የገጣሚያን ማኅበር
18.6K subscribers
211 photos
11 videos
10 files
372 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር ፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ፦ስለ ወንጌል ፦ስለቤተክርስቲያን👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/channel/UCu6J21bKGYAwu8GxXoywbmA
Download Telegram
#ጣፋጩ #ቆምጣጤ _

  
እራሱን የካደ ደም ግባት የሌለው
    ለሰው ልጆች ብሎ ቀራንዮ የወጣው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ እየሱስ ብቻ ነው
  
    መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
    ቆምጣጤን ሊጠጣ እሱ በኔ ተራ
 
    ጉልበቱ ከዳው ፍፁም ዝም አለ
    እንደሚታረድ ጠቦት ለሰዎች ተታለለ

    ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መራራ የሆነው
   ብሩክ ሆኖ ሳለ እርጉም የተባለው
   ዝም ያለው ፍቅር አስገድዶት ነው

   የፍቅር ትርጉም ሊያሳየን ወዶ
   ክርስቶስ እየሱስ በራሱ ላይ ፈርዶ

   ከላይ ከሰማያት እየሱስ ሲመጣ
   የኔን እና ያንቺን ቆምጣጤ ሊጠጣ

    ቁልቁል ወረደ ጣፋጩ ፅዋ
    ስለኔ ስላንተ ክርስቶስ ሊሰዋ

    ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደ ትንሽ ነጠብጣብ
    ክርስቶስ ተፃፈ በልቤ መዳብ

    እርቃኑን ሲያቃስት ህመሙን ሲተውን
    የተፃፈል ይሄ ነው ታሪካችን

    በአብ ታቅዶ በወልድ የተፈፀመው
    እርሱ በኛ ፋንታ መራራ የሆነው

    በመስቀል ላይ ሆኖ ተፈፀመ ያለው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ ክርስቶስ ብቻ ነው
                           ....................

                  ገጣሚ :- ታምራት ግርማ
                   𝖕𝖔𝖊𝖒 :- 𝖙𝖆𝖒𝖊𝖝 𝖌𝖎𝖗𝖒𝖆


React ❤️🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394