ዜና: በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 82 የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በፑንትላንድ የሚንቀሳቀሰው የአይ ኤስ የሶማሊያ ክንፍ በተለያዩ ሀገራት እንዲሁም በኢትዮጵያ ለመስፋፋትና የሽብር ቡድኑን ሴሎች ለመመስረት የሚያደርገውን ጥረት በተመለከተ የመረጃ ስምሪትና ጥናት ሲደረግ ቆይቷል።
በዚህም የሽብር ቡድኑ በፑንትላንድ አሰልጥኖ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሰማራቸው 82 ተጠርጣሪዎች ተለይተው ከፌዴራል ፖሊስና ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመላክቷል።
ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ፣ አዳማ፣ ሃሮማያ፣ ሻሸመኔ፣ ባሌ፣ ጅማና ሻኪሶ ከተማ ዙሪያ፤ በአማራ ክልል ከሚሴ አካባቢ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞንና ሃላባ ቁሊቶ ከተማ፤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማና በሐረሪ ክልል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል።
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/753078417237115/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

በ #ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የሚመራ ልዑክ ከ #ትግራይ ክልል መሪዎች ጋር ለመወያየት ወደ #መቀለ አመሩ።
የሃይማኖት አባቶቹ በአሁኑ ሰዓት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከፌደራል እና ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር እየመከሩ ይገኛሉ።
ልዑኩ ወደ ትግራይ ያመራው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ “ትግራይ ወደ ግጭት፤ ወደ ጦርነት እንዳይገባ በሀገሪቱ የሚገኙ የሐይማኖት አባቶች በአቸኳይ ስራችሁን አሁን ጀምሩ፤ ከተጀመረ በኋላ ብትናገሩ ዋጋ የለውም” ሱሊ ካስጠነቀቁ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው።
ፎቶ- ትግራይ ቴሌቭዥን

ዜና፡ የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት #በትግራይ ክልል የሚገኙ 84 ወረዳዎች ላይ የምግብ እርዳታ አቅርቦት እንደሚቀጥል ተገለጸ
የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት (#ዩኤስኤድ) በትግራይ ክልል የሚገኙ 84 ወረዳዎችን የሚሸፍን የምግብ እርዳታ አቅርቦት እንደሚያቀርብ የትግራይ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን አስታወቀ።
በነዳጅ እጥረት ሳቢያ አንድ ነጥብ 9 ሚሊዮን ለሚጠጋ የክልሉ ተረጂ መድረስ የነበረበት የምግብ እርዳታ እንዳልደረሰ ኮሚሽኑ ጠቁሟል፤ በክልሉ መጠለያዎቹ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል 50 በመቶ ያህሉ ብቻ የተወሰነ የምግብ እርዳታ እንዲደርሳቸው መደረጉን አመላክቷል።
#በአሜሪካ በኩል ይመጡ የነበሩ ረድኤቶች በአለም የምግብ ፕሮግራም አማካኝነት በክልሉ ለሚገኙ ተረጂዎች ይዳረስ የነበረ መሆኑን ያወሱት ኮሚሽነሩ አሁን ላይ #በካቶሊክ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ለሚመራው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥምረት ለጋራ የአደጋ ጊዜ ኦፕሬሽን (ጄኦፒ) መሰጠቱን አመላክተዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8513

