ዜና: በ #አፋር ክልል መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ሲጎዱ ከ1 ሺህ 800 በላይ ቤቶች ተቃጠሉ
በአፋር ክልል ዳሎል ወረዳ ትናንት ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት አከባቢ በደረሰ ምክንያቱ ባልታወቀ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱንና 1 ሺህ 805 ቤቶች መቃጠላቸውን የዳሎል ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን አሕመድ ገለጹ።
በአደጋው በበዳ-አድሙሩግ ቀበሌ 600 ሱቆች፣ 950 ምግብ ቤቶች እና 255 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ኃላፊው ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከ20 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት በእሳት አደጋው መሞታቸውን ገልጸው
ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።
አክለውም በክልበቲ ረሱ ዞን የሚገኘው የአብኣለ እና በራህሌ ሆስፒታል ባለሙያዎች በአከባቢው በመገኘት የሕክምና ድጋፍ እየሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የተነሣውን እሳት እስካሁን ድረስ ማጥፋት አለመቻሉ የተገለጸ ሲሆን በአደጋው ቤት ንብረት የወደመባቸው የቀበሌዋ ነዋሪዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተመላክቷል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከ #ትግራይ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከትግራይ የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወከሉ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ጋር መወያየታቸውን አስታወቁ።
በውይይቱ በተለይም የተፈናቃዮች ጉዳይ፣ የትግራይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ ሁኔታዎች ላይ በዋናነት ምክክር የተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች እንደነበሩ ተገልጿል።
በፐብሊክ ዲፕሎማሲው አባላት በኩል በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን፣ መንግስት ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ መስራት እና ህዝባዊ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀቱን ሊቀጥል ይገባል የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰራጩት መልዕክት ገልጸዋል።
በመልዕክቱ፤ በፐብሊክ ዲፕሎማሲው አባላት ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት እና የትግራይ ህዝብ ድምጽ በትክክል የሚሰማባቸው ክፍት መድረኮች መቋቋም እንዳለባቸው አሳስበዋል ብሏል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid033Wr2LPUY7tZ3ghRtmqXzaaPwWEgGTzuuhYHmLpXseENdAijYmkfhzKHjWK3JETakl

ርዕስ አንቀጽ፡ አዲሱ የሲቪል ማህበራት ረቂቅ ህግ የቀረችውን አነስተኛ ምህዳር እንዳያሳጣን ያሰጋል፣ ሳይዘገይ ሊቀለበስ ይገባዋል!
#በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ወደኋላ እየተመለሰ ነው የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት መንግስት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ አፋኝ ቁጥጥርን በመመለስ፣ ድርጅቶቹን ለመቆጣጠር የሚያስችለው አዲስ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ እያዘጋጀ ይገኛል።
በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን (ACSO) ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ አዋጁ በማህበራቱ ላይ የሚደረግን ቁጥጥር ለማስተካከል ተብሎ የቀረበ ብቻ አይደለም፤ በቀጥታ መሰረታዊ በሆኑት የመደራጀት፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ እና በተጠያቂነት መብቶች ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው።
በዚህ ወሳኝ ወቅት ማለትም ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ አንድ አመት በቀረበት እንዲሁም ያልተፈቱ ግጭቶች እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በተበራከቱበት፣ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች።
አለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ ሲቪል ማህበረሰብ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ዝም ማለት የለባቸውም። በእንዲህ አይነት ጊዜያት፤ ዝምታ ገለልተኝነት አይደለም፣ ተባባሪነት ነው። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8544

Addis standard
አዲሱ የሲቪል ማህበራት ረቂቅ ህግ የቀረችውን አነስተኛ ምህዳር እንዳያሳጣን ያሰጋል፣ ሳይዘገይ ሊቀለበስ ይገባዋል! - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11/ 2017 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ወደ ኋላ እየተመለሰ ነው የሚል ስጋት ባየለበት ወቅት መንግስት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ አፋኝ ቁጥጥርን በመመለስ፣ ድርጅቶቹን ለመቆጣጠር የሚያስችለው አዲስ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያዘጋጀ ይገኛል። በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን (ACSO) ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ አዋጁ…
#ኢሰመኮ የኮሚሽነሮቹ ሰራ መልቀቂያ በምክር ቤቱ ተቀባይነት ማግኘቱን ገለፀ፤ ላበረከቱት አስተዋፅኦም ምስጋና ችሯል
የ #ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአረጋውያን እና የአካል ጉዳተኞች መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ያቀረቡትን ጥያቄ የተ/ ም/ቤት መቀበሉን ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. አስታወቀ።
ኢሰመኮ ትናንት ሐመሌ 11 ቀን ባወጣው መግለጫ፤ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እና ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ "ላበረከቱት ቀና የሰብአዊ መብቶች አገልግሎት ያመሰግናል" ብሏል።
በሰጡት አመራር የኢሰመኮን ሥራ በማጠናከር፣ ተደራሽነቱን በማስፋት እና በሕዝብ እንዲሁም በዓለም አቀፍ አጋሮች ዘንድ መተማመንን በማሳደግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሚና አበርክተዋል ሲል ገልጿል።
የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር "የአመራር ስልት" ጋር በተያያዘ "ተገፍተው" እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል።
"አሳታፊነትን" ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን "አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን" ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ምንጮ አመልክተዋል።
ኢሰመኮ በመግለጫው፤ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ እንዲሁም ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ በኢሰመኮ በነበራቸው ቆይታ "በትጋት፣ በታማኝነት እና በቁርጠኝነት ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበር እና ጥበቃ አገልግለዋል" ሲል ገልጿል።
https://www.facebook.com/share/p/16pDJ6zRqC/

#የሞሳድ ኃላፊ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ #ኢትዮጵያ፣ #ሊቢያና #ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ መጠየቃቸው ተዘግበ
የ #እስራኤል የስለላ ድርጅት (ሞሳድ) ኃላፊ ዴቪድ ባርኔያ የጋዛ ነዋሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ኢንዶኔዥያ ለማዘዋወር #አሜሪካ ድጋፍ እንድታደርግ የሀገሪቱን ልዩ መልዕክተኛ መጠየቃቸው ተዘግበ።
የሞሳድ ኃላፊው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ባደረጉት ጎብኝት ወቅት መሆኑን አክሲዮስ ዘግቧል።
እስራኤል ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ለማዘዋወር የትራምፕን አስተዳደር እርዳታ እየፈለገች መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮችን ጠቅሶ የዜና አውታሩ ዘግቧል፣
ሁለቱ ምንጮች እንደገለፁት፤ የሞሳዱ ኃላፊ ባርኔያ፤ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኔዥያ እና ሊቢያ ከጋዛ የፍልስጤማውያን ስደተኞችን ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል ሲሉ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ተናግረዋል። እናም ዋሽንግተን እነዚህ ሀገራት ስደተኞችን ለማዛወር እንዲስማሙ “ማበረታቻ” መስጠት አለባት ማለታቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ስቲቭ ዊትኮፍ በጉዳዩ ላይ ቁርጠኛ አልነበረም ሲሉ አንደኛው ምንጭ ገልጿል።
የአሜሪካ ባለስልጣናትም ከአረብ ከሀገራት ተቃውሞ የሚያከትል በመሆኑ ዋይት ሀውስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ የማስወጣት ፍላጎት እንደሌለው ገልጸዋል ሲል ዘገባው አክሏል።
ከወራት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥ ግንባት ሲጀመር የጋዛ ነዋሪዎች በሙሉ ላልተወሰነ ጊዜ ወደሌላ ቦታ እንዲዘዋወሩ ሀሳብ ማቅረባቸው ይታወቃል። ሀሳቡን የእራኤሉ መሪ ኔታንያሁ እና ጥምረታቸው ሲደግፉ፣ የአረብ ሀገራት እና አብዛኛው የምዕራቡ ዓለም በብርቱ ተቃውመውታል።

ዜና: እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "በፍትሕ ስም የባርነት እና የጭቆና ቀንበርን ማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል" አሉ፤
ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት እንደማይቀርቡ አስታወቁ
በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች "በፍትሕ ስም የባርነት እና የጭቆና ቀንበርን ማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል" ሲሉ ለችሎቱ አቤቱታ አቀረቡ። አቤቱታቸው ምላሽ ካላገኘ ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት እንደማይቀርቡ አስታወቀዋል።
አንደኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው የተከሳሾቹን አቤቱታ በጽሑፍ ለፍርድ ቤት ማቅረባቸውን ጠበቃ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
አዲስ ስታንዳርድ በተመለከተው አቤቱታ ተከሳሾቹ "ከህግ አግባብ ውጭ በእስራትና በመንግስታዊ እገታ ፍትሕ ተነፍገን ከቆየን ሁለት አመታትን አስቆጥረናል" ብለዋል።
በተጨማሪም "ከነገ ዛሬ የፍትሕ ሂደቱ ይሻሻል ይሆናል ብለን ብንጠብቅም ከጊዜ ጊዜ ሂደቱ ከድጡ ወደ ማጡ እየሆነ በእኛ በተከሳሾች ላይ ሰፊ የመብት ጥሰትና በደል እየተፈጸመብን ይገኛል" ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል።
"ችሎቱ ሙሉ በሙሉ ለመንግስትና ለገዢው ፓርቲ ወግኗል" ያሉት ተከሳሾች፤ አክለውም "ያልተቋረጠ ጫናና ይሉኝታ ቢስ ውሳኔዎችን በተደጋጋሚ ፈጽሞብናል" ሲሉ አቤቱታ አቅራቢዎቹ በፍርድ ቤቱ ተፈጸሙ ያሏቸውን አስር "ኢ-ፍትሐዊ ውሳኔዎች" በዝርዝር በአቤቱታቸው ላይ አስፍረዋል።
ዝርዝር መረጀውን ለማንበብ: https://addisstandard.com/Amharic/?p=8550

እነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "በፍትሕ ስም የባርነት እና የጭቆና ቀንበርን ማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል" አሉ፤ ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት እንደማይቀርቡ አስታወቁ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም:- በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ ክስ የተመሠረተባቸው ተከሳሾች “በፍትሕ ስም የባርነት እና የጭቆና ቀንበርን ማስተናገድ የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ። አቤቱታቸው ምላሽ ካላገኘ ጉዳያቸውን ለመከታተል ችሎት እንደማይቀርቡ አስታወቀዋል። ተከሳሾቹ የጽሑፍ አቤቱታቸውን ያቀረቡት ረቡዕ ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ጉዳያቸው ለሚታይበት ለፌደራል…
ልዩ ዘገባ፡ የማዕድን እሰጥአገባ፣ #የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ
- ሺንግሹ የወርቅ ፕሮጀክቱን አለመሸጡን አስተባብሏ፤ ግዢ የፈጸመው የአውስትራሊያው አስካሪ ዝምታን መርጧል
#በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ዢንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ (Hong Kong Xingxu Mining International Investment Co. Ltd) ፈቃዶቹ እንዲሰረዙ መጠየቁ ተገለጸ።
ባለስልጣኑ ለማዕድን ሚኒስቴር ሐምሌ ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ኩባንያ የፌደራል እና የክልሉን መንግስት አዋጆች ባለማክበር፣ ስራውን ባግባቡ ባለማከናወን እና የአካሄድ ጥሰቶችን በመፈጸም “የገባውን ውል አላከበረምል” ሲል በመግለጽ የተሰጠው የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠይቋል።
ባለስለጣኑ በተጨማሪም “በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ያገኘውን የታደሰ የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ “እውቅና እንደማይሰጠው” አስታውቋል።
አስካሪ ሜታልስ የነጆ ወርቅ ፕሮጀክትን ሙሉ በሙሉ ጠቀለለው በሚል የቀረበውን መረጃ በተመለከተ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የሆንግኮንጉ ኩባንያ ሺንግሹ ማዕድን የሀገር ውስጥ ስራ አስኪያጅ ሱራፌል ወንድማገኝ የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።
በአውስትራልያው አስካሪ ሜታልስ እና በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ መካከል የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ እና አንድምታውን በተሻለ ለመረዳት አዲስ ስታንዳርድ ለአስካሪ ሜታልስ በይፋዊው የኢሜይል አድራሻ እንዲሁም በቀጥታ ለአስካሪ ሜታልስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጂኖ ዲአና ጥያቄ ቢልክም ምላሽ አላገኘም። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8557

የማዕድን እሰጥአገባ፣ የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ - Addis standard
ሺንግሹ የወርቅ ፕሮጀክቱን አለመሸጡን አስተባብሏ፤ ግዢ የፈጸመው የአውስትራሊያው አስካሪ ዝምታን መርጧል በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12/ 2017 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ አሜሪካ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች ሲሉ የተሳሳተ ንግግር አደረጉ
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ዕለት የሪፐብሊካን ሴናተሮችን በዋይት ሀውስ ተቀብለው ባስተናገዱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአሜሪካ የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለት ሲናገሩ ተደምጠዋል።
“ኢትዮጵያ ግድቡን የገነባችው በአብዛኛው በአሜሪካ ገንዘብ ነው” ሲሉ በአንድ ወር ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ
ተናግረዋል።
እውነታው ግን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተገነባው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ መዋጮ እና በአገር ውስጥ ሀብት መሆኑ ነው። በተጨማሪም ግድቡ ለግብፅ የውሃ ደህንነት ምንም አይነት ስጋት አይፈጥርም።
በድጋሜ አዲስ ስታንዳርድ የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን እንዲያጠናክር እና እነዚህን አሳሳች ትርክቶች ለመመከት እና ማስተካከያ ለማድረግ ጠንካራ አቋም እንዲይዝ በድጋሚ ጥሪ ያቀርባል።

ዜና፡ ኢፈርት በክልሉ የተፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት ሰለባ ሁኗል፣ለህዝቡ ጥቅም ሲባል ጊዜያዊ አስተዳደር ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል - ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ
#የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኢፈርት) እና ያቀፋቸው ድርጅቶች በትግራይ ክልል የተፈጠረው ልዩነት ሰለባዎች ሁነዋል ሲሉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለጹ።
በዚህም ምክንያት የሶስተኛ ወገን ጣልቃ እንዲገባ የሚያደርግ እና እየሰፋ የሄደ ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ለሁለት ቀናት ሐምሌ 12 እና 13 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀለ ከተማ በተካሄደው ትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኢፈርት) አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ተቋሙ ስላጋጠመው አደጋ እና ከተሳታፊዎቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በኢፈርት የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ ጉዳዩ በህግ እንዲታይ መቅረቡን ጠቁመው ይህም በባሰ ደረጃ ጉዳዮቹን ሊያወሳሰበው ይችላል ብለዋል፤ ተቋሙ ላጋጠመው ችግር ሁሉም መወገኖች በከፍተኛ የህዝብ ሀላፊነት በምክክር እና በትዕግስት እንዲፈቱት አሳስበዋል።
ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለህዝብ ጥቅም ሲባል የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለበት ሃላፊነት እጁን በማስገባት ሊፈታው እንደሚገደድ አሳታውቀዋል፤ “ለህዝቡ ጥቅም ሲባል የጊዜያዊ አስተዳደሩ ጣልቃ ለመግባት ይገደዳል” ብለዋል።
በኢፈርት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አንድ ሶስተኛ የምክር ቤቱ አባላት ፒቲሽን በማሰባሰብ ጉባኤ መጥራት እንደሚችሉ መደንገጉን ተከትሎ የተጠራ ጉባኤ ነው ተብሏል
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02rU7Rj3N6tiR8rpks5mREj7NLtZ8JvGHea8yHq4TXjHuDSV9izngTcrVL8aVyqWCdl

#ግብፅ በጋዛ እና #ኢትዮጵያ ግድብ ዙሪያ #አሜሪካ ያቀረበችው የሰጥቶ መቀበል ሀሳብ ውድቅ አደረገች
እስራኤል በጋዛ ደቡባዊ ክፍል ማቆያ ካምፕ ለመገንባት ያላትን እቅድ ግብፅ የምትደግፍ ከሆነ በምላሹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ግድብ ውዝግብ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ያቀረበችውን ሀሳብ የግብፅ ባለስልጣናት ውድቅ አድረጉ።
ግብፅ በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ላይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት አሜሪካ ያቀረበችውን የሰጥቶ መቀበል ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች። ይህ ሀሳብ እስራኤል የጋዛን ህዝብ ወደ ራፋህ እንድታዘዋውር ካይሮ ድጋፍ እንድትፈቅድ የሚጠይቅ እንደሆነ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማሲ ምንጮች ለአል አረቢ አል ጃዲድ ገልጸዋል።
አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ለዜና ምንጩ እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት “ቆራጥ ጣልቃ ገብነት” ብለው የጠሩትን ሀሳብ አቅርበው ነበር።
በምላሹ ግብፅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን ከራፋህ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ለማቆየት የእስራኤልን እቅድ መደገፍ ይኖርባታል።
ዲፕሎማቱ ለአል አረቢ አል ጃዲድ እንደተናገሩት የካይሮ ባለስልጣናት እቅዱን ፍልስጤማውያንን ድንበር አቋርጠው ወደ ግብፅ እንዲገቡ የማስገደድ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
እስራኤል በጋዛ ደቡባዊ ክፍል ማቆያ ካምፕ ለመገንባት ያላትን እቅድ ግብፅ የምትደግፍ ከሆነ በምላሹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ግድብ ውዝግብ ውስጥ ጣልቃ ለመግባት ያቀረበችውን ሀሳብ የግብፅ ባለስልጣናት ውድቅ አድረጉ።
ግብፅ በኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ላይ ያለውን ቀውስ ለመፍታት አሜሪካ ያቀረበችውን የሰጥቶ መቀበል ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች። ይህ ሀሳብ እስራኤል የጋዛን ህዝብ ወደ ራፋህ እንድታዘዋውር ካይሮ ድጋፍ እንድትፈቅድ የሚጠይቅ እንደሆነ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማሲ ምንጮች ለአል አረቢ አል ጃዲድ ገልጸዋል።
አንድ የግብፅ ዲፕሎማት ለዜና ምንጩ እንደተናገሩት የትራምፕ አስተዳደር አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ያለውን ውዝግብ ለመፍታት “ቆራጥ ጣልቃ ገብነት” ብለው የጠሩትን ሀሳብ አቅርበው ነበር።
በምላሹ ግብፅ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንን ከራፋህ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ ካምፕ ውስጥ ለማቆየት የእስራኤልን እቅድ መደገፍ ይኖርባታል።
ዲፕሎማቱ ለአል አረቢ አል ጃዲድ እንደተናገሩት የካይሮ ባለስልጣናት እቅዱን ፍልስጤማውያንን ድንበር አቋርጠው ወደ ግብፅ እንዲገቡ የማስገደድ እርምጃ አድርገው ይመለከቱታል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና፡ ሶማሊያ በባህር ክልሏ በርካታ ሀገራት በሚሳተፉበት የባህር ላይ የጦር ልምምድ #ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች
በቀጣይ #በሶማሊያ ባህር በሚካሄደውና በርካታ ሀገራት በሚሳተፉበት የባህር ላይ የጦር ልምምድ ለመካፈል ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ጥያቄ ሶማሊያ ውድቅ ማድረጓ ተገለጸ፤ ኢትዮጵያ አለምአቀፍ ህግን በመጣስ እንዲሁም ሊዓላዊነቴን በመዳፈሯ ነው የከለከልኳት ብላለች።
ኢትዮጵያ በርካታ ሀገራት ባሳተፈ መልኩ በሶማሊያ የባህር ላይ የጦር ልምምድ ለመሳተፍ ጥያቄ ያቀረበችው በአዲስ አበባ በተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ መሆኑን የሀገሪቱ የመካላከያ ሚኒስቴር አስታውቀዋል።
የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉን የሶማሊያ የመካላከያ ሚኒስትሩ አህመድ ሞአሊም ፊቂ ተናግረዋል፤ ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ የባህር ላይ የጦር ልምምዱ በርካታ ሀገራትን በማሳተፍ ይከናወናል ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8569

ሶማሊያ በባህር ክልሏ በርካታ ሀገራት በሚሳተፉበት የባህር ላይ የጦር ልምምድ ኢትዮጵያ ለመሳተፍ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14/ 2017 ዓ/ም፦ በቀጣይ በሶማሊያ ባህር በሚካሄደውና በርካታ ሀገራት በሚሳተፉበት የባህር ላይ የጦር ልምምድ ለመካፈል ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ጥያቄ ሶማሊያ ውድቅ ማድረጓ ተገለጸ፤ ኢትዮጵያ አለምአቀፍ ህግን በመጣስ እንዲሁም ሊዓላዊነቴን በመዳፈሯ ነው የከለከልኳት ብላለች። ኢትዮጵያ በርካታ ሀገራት ባሳተፈ መልኩ በሶማሊያ የባህር ላይ የጦር ልምምድ ለመሳተፍ ጥያቄ ያቀረበችው በአዲስ…
ዜና: በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተከሰተ የመሬት ናዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኣሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ ኮመር ቀበሌ በተከሰተ የመሬት ናዳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ም/ ኮማንደር አሸናፊ ሃይሌ እንደገለጹት በቀበሌው ትናንት የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ናዳ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡
አያይዘውም በአደጋው የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አባት እና እናት ከሶስት ልጆቻቸው ጋር ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም አደጋው በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቅሰው÷ ከ200 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አመልክተዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው በረደሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸው÷ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
የክረምቱን ዝናብ ተከትሎ ለመሬት መንሸራተት እና ናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች አስፈጊውን ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የዘገበው ኤፍ ኤም ሲ ነው፡፡