Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
467 subscribers
3.09K photos
201 videos
46 files
2.14K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
‹‹በኸንደቅ ዘመቻ ግዜ ብህብረት ትልቅ ቁፋሮ እየቆፈርን ሳለ ከአቅማችን በላይ የሆነች ቋጥኝ ቁፋሮውን አስተጓጎለችብን።›› ይላል ዐብዱላህ ቢን ጃቢር

ነቢን ሰዐወ ወደ ቋጥኙ ጠራናቸው። ነቢ መጡ፤ እርቧቸው ሆዳቸው ላይ ድንጋይ አስረዋል። ነቢን ሰዐወ ጨምሮ ሁላችንም ምግብ ከቀመስን 3 ቀናት አልፈዋል። ነቢ መቆፈርያቸውን ይዘው በረሀብ አንጀት ቋጥኙን ቢመቱት ተፈረካከሰ።

‹‹አንቱ ነቢ! ቤት ደርሼ ልምጣ ይፍቀዱልኝ!›› አልኳቸው፤ ፈቀዱልኝም።
ቤቴ ሄጄ ባለቤቴን አገኘኋት፦‹‹ነቢ ተርበዋል፤ ሚቀመስ ምን አለሽ?›› አልኳት።
‹‹ትንሽ የገብስ ዱቄት እና አንዲት ግልገል አለች›› ብትለኝ ግልገሏን አርደን ገብሱን አቦካን።

ስጋውን በድስት ጥደን የገብስ ሊጡ ኩፍ እስኪል ድረስ ወደ ነቢ ሮጥኩ፤ ወደ ጆሮዋቸው ጠጋ አልኩ'ና፦‹‹አንቱ ነቢ! ትንሽ ግልገል ነበረችኝ እሷን አርጄ ትንሽዬ ዳቦም ጋግርያለሁ። አንድ ሰው ይያዙና እኔ ቤት እንሂድ›› አልኳቸው ብቻቸውን መብላት እንደማይወዱ ስለማውቅ።

‹‹ባለቤትህ ጋር ሂድ'ና እኔ እስክመጣ ድረስ ድስቱንም ምጣዱንም ከእሳት እንዳታነሳው ንገራት›› አሉ።
ከዝያም ወደ ተሰበሰበው ህዝብ ዙረው፦‹‹እናንተ ሰዎች! ጃቢር ምግብ አዘጋጅቷል ሁላችሁም ኑ›› ብለው ተጣሩ።

በድንጋጤ ወደ ሚስቴ ሮጥኩ፦‹‹ዛሬ ጉዳችን! ነቢ ብቻቸውን ስጠራቸው መላ ህዝቡን ይዘውልሽ እየመጡ ነው›› አልኳት።
‹‹የምግቡን መጠን ነግረኃቸዋል?›› አለች።
‹‹አዎን›› አልኳት።
‹‹እንግዲህ ነቢ ሰዐወ ከኛ በላይ ያውቃሉ›› ብላ ስራዋን ቀጠለች።

ነቢ ሰዐወ ህዝቡን ይዘው መጡ። ነቢ ሰዐወ ወደ ማብሰያችን ዘልቀው ገብተው በስጋውም በሊጡም ላይ ዱዓ አደረጉበት'ና፦‹‹ጃቢር! ባለቤትህ ይህንን ሊጥ ብቻዋን ማቡካት ስለማትችል አጋዥ ጎረቤት ጥራላት›› አሉኝ።

ባለቤቴም ህዝቡ በልቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ምጣዱንም ድስቱንም ከእሳት እንዳታነሳ ታዘዘች። እሷ ትጋግራለች ከስር ስር የጋገረችው ለህዝቡ ይከፋፈላል።

ከአንድ ሺህ በላይ የሆኑት የተራቡ ዘማቾችም ለአስር አስር ተመዳድበው ተቀመጡ። ህዝቡ ጠግቦ በላ፤ ትሪ ላይም አስቀርተው ተነሱ። ግና ድስቱም ሙሉ ሊጡም አልጎደለ።

ነቢ ሰዐወ ህዝቡን ካበሉ በኋላ፦‹‹ለቤት ሚበቃችሁን አስቀሪ ለሰፈር ሰውም አከፋፍዪ›› ብለዋት ሄዱ።

عليه افضل الصلاه والسلام ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم ياحبيب يارسول الله صلى الله عليه وسلم
ምንጭ፦
كتاب المغازي للبخاري

