የገጣሚያን ማኅበር
17.2K subscribers
187 photos
9 videos
10 files
278 links
እዚህ ማኅበር ውስጥ የሚካተቱ የስነ-ጽሁፍ ይዘቶች፦
👉መንፈሳዊ ግጥም
፦ስለ ሀገር
፦ስለ እግዚአብሔር ፍቅር
፦ስለ ወንጌል
፦ስለቤተክርስቲያን
👉መነባነብ
👉ግጥማዊ ትረካ
ይቀላቀሉን
Channel👉 @Ye_Getamian_Mahiber
Group👉 @yegetamianmahiber
YouTube https://www.youtube.com/@Poetscoun
Download Telegram
   መልስ  



ዘጸ 12:11
አሸናፊውን ልናገር
አሁን ደግሞ አንድ ጊዜ በጌታ
ፍቅር ወደ ዩቲዩብ ቻኔላችን
ሄደን #Subscribe #Share
And #Comment አድርገን
እንመለሳለን።ተባረኩልኝ❤️
ሊንክ👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
Go Go Go............
አንደኛ የወጣው 🏆 @Tameeeeeee
ሁለተኛ የወጣው  🏆@Ababiti2
ሶስተኛ የወጣው 🏆 @BirukkD

Congra👏👏👏👏👏👏👏👏🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳 shlmatachun wsedu inbox🤗🤗🤗🤗🤗
ፕሮግራማችንን ጨርሰናል

ክብር በሰማይ ለእግዚአብሔር
በረከት በምድር ለሰው ልጆች
አስከ አለም ፍጻሜ ይሁን

አሜን 🙏🙏🙏🙏


ስትሳተፉ እና ስታገለግሉ
የቆያችሁ

ዘመናችሁ በተድላ
ዕድሚያችሁ በልምላሜ
በጌታ ቤት ይልቅ

ጌታ ረጅም ዕድሜና
ፍጹም ጠና ይስጣችሁ

ተባረኩ ዘራቹ የጠላትን
ደጅ ይውረስ
ወደ ኢየሱስ አደባሁኝ ቀድሞ ሞቶ ነበር
ጭንቀት ቢጤ ጀማመረኝ
የዚህ ሰውስ ነገር ልቤን ነው የሰለለኝ
ብዙዎችን እዚህ ቦታ አድምቺያለሁ
ጠፍተውኛል አቁስያለሁ
አሁን ግን እንጃልኝ ወደ ጥማት ገባሁ
የሞት ፍራት ፈራሁ
ጀግና ሰው አይደለሁ መውጊያዬን አነሳሁ
በድፍረቴ ፍራሀቴን እየቀማሁ
ተንደርድሬ ጎኑን ወጋሁ
ከቆዳው ስር ደም ተተፋ ሚነዝር ውብ መአዛ
በተሰቀለበት ሰውነቴን ነካ
በጦር ጎኑን ወጋሁ አየሁ አስደናቂ
ብርሀን ፈንጣቂ
ፊቴ ላይ አረፈ የደም ፍንጣሪ
ሰቅዬ አላውቅም ሞቶ ተናጋሪ
እርጥበት ወረረኝ የመሲሕ ደም ነካኝ
ገድየው ገደለኝ
ግፈኛ ጉልበቴ ቀድሞ ነው የነካኝ
ለካ ጀግና ሰው ነው ሰቃይን አፍቃሪ
ሞቶ አሸነፈኝ ትሁቱ ተዋጊ
እኔ ማቀው ታሪክ ወይ መሞት ወይ መግደል
ዛሬ ተቀየረ ገድሎ በመገደል
   እኔ እኮ ነኝ
            ✍️ጵንኤል አበራ
....ሕይወት ኢየሱስ ነው
ከጥንት የሰማነው በነብያት ተፅፎ
ቃል የነበረው ወልድ በማሪያም አርፎ
በይሁዳ ቤቴልሄም በዳዊት ከተማ
መስፍን መወለዱን ሄሮድስ ሲሰማ

