Yop Poem ️
7.77K subscribers
89 photos
6 videos
25 files
59 links
፨Yop Poem
አዳዲስ እና የቆዩ ግጥሞችና ወጎችን በቀላሉ ያገኙበታል። 🤲
እርስዎም የግጥም ተሰጥዖ ካልዎት መልቀቅ ይችላሉ።👐
Our main channale :- @Utophiainfo

ቻናላችንን #share ያድርጉ👍

for promo & cross 👉 @Yared642
Download Telegram
Forwarded from 😂ኑ ፍረሱ😂 (Pain Killer)
ሴጣን ግን ዋነኛው ስራው
.
.
.
.
.
የድሮ ሚስቶቻችንን ቆንጆ ማድረግ ነዋ🤔


@Nu_fresu
------_ፍቅር ያጣ ጎጆ_------

ቃላት ተሰባጥረው ወደ ሀረግ አመሩ
ሀረጋት ተወዳጅተው ለቃል ነፍስ ዘሩ
እኔ ደካማዋ ከእህት ተወንድሜ
                      መፋቀር ተስኖኝ
አለሁ አሁን ድረስ በኩርፊያ ታጅቤ
                      የደም ስካር ከቦኝ።

በቃሽ ባይ ያጣችው ይቺ ምስኪን እናት
የጥንት ታሪኳን ሀሰት ሰውሮባት
ልጆቿ በደም ተቃብተውባት
እነሱን ማስማማት ዛሬ ላይ አቅቷት
አስታራቂ ከውጭ ባዕዳን መጡላ።
በደም እየዘራች በደም እየበላች
ትኖራለች ዛሬም እንዲሁ እያነባች።

"የልዩነት ውበት ደምቆ የሚታየው
እኛ ስንዋደድ ፍቅር ሲኖረን ነው።"
ባይ ሀሳቢ ጠፍቶ ሁሉ አመካኝቶ
የአመራር ጥበብ የተካነ ጠፍቶ
ቤታችን ታፍኗል ጪስ አጫሹ በዝቶ።


        @Yoppoem
Waver don't post 👍👍👍
አናውቅም
            በመኩሪያ ሙራሼ

በገደል በሜዳው ዓይናችን ብንሰድ
ሕይወት እግሩ ይዞት 'ምናየው ይበዛል የሚወለጋገድ

"ቁርስ መብያ" ሲለን አፈር ብላ እያልነው
"ምሳ መብያ" ሲለን ሠርተህ ብላ እያልነው
"ራት መብያ" ሲለን ምን ገዶኝ እያልነው
ሠርቶ እንዲቀየር ሳንነግረው መንገድ
ተማርንበት መንገዳገድ
አድርገን ቀረጽነው በሰው ዘር ጨክኖ በእሳት የሚያነድ

ሰው ሰውን ሆኖ ለሰው የሚጠቅም
የእሱ መኖር ለእኛ 'ሚሆን አቅም
ያን ኑሮ ኖረነው አና'ቅም

አናውቅም....አናውቅም

@Yoppoem
ታመህ ነው
            ያልሽኝ ቀን
አጠይቂኝ አቦ
            የያዘኝ ሰቀቀን
ደና ነኝ እንዳልል
                አካሌ አግጦ
ቆስዬለሁ ይላል
            ወደ አንቺ አንጋጦ
ታምሜአለሁ እንዳልል
              ቅሰት ተፀናውቶኝ
ስቃይ የነወዘው
            እንባሽን ፈራሁኝ
ታድያ ምንኑን ላርዳሽ
          ምን ይውጣ ከአፌ
ቃል እኮ አጣሁኝ
          ለሰባራው ክንf

@Yoppoem
በኦንላይን አማራጭ ካሉበት ሆነው ይማሩ፤ ሁልጊዜም ምዝገባ ሁልጊዜም ትምህርት አለ!
ይህን መልእክት ሌሎችም ያጋሩ !
በማኅበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከተሉን
ፌስቡክ ፦ https://www.facebook.com/AmdehaymanotSundayschool/
ዩትዩብ ፦ https://youtube.com/channel/UC_USHmHSlXg_-g0wwsPcQCg
ቲክ ቶክ፦ https://vm.tiktok.com/ZML9jVNJW/
ቴሌግራም፡ https://t.me/Amde_Haymanot_Sunday_School
◦◦●◉ የግጥም ጥም

