ዜና: በ #ኬንያ በታሪካዊው የ"ሳባ ሳባ" ዕለት በተካሄደ የጸረ- መንግስት ተቃውሞ ቢያንስ 10 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ
የኬንያ ፖሊስ ሰኞ ዕለት በታሪካዊው የ "ሳባ ሳባ" ቀን የተካሄደውን የፀረ-መንግስት ተቃውሞ ተከትሎ ከሰልፈኞች ጋር በተፈጠረ ግጭት በትንሹ 10 ሰዎች መሞታቸውን መንግሥት የሚቆጣጠረው የኬንያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።
ተቃዋሚዎቹ በፖሊሶች ላይ እሳት በመለኮስ እና ድንጋይ በመወርወር ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን፤ ፖሊስ በአጸፋው በተቃዋሚዎቹ ላይ የተኩስ እና አስለቃሽ ጭስ እሩምታ መክፈቱ ተነግሯል።
ተቃውሞውን ተከትሎ ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መታሰራቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት (NPS) አስታውቋል።
የአገልግሎቱ ቃል አቀባይ የሆኑት ሚካኤል ሙቺሪ በሰልፎቹ ወቅት "አንዳንድ ግለሰቦች ዘረፋ እና የፖሊስ መኮንኖች ላይ ጥቃት መሰንዘርን ጨምሮ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች እና ሥርዐት አልበኝነት ላይ ተሳትፈዋል" ሲሉ ገልጸው፣ በአጠቃላይ 567 ሰዎች መታሰራቸውን ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ እያንዳንዱ ሪፖርት የተደረገ ክስተት ላይ "ተጨማሪ ምርመራ" እንደሚደረግበት ገልጸዋል።
ጸረ-መንግስት ተቃውሞዎቹ ከ47ቱ አውራጃዎች በ17ቱ ውስጥ ሪፖርት መደረጉን የዘገበው ፍራንስ 24 ነው።
https://www.facebook.com/100076048904470/posts/747225941155696/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

ዜና፡ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ
የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረጉት የስራ ማቆም ጋር በተያያዘ በባህር ዳር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ።
ዶ/ር ዳንኤል በአሁኑ ሰዓት በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው ሰባታሚት ማረሚያ ታስሮ እንደሚገኝ ጠቅሶ፤ "የተሻለ የሥራ ሁኔታና ክፍያ እንዲኖር በሰላማዊ መንገድ ጥሪ በማቅረባቸው ብቻ መታሰር የለባቸውም፤ ፖሊስ በአስቸኳይ ሊለቃቸው ይገባል" ሲል አሳስቧል።
"የኢትዮጵያ መንግስት እንደ ዶ/ር ዳንኤል ከመሳሰሉ ቅሬታዎቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ከሚያቀርቡ የህክምና ባለሙያዎች ጋር መነጋገር አለበት" ያለው ሂውማን ራይትስ ዎች፤ "አሁን ያለው አካሄድ ግን ኢትዮጵያን ለመናገር እና ሀሳብን ለመግለጽ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ከሆኑ ቦታዎች መካከል አንዷ መሆኗን ያረጋግጣል" ብሏል።
ተጨማሪ ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8369

Addis standard
የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ንቁ ተሳታፊ ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠየቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሓምሌ 1/ 2017 ዓ/ም፦ የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ካደረጉት የስራ ማቆም ጋር በተያያዘ በባህር ዳር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙት ዶ/ር ዳንኤል ፈንታነህ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ የመብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠይቋል። ዶ/ር ዳንኤል በቅርቡ የተሻለ የሥራ ሁኔታን፣ በቂ ደሞዝን እና ለሀኪሞች ደህንነት ጥበቃ እና ከለላ እንዲሰጥ በመጠየቅ በመላው…
ዜና፡ #ግብጽ በድጋሚ የቀይ ባህር ደህንነት ላይ ትኩረት አደርጋለች፣ ከሶማሊያ ጋር ጠንካራ ወታደራዊ ግንኙነት ለመመስረት ቃል ገብታለች