መኳንንት አዋቂዎች ሁሉንም ጠራና
ኮከብ ቆጣሪዎችንም ደግሞ አስመጣና
ጠየቀ በፅኑ የታሪክ ሊቃውንትን
ማመን ስላቃተው ሰብዓሰገሎችን

እኔን የገረመኝ የታሪክ አዋቂዎች
ከዋክብትን ቆጥረው ጊዜ ጠቋሚዎች😧
ለንጉሳቸው ጊዜ ቀን ቦታ ነግረው
ምነው ሳይደንቃቸው ተኙ ተመልሰው

ሰብአሰገል መተው ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
በነብዩ አፍ ያለውን እግዚአብሔር
በኮከብ ተመርተው ቤተልሄም ሲደርሱ
የቤቴልሆም አዋቂዎች ሚስጥሩን ረሱ

እውነት ነው አያውቁም ኢየሱስ ሚስጥር ነው
የዘላለም ህይወት መድሀኒት በእርሱ ነው
አይመስልም ነገሩ የመጣበት መንገድ
ፍቀሩ ወረት የለው ሁሉን በአንድ ሚወድ
ይህ እውነት ገብቶኛል እመሰክራለሁ
በስሙ ላመኑት ህይወት ኢየሱስ ነው
ብዙዎች ተከተሉት እንጀራ ፍለጋ
ለስጋቸው ረሀብ ሊሞሉ ማድጋ

ሸክፈው ከመና የሄዱት ስንቃቸው
ከሰፈር ሲደርሱ አለቀ ከእጃቸው
ከሰማይ የመጣህ የህይወት እንጀራ
እየፈካህ ምትሄድ የንጋት ጮራ
የማትደርቅ ምንጭ ነህ ባለ ብዙ ዝና
ነብሴን ላረስርሳት ከአንተ ልጠጣና

ስጋህም መብል ነው ደምህ የህይወት ዉሃ
የዋርካ ጥላ ነህ በሀሩር በረሃ
እጅህን ሳይሆን ፊትህን ሁልጊዜ እሻለሁ
ማራናታ ኢየሱስ ላይህ ናፍቃለሁ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ተፃፈ በጌታሁን አናሞ
@GetahunAnamo

📥Group :  @yegetamianmahiber
📥Channel : @Ye_Getamian_Mahiber
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
      🔺🀄️🀄️ሉን🔺
           Join us
         🎯     ♡         ❍ㅤ    ⌲ 
ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ
#ጣፋጩ #ቆምጣጤ _

  
እራሱን የካደ ደም ግባት የሌለው
    ለሰው ልጆች ብሎ ቀራንዮ የወጣው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ እየሱስ ብቻ ነው
  
    መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ
    ቆምጣጤን ሊጠጣ እሱ በኔ ተራ
 
    ጉልበቱ ከዳው ፍፁም ዝም አለ
    እንደሚታረድ ጠቦት ለሰዎች ተታለለ

    ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መራራ የሆነው
   ብሩክ ሆኖ ሳለ እርጉም የተባለው
   ዝም ያለው ፍቅር አስገድዶት ነው

   የፍቅር ትርጉም ሊያሳየን ወዶ
   ክርስቶስ እየሱስ በራሱ ላይ ፈርዶ

   ከላይ ከሰማያት እየሱስ ሲመጣ
   የኔን እና ያንቺን ቆምጣጤ ሊጠጣ

    ቁልቁል ወረደ ጣፋጩ ፅዋ
    ስለኔ ስላንተ ክርስቶስ ሊሰዋ

    ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደ ትንሽ ነጠብጣብ
    ክርስቶስ ተፃፈ በልቤ መዳብ

    እርቃኑን ሲያቃስት ህመሙን ሲተውን
    የተፃፈል ይሄ ነው ታሪካችን

    በአብ ታቅዶ በወልድ የተፈፀመው
    እርሱ በኛ ፋንታ መራራ የሆነው

    በመስቀል ላይ ሆኖ ተፈፀመ ያለው
    ጣፋጩ ቆምጣጤ ክርስቶስ ብቻ ነው
                           ....................

