የገጣሚያን ማኅበር
18.6K subscribers
211 photos
11 videos
10 files
372 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
Download Telegram
  ጥያቄ ሰባት

ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንኖራለን።

ሀ/እውነት

ለ/ ሀሰት
   መልስ  



ለ/ ሀሰት
ሮሜ 5:10
ጥያቄ ስምንት
   ጥያቄ ስምንት 

ፋሲካ ለምንድነው የሚከበረው?

ሀ/ ክርስቶስ ከሞት መነሳቱን አስመልክቶ

ለ/ የእስራኤላውያን ነፃ መውጣትን አስመልክቶ

ሐ/ የአይሁድ ስርዓት ስለሆነ

መ/ ሁሉም
   መልስ  


ለ/የእስራኤላውያን ነፃ መውጣትን አስመልክቶ
ጥያቄ ዘጠኝ
ጥያቄ ዘጠኝ 

⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረው

ይሄንን ቃል ምን ማለት እንደፈለገ አስረዱ?
አብዛኞቹ መልሳችሁታል🙏
መልሱ ትህተታናው ነው🙏🙏🙏😍😍😍
የመጨረሻ ጥያቄ
ጥያቄ አስር 


“ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ፥ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።”

የሚለው ቃል ምን ክፍል ለይ ይገኛል?
   መልስ  



ዘጸ 12:11
አሸናፊውን ልናገር
አሁን ደግሞ አንድ ጊዜ በጌታ
ፍቅር ወደ ዩቲዩብ ቻኔላችን
ሄደን #Subscribe #Share
And #Comment አድርገን
እንመለሳለን።ተባረኩልኝ❤️
ሊንክ👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
Go Go Go............
አንደኛ የወጣው 🏆 @Tameeeeeee
ሁለተኛ የወጣው  🏆@Ababiti2
ሶስተኛ የወጣው 🏆 @BirukkD

Congra👏👏👏👏👏👏👏👏🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳 shlmatachun wsedu inbox🤗🤗🤗🤗🤗
ፕሮግራማችንን ጨርሰናል

ክብር በሰማይ ለእግዚአብሔር
በረከት በምድር ለሰው ልጆች
አስከ አለም ፍጻሜ ይሁን

አሜን 🙏🙏🙏🙏


ስትሳተፉ እና ስታገለግሉ
የቆያችሁ

ዘመናችሁ በተድላ
ዕድሚያችሁ በልምላሜ
በጌታ ቤት ይልቅ

ጌታ ረጅም ዕድሜና
ፍጹም ጠና ይስጣችሁ

ተባረኩ ዘራቹ የጠላትን
ደጅ ይውረስ
ወደ ኢየሱስ አደባሁኝ ቀድሞ ሞቶ ነበር
ጭንቀት ቢጤ ጀማመረኝ
የዚህ ሰውስ ነገር ልቤን ነው የሰለለኝ
ብዙዎችን እዚህ ቦታ አድምቺያለሁ
ጠፍተውኛል አቁስያለሁ
አሁን ግን እንጃልኝ ወደ ጥማት ገባሁ
የሞት ፍራት ፈራሁ
ጀግና ሰው አይደለሁ መውጊያዬን አነሳሁ
በድፍረቴ ፍራሀቴን እየቀማሁ
ተንደርድሬ ጎኑን ወጋሁ
ከቆዳው ስር ደም ተተፋ ሚነዝር ውብ መአዛ
በተሰቀለበት ሰውነቴን ነካ
በጦር ጎኑን ወጋሁ አየሁ አስደናቂ
ብርሀን ፈንጣቂ
ፊቴ ላይ አረፈ የደም ፍንጣሪ
ሰቅዬ አላውቅም ሞቶ ተናጋሪ
እርጥበት ወረረኝ የመሲሕ ደም ነካኝ
ገድየው ገደለኝ
ግፈኛ ጉልበቴ ቀድሞ ነው የነካኝ
ለካ ጀግና ሰው ነው ሰቃይን አፍቃሪ
ሞቶ አሸነፈኝ ትሁቱ ተዋጊ
እኔ ማቀው ታሪክ ወይ መሞት ወይ መግደል
ዛሬ ተቀየረ ገድሎ በመገደል
   እኔ እኮ ነኝ
            ✍️ጵንኤል አበራ
....ሕይወት ኢየሱስ ነው
ከጥንት የሰማነው በነብያት ተፅፎ
ቃል የነበረው ወልድ በማሪያም አርፎ
በይሁዳ ቤቴልሄም በዳዊት ከተማ
መስፍን መወለዱን ሄሮድስ ሲሰማ

መኳንንት አዋቂዎች ሁሉንም ጠራና
ኮከብ ቆጣሪዎችንም ደግሞ አስመጣና
ጠየቀ በፅኑ የታሪክ ሊቃውንትን
ማመን ስላቃተው ሰብዓሰገሎችን

እኔን የገረመኝ የታሪክ አዋቂዎች
ከዋክብትን ቆጥረው ጊዜ ጠቋሚዎች😧
ለንጉሳቸው ጊዜ ቀን ቦታ ነግረው
ምነው ሳይደንቃቸው ተኙ ተመልሰው

ሰብአሰገል መተው ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
በነብዩ አፍ ያለውን እግዚአብሔር
በኮከብ ተመርተው ቤተልሄም ሲደርሱ
የቤቴልሆም አዋቂዎች ሚስጥሩን ረሱ

እውነት ነው አያውቁም ኢየሱስ ሚስጥር ነው
የዘላለም ህይወት መድሀኒት በእርሱ ነው
አይመስልም ነገሩ የመጣበት መንገድ
ፍቀሩ ወረት የለው ሁሉን በአንድ ሚወድ
ይህ እውነት ገብቶኛል እመሰክራለሁ
በስሙ ላመኑት ህይወት ኢየሱስ ነው
ብዙዎች ተከተሉት እንጀራ ፍለጋ
ለስጋቸው ረሀብ ሊሞሉ ማድጋ

ሸክፈው ከመና የሄዱት ስንቃቸው
ከሰፈር ሲደርሱ አለቀ ከእጃቸው
ከሰማይ የመጣህ የህይወት እንጀራ
እየፈካህ ምትሄድ የንጋት ጮራ
የማትደርቅ ምንጭ ነህ ባለ ብዙ ዝና
ነብሴን ላረስርሳት ከአንተ ልጠጣና

ስጋህም መብል ነው ደምህ የህይወት ዉሃ
የዋርካ ጥላ ነህ በሀሩር በረሃ
እጅህን ሳይሆን ፊትህን ሁልጊዜ እሻለሁ
ማራናታ ኢየሱስ ላይህ ናፍቃለሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ተፃፈ በጌታሁን አናሞ
@GetahunAnamo

📥Group :  @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#ጣፋጩ #ቆምጣጤ _

  
እራሱን የካደ ደም ግባት የሌለው
    ለሰው ልጆች ብሎ ቀራንዮ የወጣው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ እየሱስ ብቻ ነው
  
    መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
    ቆምጣጤን ሊጠጣ እሱ በኔ ተራ
 
    ጉልበቱ ከዳው ፍፁም ዝም አለ
    እንደሚታረድ ጠቦት ለሰዎች ተታለለ

    ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መራራ የሆነው
   ብሩክ ሆኖ ሳለ እርጉም የተባለው
   ዝም ያለው ፍቅር አስገድዶት ነው

   የፍቅር ትርጉም ሊያሳየን ወዶ
   ክርስቶስ እየሱስ በራሱ ላይ ፈርዶ

   ከላይ ከሰማያት እየሱስ ሲመጣ
   የኔን እና ያንቺን ቆምጣጤ ሊጠጣ

    ቁልቁል ወረደ ጣፋጩ ፅዋ
    ስለኔ ስላንተ ክርስቶስ ሊሰዋ

    ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደ ትንሽ ነጠብጣብ
    ክርስቶስ ተፃፈ በልቤ መዳብ

    እርቃኑን ሲያቃስት ህመሙን ሲተውን
    የተፃፈል ይሄ ነው ታሪካችን

    በአብ ታቅዶ በወልድ የተፈፀመው
    እርሱ በኛ ፋንታ መራራ የሆነው

    በመስቀል ላይ ሆኖ ተፈፀመ ያለው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ ክርስቶስ ብቻ ነው
                           ....................

                  ገጣሚ :- ታምራት ግርማ
                   𝖕𝖔𝖊𝖒 :- 𝖙𝖆𝖒𝖊𝖝 𝖌𝖎𝖗𝖒𝖆


React ❤️🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
👆👆👆👆👆👆👆
አዲስ ግጥም በዩቲዩብ ቻኔላችን
ተለቋል ገብታችሁ ተባርኩበት🥰