Bilaluna Edris
545 subscribers
3.35K photos
276 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
Bilaluna Edris
Photo
በረሃማዋ ዱባይ በ75 ዓመት ውስጥ አስተናግዳው አታውቅም የተባለ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ተጥለቀለቀች።

የተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መዲና የሆነችው ዱባይ ባለፉት 75 ዓመታት ካስመዘገበችው ከፍተኛ የተባለ የዝናብ መጠን ከሰኞ እኩለ ሌሊት ጀምሮ አስተግዳ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች። በዱባይ የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የዐረብ ባህር ገብ መሬቶችንም ጭምር በማካለል ለሰው ነፍስ መቀጠፍና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል።

ከሥፍራው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በተለይ ዱባይ ከተማ በጎርፍ መጥለቅለቋን ተከትሎ የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ተስተጓጉሎ የአውሮፕላን በረራዎችም እንዲዘገዩ ተደርጓል።

ከሰኞ እኩለ ሌሊት እስከ ትላንት ማክሰኞ አመሻሽ በዱባይ የተመዘገበው የዝናብ መጠን ከዚህ ቀደም ከተማዋ በአንድ ዓመት ከመንፈቅ ጊዜ የምታስተናግደው መሆኑንም የሜትሮሎጂ ባለሞያዎች ገልፀዋል።

በዱባይ ከተማ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ መኖሪያ ቤቶችንና የገበያ ማዕከላትን በማጥለቅለቅ ትምህርት ቤቶችም ዝግ እንዲሆኑ አስገድዷል። በከተማዋ ውስጥ የሚገኙት ታዋቂዎቹ የገበያ ማዕከላት ዱባይ ሞል እና ሞል ኦፍ ኤምሬትስም ከጎርፉ መጥለቅለቅ አልተረፉም። የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት ጎርፉን ለማስመጠጥ ሙከራ ሲያደርግ፣ የኤምሬቶች ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ማዕከል የዱባይ ነዋሪዎችን በቻላችሁት አቅም ሁሉ እራሳችሁን በጎርፉ ከተጥለቀለቁ አካባቢዎች አርቁ የሚል የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ መልዕክት አስተላልፏል።

የተመዘገበው ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንደ ዱባይ ባይሆንም በአካባቢው የሚገኙትን ባህሬን፣ ኦማን፣ ኳታር እና ሳዑዲ ዐረቢያንም አዳርሷል። የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በኦማን የ18 ሰዎች ሕይወት መቀጠፉን ዘግቧል። ጎርፉ ሕይወታቸውን ከተጠቃቸው ውስጥ 10 ሕፃናት ይገኙበታል።

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶችና በዐረብ ባህር ገብ ሀገራት ለተመዘገው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የአየር ንብረት ለውጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል። ለዚህ የአየር ንብረት ለውጥ መነሻ ነው የሚባሉት ሰው ሰራሽ ችግሮች መሆናቸውን ባለሞያዎች ያነሳሉ።

በጎርፍ ከተጠቁት መካከል በበረሃማዋ ዱባይ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ የተለመደ ባለመሆኑ ለጎርፍ መውረጃ የሚያገለግል ቦይ በሥፋት ቀድሞ ስላልተገነባ አደጋውን አስከፊ እንዳደረገው ተነግሯል።

@ https://t.me/Xuqal
“ተዋጊዎቻችን እና እኛ የያዝናቸው Sukhoi 24 አውሮፕላኖች ተልእኳቸውን ለመወጣት ምቹ ሁኔታ ላይ ናቸው!”
የኢራን ጦር አየር ሃይል አዛዥ
#አልጀዚራ

@ https://t.me/Xuqal
ቁርዓንን ድምፇን ከፍ አድርጋ እየቀራች እሱም እያዳመጣት ነበር …

እየቀራችን እያለ እዚች አያ ጋር ስትደርስ…

«ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ»

ድምፇን ዝቅ አደረገች…

እሱም ፈገግ አለና እንዲህ አለ ፦

" አንቺ የመጀመሪያቸው ፣ ሁለተኛቸው ፣ ሶስተኛቸውና አራተኛቸውም ነሽ "

@ https://t.me/Xuqal
የሮቦቲክስ አባት: ኢስማኤል አል-ጃዛሪ (1136-1206)

ኢስማኢል አል-ጃዛሪ ፖሊማትስ ነበር፡ ምሁር፣ ፈጣሪ፣ ሜካኒካል መሐንዲስ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ አርቲስት እና የሒሳብ ሊቅ የነበረ ከጃዚራ ስርወ መንግስት ስር በነበረችው ከሜሶጶጣሚያ የተገኘ ምሁር ነው።

