የገጣሚያን ማኅበር
19.2K subscribers
227 photos
11 videos
11 files
465 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
Download Telegram
#ጣፋጩ_ቆምጣጤ

እራሱን የካደ ደም ግባት የሌለው
ለሰው ልጆች ብሎ ቀራኒዮ የወጣው

እርሱ በኛ ፈንታ መራራ የሆነው
ቆምጣጤን የጠጣው ክርስቶስ ብቻ ነው

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
ቆምጣጤ ሊጠጣ እርሱ በኔ ተራ

ጉልበቱ ከዳው ፍፁም ዝም አለ
እንደ ሚሰዋ ጠቦት ለሰው ተታለለ

ቁሉቁል ወረደ ጣፋጩ ፅዋ
ስለኔ ስላንተ ክርስቶስ ሊሰዋ

ከላይ ከሰማያት እየሱስ ሲመጣ
የኔን እና ያንቺን ቆምጣጤ ሊጠጣ

ከዚያ ግሳንግስ ከዚያ ሁሉ ጣጣ
እየሱስ ሲያድነን አልገባም መረጣ

መስፈርት ሳያስቀምጥ እንዲሁ ነው የወደደን
በእንድያ ልጁኮነው አብ የመረጠን ።

ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መራራ የሆነው
ብሩክ ሆኖ ሳለ እርጉም የተባለው
የመርገም ጨርቃችን እርሱ ነው ያፀደቀው

የፍቅርን ትርጉም ሊያሳየን ወዶ
ክርሰቶስ እየሱስ በራሱ ላይ ፈርዶ

ተፈፀመ አለ በመስቀል ላይ ታርዶ

             ሳይለየን ያቆየን

           

     
                #ገጣሚ_:- #_ታምራት_ግርማ


@Ye_Getamian_mahiber
@Ye_Getamian_mahiber
@Ye_Getamian_mahiber
#ጣፋጩ #ቆምጣጤ _

  
እራሱን የካደ ደም ግባት የሌለው
    ለሰው ልጆች ብሎ ቀራንዮ የወጣው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ እየሱስ ብቻ ነው
  
    መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
    ቆምጣጤን ሊጠጣ እሱ በኔ ተራ
 
    ጉልበቱ ከዳው ፍፁም ዝም አለ
    እንደሚታረድ ጠቦት ለሰዎች ተታለለ

    ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መራራ የሆነው
   ብሩክ ሆኖ ሳለ እርጉም የተባለው
   ዝም ያለው ፍቅር አስገድዶት ነው

   የፍቅር ትርጉም ሊያሳየን ወዶ
   ክርስቶስ እየሱስ በራሱ ላይ ፈርዶ

   ከላይ ከሰማያት እየሱስ ሲመጣ
   የኔን እና ያንቺን ቆምጣጤ ሊጠጣ

    ቁልቁል ወረደ ጣፋጩ ፅዋ
    ስለኔ ስላንተ ክርስቶስ ሊሰዋ

    ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደ ትንሽ ነጠብጣብ
    ክርስቶስ ተፃፈ በልቤ መዳብ

    እርቃኑን ሲያቃስት ህመሙን ሲተውን
    የተፃፈል ይሄ ነው ታሪካችን

    በአብ ታቅዶ በወልድ የተፈፀመው
    እርሱ በኛ ፋንታ መራራ የሆነው

    በመስቀል ላይ ሆኖ ተፈፀመ ያለው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ ክርስቶስ ብቻ ነው
                           ....................

                  ገጣሚ :- ታምራት ግርማ
                   𝖕𝖔𝖊𝖒 :- 𝖙𝖆𝖒𝖊𝖝 𝖌𝖎𝖗𝖒𝖆


React ❤️🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394