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ አሁንም በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስተላልፈዋል፤ የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ግብጽ #ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ቃል ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልዕክት በድጋሚ ያስተላለፉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን በግብፅ የባህር ጠረፍ ከተማ ኤል አላሜይን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፤ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል ተብሏል።
ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በግብጽ በኩል የወጣው መግለጫ አንደሚያትተው መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል፣ በተለይም በሶማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ በዝርዝር ተነጋግረዋል ብሏል።
ፕሬዝዳንት አልሲሲ በተደጋጋሚ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ አስተያየት ሰጡ ወይንም ተወያዩ የሚሉ አገላለጾች መሰማት የጀመሩት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2024 መጀመሪያ ላይ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ነው።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ምንም አይነት ድምጽ እየተሰማ ባይሆንም ኢትዮጵያውያ በቀጥታ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት አሁንም ከግብፅም ሆነ ከሶማሊያ በኩል በጥርጣሬ እና በስጋት የሚታይ ነው።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8379

ግብጽ በድጋሚ የቀይ ባህር ደህንነት ላይ ትኩረት አደርጋለች፣ ከሶማሊያ ጋር ጠንካራ ወታደራዊ ግንኙነት ለመመስረት ቃል ገብታለች - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1/ 2017 ዓ/ም፦ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ አሁንም በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስተላልፈዋል፤ የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ግብጽ ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ቃል ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልዕክት በድጋሚ ያስተላለፉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን…
ዜና: የ #ኢትዮጵያ እና #ናይጄሪያ የአየር ኃይሎች የሰው አልባ አውሮፕላኖችን በጋራ ለማልማት ተነጋገሩ
የኢትዮጵያ እና የናይጄሪያ አየር ኃይሎች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በጋራ ለማልማት እና የመከላከያ ትብብራቸውን ለማጠናከር እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ።
የናይጄሪያ አየር ኃይል (NAF) ልዑካን ቡድን ከማክሰኞ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት የቆየ ጉብኝት አድርጓል።
ጉብኝቱ በናይጄሪያ አየር ኃይል የሥልጠና ዳይሬክተር ኤር ኮሞዶር አሊ ሁሴኒ ኢድሪስ የተመራ ሲሆን፣ በአየር ላይ ቴክኖሎጂ፣ በጋራ ሥልጠና እና በአፍሪካ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በጋራ ማምረት ላይ ትኩረት ማድረጉን የናይጄሪያ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
ይህም በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር ለማሳደግ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና መሥሪያ ቤትን፣ የአቪዬሽን ዲፖ ጥገና ማዕከል፣ የደጀን አቪዬሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እና የአየር ኃይል አካዳሚን ጨምሮ ቁልፍ ወታደራዊ ተቋማትን መጎብኘታቸው ተጠቁሟል።
እንዲሁም በበረራ ጥገና በተለይም ለኤል-39 ጄቶች እና ማይ ሲሪየስ ሄሊኮፕተሮች የቴክኒክ ትብብርን ስለማስፋት እንዲሁም የጋራ የአብራሪዎች ቴክኒሻን ስልጠና፣ የዶክትሪን ልውውጥ እና የኤሮ-ስፔስ ምርምር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት መደረጉ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የናይጄሪያ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አዛዦችን በናይጄሪያ የአየር ውጊያና ስልጠና ማዕከል እንዲሁም በአየር ሀይል ጦር ኮሌጅ የላቀ ስልጠና እንዲወስዱ ጋብዘዋል።