"የረቀቁ መካኒካል መሳሪያዎችን የተመለከተ እውቀት"የሚለው መጽሃፍ የተፃፈውም በመካከለኛው ዘመን ጃዛሪ በ 12 ኛው ክፍለ ዘመን በአረበኛ ቋንቋ በኢስማኢል አል-ጃዚሪ ነበር የተፃፈው።

በተጨማሪን ከሃምሳ በላይ የሆኑ ሜካኒካል መሳሪያዎችን እና አውቶሜትቶችን፣ ሰዓቶችን፣ የውሃ ማሳደግያ ማሽኖችን፣ የሙዚቃ አውቶሜትሮችን እና የሰው ልጅ ሮቦቶችን ጨምሮ የመጀመሪያ ግኝትን ያስገኘው የመጀመሪያው የአለማችን የፈጠራ ባለሙያም አል-ጃዛሪ ነበር።

በመፅሀፉ ስለ እያንዳንዱን መሳሪያ ዝርዝር መመሪያዎችን ፅንስ ሀሳቦችን በመፅሁፉም ያትታል።በተጨማሪም ታሪኮችን እና ታሪካዊ ማጣቀሻዎችን ያካትታል።

መጽሐፉ በአውሮፓውያን የሰዓት አወጣጥ እና አውቶማቲክ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሲሆን በመካከለኛው ዘመን በእስልምናው ዓለም ውስጥ ስለ ዕለታዊ ኑሮ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ግንዛቤዎችን ይሰጣል። በዘመናዊው የሮቦቲክስ ቁልፍ ፅንሰ-ሀሳቦች ላይ ተጽእኖ ያሳደረም ነው የአል-ጀዚሪ መጽሐፉ

@ https://t.me/Xuqal
ዝናብ ሲመጣ ብዙ ሰው ለማሳለፊያ ጃንጥላ ይይዛል፡፡ ሲያባራ ጃንጥላ ሸክም ይሆንበታል፡፡ ይህን ጃንጥላ የት ልጣለው ይላል፡፡

ከሰዉም መካከል ችግር ሲገጥመው ባንተ የሚጠለል አለ፡፡ ወጀቡን  ለማሳለፍ። ጥቅሙን ሲጨርስ ግን ለዐይን ይጠላሃል፡፡ ሊርቅህ ይጣደፋል፡፡

አንዳንዱ አዲሱ ባልዲ መያዙን ሳያውቅ አሮጌ ነው ያለዉን አውጥቶ ይጥላል። አዲስ ጓደኛ ስላገኘ ነባሩን ይረሳል። ሌላ ሰው መጣ ብላችሁ ሰው አትግፉ። ሰዉንም ለመርሳት ሰው አትጠቀሙ።

ጌታዬ ሆይ ከወረተኞች አታድርገን፡፡ 🤲

@ https://t.me/Xuqal
"የአደም ልጅ ሆይ !! በአንተና በአላህ መካከል ማንም ፤ የማያቀው ወንጀል አለ ፤ ይቅር ሊልህ ከፈለክ አንተም ከሰዎች ይቅር በል ፤ እንዲሰርዝልህ ከፈለክ አንተም ከልብህ የሰዎችን በደል ሰርዝ። ምክንያቱም ምንዳ በስራ አይነት ነውና"

   📚 بدائع الفوائد ( 2/468)

@ https://t.me/Xuqal
#ሀገረ_ቱርክ
.
በቱርኮች ዘንድ ከተለመዱት ልማዶች አንዱ መስጂድ ውስጥ ገብተው ትንሽ ጫማ ካዩ የሳንቲም ገንዘብ በማስቀመጥ አንድ ልጅ ከመስጂድ ወጥቶ ጫማውን  ሊለብስ ሲመጣ ገንዘቡን ያገኛል... እና ደስተኛ ይሆናል በሰላቱም ይበረታታል, እናም ልቡ በመስጂድ ፍቅር ይንጠለጠላል!
.
...በጣም ስለወደድኩት ነው😊

@ https://t.me/Xuqal
እስራዔል ከቀናት በፊት ከኢራን በደረሰባት የሚሳዔል ጥቃት 1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት ደርሶባታል ተባለ፡፡

የእስራዔል ጦር የቀድሞው የኢኮኖሚ ዋና አማካሪ ብርጋዴር ጄነራል ራም አሚናች ለ Bloomberg በሰጡት ቃል፣ "በእስራአል፤ ፈረንሳይ፤ እንግሊዝ፤ አሜሪካና ጆርዳን የጋራ ጥረት የተገታው ጥቃት 1.1 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ጉዳት አድርሷል" ብለዋል፡፡ 

እንደ Sputnik ዘገባ ከሆነ ደግሞ፣ ኢራን ጥቃቱን ባደረሰችበት ወቅት 130 ሚልየን ዶላር ወጪ ያደረገች ሲሆን፤ እስራዔል ጥቃቱን ለመመከት ከ1.3 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ አውጥታለች፡፡

@ https://t.me/Xuqal
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የወላጆች ሀቅ !