ግጠም ግጠም ሲለኝ ስገጥም ስገጥም፣
ይኸው ደርሻለኹ እስከ... የግጥም ጥም።
አልገጥምም አልኩና ብቀመጥ አርፌ፣
ይወጋጋኝ ጀመር ውስጤ እንደ መርፌ።
ደግሞ ልጻፍ ብዬ አቅጄ ብነሣ፣
የትኛውን ትቼ የትኛውን ላንሣ?
      ብዬ ስወላውል
ሳድር... ደግሞም ስውል

ግጥም ማ'ነሽ አንቺ ብዬ ብጠይቃት፣
       ዝም አለችኝ...
ለካ ይህቺም ግ ጥ ም ናት
በዝምታም መልስ ያላት

ቢጽፉሽ ቢጽፉሽ አታልቂም እያልኳት።
ግጥምን እሷን ነው የጻፍኳት
ንገሯት ... ገጠምኳት

ለ ግ ጥ ም ግጥም ገጠምኩላት!

@Yoppoem
!!!!

ፈገግ ብየ አልፌው ተታለለ ስንቱ
አሁን ግን ደከመኝ
ለጠየቀኝ ሁሉ ደህና ነኝ ማለቱ
አጣጥፎ ጥሎኛል ችሎ ባይሰብረኝም
ከመሞት በልጦብኝ መኖር አይስበኝም
እኔም ህልሜን አልተው እሱም አይደረስ
                        ...ምናምን አትበለኝ
አይጥለኝም እንጂ እኔም ህመም አለኝ

ይልቅ እሱን ተወው..
አባብሎ ያቀፈህ ምቾትህን እርሳው
ብሶትህን ጣልና ብርታትህን አንሳው
ዳህ ተራመድ ሩጥ ህልምህን ብለጠው
ነገህ ላይ ለመቆም ትናንትን እርገጠው
በትልቁ አልመህ ትልቅ ነገር ሥራ
ከመውደቅህ በላይ ተስፋ መቁረጥ ፍራ

ግድየለም ሞክረው እንደው ባይመስልህም
መሮጥ እንደመቆም ቶሎ አያዝልህም🥵
ያስጎመዠ ሁሉ አይበላም ጣፍጦ
አንተ ህልምህን እመን
ማረፍ አያሾምም ከድካምህ በልጦ

ውደቅ ጣር ተነሳ ተጋጋጥ ይድከምህ
እንቅልፍህን እጣው ለነገ ላይጠቅምህ
ሚያባብልን ሙቀት
ሚሸፋፍን ምቾት ወደዛ ጣልና
ለራስህ አሳምን
አልችልም አትበለው ሞክር እንደገና
በብዙ ስትቆፍር ባንዱ ታገኛለህ
    ድል የሚሰጥህን የህይወትን መፍቻ
ካንተ ሚጠበቀው
     የላዩን ጌታ አምኖ መጣር መጋር ብቻ!


         @Yoppoem
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
Forwarded from .
Forwarded from .
Audio
Yop Poem ️ pinned an audio file
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ 18 አመቷ ወጣት እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 2
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ 18 አመቷ እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 3...
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
ክፍል 4
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰
የ18 አመቷ ወጣት እዉነተኛ አሳዛኝ ታሪክ ክፍል 5
የዜግነት ክብር
     ተምሬ ያደግሁት...
የዜግነት ክብር በማለት ዘምሬ
   class የምገባ...
ስለ ሰንደቅ ክብር ብዙ ተመክሬ
ከክላስ ውስጥ ደግሞ...
የቀለሙን ትርጉም በ civics ተምሬ
   እንዲህ ነው ያደግሁት...
  ሶስቱንም ቀለም...
በወርድ እና እርዝመት በእኩል ቀምሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
.ልዩነታችንን እንደ ጌጥ ቆጥሬ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
የክልልን ትርጉም
ብዙውን ሳላውቀው ብዙ ሳልረዳ
አስራ አንዱን ክልል
ሁሉንም አይቼ እንደ እናቴ ጓዳ
ሁሉን ቋንቋ ልወርስ
ሀሳቤን ስሸክፍ ምኞቴን ስነዳ
እንዲህ ነው ያደግሁት...
በሶስቱ ቀለም በአንድ ሰንደቅ ታጥሬ አረንጓዴ...ቢጫ...ቀይ
በልቤ ዙፋን ላይ በእኩል ቀምሬ
       ታድያ ምነው ዛሬ
አረንጓዴ ቢጫው ቀለሙ እየጠፋ
  ቀዩ ቀለም ብቻ ከሰንደቁ ሠፋ
የዜግነት ክብር...

                     
@Yoppoem
Forwarded from ❤Ⓢⓔⓛⓘⓝⓐ🥰