በ #ኦሮሚያ ክልል በውጪ ዜጎች አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ መሆኑን ባለስልጣኑ ገለፀ
በኦሮሚያ ክልል የውጪ ዜጎች በ #ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘንን በ15 ሺህ ዶላር እያደኑ መሆኑን ክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።
የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦና ያዴሳ፤ “የውጪ ዜጎች አንድ አጋዘን ለማደን 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፍላሉ፤ ያደኑትንም አጋዘን ከአንገት በላይ ያለው አካል ይዘው መሄድ ይችላሉ” ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ፤ የደጋ አጋዘን በ #አርሲ እና #ባሌ ተራራማ ስፍራዎች እንዲሁም በ #ምዕራብ_ሀረርጌ በስፋት የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው የውጪ ሀገር ዜጎችም ለስፖርታዊ አደን የሚመርጡት ብርቅዬ እንስሳ መሆኑን ተናግረዋል።
አሁን ላይ በአዳባ እና ዶዶላ አካባቢዎች ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ለውጪ ዜጎች የደጋ አጋዘንን ለአደንነት እንዲያቀርቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አደኑን የሚያደርጉት የውጪ ዜጎች ፈቃድ የሚሰጣቸው ሲሆን፤ በአካባቢው ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ያረጀ ወንድ የደጋ አጋዘን ተመርጦ እንዲያድኑ ይደረጋል ሲሉ ለኢፕድ ተናግረዋል። ማንኛውንም የደጋ አጋዘን ማደን ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ከአደኑ የሚገኘው ገቢ 70 በመቶ ለኢንተርፕራዞች የሚገባ መሆኑና 30 በመቶውን መንግስት እንደሚወሰድም አቶ ቦና ተናግረዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘን ለውጪ ሀገር ዜጎች ለሕጋዊ አደን በማቅረብ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ዜና:በመዲናዋ ደንብ የተላለፉ ከ68 ሺህ በላይ እግረኞች መቀጣታቸው ተገለጸ
በአዲስ አበባ ከተማ ከ68 ሺህ በላይ ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸውን የከተማዋ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበበው ሚዴቅሳ በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ላይ በተደረገ ቁጥጥር 68 ሺህ 640 ደንብ ተላላፊ እግረኞች መቀጣታቸውን ተናግረዋል።
ከነዚህም መካከል 30 ሺህ 616 የሚሆኑት በገንዘብ እንዲሁም 37 ሺህ 790 እግረኞች ደግሞ የአገልግሎት ስራ እንዲሰሩ መደረጋቸውን ጠቁመዋል።
ቅጣቱ የተላለፈው ዜብራ ጠብቀው የማይሻገሩ፣ አደባባይ የሚያቋርጡ፣ እንዲሁም የትራፊክ መብራት በማያከብሩ እግረኞች ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
አክለውም ከ80 በመቶ በላይ የትራፊክ አደጋ ተጎጂ እግረኞች መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህንን ለመከላከል የእግረኛ መንገድ ማሻሻል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም እግረኞች የትራፊክ ደህንነት ህጎችን በማክበር በተሽከርካሪ ከሚደርስ አደጋ ብሎም ሞት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ማሳሰባቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/jgdsjm

ዜና፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመኑ 49 አዋጆችን ማጽደቁን አስታወቀ
#የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመኑ ከቀረቡለት 56 አዋጆች ውስጥ 49 አዋጆችን ማጽደቁ ተገለጸ።
ምክር ቤቱ የስራ ዘመኑን አፈጻጸም አስመልክቶ ባቀረበው የዕቅድ ክንውን ሪፖርት እንዳስታወቀው ካጸደቃቸው 49 አዋጆች ውስጥ 34 አዋጆች ለቋሚ ኮሚቴዎች ተመርቶ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት ተደርጎ በሁለተኛ ንባብ ጸድቀዋል ብሏል።