ያለቀሰበት ነገር፣ አለቃቀሱም ጭምር ያስለቅሳል!

ተመልከቱት


@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris
Photo
የምላሱ ቅልጥፍና፣ የንግግሩ አንደበተ ርቱዕነት፣ መልካም ስነ ምግባሩ፣ ፊቱ ላይ የሚታየው ብርሀን እና የፈገግታው ማማር ያስገርመኝ ነበር....ልክ  ከቁርኣን ሰዎች አንዱ እንደሆነ በነገሩኝ ጊዜ ግን አግራሞቴ ይወገድ ነበር..!
ይላሉ ቀደምቶቻችን...ስለ ቁርአን ስነ ምግባር ማሳመር በሚናገሩ ጊዜ ❤️

ቁርኣን ባለቤቱ ሳያውቅ እና ሳያስተውል ተርቢያን ያስተምረዋል....

ቀልዱ እየቀነሰ ይሄዳል፣ አንደበተ ርቱዕነቱ በንግግሩ ውስጥ ይታያል፣ ንግግሩ ከተገቢው ቃል የጸዳ ነው፣ አሉባልታ የሆኑ መጃሊሶችንና እና ስራ ፈት እና ጥቅም አልባ የሆኑ ነገሮችን ይርቃል።

"ቁርኣን የተለየ እና ያማረን ስብዕና ያላብሳል
ፍጹም የተለየ...

ጊዜያችንን እና ጥረታችንን ለቁርኣን ሰጥተን  በእሱ ላይ ምንም ተጽእኖ አለማግኘት የማይቻል ነገር ነው....
መጥፎ ልማዶቻችን እንደነበሩ ሆነው ይቀጥላሉ ማለት  የማይቻል ነው!

በነፍሶቻችን  እና በኹሉቃችን ላይ የቁርአንን በረካ ላለማግኘት የማይቻል ነው

በፈተና ጊዜዎቻችን እንኳን ለአላህ ቀዷዕ እና ቀደር እጅ እግር መስጠታችንን እንደ አንድ ልማድ ሆኖ እናገኘዋለን....

ከአላህ የሆነ መረጋጋት እና ተስሊም ልክ ምንም እንዳልገጠመን ነገር በልባችን ውስጥ ይወርዳል.....

ወላሂ ከቁርዐን ሚስጢሮች ውስጥ አስደናቂው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ....

ልክ ወደኛ የወረደ ያህል እንዲሰማን ያደርገናል...
ልክ ቁጭ ብለን አናቅፆቹን ማንበብ ስንጀምር ቀልባችንን ያረጋጋልናል....
አንዳንዱ አያ ይፈውሰናል ፣ አንዳንዱ ይገስፀናል....አንዳንዱ  ያስታውሰናል .....አንዳንዱ ያፅናናናል....አንዳንዱ ህመማችንን ያቀልልናል....አንዳንዱ ያስጠነቅቀናል....

አንዱ በራሳችን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ያጠናክርልናል....
አንዱ ደግሞ በውስጣችን የሚገኘውን መጥፎ ባህሪም ያስወግድልናል....፥
ወላሂ ሙሉ በሙሉ የህይወታችንን ሂደት ወደ ተሻለ እና ገር የሆነ መንገድ ይመራል...

Just imagine በአላህ....ልክ ከፍቶን ጨንቆን ባለበት ሰዐት  ሱረቱል መርየምን ስንቀራ.....ከዛ ጀሊሉ
أَلَّا تَحْزَنِي
ሲለን...🥹
እኛን እያናገረ አይመስለንም.....
إِنَّا نُبَشِّرُكَ
ሲለን እኛን  የሚያናግረን ያህል እየተሰማን አይናችን የሚያቀረው እንባ...🌸

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَٰنُ وُدًّا
ሲለን ከዚህ አያ ፍቅር የሚያስይዘን ልዩ ስሜት....🌸🌸 ❤️

አንዴ
ياعبادي الذين آمنوا
እያለ እየጠራን ሲያረጋጋን...😊

አንዴ ደሞ
وَلَقَدْ نَعْلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدْرُكَ بِمَا يَقُولُونَ
እያለ አብሽሩ እኔ ጌታችሁ የሁላችሁንም ሀል አውቃለው....ሰዎች የማይሆን ቃል ተናግረው ቀልባቹን ሲሰብሩ..🥹
ሰው ሀቃችሁን ሲበላባችሁ....
ከልባችሁ የፈለጋቹት ሀጃ ሳይሳካ ሲቀር...
ከልባችሁ ስታዝኑ....
በጣም የምትወዱት ሰው ሲለያችሁ 😢
each &every ሀላችሁን ተመልካች ነኝ አውቃለው ብሎ ከዛ ምንድነው ሚለን....

فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ
ኑ ወደኔ....❤️ እኔን አጥሩኝ....ቀልባችሁ እንዲረጋጋ ....ሰብር እንድታደርጉ .... ቁዋን እንድሰጣችሁ ኑ ወደኔ ....
እኔ ጋር ቅርብ መሆን ከፈለጋችሁ ሱጁዳችሁ ላይ ታገኙኛላችሁ ይለናል...

ታድያ በአላህ ከዚ በላይ እረፍት ምን አለ....
فإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا* إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا
እያለን....
فَإِنِّي قَرِيبٌ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ
እያለን ...
لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ

እያለን
ولا تهِنوا ولا تحزنوا
እያለን
وما كان ربك نسياً
እያለን....
ብዙ ለሊቶችን ለብቻህ ቁጭ ብለህ ያለቀስክበትን ምረሳ ይመስሀል...
ቀልብህ ሚጠግነው አጥተህ የሀዘን ስሜት እወረረህ ደጃፌ ላይ እኔን በመከጀል የቆምክበትን ጊዜ ምረሳ ይመስልሀል...
እያለን እኮ ነው....

እንደ ቁርአን ልብ ሚያረጋጋ እና ከፍ የሚያደርግ  ነገር ምን አለ በጀሊል🌸🌸

ጂብሪል አለይሂ ሰላምን ተመልከቱ....ቁርአንን ይዞ ወረደ....ከመላኢካዎቹ ሁሉ ደረጃው ከፍ ያለ መልአክ ሆነ....በቁርአን ውስጥም አል-ሩህ አልአሚን የተባለ elegant ስያሜን አገኘ...🌸

ወማ የንጢቅ አኒል ሀዋ የተባሉት....ለኛ ረህመት ሆነው የተላኩት የኛ ፍቅር ነቢይ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዘንድ
ወረደ.....🌸
ከአንቢያዎቹ ሁሉ የተከበሩ...በአኺራ ላይ ሸፋአቸው ተቀባይነት የሚያገኙ.... ከፍ ያሉ መልዕክተኛ ሆኑ..😘

እኛን ደሞ ተመልከቱ በአላህ 🥹 የሙሀመድ ኡማ የሆንነው እኛ ላይ ቁርአን ወረደ.....
ከሌሎቹ ኡማዎቹ ሁሉ እኛ በላጭ ህዝብ ሆንን 🌸

ረመዷንን ተመልከቱት ደሞ.....ቁርአን የወረደበት ልዩ ወር.... ከወራቶቹ ሁሉ በላጭ ወር ሆነልን...
إنا أنزلناه في ليلة القدر ❤️
ለይለቱን ቀድርን ደሞ እይዋት.... ቁርአን በዛች በተከበረች ለሊት ወረደች.....
ከለሊቶቹ ሁሉ በላጭ ለሊት ሆነችልን🥰
የአንድ ሺህ ወርን ስራ ያህል ምታስተካከልልን የተከበረች ለሊት ሆነችልን..💜

ፈወላሂ ይህ ቁርአን በአንድ ባሪያው ልብ ላይ ከሰረፀ ከሰዎች ሁሉ በላጭ ይሆናል...

ከዕብ ኢብኑ ማሊክ ....
"وَالسَّابِقُونَ السَّابِقُون أُولَئِكَ الْمُقَرَّبُونَ‏"
የምትለዋን አያ ሲፈስር....
هُم أهل القرآن
.... ይለናል....
❤️
ኑ ተሽቀዳድመሙ....እኔ ዘንድ ቅረቡ ....ወደኔ ተጣሩ....ወሏሂ ልዩ ኢላህ እኮ ነው ያለን....🥰❤️

አሁን እኛ ቢያንስ ቁርአንን እናነባለን....እናዳምጣለን.....በቻልነው አቅም እናስተነትናለን....
أَمْ عَلى قُلُوبٍ أَقْفالُها
ከተባሉት ብንሆን ምን ይውጠን ነበር ....
ከቁርአን ልባችን የታተመ ቢሆን ምን እንሆን ነበር...

“ምስጋና ለአላህ የተገባዉ ይሁን....
ቁርአንንም ልክ እንደ ረመዳን በአመት አንዴ ብቻ ብናገኘው ምን እንሆን ነበር....
የተወሰነ ጊዜና ቦታ ቢመደብለት እንዴት እንንሆን ነበር....አልሀምዱሊላህ.....እኛ ባሪያዎቹ በተጨነቅን....ዱንያ በጠበበችን ጊዜ አንስተን ምናነበው ላደረገን ጌታ  ምስጋና ይገባው....

ወላህ ቁርