባ ማቅረባቸው ይታወሳል፤ ይህንንም ተከትሎ ባንኩ ምንም ገንዘብ አልተዘረፍኩም ሲል መግለጫ በማውጣት አስተባብሎ ነበር። ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8593

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከሰባት ቢሊየን ብር በላይ የማጭበርበር ሙከራ አድረገዋል በተባሉ 14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ሁለቱ የደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ናቸው - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15/ 2017 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰባት ቢሊየን 735 ሚሊየን ብር የማጭበርበር ሙከራ አድርገዋል በተባሉ በ14 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ፤ ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች መካከል ሁለቱ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች መሆናቸውን አስታውቋል። በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ መገናኛ ብዙሃን “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ…
ዜና: የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የትራምፕን አስታየት አጣጣለ
የ #ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግደቡን በተመለከተ በተደጋጋሚ የሰጡትን አስታየት ውድቅ አደረገ።
ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተገነባው በአበዛኛው በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ነው” ተደምጠዋል።
የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት፤ በ2017 በጀት ዓመት የነበረ እንቅስቃሴን አስመልክቶ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አዲስ ስታንዳርድ ተገኝቶ ዶናልድ ትራምፕ ፕሮጀክቱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ዙሪያ ጥያቄ አቅርቧል።
ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ም/ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፍቅርተ ተአምር፤ “ማንም አካል ተነስቶ እኔ ነኝ የሰራሁት ቢል ያለምንም ማስረጃ ምንም ማድረግ አይችልም” ብለዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8590

የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የትራምፕን አስታየት አጣጣለ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15/ 2017 ዓ.ም:-የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በግደቡ ላይ በተደጋጋሚ የሰጡትን አስታየት ውድቅ አደረገ። ትራምፕ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተገነባው በአበዛኛው በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ ነው” ተደምጠዋል። የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት…
ዜና: የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቀ
ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የነበረው የንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መለቀቁን የስራ ባልደረቦቹ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ፍርድ ቤቱ መወሰኑንና ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት አካባቢ መለቀቁን ባልደረቦቹ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ዶ/ር ዳንኤል ከእስር መፈታቱን "አዎንታዊ እርምጃ" ሲል ገልፆ፤ "ማንኛውም የጤና ባለሙያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መብቱን በመጠየቁ ወይም ለጤና ስርዓት ማሻሻያዎች በመሟገቱ ያለ ፍትህ የሚደረግ እስራትን አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8614

የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/ 2017 ዓ.ም:- ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ የነበረው የንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በ15 ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መለቀቁን የዶክተር ዳንኤል የስራ ባልደረቦች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ዶክተር ዳንኤል ፈንታነህ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ ከእስር እንዲፈታ ወስኖ እንደነበረ ባልደረቦቹ…
ዜና፡ ማርኮ ሩብዮ እና ጠ/ሚኒስትር አብይ በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ፤ ሩብዮ “በአፍሪካ ቀንድ ምክክር እና መረጋጋት ያስፈልጋል” ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል
#የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩብዮ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በስልክ መወያየታቸው ተገለጸ።
“#በአፍሪካ ቀንድ ምክክር እና መረጋጋት ያስፈልጋል” ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ባወሩበት ወቅት አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል።
#የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ጠ/ሚኒስትር አብይ ከማርኮ ሩብዮ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት “በኢትዮጵያ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ኢኮኖሚ እድገት ላይ ያላቸውን የጋራ ግቦች” ዙሪያ ተነጋግረዋል ብሏል።
ማርኮ ሩቢዮ “በአፍሪካ ቀንድ ምክክር እና ቀጠናዊ መረጋጋት ያስፈልጋል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው መናገራቸውንም መግለጫው አመላክቷል።
ማርኮ ሩብዮ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ አወድሰዋል ያለው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ ማሻሻያዎቹ “ለአሜሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋት ያላቸውን አቅም በማጉላት” መግለጻቸውንም አስታውቋል።
ከወራት በፊት መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ ጋር በስልክ ማውራታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ የሰጡትን መግለጫ ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል።
ማርኮ ሩብዮ እና ጠ/ሚኒስትር አብይ በስልክ የተወያየቱ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ዙሪያ ነው ሲሉ ቃልአቀባዩ መናገራቸውም በዘገባው ተገልጿል።