                  ገጣሚ :- ታምራት ግርማ
                   𝖕𝖔𝖊𝖒 :- 𝖙𝖆𝖒𝖊𝖝 𝖌𝖎𝖗𝖒𝖆


React ❤️🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
👆👆👆👆👆👆👆
አዲስ ግጥም በዩቲዩብ ቻኔላችን
ተለቋል ገብታችሁ ተባርኩበት🥰
ዕምነቴ ወዴት ነው?

እየሱስ ሲናገር....
ከእዚያ ባህር ማዶ እንሂድ ተሻግረን
ባህሩን እንቅዘፍ በልጀባው ለይ ወተን
ደቀመዛሙርቱ...
እሺ እንሂድ አሉ በቶሎ ተስማምተው
ጉዞውን ጀመሩ ቦታ ቦታ ይዘው
እየሱስም ገብቶ ሸለብ እንዳረገው
አለም ተናወጠች አምላኳ ሲደክመው
ጌታ...ሆይ ጌታ...ሆይ ኧረ ልንጠፋ ነው
እባክህ ተነስተህ ማዕበሉን አስቁመው
ጌታም ተነሳና ንፋሱን ገሰፀው
ነፋስንና ማዕበልን ያዛል😱
እነርሱም ይታዘዙታል😃
ለመሆኑ ይህ ሰው ስሙ ማን ይባላል 🤔
ኢየሱስ ሲናገር.........
ዕምነታችሁ ወዴት ነው ?
አብረን ምንጓዘው በኔ ሳታምኑ ነው ?
ቃሌን የምትሰሙኝ እንዲሁ በከንቱ ነው ?
ስሜ እሳት አለው ይገድላል ያድናል
ስሜ መንሽ ይባላል
ስንዴና ገለባን መለየት ይችላል
መነገጃ መስሎት ገንዘብ መሰብሰቢያ
በኔ ውስጥ የሚኖር ለመሰለው ለዚያ
እውነተኛ መስሎ በከንቱ ለሚኖር
ይሄንን ሰው እኔ አላውቅህም ከምር
ብዬ ሳልናገር.......
ይነሳ ይታጠቅ ወገቡንም ይሰር
ደህንነትን ይድፋ ልክ እንደ እራስቁር
ፍላፃን ለማጥፋት ይመክት ጋሻ ጦር
ዕምነቱና ቃሌን በአንድ ለይ ይዞ
እኔ ያለሁበትን ይከተል ያን ጉዞ።

