Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
502 subscribers
3.27K photos
240 videos
46 files
2.19K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ፍልስጤም በሚያማምሩ የወይራ ዛፎቿ ትታወቃለች።  ፍልስጤማውያን ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ሥር የሰደደ ትስስር ይወክላሉ ይባልላቸዋል። ፍልስጤማውያኑ የወይራ ዛፎቻቸውን በፍቅር እና በአድናቆት ነው የሚንከባከቧቸው። ከ 4,000 ዓመታት በላይ እድሜ ካላቸው ጥቂት የዓለማችን ጥንታዊ የወይራ ዛፎች መካከል ናቸው በፍልስጤም የሚገኙት። በጥራቱ ምርጥ የተባለለትን የወይራ ዘይት ያቀርባሉ። በእስራኤል ወረራ በተያዙት ዌስት ባንክ እና ጋዛ በሚገኙ የእርሻ መሬቶቻቸው ግማሹ የፍልስጤም የወይራ ዛፍ ተተክለው የሚገኙበት ነው። በነዚህ ቦታዎች ብቻ የተተከሉ ወይራ ዛፎች ቁጥር 10 ሚሊዮን ይደርሳል።
ለእያንዳንዱ ፍልስጤማዊ የወይራ ዛፍ ማለት የትውልድ ትስስርና የፅናት ተምሳሌት ነው። እናት ልጆቿን እንደምትንከባከበው ሁሉ የወይራ ዛፍ መሬታቸውን በየቀኑ በመንከባከብ ያሳልፉ ከነበሩ ቅድመ አያቶቻቸው ጋር ያሰናስላቸዋል።
ወይራ በእስልምና የተባረከ ፍሬ ነው። ይህም በቁርኣንና በሐዲስም በተደጋጋሚ ተጠቅሷል።  የወይራ ዛፍ መትከል ለብዙ አመታት የወይራ ፍሬዎችን ለትውልድ ያበረክታል። ይህ የማይቋረጥ ልግስና ተግባር (ሰደቃህ ጃሪያህ) ምንዳ ያጎናፅፋል። እርሶንም ሆነ የሚወዷቸውን ሰዎች ከህልፈትዎ በኋላም ሊጠቅም ይችላል።  የወይራ ዛፍ "የሕይወት ዛፍ" ተብሎም ይጠራል።
    ይህ በንዲህ እንዳለ እስራኤል በዚህ አመት ፍልስጤማውያኑ የወይራ ፍሬ እንዳይለቅሙ ከልክላቸዋለች። ይህ ወቅት ለፍልስጤማውያን የወይራ ፍሬያቸውን ለቅመው ትኩስ የሆነውን የወይራ ዘይት ለገበያ የሚያጓጉዙበት የአመቱ ወሳኝ የመኸር ወቅት ነው።

#Gaza #ጋዛ #israel #ፍልስጤም #Palestine #olivetree #OlivePalestine #PaleatineOlive

https://t.me/Xuqal
https://ummalife.com/BilalunaEdris1