15 አዋጆች ደግሞ የህዝብ ውይይት ሳይደረግባቸው ወደ ሁለተኛ ንባብ ተሸጋግረው መፅደቃቸውን አመላክቷል።
ለምክር ቤቱ ከቀረቡት 56 የሚሆኑ አዋጆች ውስጥ ሰባቱ አለመጽደቃቸውን የጠቆመው ምክር ቤቱ በተጨማሪም ከ2016 የተሸጋገሩ 2 አዋጆችም በተጠናቀቀው የምክር ቤቱ የስራ ዘመን በ2017 ዓ.ም አለመጽደቃቸውን አስታውቋል፤ አዋጆቹ ምን መሆናቸውን አልጠቀሰም።
በአጠቃላይ 9 አዋጆች ወደ 2018 በጀት ዓመት መሻገራቸውን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ባቀረቡት የምክር ቤቱን የ2017 በጀት ዓመት የተጠቃለለ የዕቅድ ክንውን ሪፖርት ተመላክቷል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በስራ ዘመኑ የአስፈጻሚ ተቋማት ሚኒስትሮች በምክር ቤቱ በአካል በመገኘት የስድስት፣ የዘጠኝ እና 11 ወራት የዕቅድ ክንውን ሪፖርት እንዲያቀርቡና ከአባላትና ከሕዝቡ በተነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ምላሽና ማብራሪያ እንዲሰጡ መደረጉንም አስታውቋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም የስራ ዘመኑ 43 መደበኛ ስብሰባዎችና 3 ልዩ ስብሰባዎች ማካሄዱን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዜና፡ 90ኛ አመቱን ያስቆጠረው #የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከመንግስት ሆነ ከታጣቂዎች በኩል የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ትብብር እያገኘ መሆኑን አስታወቀ
90ኛ አመቱን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ባለፉት ስምንት ወራት ከመንግስት በኩልም ሆነ በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በኩል የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ትብብር እያገኘ መሆኑን አስታወቀ።
የማህበሩ የሰብአዊ ዲፕሎማሲ እና የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ መስፍን ደረጀ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት “ባለፉት ስምንት ወራት በመላ አገሪቱ ተደራሽ መሆን ችለናል” ሲሉ ገልጸው “የተደራሽነት ችግር የለብንም የትም የሀገሪቱ ቦታ ተንቀሳቅሰን ሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ ችለናል” ብለዋል።
ባለፉት አመታት “15 የማህበሩ ሰራተኞች መገደላቸውን” ያወሱት አቶ መስፍን “የአንቡላንስ ሹፌሮች፣ በስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች ህይወታቸው ካለፉት መካከል ይገኙበታል፣ የቆሰሉም አሉ” ብለዋል።
“ባለፉት ስምንት ወራት በተሽከርካሪዎቻችን ላይ በተለይም በአንቡላንሶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት የለም”፤ “ሰራተኞቻችን፣ በጎ ፈቃደኞቻችን ላይም እንዲሁ የደረሰ ጉዳት የለም” ሲሉ ገልጸዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=8383

90ኛ አመቱን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከመንግስት ሆነ ከታጣቂዎች በኩል የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ትብብር እያገኘ መሆኑን አስታወቀ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2/ 2017 ዓ/ም፦ 90ኛ አመቱን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ባለፉት ስምንት ወራት ከመንግስት በኩልም ሆነ በሀገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በኩል የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስ ትብብር እያገኘ መሆኑን አስታወቀ። የማህበሩ የሰብአዊ ዲፕሎማሲ እና የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ መስፍን ደረጀ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት “ባለፉት ስምንት ወራት…
ጥልቅ ትንታኔ፡ በፈተናዎች አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የ #ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተፈናቃዮች እስከ ውስጣዊ ፖለቲካ ያሉ ተግዳሮቶች መፍታት ይችል ይሆን?