(እስከዛሬ ጥያቄ በመጠየቅ የምናውቃት Boss ገጥማለች)👍😊

እስቲ አንዴ ለBoss ❤️🥰


Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
ጴጥሮስና ይሁዳ ምን እያሉ ነው😁😁
ለካ የዛነም ሶሻል ሚድያ አለ 😂
በሀጢያት አለም ስኖር ገና ያኔ
በጨለማ ስጓዝ ብርሀን ጠፍቶ ከኔ
መድሀኒት በሌለው በሀጢያት በሽታ
ተይዤ ስማቅቅ እረፍቴንም ሳጣ
ነፍሴ በብዙ ጭንቅ በብዙ መከራ
በስቃይ ስትወጣ የህይወትን ተራራ
ቀን ከቀን ሲጨልም የመኖሬ ተስፋ
መንፈሴ ሙት ሆኖ ሰኖር ሳንቀላፋ
የስጋዬ ደስታ ነፍሴን አስጨንቋት
ሠላምና እረፍት ከቶ አሳጥቷ
ለስጋዬ ቢመች ያለሁበት አለም
ለነፍሴ ሰላምን ሊሠጣት አልቻለም
ህይወት ከንቱ ሆኖብኝ ዝም ብዬ ስኖር
ብርሀን በሌለበት ጨለማ ስዳክር
ገብቼ ስጠፋ ወደ ሀጢያት መንደር
ሚያወጣኝ አጣሁ ካለሁበት ሠፈር
ብዙዎች ሞከሩ ነገር ግን አልቻሉም
እኔን ከዚያ ማውጣት አቃተቸው ሁሉም
ይሄን ስመለከት በጣም ተስፋ ቆረጥኩ
እንደዚህ ከምኖር መሞቴንም መረጥኩ
እንደዚህ በሆነ ከባድ ህይወት ስኖር
አንድ አዳኝ መጣልኝ ከላይኛው አገር
ወደኔ ተጠጋ እኔ ጌን ሸሸሁት
ከሰው ሲለይብኝ እጅጉን ፈራሁት
እሱ ግን አሁንም ቀረበ ወደኔ
ልጄ በኔ እመኚ ትድኛለሽ ያኔ
ብሎ ሲናገረኝ እጅጉን ገረመኝ
ምን አይነት ሀይል ነው እኔን የሚያድነኝ
ብዞዎች እኮ አልቻሉም እኔ ከዚ ማውጣት
ለስጋዬ እንጂ ለነፍሴ ሰላም መቼ እነሱ ሰጧት
ብዬ ስናገር ተስፋ እንደሌለኝ
የምለውን ሁሉ ዝም ብሎ አደመጠኝ
ከዛ ግን ነገረኝ የህይወትን መንገድ
አሳየኝ ብርሀኑን በዛ እንድራመድ
ላንቺ ነው  ኮ ነው ልጄ የተወጋው ጎኔ
ላንቺ ኮ ነው ልጄ የታመምኩት እኔ
ህመምሽን ወስጄ የእኔ ላደርገው
የሀጢያትሽን እዳ በላዬ ላኖረው
እድፍሽ እንዲነፃ ደሜ  የፈሰሰው
ነፊ ስሽ እንድትድን ነፍሴ የተጨነቀው
ደዌሽን ልቀበል ሸክምሽ ልሸከም
የአንቺን ቀንበር ላደርግልሽ ለዚብ
ለዚ ነው የተላኩት ከላይ ከአባቴ ዘንድ
በእኔ እንድትሄዱ ወደ እውነት መንገድ
የሀጢያት ትብታብ በደሜ ሊበጠስ
እድሜና ዘመንሽ በእኔ ሊቀደስ
ከሀጢያት መንደር በደሜ ልስብሽ
ህይወትን ሰጥቼ የአብ ልጅ ላደርግሽ
ሙት የነበርሽውን በኔ ህይወት አጌኜተሽ
ደግመሽ ላትገቢ ከጨለማ ወተሽ
በብርሀን በተስፋ ኑሪ ተዘልለሽ
ስላንቺ ሚማልድ ጌታ በላይ አለሽ
ብሎ አበረታኝ በአንደበቱ ቃል
የሀጢያትን ቀንበር አረገልኝ ቀሊል
ሙቱ መንፈሴ ዛሬ ህያው ሆነ
ጨለማ አበቃ ቀንበር ተሠበረ
ከሀጢያት መንደር ደሙ ስቦ አወጣኝ
ጉልበታሙ ደሙ እኔን ህያው አረገኝ
ስለዚህ አንድ እውነት ዛሬ ልንገራቹ
ህይወት ጨልሞ  ግራ ለገባቹ
ማነው ሚያወጣኝ ብላቹ የፈራቹ
የልጁ የእየሱስ ደም ዛሬም አለላቹ
የሀጢያት እስራት በደሙ ሊበጠስ
ህይወታቹ ሁሉ በጌታ ሊቀድስ
ኑ ወደ ጌታ መድሀኒት አለው
እቅፉ አልሞላም ዛሬም ይጠራል ሰው
ስላናንተ የፈሰሰው ደም ዛሬም ይሠራል
ጌታ ለልጆቹ አሁንም ይራራል
እኔስ በእየሱስ እረፍት አግኝቻለው
በደሙ ታጥቤ ዛሬ ህያው ሆኛለው
ይኸው ባደባባይ እመሰክራለው
የጌታዬ ደሙ ያነፃል አምናለው
አንድ አዋጅ ላውጅ ነው ስሙኝ እባካቹ
መንፃት ምትፈልጉ በሀጢያት ያላቹ
የልጁ የእየሱስ ደም ከሀጢያት  ያነፃል
ህይወት ለፈለገ ዛሬም ደሙ ይሠራል
          ስም ፦ዲቦራ ዳንኤል
          ርዕስ፦ ደሙ