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለው ዱዓ ያደርጉ ነበር

አላህ ሆይ ካንተ ውጭ ማንም ለመልካም ፀባይ ሊገራኝ አይችልምና ያማረ ፀባይን አግራልኝ። ካንተ ውጭ ከመጥፎ ፀባይ የሚያርቀኝ የለምና ከመጥፎው አንተው አርቀኝ) ይሉ ነበር።

(ሙስሊም ዘግበውታል)

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
እጁ ከፍርስራሹ መሐል ይታያል። ከአፈሩ በላይ ትበያ ለብሷል።  በወራሪዋ ሚሳኤል ተደብድቦ የሞትን ፅዋ ከተጎነጨ ሶስት ወራት ተቆጥሯል። ጀናዛው ሲገኝ አካሉ ምንም አልሆነም ነበር። አዲስና ትኩስ ሰውነቱም አይሸት በምስጥም አልተበላ። ሊያፈጥርበት በእጁ የያዛት ተምር ከጭብጡ ስር ችግኝ ሆና በቅላለች። 
ያ አላህ እድለኝነትህ ዱንያ ላይ መታየት በላይ እድለኝነት አለ?

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እነዚህን ቀናት ታሪክ ከቶም ሊረሳቸው የማይችላቸው ቀናቶች ናቸው…🥹

በ ሰሜን ገዛ ውስጥ ከፈረሰ መስጂድ የጁምአ ኹጥባ

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ከቀደምቶች አንዱ፡

ኢብሊስ የሰው ልጅን ከማስተከዝና ተስፋ ከማስቆረጥ በላይ የሚያስደስተው ነገር የለም ብሏል።

ነገሮች ሁሉ የጨለሙብህ፡ ምንም ተስፋ የሌለህ፡ ህይወት ሁሉ የጨለመችብህና ፊቷን ያዞረችብህ አድርጎ ያሳየሀል።

ወንድሜ ሆይ!

እንኳን ተራና ጠፊ የሆነችዋን ዱንያ ቀርቶ፡ የምንናፍቃቸው ረሱልንﷺ በጀነት ማየትን ከጌታችን እንከጅል የለ?

የሱን ፊት ማየት እንከጅል የለ?

ከሶሀባዎች ጋር በጀነት አብሮ መቀማመጥን ተስፋ እናደርግ የለ?

ታዲያ ለከሀዲው እንኳን በሚያምበሻብሽበት ተራና ጠፊ በሆነው ዱንያ ጉዳይ ላይ ምን ተስፋ አስቆረጠህ?

ይልቁንስ ዱዓ ተቀባይነት ይገኝበታል ተብሎ በጣም በሚከጀልበት ሰአት ላይ ነህና፡

ዱዓ አብዛ፡ በረሱል ﷺ ላይ ሶለዋት አብዛ፡ ሰበቡን አድርስ

ከዛም ተስፋ መቁረጥን ተስፋ አስቆርጠው!

🌸صلوات ربي وسلامه عليه

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ምስሉ ልብን ቀስፎ ይይዛል። ታዳጊው ቅጠል ሲበላ አንጀትህ ይላወሳል። ልትጎርሰው የያዝከውን ወደ አፍህ መክተት ያቅትሀል። ኡኹዋ ነዋ!

እርሱ ግን ብርቱ ነው ለነገው ድሎት ዛሬን በቅጠል ያሳልፋል። ያድጋል የጀግንነት ገድሉን ፈፅሞ ገሎ በክብር ይወድቃል።

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
"ሞት ልታመልጠው አትችልም ከሱ ከሸሸህ ይደርስብሃል ከተቃረንከው ያሸንፍሃል"

ኢማም ዐሊይ ረዲየሏሁ ዐንሁ
"ከሴት ልጅ ላይ ሃያዕን ካጣህ ስለመጥፎ አሟሟቷ አትጠይቅ"

ሸይኽ ሙሃመድ ቢን ሳሊህ አል ዑሰይሚን ረሂመሁላህ
አላህ፤ እንኳን ለ1446 ዓመተ ሂጅራ ዐዲስ ዓመት አደረሰን!!
1446 ዓ.ሒጅራ
ደስ ደስ የሚል ነገር የምናገኝበትና የምንሰማበት ዓመት ያድርግልን 🥰
ጭንቅላቱን ከትራስ ጋር እንዳገናኘ እንቅልፍ የሚወስደው ሰው ፤ ያለበት ኒዕማ ቀላል እንዳይመስለው

ጌታህን አመስግን
ቲስበሑ 😍