በትግራይ ክልል በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲቆም ያስቻለውን የ #ፕሪቶርያው የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የተመሰረተው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በአቶ ጌታቸው ረዳ ለሁለት አመታት ሲመራ ቆይቶ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተሾመዋል። ይህ የስልጣን ርክክብ በበርካቶች ዘንድ በክልሉ ዳግም ግጭት ሊቀሰቀስ የሚችልበትን ክስተት ያስቀረ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል። ይሁን እንጂ አዲሱ አመራርም ቢሆን ክልሉን ከፈተናዎችና ከግጭት ስጋት ነጻ ማውጣት የቻል አይመስልም።
ለዚህ አንዱ ማሳያ በቅርቡ በክልሉ ደቡብ ምስራቅ ዞን #ዋጀራት ወረዳ “በትግራይ የጸጥታ ሀይሎች እና በ #አፋር ክልል ሲሰለጥኑ የነበሩና ራሳቸውን “የትግራይ የሰላም ሃይሎች” በሚል የሚጠሩ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ነው።
እንደ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃነ አፅብሃ ገለጻ፤ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ተፈናቃዮችንም ሆነ የክልሉ ግዛቶች ለማስመለስ “በአቶ ጌታቸው ረዳ አካሄድ የሚጓዙ ከሆነ ብዙም ርቀት መጓዝ አይችሉም” ሲሉ ገልፀው፤ በተለይ “በሁለት ጎራ ሆኖ ስልጣኑን ለማደላደል የሚላፋው የህወሓት ቡድን” ብዙም ላያንቀሳቅሳቸው ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
የጊዜያው አስተዳደሩ "ትልቁ ፈተናውም፣ ፈተናዎቹንም ለማለፍ ጉልበት ሊሆነው የሚችለውም የፌደራል መንግስቱ ነው" ያሉት አንድ የታሪክ ተመራማሪ፤ የፌደራል መንግቱ ምን ያክል ጊዜ አስተዳደሩን ደግፈዋል የሚለው ወሳኝ ነው ብለዋል።
ሙሉ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8386

በፈተናዎች አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተፈናቃዮች እስከ ውስጣዊ ፖለቲካ ያሉ ተግዳሮቶች መፍታት ይችል ይሆን? - Addis standard
በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene አዲስ አበባ፣ ሓምሌ 2 / 2017 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል በተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲቆም ያስቻለውን የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነትን ተከትሎ የተመሰረተው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በአቶ ጌታቸው ረዳ ለሁለት አመታት ሲመራ ቆይቶ ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተሾመዋል። ይህ የስልጣን ርክክብ በበርካቶች ዘንድ በክልሉ ዳግም…
ዜና: #ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርጋትን የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸም ማስመዝገቧን ባለስልጣኑ አስታወቀ
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከላከችው የቡና ምርት 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 326 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዶ፤ ከእቅዱ በላይ በማሳካት 470 ሺህ ቶን ኤክስፖርት አድርጎ 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።
የተገኘው ገቢ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርጋት መሆኑን የጠቀሱት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፤ አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ሦስተኛዋ ቡና አምራችና ላኪ አገር የሚያደርጋት መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን አስታውሰው፤ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም በ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ያህል ብልጫ ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
ከቡናው ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የፖሊሲ ሪፎርም መደረጉን የገለጹት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፤ በዚህም አርሶ አደሮች ቡናን በቀጥታ ለውጭ የሚያቀርቡበት ሥርዓት መመቻቸቱን ጠቅሰዋል።
በተጨሪም የቡና አቅራቢዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና ዋጋ ላይ ያላቸው የመደራደር አቅም ከፍ እንዲል መደረጉም ከቡና የሚገኘው ገቢ እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አመልክተዋል።