React❤️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
ቅዱሳን ሠላም እላችኋለሁ።

ትንሽ ቅር ብሎናል እዝህ ቻኔል ላይ
15k በላይ አባላት አሉ።በርካታ
ገጣሚያንም አሉ።እስከአሁን ድረስ
ከአንድ ሽህ በላይ ግጥሞችን ያክል
Share አድርገናል።ገጣሚያንን
በእውነት እግዚአብሔር ይባርካቸው።
ቅረታችን ብዙ ሰው ይከታተላል ግን
ካነበባችሁ ብኃላ ገጣሚያንን ብዙ
ሰው እያበረታታ አይደለም። Reaction
ስጡ በcomment መስጫ ላይ ባርኳቸው። ትንሽ ነገር ነው ግን ጸሐፊዎች ያበረታታል።አስተውሉ ብዙዎች ጸጋቸውን ያካፍላሉ።በጸጋቸው የተጽናናችሁ ትኖራላችሁ።መባረክ አያስከፍልም
ስቀጥል reaction ማድረግም ቀላል ነው ብዙ ካወራሁ ከልቤ ይቅርታ።

 የዩቲዩብ ቻኔላችንም Subscribe
                   ያድርጉ

  
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394


        የገጣሚያን ማህበር
መቆየት
ተወስጄ በሚታየው
"አገልግሎት" በተባለው
መርጋት ተስኖኝ
መቆም አድክሞኝ
ማድመጥ አልቆብኝ
መጠበቅ ጠፍቶኝ
ተራገብኩኝ..
በቻዬን አውርቼ
አንተንም ዘንግቼ
መማር አቁሜ
ተረጋግቼ
አደግሁ ተጣምሜ
ከእውነት ጠፍቼ
የሚያስፈልገውን ሳላስቀድም
አቅቶኝ ማለት "ዝም"
ባከንኩኝ ....
ጥቂቷን አጣሁ
ከእግርህ ስር ጠፋሁ
በልጦብኝ መታየት
አልቻልኩም መቆየት።

#በእምኒ
ጥቅምት 2013

React❤️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
በነፃ ሸምቱ

ገበያ አዘጋጀ  አብ ህይወት ለመሸጥ
በነፃ ሊነግድ በነፃ ሊለውጥ
አዋጅ አዋጅ ኑ ሸምቱ እያለ
ግዙ ውሰዱ ብሎ ጥሪ አከታተለ
ግን በዚ መኃል ገንዘብ ያለው የሚል
ጥሪ አልጨመረም አላወጣምም ቃል
መልሶ መላልሶ ገንዘብ የሌላችሁ
እናንት ኃጢአተኞች ጥም የገደላችሁ
ወደ ህይወት ምንጩ ወደ ውሃው ኑ ና
በነፃ ገዝታችሁ እርኩ ጠጡኝና
            እናም
ኃጢአተኛ ሁሉ ይህን ድምጽ ሰምቶ
በእምነት መጋፋት ለመርካት ጠጥቶ
       ደግሞ የሚገርመው
ምንጩ እየተቀዳ አያልቅ ተጠጥቶ
ሌላውን ይጠብቃል የጠጣን ሸኝቶ
የጠጣው ሰው ሁሉ  ድግሱን የሰማ
አንድ ጊዜ እረክቷል ዳግም ላይጠማ


ኢሳ 55፥1
ሞገስ ሳሙኤል

React❤️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
አብራችሁን በግጥማችሁ
ለማገልገል የምትፈልጉ
ልጆች መድረክ ክፍት ነው
በውስጥ መስመር ማናገር
ትችላላችሁ።
👉 @S_o_L_e_N_y
ጸጋችሁን አካፍሉ

ማስታውቂያ
ግጥም ስትልኩልን
1) ከድምፅ ጋር አንድ ላይ ብሆን
2) ራሳችሁ የጻፋችሁ ግጥም ብሆን (ሰው የጻፈውን  አትላኩ)
3) ከግጥሙ መጨረሻ የገጣሚ ሙሉ ስምና ግጥሙ የተጻፈበት ቀን ብቀመጥ

       እግዚአብሔር ይባርካችሁ
         ከገጣሚያን ማህበር
ዳይኖሰር የአገሬ ታሪክ📝
ለመጥፋት የተቃረበ.. ብርቅየም  ያይደለ ዛሬ፣
ለነበር ታሪክ የበቃ... የአገሬ የጥንቱ  ፍሬ፣
የባህል የእምነት ስርዓቷ..  ሁሉም   ትውፊት  ገንዘቧ፣
ጠፍቷል እንደ ዳይኖሰር.. ፍፁም ሞቷል  ከልቧ፣
ምሁራን ቢመራመሩ ሊሂቃናት ቢመሳጠሩ ፣
የጥንቱን የጠፋው መልኳን ከዛሬው ቢያነፃፅሩ፣
እንዴት አፅም ሊማርክ!  ተሽሎ ቀልብን ሊገዛ፣
እያደር ለኮሰምነ... ለሆነው   የታሪክ   ጤዛ፣
ግና ቢጠፋ  ታሪኳ... ለነበር እንኳን ቢቸግር፣
አፅሟ ግን ፍፁም   ህያው ነው  ይኖራል ሳይበላው አፈር፣
ዛሬ ግን መልኳ ሌላ ነው ..  ህብሯ  እንግዳ ነው..ገጿ ብዙ ነው ፣
ዳይኖሰር የአገሬን ታሪክ .. የጥንቱን  ስጋ እንዲነሳ  ማን ደፍሮ ጥበብ በቸረው!
be21✍️
ቀራኒዮ ጉዞ ላይ

ደና ነህ ስትባል ሰው እንዳያውቅብ
ብለ ትመልሳለ አው ደና እኮ ነኝ
ፊት ላይ ሲነበብ ሰላም እንዳልሆንክ
ለሰው እንዳይታይ የልብ ስብራትክ
በሳቅ ሸውደ ከላይ ለሚያይህን
ላየ ሰው ደና የሆንክ ቢመስልህ
በሁሉም ፈት እያስመሰልክህ
ብትናገር አውቀ እንደማይራዳክ
ችግር ለሰው ልጆች ማታካፍለው
ለማሸነፍ ብትሮጥ ታግለ ብቻህን
ህመም እንዳይታይ ብቻክን ብትሆን
በሰወች መሃል እኛን ልታቆም
ብዙ ተግለ ለኛ ባይገባንም
ከመታገል አልፈ አሸንፈ ቆም
ሰወች እንዳሉት ብቻውን የኖር
ህመሙ እንዳይታይ በሳቁ የሸፈነ
በፈገግታ እያዋዛ ለምን አታለልከን
ብዬ ልናገር እኔ የለኝም አቅም
ይቅርታ አርግልኝ ካንተ ፊት አልወጣም
ልጅነት ቀርቶ ባሪያክ እንኳን ብሆን
አተረፍኩ እንጂ መች እከስራለውኝ
ጌታ ኢየሱስ በጣም ወድሃለውኝ

          ማስረሻ

React❤️

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
ሠላም ቅዱሳን እንዴት አመሻችሁ
እስቲ አንዴ ሁላችሁም የዩቲዩብ
ቻኔላችንን ሰብስክራይብ
በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። አገልግሎቱንም ይደግፉ❤️🥰

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394
ሁሉም እኔን ይመስላሉ!


ለምሳሌ
ትላንት ጮኾ የጠራው ዓይነ ስውሩ
ጠርቶት ሲጨነቅ በግርግሩ
"ዝምበል" እያሉት ከእሱ የደረሰው
እኔን ይመስላል ያ ለማኝ ሰው
በእርግጥ...
ዓይን ነበረኝ እንደ ምልክት ያገለገለኝ
አምኜው ስጓዝ ገደል ሚጥለኝ
ያላስመለጠኝ ስንቴ ስሰበር
እንዲያይ ተፈጥሮ አያይም ነበር።
ደግሞም

የልብ ብርሃን ተስፋ ሚዝበት
ለጨለማዬ ፋና ሞጋበት
አልነበረኝም ብርሃን ለቤቴ
ዘይት አልባ ነው ሸክላ ማኅቶቴ
የለኝም ለእግሬ ጭላንጭል መብራት
መርቶ ሚያደርሰኝ ለንጉስ እራት
አልነበረኝም የመንገድ መብራት።


በርግጥ...
ዓይን ነበረኝ እንደ ምልክት ያገለገለኝ
አምኜው ስጓዝ ገደል ሚጥለኝ
አልጠቀሙኝም ማቃጭላቸው ሳንቲሞች እንኳን
መቼ አስገቡኝ ከህይወት ድንኳን
አልነበረኝም የተስፋ ፋኖስ
እየሱስ ብሎ የዳነው ለማኝ
እኔን ይመስላል በርጠለሚሆስ
   ለካስ...
ለእውር መነፅር ስውር ቃል አለች
ሰው እየሱስ ሲል ዓለም ታንሳለች
ፈጣሪያቸውን ፍጥረት ያውቁታል
አፍ እየሱስ ሲል ዓለም መስህቧ ይረቋቆታል።
ለካስ ሰው ያያል...

ሰው ያያል ለካ እየሱስ ብሎ
ማምለጥ ይቻላል እየሱስ ብሎ
ፍቅሩ የነካው ሰው ይከተለዋል
          መረቡን ጥሎ
መረብ ኑሮዬ ፤ መረብ ትዳሬ ፤መረብ ህይወቴ
የህይወት ተስፋዬ ፤ምድር ላይ መክበር፤ ነበር ስለቴ

መረበኛ ነኝ ዘውትር የምውል በአጢአት ማህበል
እድፌን ነክተ እንዳትቆሽሽ ፤ ከእኔ ራቅ በል

ያለው ጴጥሮስ ልቡን ሲያየው ልቡ ተስቦት
ቃል ደማ ካፉ ፤የነፍሱን ደምስር፤ ፍቅር አልቦት

ስለቆሻሻው የሚነቅፈውን ሊሰማ ቢጥር እሱን ሊያደምጠው
እርሱ ግን መልሱ "ተከተለኝ ነው ሰው ሊያስጠምደው"

ነጥቆ ሊያወጣው፤ ከሞት ከተማ ፤ ከሙታን ግርግም
ምርጫ ተወለት ፤ ልዝቡን ቀንበር ፤ ቀሊሉን ሸክም

ማራኪው ፍቅሩ ፤ ጥልቁ ትህትናው፤ ልቡን ቢስበው
   መረቡን ጥሎ ፤
    ኑሮውን ጥሎ
ትዳሩን ጥሎ ፤ ተከትሎታል ጴጥሮስ አበው
ደግ አረገ...
ይኖር የነበር ፤ በማረፊያ አልባ ፤ የኑሮ እንጥልጥል
በሕያው መዝገብ ፤ አይሰፍርም ነበር ፤ መረቡን ባይጥል
ትላንት በእሱ..
ከአጢሀት ውቂያኖስ ፤ ሰማይ የገባው፤ በህይወት መሰላል
ፃድቁ አባቴ አበው ጴጥሮስ እኔን ይመስላል ።
ይኸው
እንካቸው ደካሞች ብሎ ፤ የነገረኝ ቅዱስ ቃሉ
ቆም ብዬ ሳጤናቸው ፤ ሁሉም እኔን ይመስላሉ ።