Addis standard
የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በትግራይ ክልል የሚገኙ 84 ወረዳዎች ላይ የምግብ እርዳታ አቅርቦት እንደሚቀጥል ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9/ 2017 ዓ/ም፦ የአሜሪካ የረድኤት ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በትግራይ ክልል የሚገኙ 84 ወረዳዎችን የሚሸፍን የምግብ እርዳታ አቅርቦት እንደሚያቀርብ የትግራይ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን አስታወቀ። በነዳጅ እጥረት ሳቢያ አንድ ነጥብ 9 ሚሊዮን ለሚጠጋ የክልሉ ተረጂ መድረስ የነበረበት የምግብ እርዳታ እንዳልደረሰ ኮሚሽኑ ጠቁሟል፤ በክልሉ መጠለያዎቹ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል…
ዜና፡ በ #ፈንታሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ስድስት ሰዎች በኮሌራ በሽታ ህይወታቸው አለፈ
በ #ኦሮሚያ ክልል በፈንታሌ ወረዳ በመሬት በተከሰተው መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ስድስት ሰዎች በንፁህ ውሃ እጦት ምክንያት በተከሰተ የኮሌራ በሽታ መሞታቸውን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አሰቦት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
ኃላፊው ተፈናቃዮቹ ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማጣታቸው የዝናብ ውሃን ለመጠጥነት እየተጠቀሙ መሆኑን በመግለጽ፤ "በርካታ ሰዎች በኮሌራ በሽታ ተይዘው ስድስት ሰዎች ሞተዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ፤ "ከዚህ ቀደም እርዳታ በቡሳ ጎኖፋ እና በእርዳታ ድርጅቶች በኩል ይሰጥ ነበር" ሲሉ ገልጸው፤ አሁን ግን ሲደረግልን የነበረው እርዳታ “ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል” ብለዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በ #አፋር ክልል እንደ ዱለቻ እና አዋሽ ፋንታሌ ካሉ ወረዳዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በእርዳታ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።
ከአፋር ክልል ዱለቻ ወረዳ መፈናቀላቸውን የተናገሩት መሀመድደወል ኦስማን፤ "የሰብዓዊ እርዳታ ቢያንስ ላለፉት ሶስት ወራት ተቋርጧል" ሲሉ ጠቅሰው፤ ተፈናቃዮቹ በምግብ እና የመጠጥ ውሃ እጦት ችግር ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8515

በፈንታሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ስድስት ሰዎች በኮሌራ በሽታ ህይወታቸው አለፈ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9/ 2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል በፈንታሌ ወረዳ በመሬት በተከሰተው መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ ስድስት ሰዎች በንፁህ ውሃ እጦት ምክንያት በተከሰተ የኮሌራ በሽታ መሞታቸውን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀመድ አሰቦት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። አቶ መሀመድ “በኦሮሚያ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ…
ዜና፡ አይ ኤም ኤፍ #የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደናቀፍ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ፣ የጸጥታ ስጋት እና እርዳታ ማሸቆለቆል አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል
- በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 ከአምስት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ የምግብ ወይም የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል ብሏል
አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ኢትዮጵያ ከተቋሙ ባገኘችው በ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ECF) የታጀበው እና እያካሄደች ያለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እንቅፋት ሊያጋጥመው ይችላል ሲል ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት አስጠነቀቀ።
ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ስታገኘው የነበረው ከፍተኛ የሆነ የውጭ እርዳታ ማሽቆልቆሉ እንዲሁም በሀገሪቱ የሚስተዋለው ተቋሙ ደካማ ሲል የገለጸው የፀጥታ ሁኔታ ዋነኛ ችግሮቿ ናቸው ሲል ለማሻሻያው አለመሳካት በምክንያትነት አስቀምጧል፤ በተጨማሪም ተቋሙ በሪፖርቱ የትይዩ የውጭ ምንዛሬ (ጥቁር ገበያ) እያንሰራራ መምጣቱም ለኢኮኖሚ ማሻሻያው እንቅፋት መሆኑን ጠቅሷል።
አይኤም ኤፍ በሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያው እንዲሳካ ለማድረገ የሄደበትን ርቀት አወድሷል፤ ተቋሙ አስቸጋሪ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት ፈጽሟቸዋል ብሎ ካወደሳቸው እርምጃዎች መካከልም የድጎማ ቅነሳን ማካሄዱ፣ የታክስ ማዋቅሩ ላይ ማሻሻያ ማድረጉ፣ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲን መከተሉ የሚሉት ይገኙበታል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8520

አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደናቀፍ ይችላል ሲል አስጠነቀቀ፣ የጸጥታ ስጋት እና እርዳታ ማሸቆለቆል አሳሳቢ ነው ሲል ገልጿል - Addis standard
በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 ከአምስት ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ የምግብ ወይም የሰብአዊ እርዳታ ያስፈልገዋል ብሏል አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9/ 2017 ዓ/ም፦ አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ኢትዮጵያ ከተቋሙ ባገኘችው በ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ የብድር አቅርቦት (ECF) የታጀበው እና እያካሄደች ያለችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እንቅፋት ሊያጋጥመው ይችላል ሲል ትላንት ሐምሌ 8 ቀን…
ዜና: በ #አፋር ክልል ከባድ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ከ50 በላይ ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደረሰ
በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ ትናንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከባድ ነፋስ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ ከ50 በላይ ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን የአፋር ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
በኮሚሽኑ የሎጂስቲክስ ኦፕሬሽን ቁጥጥር ዳይክሬተር የሆኑት አቶ አሊ መሀመድ በአደጋው የ1 ሰው ሕይወት ማለፉን እና በ32 ሰዎች ላይ ከባድ፤ በ22 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።
በዚህም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ ዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን፤ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በ3 ባንኮች፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማቶች እንዲሁም በ5 የጨው ፋብካዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ጠቁመዋል።
በተከሰተው አደጋ በከተማው ጉዳት ያልደረሰበት አንድም ቤት አለመኖሩን የገለጹት አቶ አሊ፤ አያይዘውም ትምህርት ቤቶች እና ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት በአደጋው እንደተጎዱ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ #መቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ አንድ አውሮፕላን መጠነኛ የመንሸራተት እክል እንዳጋጠመው ገለፀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥሩ ET-298 የሆነ አውሮፕላን በትናንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስቶ መቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ካረፈ በኋላ ከመንደርደሪያው መጠነኛ የመንሸራተት እክል አጋጥሞታል ሲል ገልጿል።
አውሮፕላኑ በሚያርፍበት ጊዜ ዝናብ እየዘነበ እንነበር አየር መንገዱ ባወጣው አጭር መግለጫ ገልጿል።
በሁለት የበረራ ሰራተኞች ላይ መጠነኛ ጉዳት ከማጋጠሙ ወጭ በመንገደኞቻችን ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰና በሰላም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደረጓል ብሏል።
የበረራ ሰራተኞቹ ለተጨማሪ የህክምና ዕርዳታ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና መስጫ ተቋም ተወስደው ከታከሙ በኋላ ወደ ሆቴል እንዲሄዱ ተደርገዋል ተብሏል።
አየር መንገዱ ለተፈጠረው የደንበኞች መጉላላት ይቅርታ ጠይቆ ተጨማሪ መረጃ ሲኖር የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።
ባሳለፍነው አመት ጥር ወር አየር መንገዱ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቀሌ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ መጠነኛ አደጋ እንዳጋጠመው ይታወቃል።
በጉዳቱ በመንገደኞች እና በበረራ ሰራተኞች ላይ ያጋጠመ ምንም አይነት ጉዳት አለመኖሩንም በወቅቱ አየር መንገዱ አረጋግጧል፡፡

የ #ኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነርን ጨምሮ ሁለት ኮሚሽነሮች የሥራ ዘመናቸው ሳይጠናቀቅ መልቀቂያ አስገቡ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና የተቋቋሙ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተገለፀ።
ኮሚሽነሮቹ ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መልቀቂያ ማስገባታቸውንና የሦስት ወር ማስጠንቀቂያ ጊዜ መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የከፍተኛ ኮሚሽነሮቹ የሥራ መልቀቅ ከአዲሱ ዋና ኮሚሽነር "የአመራር ስልት" ጋር በተያያዘ "ተገፍተው" እንደሆነ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኮሚሽኑ ምንጮቹ ተናግረዋል።
"አሳታፊነትን" ይከተል የተነበረው የተቋሙ አሠራር ባለፉት ወራት ለሥራ ኃላፊዎች እና ለሠራተኞቹ ውሳኔዎቹን "አለማሳወቅ፣ አለማሳተፍ እና መመካከርን" ወደ ጎን ማለቱ ለኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች መልቀቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አመልክተዋል።
የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አሳታፊነት በኮሚሽኑ "አደረጃጀት" ላይ የተመሠረተ እንደነበር ያነሱት የቢቢሲ ምንጮች፤ ተቋሙ ባለፉት ወራት ያለ ምክክር እና እውቅና ሠራተኞቹን ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ መመደብ እንዳለ አመልክተዋል።
ይህን የአመራር ስልት "ለሰብዓዊ መብት የማይሠራ" ያሉት ምንጮቻችን፤ ባለፉት ስድስት ወራት "ያለ ምክንያት" አምስት ዳይሬክተሮች የሥራ መደብ ላይ ሽግሽግ መደረጉን መናገራቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው።
ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መለሰ እና ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሐዋርያ ሰኔ 18/2013 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው ልዩ ጉባኤ የተሾሙ ሲሆን፣ ተቋሙ ባካሄደው ለውጥ ስማቸው ይነሳል።

ዜና፡ "የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ
#የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ "የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት #በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።
ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረዳ አንድሪው ምቦጊሪን ጋር በነበራቸው ቆይታ “ያለ ደህና መጠለያ እና ምግብ ተጥለው በከፍተኛ ችግር ላይ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለአምስተኛ የክረምት ወራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ህይወታቸውነ እያሳለፉ ማየት በጣም ከባድ ነው” ሲሉ መናገራቸውን ከጽ/ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን በበኩላቸው በክልሉ በተካሄደው አስከፊ ጦርነት ሳቢያ ቤታቸውን ጥለው የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎችን ተቋማቸው ተቀብሎ መጠለያ እና ምግበ እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውሰው በቀጣይ በሚደረገው የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ይሁን በቀያቸው እስኪቋቋሙ ድረስ ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባታቸውን መረጃው አካቷል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8525

"የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው" - ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/ 2017 ዓ/ም፦ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ “የተፈናቃዮችን ሙሉ ደኅንነታቸውን ባስጠበቀ መልኩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲመለሱ ማድረግ የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው” ሲሉ ገለጹ። ፕሬዝዳንቱ ይህንንያሉት በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዳይሬክተር አንድሪው ምቦጊሪን ትላንት ሐምሌ 9 ቀን…
ዜና: የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ 8324 ብር እንዲሆን የስራ ማህበራት በሰፊው የጠየቁት አዋጅ ያለ ማሻሻያ 2000 ብር ሆኖ ፀደቀ
የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ 8324 ብር እንዲሆን የስራ ማህበራት በሰፊው ሲጠይቁ የቆየው ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ሳይደረግበት 2000 ብር ሆኖ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፀደቀ።
አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው የማሻሸያ አዋጅ ከግብር ነጻ መነሻ ደመወዝን ከነበረበት 600 ብር ወደ 2000 ብር ከፍ እንዲል አድርጓል። እንዲሁም 35 በመቶ ግብር መጣል የሚጀምርበትን የደመወዝ መጠን ደግሞ ከነበረበት 10,900 ብር ወደ 14 ሺህ ብር ከፍ አድርጓል።
አዋጁ “ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች የኑሮ ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም” በሚል በተለይም ከኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራዊ ኮንፌዴሬሽን በኩል ትችት ቀርቦበታል።
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው ከኢቢሲ ጋር አድርገውት በነበረው ቃለመጠየቅ ላይ ስለ ማሻሸያ አዋጁ ሲናገሩ፤ “መኖር ከማይችል እና በልቶ ከማያድር ሰው ግብር አትሰበስብም ” ብለዋል።
“እንደ ሀገር ግብር መሰብሰብ አለበት ልማትም መቀጠል አለበት” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ አክለውም የሰው ህይወትም መቀጠል አለበት ሰው እየተራበ መስራት እና ምርታማ መሆን አይችልም” ሲሉ ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8529&=1

የደመወዝ የገቢ ግብር መነሻ 8324 ብር እንዲሆን የስራ ማህበራት በሰፊው የጠየቁት አዋጅ ያለ ማሻሻያ 2000 ብር ሆኖ ፀደቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/2017 ዓ/መ:- የደመወዝ ገቢ ግብር መነሻ 8324 ብር እንዲሆን የስራ ማህበራት በሰፊው ሲጠይቁ የቆየው ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ሳይደረግበት 2000 ብር ሆኖ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፀደቀ። ምክር ቤቱ አዋጁን ያጸደቀው ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በ5 ተቃውሞ እና በ12 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው። አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው የማሻሸያ…
ዜና: #ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል አዋጅ ማሻሻያ በምክር ቤቱ ፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው በ2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው አፀደቀ።
የታገደ የፖለቲካ ፓርቲ እገዳው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜያት ከማንኛውንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ፣ በየትኛውም ደረጃ በሚደረግ ምርጫ ላይ እንዲሁም በጋራ ምክር ቤቱ ውስጥ መሳተፍ ይከለክላል። ከመንግስት ከሚሰጥ ደጋፍ ተጠቃሚም አይሆንም።
በጸደቀው አዋጅ ዙሪያ አስተያየታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የሰጡ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር አመራሩ ጎበዜ ጎኣ “ምርጫ ቦርድ አሻሻሎ ባስጸደቀው ህግ ገዢው ፓርቲ ብቻውን ቢወዳደር እንጂ ሌላው ሰው የሚወዳደርበት ምንም አይነት ሜዳ የለም” ብለዋል። “ፓርቲዎችን ከምርጫ ሜዳ የሚያስወጣ ነው” ሲሉም ተችተዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8537

ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል አዋጅ ማሻሻያ በምክር ቤቱ ፀደቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/2017ዓ/ም:- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲን ከምዝገባ ከመሰረዙ በፊት እስከ አምስት ዓመት ማገድ የሚያስችል የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን አፀደቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው በ2ኛ አስቸኳይ ስብሰባው፤ የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር…
ዜና: የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርት የገበያ ድርሻ ወደ 41 በመቶ ማደጉ ተገለጸ
የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርት የገበያ ድርሻ ወደ 41 በመቶ ማደጉን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ ገለጹ።
ሚንስትሯ ይህን የገለጹት የአርማወርሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የካሳቫ ስታርች ምርት የአዋጭነት ጥናትን ለፋርማሲዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎችና ለባለድርሻ አካላት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬህይወት አበበ በዚሁ ወቅት፥ የሀገር ውስጥ የመድሀኒት የማምረት አቅምን ለማሳደግ ሰፋፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው አርመር ሀንሰን ኢንስቲትዩት በጥናትና ምርምር በመደገፍ ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል።
በመድሃኒት ግዥ ሂደት የሀገር ውስጥ መድሃኒት አምራቾች የሚያቀርቧቸው መድሃኒቶች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው የገለጹት ሚኒስትሯ በዚህም ባለፉት ዓመታት የሀገር ውስጥ የመድሃኒት ምርት መጨመሩን እና የገበያ ድርሻውም ከ8 በመቶ ወደ 41 በመቶ ከፍ ማለቱን ጠቁመዋል።
ሆኖም ከግብዓት አንጻር አሁንም አብዛኛው ከውጭ የሚገባ መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህን ለማስተካከል ለመድሃኒት ግብዓት የሚውሉ በርካታ ጸጋዎችን ወደ ጥቅም መቀየር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው ደግሞ የካሳቫ ምርት ላይ የተደረገው የፋርማሲዩቲካል አዋጭነት ጥናት በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
አክለውም ኢንስቲትዩቱ በቀጣይም ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸውን የምርምር ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በ #ሰሜን_ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ከ3 ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ በአንድ ለሊት “በታጣቂዎች” መዘረፉ ተገለጸ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ መዘዞ ንዑስ ወረዳ ሐምሌ 9/2017 ዓ.ም ከሶስት ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ተዘረፏል ሲል የወረዳው ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ገለጸ።
የጣርማበር ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ዘረፋው የተፈጸመው “ፅንፈኛ ኃይሎች” ሲል በጠራቸው አካላት መሆኑን ትናንታ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ቸርነት፤ “በንዑስ ወረዳዉ ከሚገኙ ከ #ቡና ባንክ 11ሚሊዮን 550 ሺህ ብር፣ ከ #ፀዳይ ባንክ 1 ሚሊዮን 28ሺህ ብር እንዲሁም ከ #አባይ ባንክ 29 ሚሊዮን 365ሺህ ብር በአጠቃላይ 41ሚሊዮን 943 ሺህ ብር በፅንፈኞች ተዘርፏል” ብለዋል።
ዘረፋው በዕለቱ ከሌሊቱ 7 ሰዓት መፈጸሙን የገለጹት ኃላፊው፤ “ፅንፈኛ ሀይል” ሲሉ የጠሩት አካል “የህዝብን ሀብት መዝረፍና ማዉደም የዘወትር ተግባሩ አድርጎ ቀጥሏል” ሲሉ ወቅሰዋል።
አክለውም የሰላምን አማራጭ ወደ ጎን በመተዉ "ለዘረፋ በተሰማሩ ፅንፈኞች” ላይ የህግ ማስከበር ዘመቻዉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በክልሉ ሰሜን ሽዋ ዞን የባንክ ዘረፋ መፈጸሙ ሲገለጽ የአሁኑ የመጀመርያ አይደለም። ባሳለፍነው ዓመት ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በሰሜን ሽዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ከ #ኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ “በታጠቁ ሀይሎች” መዘረፉን ወረዳው ማስታወቁ ይታወሳል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሠይድ ኢብራሂም በባንኩ ሬማ ቅርንጫፍ ላይ ተፈጸመ በተባለው ዝረፊያ "ህገ- ወጥ ፅንፈኛ" ሲሉ በጠሯቸው በአካባቢዉ በሚንቀሳቀሱ “የታጠቁ ሀይሎች" የተከወነ መሆኑን በወቅቱ ገልፀዋል።