#የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊነት ትምህርት መሰጠት መጀመሩን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የተጎዱ ዜጎችን የሚያጽናኑ፤ የተሰበሩትን የሚያቃኑና የተቸገሩትን የሚረዱ ወጣቶችን መፍጠር የሚያስችል የሰብዓዊነት ትምህርት አየሰጠ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ቶላ እንደተናገሩት፤ ያዘኑ ዜጎችን የሚያጽናኑ፤ የተቸገሩትን የሚረዱ፤ የተሰበሩትን የሚያቃኑ ወጣቶችን ለማፍራት የሰብዓዊነት ትምህርት አስፈላጊ ነው፡፡
ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ወጣቱን በሰብዓዊነት ስብዕና የሚያንጽ ሥርዓተ ትምህርት ቀርጾ እያስተማረ ይገኛል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ሥርዓተ ትምህርቱ 10 የትምህርት አይነቶችን የያዘ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በሥርዓተ ትምህርቱም የስነ-ምግባር፤ የሞራል ግንባታ፤ የሰብዓዊና ሌሎች የትምህርት አይነቶች ተካተዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የትምህርቶች ይዘት በውስጣችን ያለውን ደግነት፣ ርህራሄ፣ ሰው የመርዳት ባህልና ልምዳችንን ይበልጥ የሚያሳድጉ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ትምህርቶች በማኅበሩ የማስልጠኛ ማዕከል ለወጣቶች እየተሰጡ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት ማስጀመሪያ መርኃ-ግብር በጥር ወር ማካሄዱ ይታወቃል።
የሰብዓዊነት ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ ሳሪስ አደይ አበባ ሰፈር የተከፈተ መሆኑ በወቅቱ ተገልጿል። ትምህርቱ የሚሰጠው በስቴሻል ዲፕሎማ በሁለት ሴሚስቴር ሆኖ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው ተብሏል።

ዜና: የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል "ኤሌክትሮኒክስ በመጠቀም ትግሉን ከማረሚያ ቤት ሆኖ እያስቀጠለ እና እየመራ ነው" ሲል ፖሊስ ከሰሰ
የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ “በማረሚያ ቤቱ አመራሮች አመቻችነት ኤሌክትሮኒክ በመጠቀም ትግሉን ከማረሚያ ቤት ሆኖ እያስቀጠለ እና እየመራ ነው” ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ መግለፁን የዶ/ር ዳንኤል የስራ ባልደረቦች ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ።
በርካታ የጤና ባለሙያዎች የታደሙበት እንደነበር በተገለጸው በትናንቱ ችሎት፤ ፖሊስ “ጽንፈኛ” ሲል ከጠራቸው ሀይሎች ጋር ዶ/ር ዳንኤል “ግንኙነት እንዳለው አረጋግጠናል” ማለቱንም አክለው ተናግረዋል። የዶ/ር ዳንኤል ስልክ እና ላፕቶፕ ወደ #ኢንሳ ለምርመራ መላኩንም ለችሎቱ ገልጿል።
በዶ/ር ዳንኤል ጠበቃ በኩል ደግሞ “እስር ቤት ኤሌክትሮኒክስ ገብቶለታል ለሚለው፤ ፖሊስ ከተቋማቱ ጋር ነው መነጋገር ያለበት፤ የደንበኛዬ ችግር አይደለም” የሚል መከራከሪያ ቀርቧል።
የሀኪሙ የሙያ ባልደረባ፤ በትናንትናው ዕለት የዶ/ር ዳንኤል የፌስቡክ ገጽ ‘ኦንላይን’ ሆኖ መዋሉን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀው፤ በዓለምአቀፍ ተቋም ውስጥ በምትሰራ ግለሰብ “ዶ/ር ዳንኤል ጽፎልኝ ነበረ፤ ተፈቷል ወይ” ተብለው መጠየቃቸውን ተናግረዋል። “በዶክተር ዳንኤል ላይ ሀሰተኛ ማስረጃዎች እንዳይዘጋጁበት ስጋት አለኝ” ሲሉም ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ: https://addisstandard.com/Amharic/?p=8443

Addis standard
የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል "ኤሌክትሮኒክስ በመጠቀም ትግሉን ከማረሚያ ቤት ሆኖ እያስቀጠለ እና እየመራ ነው" ሲል ፖሊስ ለፍድ ቤቱ ገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም:- ከጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ጋር ተያይዞ በእስር ላይ በሚገው የንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ “ኤሌክትሮኒክስ በመጠቀም ትግሉን ከማረሚያ ቤት ሆኖ እያስቀጠለ እና እየመራ ነው” ሲል ፖሊስ ለፍድ ቤቱ መግለፁን የዶ/ር ዳንኤል የስራ ባልደረቦች ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቁ። ትናንት ሀሙስ ሐምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት የባሕርዳር ከተማ ከፍተኛ…
ዜና፡ “በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማከሚያ ማእከላት ወስጥ ህክምና ላይ የሚገኝ የኤምፖክስ ታማሚ የለም” ሲል #የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ
የጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ #በኤምፖክስ ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጦ በለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ወስጥ ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 25 ሰዎች ህክምናቸውን በአግባቡ ተከታትለው ሙሉ በሙሉ ከበሽታው አገግመው ወጥተዋል ሲል አስታወቀ።
በሀገራችን የመጀመሪያው የኤምፖክስ ታማሚ ከተገኘበት ከግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ ለ520 በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁሟል።
ከተመረመሩት መሃል 26ቱ በበሽታው እንደተያዙ መረጋገጡን እና ከእነዚህ ታማሚዎች መሃል የአንድ ታማሚ ህይወት ማለፉን የጠቆመው ሚኒስቴሩ “የተቀሩት 25ቱ ታማሚዎች ህክምናቸውን በአግባቡ ተከታትለው ሙሉ በሙሉ ከበሽታው አገግመው ወጥተዋል” ብሏል።
በአሁኑ ወቅት በለይቶ ማከሚያ ማእከላት ወስጥ ህክምና ላይ የሚገኝ ታማሚ የለም ሲል ገልጿል።
አሁንም ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመቆጣጠር እና የህብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅ የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በትኩረት መስራቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በየቀኑ ለህብረተሰቡ ይሰጠው የነበረውን የበሽታው ወቅታዊ መረጃ እንደአስፈላጊነቱ በየሳምንቱ መስጠት የምንቀጥል ይሆናል ብሏል።

ዜና: የ #ኦሮሞ_ነፃነት_ሠራዊት በ #ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈፀመ ሰለተባለው ጥቃት "እንደማያውቅ" ገለፀ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ባሳለፍነው እሁድ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ እና ከሰባት በላይ ቤቶች መቃጠላቸው መገለፁን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (የኦነሰ) ሰለ ጥቃቱ "እንደማያውቅ" ገለጿል።
በ #መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ ነዋሪዎች እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም “የሸኔ ታጣቂዎች” ሲሉ የጠሯቸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ፈጸሙት ባሉት ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን፣ ሰባት ቤቶች መቃጠላቸውንና “አስገድዶ መድፈር እና ዝርፊያ” መፈጸሙንም አመልክተዋል።
በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሰጡት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ተወካይ፤ "በቅርቡ በመተከል ዞን ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተደረገው ግጭት የሲቪል ሰዎች ሞት ያስከተለ ምንም አይነት ክስተት ቡድኑ እያወቅም" ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።
አክለውም "ከመደበኛ ወታደራዊ ዘመቻዎች ውጪ የተመዘገበው ብቸኛው ጥቃት የተፈፀመው በመከላከያ ሰራዊት ነው" ብለዋል። "የቤንሻንጉል ጉምዝ ሚሊሻ አባላት አካባቢውን ከኦነሰ ማስጠበቅ ባለመቻላቸው ምክንያት ዒላማ እንደተደረጉ" የገለፁት የኦነሱ ተወካይ፤ "በዚህ ውጭ በቤንሻንጉል ጉምዝ ያሉ ሰዎች ወንድሞቻችን እና ጥሩ ጎረቤቶቻችን ናቸው" ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8453

የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈፀመ ሰለተባለው ጥቃት "እንደማያውቅ" ገለፀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም:- በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ባሳለፍነው እሁድ በተፈፀመ ጥቃት አንድ ሰው መገደሉ እና ከሰባት በላይ ቤቶች መቃጠላቸው መገለፁን ተከትሎ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ሰለጥቃቱ “እንደማያውቅ” ገለፀ። በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ ነዋሪዎች እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም “የሸኔ ታጣቂዎች” ሲሉ የጠሯቸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ፈጸሙት ባሉት…
ዜና: አስተዳደሩ መዲናዋን ከጎበኙ "አንድ ሚሊየን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊየን ብር አግኝቻለሁ" አለ
በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ በተካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ከተማዋን ከጎበኙ "ከ1 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊዮን ብር መገኘቱን" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡
ከንቲባ አዳነች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም አስመልክተው ለከተማዋ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት የኮሪደር ልማቱ የአዲስ አበባ ከተማን ገጽታ እየቀየረ በመሆኑ ከተማዋ የስበት ማዕከል ሆናለች ሲሉ አንስተዋል፡፡
በዚህም በርካታ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በአዲስ አበባ እየተካሄዱ መሆናቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ አክለውም በከተማዋ በተካሄዱ ኮንፈረንሶች እና ከተማዋን ከጎበኙ "ከ1 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች 143 ቢሊዮን ብር መገኘቱን" ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም ከገቢ ባሻገር የገጽታ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ "አዲስ አበባ ባስመዘገበችው ውጤት በዓለም አቀፍ የከተሞች ኮንፈረንስ ከ115 አቻ ከተሞች መካከል ቀዳሚ ሆና መነሳቷን እንዲሁም የአፍሪካ ስማርት ሲቲ አሸናፊ መሆኗን" ጠቁመዋል፡፡
በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማትም የሥራ ባሕል አፈጻጻም እና ትብብር የተማርንበት፤ ለብዙ ሺህዎች የሥራ ዕድልን የፈጠረ እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ያደገበት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና: የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭና የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት በይፋ ተጀመረ
የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነዶች እና የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ትናንት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል፡፡
ግብይቱን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን እና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በጋራ በመሆን ነው፡፡
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ወቅት የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፤ "የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድን ለገበያ ክፍት የማድረግና የግሉ ዘርፍ የሰነድ ሙዓለ ንዋዮች ግብይት ጅማሮ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ውጤታማነት ማሳያ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው ደግሞ ገበያ መር በሆነ መልኩ የበጀት ጉድለትን ለመሙላት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፤ አካታች የፋይናንስ ሥርዓትን ለመገንባትና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የግብይት ሒደቱ የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድን በዘመናዊ መልኩ ለገበያ ክፍት በማድረግ አማራጭ የፋይናንስ አቅም ሆኖ እንደሚያገለግል ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ግልጽ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ የካፒታል ገበያ ለመገንባት፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ለማሻሻልና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማስፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መገለጹን ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡

ዜና፡ ግብጽ የከረሙት #የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ #ቱርክ በማቅናት በአንካራ ከኤርዶጋን ጋር መምከራቸው ተገለጸ
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ ትላንት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አንካራ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ጋር መምከራቸው ተገለጸ፤ #በግብጽ ካይሮ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ከቱርኩ አቻቸው ጋር በዝግ መምከራቸውን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአንካራው ስብሰባ የሁለቱ መሪዎች በቀጠናው ስላሉ ውጥረቶች መወያየታቸውን የጠቆሙት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ኤርዶጋን በቀጠናው እየተስተዋሉ ያሉ ውጥረቶች የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት የበለጠ ሊያናጉ የሚችሉ መሆናቸውን በመግለጽ ሰጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የወጡ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች #በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈረመው የአንካራው ስምምነት እክል እንዳጋጠመው እና መቆሙን አመላክተዋል፤ ከሚያዚያ ወር ወዲህ ምንም አይነት የውይይት መርሃግብረ አልተያዘም ብለዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8464

ግብጽ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ ቱርክ በማቅናት በአንካራ ከኤርዶጋን ጋር መምከራቸው ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5/ 2017 ዓ/ም፦ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ ትላንት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አንካራ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ጋር መምከራቸው ተገለጸ። በግብጽ ካይሮ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ከቱርኩ አቻቸው ጋር በዝግ መምከራቸውን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ባሳለፍነው ሳምንት የወጡ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች በኢትዮጵያ እና…
ዜና: በሺህዎች የሚቆጠሩ የ #ደቡብሱዳን ስደተኞች በሀገሪቱ ያለውን ውጊያ በመሸሽ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ
በደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦር እና በተቃዋሚዎች መካከል የሚደረገዉን ዉጊያ የሸሹ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የሐገሪቱ ዜጎች ምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል መግባታቸዉን የክልሉ ባለሥልጣናትና የተባበሩት መንግሥታት የሥደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) አስታወቁ።
ካለፈው መጋቢት ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ሱዳን መንግሥት ጦርና በመንግሥት ተቃዋሚ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ወደ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ክልል ዋንታዋ ወረዳ መግባታቸውን የዋንታዋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋትዊች ቡዝ ገልጸዋል።
“ለስደተኞቹ በቂ ምግብ እየቀረበላቸው አይደለም” ያሉት አስተዳዳሪው፤ በግምት የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ 50ሺህ ያክል ስደተኞች ማታር እና ሙን በተሰኙ የወረዳው አካባቢዎች ህብረተሰቡ ያለውን እያካፈላቸው እየኖሩ እንደሆነ አክለዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በዋናነት ሴቶችና ህፃናት የሚበዙባቸው ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ፣ ጋምቤላ ክልል፣ ዋንታዋ ወረዳ እንደገቡ ማረጋገጡን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡
ኮሚሽኑ ለጣቢያው በላከው ደብዳቤ እንዳሳወቀው ስደተኞቹ በድንገት አካባቢያቸውን በመልቀቃቸው ለምግብ እጥረት፣ ለህክማና እጦት፣ ለመጠለያና ለሌሎች ችግሮች የተጋለጡ እንደሆኑ ገልጧል፡፡
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/750166294194994/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ዜና: ከ19 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸው ተገለጸ
ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እስካሁን 19 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የህግና ፖሊሲ ዘርፍ ኃላፊ ጋብሬላ አብርሃም ገለጹ።
ኃላፊዋ በአዲስ አበባ እና በክልል የዲጂታል የመታወቂያ ምዝገባ ማከናወንና ከተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም እስካሁን 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን ነዋሪዎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውንና ከ55 ተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የነዋሪዎችን የመታወቅ መብት ለማረጋገጥ፣ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባዮች መካከል መተማመን እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልጽነት፣ተጠያቂነትና የተሳለጠ አሰራር ለመዘርጋት የዲጂታል መታወቂያ ተግባራዊ መደረጉንም አንስተዋል።
አያይዘውም በ2018 በጀት አመት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን የበለጠ ለማሳደግ እቅድ መያዙንና ከተቋማት ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በቅርቡ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር 15 ሚሊየን መድረሱን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ማስታወቁ ይታወሳል።

#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ ክልል 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማስገባቱ ተገለጸ
ከሌሎች ማዕድን ምርት 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡም ተገልጿል
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት አቅዶ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አድማሱ ሞርካ፤ ከዕቅዱ በላይ የተከናወነበት ምክንያት መንግስት ለወርቅ አቅራቢዎች ያደረገው “ማበረታቻ እና ህገ-ወጥ ግብይት” መቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፉ እንዲነቃቃና አምራቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል።
በክልሉ የተመረተው ወርቅ በአነስተኛና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አሳድጓል ነው ያሉት።
ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰልና እምነበረድ በስፋት እየተመረተ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
አቶ አድማሱ ከማዕድን ምርቱ 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡንም ጠቅሰው፤ በቀጣይ ትላልቅ ካምፓኒዎችን በመጋበዝ በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ለማሰማራት ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ከሌሎች ማዕድን ምርት 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡም ተገልጿል
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 500 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ለማስገባት አቅዶ 4ሺህ 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማስገባቱን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አድማሱ ሞርካ፤ ከዕቅዱ በላይ የተከናወነበት ምክንያት መንግስት ለወርቅ አቅራቢዎች ያደረገው “ማበረታቻ እና ህገ-ወጥ ግብይት” መቀነስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዘርፉ እንዲነቃቃና አምራቹ ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቅሰዋል።
በክልሉ የተመረተው ወርቅ በአነስተኛና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች መሆኑን ገልጸው፤ ይህም የህብረተሰቡን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አሳድጓል ነው ያሉት።
ከወርቅ በተጨማሪ የድንጋይ ከሰልና እምነበረድ በስፋት እየተመረተ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ የሚገኙ የማዕድን ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
አቶ አድማሱ ከማዕድን ምርቱ 49 ሚሊዮን ብር መሰበሰቡንም ጠቅሰው፤ በቀጣይ ትላልቅ ካምፓኒዎችን በመጋበዝ በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ለማሰማራት ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm
ዜና: #ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን የብሔራዊ ጥቅሟ ወሳኝ አካል አድርጋ እየሰራች ነው_ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን የብሔራዊ ጥቅሟ ወሳኝ አካል አድርጋ እየሰራች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም ተስፋዬ ገለጹ።
ኃላፊው ይህን የተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከተለያዩ የጎረቤት አገራት ለመጡ ዲፕሎማቶች እየሰጠ ባለው ሥልጠና መድረክ ላይ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም ተስፋዬ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ “ኢትዮጵያ ብልጽግናን፣ ሰላምንና መረጋጋትን የሚመለከተውን የብሔራዊ ጥቅሟን የቀጣናው እጣ ፈንታ ወሳኝ አካል” አድርጋ ትመለከታለች።
ቀጣናው ሽብርተኝነት፣መፈናቀል፣ የርስ በርስ ግጭትና ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ የቀጣናው ተግዳሮቶች ለመቋቋም በርካታ ጠቃሚ እርምጃዎችን እየተወሰደ መሆኑን መናገራቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳም የሥልጠናው አላማ ትብብርን ማጠናከርና በሕዝቦች መካከል ጥልቅ ግንዛቤን ማጎልበት መሆኑን ጠቅሰው፤ በጋራ ችግሮች ላይ የትብብር መድረኮችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ዲፕሎማቶች በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ የጋራ ግቦችን ለማራመድ የሚያደርጉትን የትብብር ጥረቶች መደገፍ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

#ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት እየሰራች መሆኑን አስታወቀች
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሏት እርምጃዎች ላይ እየሰራች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ከሀገራት ጋር የተደረሱ ስምምነቶች መኖራቸውም ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፤ ውሳኔው ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማጠናከር፣ የንግድ ሚዛንን ለመጠበቅ እና በአንድ ምንዛሪ ላይ የመመካትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመከላከል ያለመ ነው።
የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ባሳለፍነው አርብ ዕለት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያ እንደ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ካሉ ሀገሮች ጋር በምንዛሬያቸው እንዲገበያዩ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሷን ተናግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው፤ መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማመቻቸት ከአሜሪካን ዶላር ውጪ በሌሎች ምንዛሬዎች ለመገበያየት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ እየሰራ ነው ብለዋል።
ይህ እርምጃ የሀገሪቱን የውጭ ገበያዎች መዳረሻ ለማስፋት ያለመ ነው ብለዋል። አክለውም ከአሜሪካ ዶላር ውጪ ተጨማሪ ምንዛሬዎች መኖራቸው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ተናግረዋል።

#የአሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ በ #ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የማስፋፊያ ምዕራፍ ማጠናቀቁን ገለፀ
የአሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ "ቢአይቲ ማይኒንግ"፤ በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ማይኒንግ ዳታ ማዕከላት እና የቢትኮይን ማይኒንግ ማሽኖችን የማግኘት ሁለተኛ ምዕራፍ ሂደት መጠናቀቁን አስታወቀ።
ኩባንያው በህዳር ወር ኩባንያው በኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ማይኒንግ ዳታ ማዕከሎችን ለመግዛት ስምምነት ተፈራርሟል።
በታህሳስ ወር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የማስፋፍያ ምዕራፍ ማጠናቀቁን ተከትሎ ኩባንያው ለተቀሩት የመረጃ ማዕከላት ተጨማሪ 45 ሚሊዮን 278 ሺህ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለገበያ ማቅረቡን ገልጿል።
ሁለተኛው የግዥ ምዕራፍ መጠናቀቅ በኋላ የዳታ ማዕከሎቹ አጠቃላይ የኃይል አቅም 51 ሜጋ ዋት ይደርሷል ሲል ሞርኒንግስታር ዘግቧል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሜጋዋት የመረጃ ማዕከልና 17,869 ቢትኮይን ማይኒንግ ማሽኖችን 2.2 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 369,031,800 'ኤ ክላስ' ድርሻዎችን በማጣመር የተገኘ ነው።

ዜና፡ በ #ዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በኦሞ ወንዝ ሙላት መጥለቅለቃቸውና 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ
በ #ደቡብ_ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በኦሞ ወንዝ ሙላት መጥለቅለቃቸውና 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች እና የመንግስት ኃላፊ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
"የኦሞራቴ ከተማ በውሃ ተከባለች፤ የጎርፍ መጥለቅለቁ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ከተማችን ሊገባ ይችላል፤ እጣፈንታችንን ቁጭ ብለን እየተጠባበቅን ነው" ሲሉ ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ በኦምራቴ ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል።
ሌላኛው ስሜ ባይጠቀስ ያሉ እና በጎርፍ መጥለቅለቁ ምክንያት ተፈናቅለው ነበረሙስ በተባለ መጠለያ ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪ በበኩላቸው፤ "የእርሻ ቦታዎችን ሁሉ ጠራርጓል። ቤቶችን አፍርሷል። ኦሞራቴ ከተማን ለመዋጥ ደግሞ አንድ ኪ.ሜ እንኳን አይሞላም የተቃረበው" ብለዋል።
ስማቸውም ሆነ የስራ ሀላፊነታቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኦሞራቴ ከተማ የመንግስት ሀላፊ፤ የኦሞ ወንዝ ሞልቶ የቱርካና ሀይቅ ከኦሞራቴ ከተማ ከዚህ ቀደም ከነበረው 60 ኪ.ሜ ርቀት አሁን ላይ ወደ 1.3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ መጠጋቱን ጠቅሰዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8467

በዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች 'ሙሉ በሙሉ' በኦሞ ወንዝ ሙላት መጥለቅለቃቸውና 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7/ 2017 ዓ/ም፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በዳሰነች ወረዳ 34 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በኦሞ ወንዝ ሙላት መጥለቅለቃቸውና 81 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ነዋሪዎች እና የመንግስት ኃላፊ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። በኦሞ ወንዝ ሙላት የወረዳው ዋና ከተማ የሆነችው ኦሞራቴ ከተማ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በውሃው የመዋጥ ስጋት ውስጥ መግባቷን ስማቸውን እንዳይጠቀስ…
ዜና፡ #የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሆነው የቀይ ባህር #አፋር በሰመራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት ህዝባዊ ጉባኤ ማካሄዱ ተገለጸ
- “በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ውጥረት መንገሱን ጠቁሞ የአፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል” ብሏል
በኤርትራ በተቀዋሚነት የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በአፋር ክልል #ሰመራ-ሎጊያ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ በታደሙበት ሕዝባዊ ጉባኤ ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ ማካሄዱ ተገለጸ።
ድርጅቱ በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፤ጉባኤው የተዘጋጀው በቀይ ባሕር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና በሌሎች የሲቪክ ማህበራት መሆኑም ተጠቁሟል።
“#በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለስልጣናት መካከል የቃላት ጦርነትን ተከትሎ ባሁኑ ወቅት በድንበር አከባቢዎች ላይ ውጥረት መንገሱን ያመለከተው ድርጅቱ (RSADO) የቀይ ባሕር አፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል” ሲል ገልጿል፡፡
አሁን ላይ በኤርትራ ያለው መንግስት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ወደብ እንድትጠቀም ፍላጎት የለውም በማለት ስርዓቱን በመታገል የህዝባቸውንም ሆነ የኢትዮጵያን ፍላጎት ማስከበር ለነሱ በጎ አጋጣሚ መሆኑን የድርጅtu ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሀሩን አመላክተዋል፡፡
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8472

የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚ የሆነው የቀይባህር አፋር በሰመራ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የታደሙበት ህዝባዊ ጉባኤ አካሄደ - Addis standard
“በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ውጥረት መንገሱን ጠቁሞ የአፋር ህዝብ የጦርነት ሜዳ እንዳይሆን አስግቶናል” ብሏል አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ/ም፦ በኤርትራ በተቀዋሚነት የሚንቀሳቀሰው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (RSADO) በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ በታደሙበት ሕዝባዊ ጉባኤ ማካሄዱ ተገለጸ። ድርጅቱ በኤርትራ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ አጠናክሮ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እውነታ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ህዝብ በህዝባዊ መዋጮ እና በአገር ውስጥ ሀብቶች የተገነባ ነው። ለግብፅ የውሃ ደህንነት ምንም አይነት ስጋትም አይፈጥርም።
ይህ ሆኖ ሳለ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በድጋሜ ስለ ግድቡ አሳሳች አስታየት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ትናንት ሐምሌ 7፣ 2017 በዋይት ሀውስ ከኔቶ ዋና ፀሀፊ ማርክ ሩቲ ጋር ባደረጉት ስብሰባ “አሜሪካ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች” ብለው እንደሚያስቡ እና ለግብፅ የውሃ አቅርቦት ስጋት እንደሆነ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህን የተናገሩት በሰኔ ወር የተሰጡትን ተመሳሳይ አስተያየቶችን ተከትሎ ሲሆን፣ በጊዜው አሜሪካ ለግድቡ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች እናም ወደ ናይል የሚፈሰውን የውሃ መጠን “በከፍተኛ ሁኔታ” ይቀንሳል በማለት የተሳሳተ መረጃ ተናግረዋል።
አዲስ ስታንዳርድ፤ እንዲህ ያሉ ተደጋጋሚ ያልተገቡ አስታየቶች ምላሽ ካልተሰጣቸው አላስፈላጊ ቀጠናዊ ውጥረቶችን ሊያባብሱ እንደሚችሉ ያምናል። እነዚህን አሳሳች አስታየቶችን ለመፍታት እና ማስተካከያ እንዲደረግበት የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን እንዲያጠናክር እንጠይቃለን። አስ

ዜና፡ #በትግራይ ክልል የሶስት የእርዳታ ሰራተኞች የተገደሉት “ሆን ተብሎ እና ዒላማ ተደርገው ነው”- የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን ግኝት
ድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ)፤ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ/ም በማዕከላዊ ትግራይ ማሪያ ሄርናንዴዝ ማታስ፣ ቴዎድሮስ ገብረማርያም ገብረሚካኤል እና ዮሃንስ ሃለፎም ረዳ የተባሉ የሶስት ሰራተኞቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ “ሆን ተብሎ እና ዒላማ የተደረገ ጥቃት” እንደነበር አስታወቀ። ድርጅቱ፤ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች በአካባቢው እንደነበሩ ተረጋግጧል ብሏል።
የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን የስፔን ፕሮግራም ፕሬዚዳንት ፓውላ ጊል፤ “ይህ በተኩስ ልውውጥ መካከል የተፈጠረ አልነበረም፣ አሳዛኝ ስህተትም አልነበረም። ባልደረቦቻችን የተገደሉት ሆን ተብሎ በተፈጸመ ጥቃት ነው” ማለታቸውን ድርጅቱ በዛሬው እለት ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።
“ሶስቱ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሠራተኞች በአቢ አዲ አቅራቢያ ግልጽ ምልክት በተደረገበት የኤምኤስኤፍ ተሽከርካሪ በመጓዝ ላይ እያሉ በቅርብ ርቀት በርካታ ጥይቶች ተተኮሰባቸው። በኋላ ላይ አስከሬናቸው በጥይት ከተደበደበውና ከተቃጠለው ተሽከርካሪያቸው 400 ሜትር ርቀት ላይ ተገኝቷል” ሲሉም ተናግረዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8475

በትግራይ ክልል የሶስት የእርዳታ ሰራተኞች የተገደሉት “ሆን ተብሎ እና ዒላማ ተደርገው ነው”- የድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን ግኝት - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ/ም፦ ድንበር የለሽ ሃኪሞች ቡድን /ኤምኤስኤፍ/ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ/ም በማዕከላዊ ትግራይ ማሪያ ሄርናንዴዝ ማታስ፣ ቴዎድሮስ ገብረማርያም ገብረሚካኤል እና ዮሃንስ ሃለፎም ረዳ የተባሉ የሶስት ሰራተኞቹ ላይ የተፈጸመው ግድያ “ሆን ተብሎ እና ዒላማ ተደርገው” መሆኑን አስታወቀ። በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተሽከርካሪዎች በአካባቢው እንደነበሩ ተረጋግጧል ብሏል።…
ዜና፡ በ #ማዕከላዊጎንደር ዞን “#የፋኖ ታጣቂዎች" ፈጸሙት በተባለ “አሰቃቂ ጥቃት” ሶስት ህጻናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ
በ #አማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን #ጭልጋ ወረዳ ጎዶ ቀበሌ ትናንት ሰኞ ሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም “የ #ፋኖ ታጣቂዎች" ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሶስት ህጻናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ስድስት ሰዎች መታገታቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳደር ም/ቤት ገለጹ። በተጫምሪም በርካታ ቤቶች በታጣቂዎቹ መቃጠላቸው ተገልጿል።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ አንድ ነዋሪ፤ ለጥቃቱ "የፋኖ ታጣቂዎችን" ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፤ በጥቃቱ ስምንት ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል። አክለውም፤ ታጣቂዎቹ አጎራባች ከሆነው የሻርዳ ቀበሌ የመጡ መሆናቸውን ገልጸው የፈጸሙትን ጥቃት "አሰቃቂ" ሲሉ ገልጸውታል።
ሌላኛው ነዋሪው በበኩላቸው እስከ አሁን 10 ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሰው፤"ሶስት ህጻናት ቤታቸው ውስጥ ተቃጥለው አስከሬናቸውን ሸፋፍነን ነው የቀበርናቸው" ሲሉ ስለ ጥቃቱ አስከፊነት አስረድተዋል። ሌሎች ያልተገኙ ሰዎችም መኖራቸውን ጠቁመዋል።
የጭልጋ ወረዳ አስተዳደር ም/ቤት ጥቃቱን ተከትሎ ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ በጎዶ ሞላሊት ቀበሌ "የአማራን ህዝብ የማይወክሉ በፋኖ ጭምብል የተደራጁ ፅንፈኛ አካል" ሲል የጠራቸው አካላት በፈጸሙት ጥቃት “ስምንት ንፁሃን አረሶ አደሮች መሞታቸውን፣ አምስት መቁሰላቸውንና ስድስት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን" አመልክቷል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8483

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን “የፋኖ ታጣቂዎች" ፈጸሙት በተባለ “አሰቃቂ ጥቃት” ሶስት ህጻናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች ተገደሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ/ም፡- በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጎዶ ቀበሌ ትናንት ሰኞ ሀምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም “የፋኖ ታጣቂዎች” ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሶስት ህጻናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ስድስት ሰዎች መታገታቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳደር ም/ቤት ገለጹ። በተጫምሪም በርካታ ቤቶች በታጣቂዎቹ መቃጠላቸው ተገልጿል። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን…
ዜና፡ “በአፋር ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል ወይንም #የአፋር ክልል መንግስት ትንኮሳ አድርገን ነው የምንወስደው” - ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ
በአፋር ክልል የሚገኙ #የትግራይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አደርገን ነው የምንወስደው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ገለጹ።
የክልሉ የሰማዕታት ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ “በዚያ በኩል የሚኖር ምንም አይነት ተነሳሽነት/እንቅስቃሴ እንደ ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ እዚያ ያሉ ሀይሎች ብቻ አድርጎ አይወስደውም፣ ወይ የፌደራል መንግስት ነው ካልሆነም የአፋር መንግስት ነው ብሎ ነው የሚወስደው” ብለዋል።
“እዛ ካሉት (ነጻ መሬት) ሀይሎች ጋር ያለው ልዩነት መቶ በመቶ መፈታት ያለበት በሰላማዊ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም ትንኮሳ ከአፋር ክልል በኩል ከመጣ ወይ የአፋር መንገስት ነው አልያም የፌደራል መንግስቱ ነው ተብሎ የሚወሰድ እንጂ የትግራይ ተወላጆች/ተጋሩ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም” ሲሉም አስታውቀዋል፤ ታጣቂዎች “የውክልና (Proxy) ሀይሎች ሁነው እንዳያገለግሉ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ሲሉ ተደምጠዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8489

“በአፋር ክልል የሚገኙ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትንኮሳ አድርገን ነው የምንወስደው” - ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ/ም፦ በአፋር ክልል የሚገኙ የትግራይ ታጣቂዎች የሚፈጽሙት ማንኛውም ትንኮሳ የፌደራል መንግስት ወይንም የአፋር ክልል መንግስት ትነኮሳ አድርገን ነው የምንወስደው ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረዳ ገለጹ። የክልሉ የሰማዕታት ኮሚሽን ባዘጋጀው መድረክ ላይ ትላንት ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሌተናል…
ዜና፡ በ #አማራ ክልል የሚገኙ ግማሽ ሚሊዮን ተፈናቃዮች ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እጥረት እንደገጠማቸው የመንግስታቱ ድርጅት አስገነዘበ
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ 500,000 የሚሆኑ ተፈናቃዮች “ከፍተኛ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የውሃ፣ የንፅህና፣ የጤና እና የጥበቃ አገልግሎቶች እጥረት” እንደገጠማቸው አስታወቀ።
ወደ 90 በመቶ የሚሆኑት አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በአካባቢው ማህበረሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ለአጭር ጊዜ በተዘጋጁ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩ ናቸው ብሏል። ከእነዚህም መካከል 22,000 ተፈናቃዮች ደብረ ብርሃን እና 10,000 የሚጠጉ ተፈናቃዮች ጃራ መጠለያ ይገኛሉ።
ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ከምዕራብ ኦሮሚያ ብቻ ከ88,000 በላይ የሚሆኑ ንፁሃን ዜጎች በግዳጅ ተፈናቅለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። ከእነዚህ ግለሰቦች መካከል ብዙዎቹ አሁን በደብረ ብርሃን (ቻይና ካምፕ)፣ ወይንሸት እና ባቄሎ በሚገኙ ሶስት መጠለያዎች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች እጅግ የሚጎሉባቸው መጠለያዎች ናቸው ብሏል።
ተጨማሪ ይመልከቱ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8498

በአማራ ክልል የሚገኙ ግማሽ ሚሊዮን ተፈናቃዮች ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እጥረት እንደገጠማቸው የመንግስታቱ ድርጅት አስገነዘበ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/ 2017 ዓ/ም፦ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ባወጣው አዲስ ሪፖርት፣ በአማራ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ የሚገኙ 500,000 የሚሆኑ ተፈናቃዮች “ከፍተኛ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የውሃ፣ የንፅህና፣ የጤና እና የጥበቃ አገልግሎቶች እጥረት” እንደገጠማቸው አስታወቀ። ወደ 90 በመቶ የሚሆኑት አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በአካባቢው ማህበረሰቦች ውስጥ የሚኖሩ…