ዜና፡ #የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፣ ውሳኔው የተላለፈው የ17 ወራት ውዝፍ የመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ነው
በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የክልሉ መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው የመሰረቱትን ክስ የሚመለከተው የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጊዜያዊ አስተዳደር ባንክን ሒሳብ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈ፤ ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የተሰየሙት ዳኞችም ክርክሮችን ከሰሙ በኋላ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስም #በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈቱትን የባንክ ሒሳቦች እንዳይንቀሳቀሱ በማገድ ወጪ የተደረገው የገንዘቡ መጠን መቼ እንደወጣና ወደ የትኛው የባንክ ሒሳብ እንደተላለፈ ማስረጃ እንዲቀርብ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።
የከሳሽ የመምህራን ማህበሩ ጠበቆች በእስር እንዲቀርቡልን ሲሉ የጠየቋቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ እና የክልሉ የፋይናንሰ ቢሮ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) ማስረጃዎቹ ከቀረቡ በኋላ እንደሚታይ በመግለጽ የዕለቱ ዳኞች ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸው ተገልጿል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8618

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የባንክ ሒሳብ እንዲታገድ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፣ ውሳኔው የተላለፈው የ17 ወራት ውዝፍ የመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ነው - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15/ 2017 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የክልሉ መምህራን የ17 ወራት ደመወዝ እንዲከፈላቸው የመሰረቱትን ክስ የሚመለከው የትግራይ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጊዜያዊ አስተዳደር ባንክን ሒሳብ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈ፤ ለሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በመቀለ ከተማ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የዋለው ችሎ የትግራይ መምህራን ማህበር…
ዜና፡ #ሚሊኒየም አዳራሽ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑ ተጠቆመ፣ በቀጣይ አመት አጋማሽ ግንባታው ይጀመራል ተብሏል
አዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንት እና ማኔጅመንት ወይም በተለምዶው ሚሊኒየም አዳራሽ ከታህሳስ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ ሊገነባ መሆኑን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኮሚዩኒኬሽን እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ሁናቸው ታዬ አስታውቀዋል።
አዳራሹን እንደ አዲስ መገንባት ያስፈለገው የአካባቢውን ገፅታ ከመቀየር አኳያ ትልቅ ድርሻ ስለሚኖረው እና ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በተሻለ መልኩ ለመስራት በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ ባሻገር አዳራሹ በአዲስ መልክ ሲገነባ እንዲሁም ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ለበርካቶች የስራ ዕድልን እንደሚፈጥርም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ታህሳስ 2018 ዓ.ም በአዲስ መልክ ግንባታው የሚጀመረው አዲስ ፓርክ ዴቨሎፕመንት እና ማኔጅመንት፣ በውስጡ ቀድሞው ሲሰጥ የነበረው አገልግሎት እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎች ታክለውበት የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ሱቆች ይኖሩታል መባሉን ከኢቲቪ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና፡ #ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ከአይኤምኤፍ ከተበደሩ 10 የአፍሪካ ሀገራት ተርታ መመደቧ ተጠቆመ
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በከፍተኛ ደረጃ ብድር ከሰጣቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገለጸ። በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር ከአይኤምኤፍ እንደምታገኝም ተጠቁሟል።
እንደ አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአይኤምኤፍ ብድር እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ አንድ ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ተጠግቷል፤ ከአፍሪካ በሰባተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።
ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት አለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ብድር እያገኙ ያሉት በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ መተንፈስ ያቃተውን ኢኮኖሚያቸውን ትንፋሽ እንዲቀጥል ለማድረግ ነው በሚል መሆኑን የጠቆመው አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደር ድረገጽ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የአይኤምኤፍ ዕዳ የረዥም ጊዜ መዘዞች ይዞ በመምጣት በአህጉሪቱ ላይ ስጋት እየፈጠረ ይገኛል ሲል አመላክቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8621

ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ከአይኤምኤፍ ከተበደሩ 10 የአፍሪካ ሀገራት ተርታ መመደቧ ተጠቆመ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16/ 2017 ዓ/ም፦ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በከፍተኛ ደረጃ ብድር ከሰጣቸው 10 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗ ተገለጸ። በተያዘው አመት 2017 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ብድር ከአይኤምኤፍ እንደምታገኝም ተጠቁሟል። ከአይኤፍኤፍ በከፍተኛ ደረጃ ከተበደሩ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ግብጽ በአንደኝነት የተቀመጠች ሲሆን እስከ ሐምሌ…
ዜና: የ #ፋኖ ኃይሎች በ #ኦሮሚያ ክልል ተደራጅተው እንደሚንቀሳቀሱ ገለፁ፤
ይሁን እንጂ በክልሉ በቅርቡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ግድያ ላይ "እጃችን የለበትም" ሲሉ አስተባብለዋል
የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የስድስት ወር ሕፃን ጨምሮ ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ በተባለው ጥቃት ላይ "እጄ የለበትም" ሲል አስተባበለ።
በክልሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “በፋኖ ታጣቂዎች” መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎችና የኖኖ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በወቅቱ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።
በጉዳዩ ላይ ለአዲስ ስታንዳርድ ማብራሪሪያ የሰጡት አንድ የፋኖ አመራር፣ “በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል” የፋኖ አደረጃጀት በክልሉ ታህሳስ 7 ቀን በይፋ ተመስርቶ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8628

