Bilaluna Edris
545 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ወደ ቤተሰቦቿ ሽምግልና ልትልክ ያሰብካት ልጅ አባት የሚሰግድበት መስጂድ ላይ ሄደህ ስትሰግድ...
እስራኤል አምናለች !

በኢራን የተፈፀመብን ጥቃት ከጠበቅነው በላይ የከፋ ነው ስትል አሁን እስራኤል ገልፃለች ።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትርን ገልፆ አልጀዚራ አሁን ባወጣው ዘገባው በኢራን የተፈፀመው የሚሳኤል ጥቃት ከጠበቅነውና ካሰብነው በላይ ነው በማለት እስራኤል ገልፃለች ። አነስተኛ ውድመት ብቻ እንደደረሰባት እስራኤል ማስተባበያ ስትሰጥ ብትውልም የኢራን ጥቃት አሳማሚ እንደነበር ለማመን ተገዳለች ።
ግዙፉ የእስራኤል የጦርጄቶች ማዘዥና አየር ማረፊያ ኔቫቲም airbase መውደሙ የተረጋገጠ ሲሆን ሌሎች በርካታ ጉዳቶችም በእስራኤል ወታደራዊ ተቋማት ላይ ደርሰዋል ። ኢራን በሰጠቺው አሁናዊ መግለጫ ወታደራዊ ጥቃቱ ከተጠበቀውም በላይ ስኬታማ ነበር ብላለች።

እስራኤል ጧት ላይ ብትፎክርም አሁን ላይ ከፍተኛ ሀፍረት ውስጥ ገብታለች ። እናም በኢራን ላይ ጥቃት ለመፈፀም ምእራባውያንን እየተማፀነች ትገኛለች ።
ኢራን በበኩሏ እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት የምትፈፅም ከሆነ ትፀፀታለች አፀፋየም ከአሁኑ በእጅጉ የከፋ ይሆናል ስትል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች ።

ድል ለኢስላማዊቷ ሪፐብሊክ ኢራን !
ውድቀት ለእስራኤል እና አጋርቿ !

@ https://t.me/Xuqal
"አሏህ ሆይ ፊቴን ካንተ ውጪ ለማንም ከመስገድ እንደጠበቅከው ካንተ ውጪ ማንንም ከመጠየቅ ጠብቀው"

ከኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ዱአዎች ውስጥ አንዱ
የሸዋል ዒድ ሚባል በዲን የተደነገገ ነገር የለም!!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن عَمِلَ عَمَلًا ليسَ عليه أمْرُنا فَهو رَدٌّ.﴾

“የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1718

ኢማሙ ማሊክ (رحمه ﷲ) እንዲህ ይላሉ፦

“በኢስላም ውስጥ አዲስ ቢድዓን ፈጥሮ ያ ቢድዐ መልካም ናት ብሎ የሞገተ በርግጥም የአላህ መልእክተኛ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ ምግቷል። ምክንያቱም አላህ እንዲህ ብሏል፦ ‘ዛሬ ለናንተ ሀማኖታችሁን ሞላሁላችሁ’ያኔ ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን አይሆንም።”

@ https://t.me/Xuqal
የሆነች ሴት በሆነ እብድ አጠገብ ታልፍለች

እብዱም መሬት ላይ በእጁ እየሳለ ነው..

ሴትየዋም አዘነችና ምን እየሰራህ ነው ስትል ጠየቀቺው ...?

እብዱም ጀነትን ስየ ለተለያየ ቦታ እየከፍፈልኩ ነው አላት...!

ሴትየዋም ፈገግ አለችና አንዱን መውሰድ ይቻላል?.. ዋጋውስ ስንት ነው ስትል ጠየቀች...?

ወደሷ ተመለከተና 10ሪያል ብቻ ነው የሚያስፈልገው አላት....

ሴትየዋም ብሩንና የተወሰነ ምግብ ሰታው ሄደች...!

የዛን ቀን ለሊት ጀነት ስትገባ ተመለከተች ህልሙን ለባልተቤቶ ነገረቺው ከእብዱ ጋር የሆነውንም አስረዳቺው...

ባልተቤቶም በሚቀጥለው ቀን ከእብዱ አንድ መሬት ለመግዛት ሄደ !

እብዱ ጋርም እንደደረሰ ከጀነት አንድ መሬት መግዛት እንደሚፈልገና ዋጋው ስንት እንደሆነ ጠየቀው ?

እብዱ እንደማይሸጥ ነገረው!

ሰውየውም ተገረመና ትናንት ለሚስቱ 10ሪያል እንደሸጠ ነገረው ።

እብዱም ሚስትህ እኮ ጀነትን አልነበረም በ10ሪያል የጠየቀቺው የኔን ደስታ ነበር የፈለገቺው !

አንተ ግን ጀነትን ነው የምትጠይቀው ጀነት ደሞ
ትክክለኛ ዋጋ የላትም ። ወደሷ መግቢያ መንገድ ሰወችን በማስደሰት ነውና

ከፊሎቻቹህ ለከፊሎቻችሁ ደስታን ተሰጣጡ
በሰወች ዘንድ ደስታን የሚበትን አላህ በጭንቅ ጊዜ ደስተኛ ያረገዋል ።

© Ibn Ahmed
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"የሰይድ ቢላልን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁት በልጅነቴ ነበር።ገጠመኙ እንዲህ ነበር።
የልጅነት የእድሜ ክፍሌን ባሳለፍኩበት መንደር ለፈጅር ሰላት በየሰፈሩ እየተንቀሳቀሰ የሚቀሰቅስ ሰው ይመደብ ነበር።ያም ሰው ወደ ቤታችን እየመጣ ይቀሰቅሰን ነበር።
ታዲያ አንድ ቀን የፈጅር ሰላት ደርሶ ሙአዚኑ ይጠፋል።ለእናቴ የቅርብ ዘመድ የነበረው የመስጂዱ ኢማም እኔን ጠየቀኝ:-
"አዛን ማውጣት ትችላለህ አንዴ?" ሲል ጠየቀኝ።
እኔም:-"አዎ እችላለሁ።" አልኩ።ከዚያ በፊት አዛን አውጥቼ ባላውቅም እንዲሁ ደስ ስላለኝ ነበር እንደዚያ ያልኩት።
ኢማሙም እሺ አውጣ አሉኝ።
እኔም እሺ ብዬ ወደ ከፍታ የሚወስደው ደረጃውን በመውጣት አዛን አወጣሁ።
ከደረጃው ወርጄ ወደ ውስጥ ስገባ መስጂዱን ከሞሉት ብዙሃን አዛውነት መካከል አንድኛው:-
"ቢላል ሆይ! አሏህ ይባርክልህ!" አለኝ።

ይህ ነበር እኔና ቢላልን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀን።አሏህ ከርሱ ጋር እንዲሰበስበኝ እለምነዋለሁ።"

በታዋቂው አሪሳላህ ፊልም ላይ የቢላልን ገፀ-ባህሪይ የተወኑት ዐሊይ አሕመድ ሳሊም "አሲር" በተሰኘው ፖድካስት ላይ ከነበራቸው ቆይታ።

@ https://t.me/Xuqal
ትውልደ አውስትራሊያዊ ነው በገበያ ማዕከሉ ውስጥ ጥቃት ሰንዝሮ ስድስት ሰዎችን ከመሬቱ ዘረረ። በጥይት ደብድቦ እስትንፋሳቸውን አቋረጠ። የአውስትራሊያና የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን ዜናውን ተቀባበሉት "አንድ ሙስሊም አሸባሪ ጥቃት ሰነዘረ" እያሉ ለፈፉ። በፍጥነት ወሬውን አሰራጩት። ከአንድ ሰአት በኋላ የድርጊቱ ፈፃሚ ስም ሲጣራ ሙስሊም እንዳልሆነ ታወቀ። የዜናው ርዕስ ተቀየረ "አንድ የአእምሮ በሽተኛ በገበያ ማዕከል ውስጥ 6 ሰዎችን ገደለ" በሚል ተስተካከለ። ለራሳቸው ለመስቀለኛ ጦረኛቸው ሰበብ አያጡም ጨዋ ያደርጉታል። ሙስሊሙን ለማጥቃት ሲሆን ግን ስም እየለጠፉ ከዚህም ከዚያም ይቦጫጭቁናል።