በቅርቡ ኡጋንዳ ኢትዮጵያን በመብለጥ በአፍሪካ ቀዳሚ ቡና ላኪ ሀገር ሆኛለሁ ስትል ማሳወቋ ይታወሳል።
ኡጋንዳ ከባለፈው የፈረንጆቹ 2024 ሰኔ ወር እስከ 2025 ግንቦት ወር ድረስ ከሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ማግኘቷን የሀገሪቱን የግብርና፣ እንስሳት እና አሳ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዜና፡ #የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ “ብር” ከዛሬ ሐምሌ 3 ጀምሮ “ከሩብል” ጋር ይፋዊ የምንዛሪ ተመን በማውጣት በሀገሪቱ ጥቅም ላይ እንደሚውል አስታወቀ
#የኢትዮጵያ መገበያያ ገንዘብ ብር ከዛሬ ሐምሌ 3 ጀምሮ ከሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል ጋር ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ወጥቶለት በቀጥታ በምንዛሬ ደረጃ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገለጸ።
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብርን በውጭ ምንዛሪ ዝርዝሮቹ ውስጥ በይፋ ማካተቱን ተከትሎ ከዛሬ ከሐምሌ 10 ቀን 2025 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ ተቀብሎ እና ጥቅም ላይ እንዲውል እንደሚደረግ አስታውቋል።
ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት መገበያያ ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን በማስቀመጥ መጠቀም እንደሚጀምር።
ማዕከላዊ ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ሩብል ከሌሎቹ የ12 ሀገራት መገበያያ ገንዘብ ጋር ያለውን ዕለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ ያደርጋል።
የባንግላዴሽ ታካ፣ የባህሬን ዲናር፣ የቦሊቪያ ቦሊቪያኖ፣ የኩባ ፔሶ፣ የአልጄሪያ ዲናር እና የኢራን ሪያል የመገበያያ ገንዘቦችን ከሩሲያው ሩብል ጋር ያላቸው ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ውሳኔ በባንኩ በኩል ይፋ ይደረጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ብር ከሩሲያ ሩብል ጋር በቀጥታ ለመገበያየት መበቃቱ የሀገራቱነ የተጠናከረ ግንኙነት ያመላክታል ተብሏል።
በዶላር የውጭ ምንዛሬ ክምችት እጥረት ለሚፈተነው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አማራጭ ተደርጎ መቅረቡ ተጠቁሟል።

ዜና፡ በ #መተከል ዞን ዳግም በተቀሰቀሰ የጸጥታ ችግር አንድ ሰው ሲገደል ከሰባት በላይ ቤቶች በታጣቂዎች ተቃጠሉ
በ #ቤኒሻንጉል_ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከሚገኙ ሰባት ወረዳዎች መካከል አምስቱ ውስጥ ዳግም በተቀሰቀሰ የጸጥታ ችግር አንድ ሰው መገደሉ እና ከሰባት በላይ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችና በክልሉ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አመራር ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ ድባጤ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ ነዋሪ በአከባቢው ከግንቦት ወር ጀምሮ ጥቃቶች ሲፈጸም እንደነበረ ገልጸው፤ አብዛኛውን ጊዜ የወርቅ ነጋዴዎች እና ባለሀብቶች፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የጸጥታ አካላት የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን አስረድተዋል።
ነዋሪው፤ በድባጤ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም "የሸኔ ታጣቂዎች" ሲሉ የጠሯቸው የ #ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ፈጸሙት ባሉት ጥቃት አንድ ሰው መገደሉንና "አስገድዶ መድፈር እና ዝርፊያ" መፈጸሙንም አመልክተዋል።
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አመራር በበኩላቸው በክልሉ መተከል ዞን ውስጥ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ማለትም ወንበራ፣ ቡለን እና ድባጤ ውስጥ "የሸኔ ታጣቂዎች" በስፋት ይንቀሳቀሳሉ ብለዋል። ታጣቂዎቹ እሁድ ዕለት በድባቴ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ ገብተው፤ "ዝርፊያ እና አሰቃቂ የሆነ አስገድዶ መድፈር ጥቃት" መፈጸማቸውን ጠቁመዋል።
ተጨማሪ ለማንበብ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8415

በመተከል ዞን ዳግም በተቀሰቀሰ የጸጥታ ችግር አንድ ሰው ሲገደል ከሰባት በላይ ቤቶች በታጣቂዎች ተቃጠሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3/ 2017 ዓ/ም፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ከሚገኙ ሰባት ወረዳዎች መካከል አምስቱ ውስጥ ዳግም በተቀሰቀሰ የጸጥታ ችግር አንድ ሰው መገደሉ እና ከሰባት በላይ ቤቶች በታጣቂዎች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችና በክልሉ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አመራር ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ ድባጤ ወረዳ ዶንቦን ቀበሌ ነዋሪ በአከባቢው ከግንቦት…