የፋኖ ኃይሎች በኦሮሚያ ክልል ተደራጅተው እንደሚንቀሳቀሱ ገለፁ፤ ይሁን እንጂ በክልሉ በቅርቡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ገድያ ላይ "እጃችን የለበትም" ሲሉ አስተባብለዋል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16/2017 ዓ/ም:- የፋኖ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ/ም የስድስት ወር ሕፃን ጨምሮ ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ በተባለው ጥቃት ላይ “እጄ የለበትም” ሲል አስተባበለ። በክልሉ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ኖኖ ወረዳ፣ ቆንዳላ ቀበሌ ሐምሌ 4 ቀን ከ16 በላይ ሰላማዊ ሰዎች “ከመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ…
ዜና: #ፌዴራል ፖሊስ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት መካከል አንዱ ለመሆን እየሠራ መሆኑን ገለጸ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት ውስጥ የሚመደብ ለማድረግ እየሠራን ነው ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ።
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድ እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባለፉት 5 ዓመታት እንደ ሀገር እና አንደ ተቋም የተሰጡ ተልዕኮዎች እውን ለማድረግ ጠንካራ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።
"በተከፈለው መሥዋዕትነት ዛሬ በሀገራችን የተሻለ ሰላም እና ደኅንነት እንዲኖር አስችሏል" ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ አያይዘውም በቅርቡ የሚመረቀው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እውን እንዲሆን ሠራዊቱ የሕይወት መሥዋዕትነት ከመክፈል ባለፈ ከደመወዙ በማዋጣት ለውጤት አድርሷል ብለዋል።
በተጨማሪም ፌዴራል ፖሊስ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት መካከል አንዱ ለመሆን እየሠራ መሆኑን መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በ2022 ዓ.ም በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት ውስጥ የሚመደብ ለማድረግ እየሠራን ነው ሲሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለጹ።
ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የ2018 በጀት ዓመት ሀገራዊ ዕቅድ እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈፃፀም ላይ የውይይት መድረክ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባለፉት 5 ዓመታት እንደ ሀገር እና አንደ ተቋም የተሰጡ ተልዕኮዎች እውን ለማድረግ ጠንካራ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።
"በተከፈለው መሥዋዕትነት ዛሬ በሀገራችን የተሻለ ሰላም እና ደኅንነት እንዲኖር አስችሏል" ያሉት ኮሚሽነር ጄኔራሉ፤ አያይዘውም በቅርቡ የሚመረቀው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እውን እንዲሆን ሠራዊቱ የሕይወት መሥዋዕትነት ከመክፈል ባለፈ ከደመወዙ በማዋጣት ለውጤት አድርሷል ብለዋል።
በተጨማሪም ፌዴራል ፖሊስ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አምስት የፖሊስ ተቋማት መካከል አንዱ ለመሆን እየሠራ መሆኑን መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ የ #አፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ የተለቀቀው መረጃ “ወደ ጠላት በኮበለለ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ” የተሰራጨ ነው ሲል ገለፀ
የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ የተለቀቀው መረጃ “ወደ ጠላት በኮበለለ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ” የተሰራጨ ነው ሲል ገለፀ። መግለጫው ተቋሙን እንደማይወክልም አስታውቋል።
በትናንትናው ዕለት የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ በተሰራጨ መግለጫ፤ “የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለታሪካዊ የአፋር ጠላት ለሆነው ለኢሳ አሸባሪዎች አሳልፎ ለመስጠት ተስማምተዋል” ሲል ከሷል።
አክሎም “የአፋር ህዝብ ጠላት ከሆነው ከ #ህወሓት ቡድን ላፈነገጠው ለእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን ማሰልጠኛና እስትራቴጂካዊ ቦታ በአፋር ልዑላዊ ግዛት ውስጥ መስጠታቸው ደርሰንበታል” ብሏል።
ይህን ተከትሎ፤ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ የፌስቡክ ፔጁን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የነበሩት ሀጅ ጃሚኢ አደም አህመድ ይዘው "ወደ ጠላት ኮብልለዋል" ብሏል። ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ “ጠላት” ሲል የጠራውን አካል በስም አልጠቀሰም።
ተጨማሪ ያንንቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8644

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ የተለቀቀው መረጃ “ወደ ጠላት በኮበለለ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ” የተሰራጨ መሆኑን አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17/ 2017 ዓ/ም፦ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ የተለቀቀው መረጃ “ወደ ጠላት በኮበለለ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ” የተሰራጨ መሆኑንና ተቋሙን እንደማይወክል አስታወቀ። በትናንትናው ዕለት የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ በወጣ መግለጫ፤ “የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለታሪካዊ የአፋር ጠላት ለሆነው ለኢሳ አሸባሪዎች አሳልፎ…
ዜና: #ቱርክ በ #ኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካላቸው ሀገራት መካከል 2ኛ ደረጃን ይዛለች ተባለ
ቱርክ በጨርቃጨርቅ፣በግብርና፣ በንግድ እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች 2.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ካላቸው ሀገራት መካከል 2ኛ ደረጃን ይዛለች ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ተናገሩ።
በቱርኩ የአለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም (World Cooperation of Industries Forum-WCI Forum) እና በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አማካኝነት የተሰናዳው ስምንተኛው የደብሊው ሲአይ (WCI) የቢዝነስ ፎረም ትናንት ረቡዕ ሐምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን በአሁኑ ወቅት ከ260 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አክለውም ዘላቂ ከሆነው የኢትዮጵያና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባሻገር የሁለቱ ሀገራት ትብብር ንግድን፣ ቴክኖሎጂን፣ ጤናን፣ ትምህርትንና ባህልን እንደሚያካትት ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የቱርክ የንግድ ካውንስለር የሆኑት ጣሃ አልፕሬን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው የንግድ ማዕከል የመሆን እምቅ አቅም ያላት እንደመሆኗ፣ የቱርክ "በምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ አጋር" እንደሆነች ተናግረዋል።
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/759334623278161/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v