ደግሞ ያ የቄሳር አስገባሪው ...ጠፊ ጣዖት ገንዘብን ሰርሳሪው

ጦጣ የመሰለው የዛፍ ላይ ሯጭ
እኔን ይመስላል ዘኪዮስ ቀራጭ
በአርባ ቀን ዕድል የተበደለው
የሀጢአት ሰው ተብሎ የተገለለው
መሲሕ ነው ሲሉት ከሩቅ ልይ ብሎ
ጦጣ የመሰለው ዛፍ ላይ ተሰቅሎ
ተስፋን ናፋቂው ቁመተ አጭሩ
እኔን ይመስላል ሁሉ ነገሩ

ጥቀርሻ ኑሮውን ነክቶ.......ካመድ ከትቢያ አንስቶ
አዚሙን አባርሮለት.........የመገበው ዕለት ዕለት
እያራቀው  ከአጢሃት ግፊት......ያከበረው በናቁት ፊት
ስንት የሰው ፊት እንዳላየ......ሊያየው ወጥቶ በሱ የታየ
ጦጣ መሳይ ዛፍ ላይ ሯጭ
                    እኔ ነኝ ዘኪዮስ ቀራጭ

ገብሬሃለው የአጢሀት ግብር......ሮጫለው ለራስ ክብር
የልብ ጭንቄን ሚሰማ..........አብሮኝ በልቶ የማያማ
እየሳመ የማይከዳ.......ናፍቅ ነበር ንፁህ እንግዳ
አገኘሁ አገኘኸኝ
አገኘሁ አንተን ጌታ..........ልቤ ጮቤ እየመታ
            አነባሁኝ መንታ መንታ
አስገረምከኝ ስሜን ጠርተኽ አወረድከኝ ከዛፌም ላይ
         ....................    ልታስገባኝ ያንተ ሰማይ
ልታደርገኝ የምድር ጨው......አልጫነቴን ልትፈጨው
በጥዑም አጅህ አንኳክተኸው የልቤን በር
ባትገባብኝ እኔ እኔን አልሆንም ነበር
እንኳን መጣክ !
እንኳን መጣክ ቤተ ሳይዳ
ከመፃጉዎች ስብሰባ ከዲዊያኖች መደዳ
በገል መንደር ለቁሰለቴ ማከኪያዎቼን ሰንቄ
ቁስሌ የውሻ አሎን ብሎኝ ስላልሻረ ተጨንቄ
ወድቄ ነበር ደቅቄ.......ጭንቄን አዳማጭ ናፍቄ
ባለሁበት ሰፈር መጥተህ.....ቁም ስትለኝ አበርትተህ
ተገረመች ቤተ-ሳይዳ
ተገረመች ቤተ-ሳይዳ ፤ እኔም አለሁ ተገርሜ
ነፍሴን ፍሰሓ ያስናፈቃት ፤ የት ገባ ያመታት እርሜ
ይገርማል...
አመራረጡ የገረመው ፤ልቤ አውንም ይገረማል፤
እንዴት የኔ ደዌ ታየው ፤ ከዛ ሁሉ ደዌ መሀል ።
ይገርማል ...
ሰማይ ሰማያት ዙፋኑ፤ምድር ማትበቃው ለተረከዙ፤
በቁም ነገር ቆጥሮኝ መጣ ፤ እኔን ሊያደርግ ደመወዙ።
ብቻ መዳኔ ግሩም ነው፤ አደራረጉም ይደንቃል፤
ማን እንደ እሱ ለእኔ ይወድቃል
ማን እንደ እሱ ለእኔ ይደቅቃል
ማን እንደ እሱ ለእኔ ይደርቃል
ማን እንደ እሱ ለእኔ ይጎዳል
ማን እንደ እሱ እኔን ይወዳል
ያሉት ሁሉ.....እኔን ይመስላሉ ።

ይኸው
እንካቸው ደካሞች ብሎ ፤ የነገረኝ ቅዱስ ቃሉ
ቆም ብዬ ሳጤናቸው ፤ ሁሉም እኔን ይመስላሉ።

የሱ መልስ

Subscribe Our YouTube Channel
https://www.youtube.com/@Poetscouncil8394