ዜና፡ ዘጠኝ ወራትን የፈጀው ጥንታዊው የ #አልነጃሺ መስጂድ እና መቃብር እድሳት መጠናቀቁ ተገለጸ፣ ርክክብ ብቻ ነው የቀረው ተብሏል
በ #ቱርክ መንግስት ድጋፍ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ጥገና ሲደረግለት የነበረው በ #ትግራይ ክልል የሚገኘው ጥንታዊው የአልነጃሺ መስጂድ እና መቃብር ቦታ እድሳት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሀይላይ በየነ ለአዲስ ሰታንዳርድ እንዳስታወቁት፤ እድስታ ሲደረግላቸው የነበሩት የመስጂዱ እና መቃብሮቹ “ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ርክክብ ብቻ ነው የቀረው”።
በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ የነበረው ታሪካዊው የአልነጃሺ መስጊድ እና መቃብር ቦታ በቱርክ መንግስት ተቋም በሆነው ቲካ (የቱርክ ድጋፍ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ) ሙሉ ለሙሉ ጥገና እንደተደረገለት ተጠቁሟል።
በአፍሪካ የመጀመሪያው የሙስሊም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው በትግራይ ክልል ነጃሺ ከተማ የሚገኘውን የነጃሺ መቃብር እና መስጂድ ለመጀመሪያ ጊዜ እድሳት የተደረገለት በ2019 ሲሆን እድሳቱ ሳይገባደድ በክልሉ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ ደጋሚ ጉዳት አስተናግዶ ተጨማሪ እድሳት እንደተደረገለት ተጠቁሟል።
ሙሉ ዘገባ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=8422

ዘጠኝ ወራትን የፈጀው ጥንታዊው የአልነጃሺ መስጂድ እና መቃብር እድሳት መጠናቀቁ ተገለጸ፣ ርክክብ ብቻ ነው የቀረው ተብሏል - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3/ 2017 ዓ/ም፦ በቱርክ መንግስት ድጋፍ ላለፉት ዘጠኝ ወራት ጥገና ሲደረግለት የነበረው በትግራይ ክልል የሚገኘው ጥንታዊው የአልነጃሺ መስጂድ እና መቃብር ቦታ እድሳት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ የቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሀይላይ በየነ ለአዲስ ሰታንዳርድ እንዳስታወቁት እድስታ ሲደረግላቸው የነበሩት የመስጂዱ እና መቃብሮቹ “ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ…
ዜና፡ የ #ትግራይ ኦርቶዶክስ አባቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ንግግር እና በትግራይ ህዝብ ሁኔታ ላይ ያላቸው ግምገማ እንዳሳሰባቸው ገለጹ
የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ በፓርላማ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር በጦርነት በተጎዳው ክልሉ ውስጥ ያለውን የሰላም ሂደት ሊያዳክም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የሃይማኖት መሪዎቹ፤ “የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ሁኔታ ግምገማ ከሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ አይደለም” ሲሉ ገልጸው፣ እንዲህ ያለው አለመጣጣም ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ሊያባብሰው እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
የሃይማኖት መሪዎቹ ረቡዕ ባወጡት መግለጫ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቦታው ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እውነታዎች መረዳትን በተመለከተ በትግራይ ህዝብ ዘንድ ስጋት እየጨመረ መምጣቱንም ገልጸዋል።
ቤተክርስቲያኗ የሽማግሌዎች ልዑክ በቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲገናኝ እንደምትልክ አስታውቃለች። መግለጫው እንደገለጸው፤ የስብሰባው ዓላማ የትግራይን ሕዝብ ስጋት ለማሳየት እና ለሰላም ሂደቱ የበለጠ ምላሽ ሰጪ እና ውጤታማ አቀራረብን ለመደገፍ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ፡https://addisstandard.com/Amharic/?p=8428