@ https://t.me/Xuqal
​▬▬ ስለ ፀሀይ ይህንን ያውቁ ኖሯል ▬▬

➥ ፀሐይ ከመሬት 149,598,023 ሚልዮን ኪሎ ሜትር ትርቃለች። ይህ ቁጥር ሲጠጋጋ መቶ ሃምሳ ሚልዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

➥ ከመሬት ተነስቶ ፀሐይ ላይ ለመድረስ ሙቀቷ ቢፈቅድ እንኳን አይቻልም። እጅግ በጣም ፈጣንና ዘመናዊ መንኮራኩር ተሠርቶ በመላክ ያለማቋረጥ ሌት ተቀን እንኳ ቢጓዝ መንኩራኩሩ ለፀሀይ ቅርብ የሆነችው ኮከብ ላይ የሚደርሰው ከ70ሺ (ከሰባ ሺ) ዓመታት በኋላ ነው።

➥ ፀሐይ የመሬትን 333,000ሺ ( ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺ) ጊዜ እጥፍ ፀሀይ ትበልጣለች። ክብደቷም፦
1.99× 10²⁷ ቁጥር ያህል ፀሀይ እንደምትመዝን ይገመታል።

➥ ፀሀይ በሴኮንድ 3.85 × 10 ×26 ዋት የሙቀት ጉልበት ታመነጫለች።

➥ የስፒል ያህል መጠን ያለው የጸሀይ ጨረር ከመነሻው ያለውን ሙቀት ይዞ መሬት ቢወድቅ በ160 ኪሎ ሜትር ርቀትና ስፋት ላይ ያለን ማንኛውንም አካል አቃጥሎ ያጠፋል።

➥ ከመነሻው ባለ ኃይሉ የአንድ ሳንቲም ስፋት ያለው የፀሀይ ውጫዊ ኃይል የሚፈነጥቀው ብርሃን፦ 2 ሚልዮን 60 ዋት አምፑሎች ከሚያመነጩት ብርሃን በላይ ያበራል።
"መልካም ስራዬ የሚያስደስትህ፤ኃጢያቴ አንዳች የማይጎዳህ አምላኬ ሆይ!
ወደ ሚያስደስትህ ስራ ምራኝ፤የማይጎዳህ ተግባሬን ይቅር በለኝ።"
እኛም የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን!!
"የሐቢባችንንﷺ ዘያሪዎች ካልኸደምኩኝ፤ልቤ አይረጋልኝም።" ይሉ ነበር።
እኚህ የመዲና ሳሊህ ሰው በዛሬው እለት ወደ አኸራ ሄደዋል።አላህ ማረፊያቸውን ያከብሯቸው፣ይወዷቸው ከነበሩት ሰይዳችን ﷺ ጋር ያድርግላቸው አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃችሁ 🤲

ለ 40 አመታት በመስጂድ አል ነበዊ ለሀጃጆችና ዑምራ ለሚያደርጉ እንግዶች ቡና ሻይ እና ተምር #በነፃ ሲሰጡ የነበሩ ሸይኽ እስማኢል አልዛይም በ96 አመታቸው ከዚህ ዐለም በሞት ተለዩ።
ረሂመሁላሁ ወገፈረለሁ

እኛም የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን

© Inside the Haramain

@ https://t.me/Xuqal
"መካሪ ባልሆኑ ህዝቦች ውስጥ ኸይር የለም እንዲሁም ምክርን በማይወዱ ህዝቦች ውስጥም ኸይር የለም"

ሰይዱና ዑመር ኢብኑል ኸጧብ

እኛ ተገላቢጦሽ ነን አይደል ?
ይህቺ ቤተሰብ ሙሉ ነበረች
ከህልማቸው ጋር
ከነፍሳቸው ጋር
በደግነታቸውና ከደስታቸው ጋር
አንድ ሰው ካለው ስሜቶች ሁሉ ጋር እና
ተቃርኖዎች እና በህይወት ላይ ባለ ጥብቅነት ሁሉ ነገር ጋ ሙሉ ነበሩ!

አሁን ግን ይህ ቤተሰብ በሙሉ ከህይወት መዝገብ ቤት ተወግዷል!💔
“አትቆጣ ጀነት ይኖርሃል።”

ረሱል (ﷺ)