የትግራይ ኦርቶዶክስ አባቶች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ር እና በትግራይ ህዝብ ሁኔታ ላይ ያላቸው ግምገማ እንዳሳሰባቸው ገለጹ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3/ 2017 ዓ/ም፦ የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በፓርላማ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ። የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር በጦርነት በተጎዳው ክልል ውስጥ ያለውን የሰላም ሂደት ሊያዳክም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የሃይማኖት መሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ግምገማ “ከህዝቡ የኑሮ ሁኔታ ጋር የሚገናኝ አይደለም”…
ዜና፡ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ በዘርና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የነበረ ቢሆንም ይህንን የሚያስቀር አሰራር ተዘርግቷል - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ባለፉት ዓመታት በነበረው አሰራር #የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ የሚወሰነው በገለልተኝነትና በበቂ መረጃ ሳይሆን በዘር፣ በትውወቅና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ነበር ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ይህን ለማስቀረት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የትምህርት ቤቶችን ሥርጭት የሚያሳይ የዲጂታል ካርታ አዘጋጅቷል ብለዋል፤ በአገሪቱ ተመጣጣኝና ፍትሃዊ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት እየተሰራ ነው ሲሉም አስታወቀዋል።
በሀገሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት ትምህርት ቤቶች ግልጽና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንዲገነቡ የሚያስችል ዲጅታል የትምህርት ቤቶች ስርጭት የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዳለበት አንስተው ለሁሉም ዜጎች ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማድረሰ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የትምህርት ቤቶች ስርጭት ካርታ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የትምህርት ቤቶችን ወቅታዊ ስርጭት፣ የመሰረተ ልማት፣ የህዝብ ብዛት እና ሌሎች መረጃዎችንም አካቶ የያዘ መሆኑን ተጠቁሟል።
በመሆኑም ለጋሾችም ሆኑ ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻዎች መረጃውን በመጠቀም ትምህርት ቤቶችን መገንባትና የድርሻቸውን ማበርከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
በዚህ የትምህርት ስርጭት ካርታ ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሰረት ሲሆን የት ይገነባሉ የሚለውን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

ዜና፡ የግብጽ እና #የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተገለጸ
#የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተገለጸ።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራ አቻቸው ኦስማን ሳሌህ በሀገራቱ መካከል በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በፖለቲካዊ ምክክር የተገኘውን ተጨባጭ እድገት ሲሉ የገለጹትን ለማሳደግ ተወያይተዋል ሲል አህራም ጋዜጣ በዘገባው አስታውቋል፤ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ብሏል።
ዘገባው በተጨማሪም ሁለቱ ሚኒስትሮች የሀገራቱን ትብብር እና ትስስረ ለማጠናከር የተወያዩት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ እና የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ያስቀመጡትን መመሪያ ተከትሎ ነው ሲል ጠቁሟል።
ሁለቱም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ባደረጉት ምክክራቸው የሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደረጉ በተለያዩ የቀጠናው ጉዳዮች መክረዋል ያለው ዘገባው በተለይም ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህረ ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቋል።
ሁለቱም ሚኒስትሮች የቀጠናውን ደህንነት እና መረጋጋት ለማሳደግ በጋራ፣ በቅንጅት የሚያካሂዱትን ትብብር መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።
የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ለመልማት የምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እንደምትደግፍ አስታውቀዋል ብሏል።
https://web.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0245VkureJjm6MCEuLe5gXML1j7vubhVwiTuFzqWMeddkED2TQu4hNK97WXb6nSEcUl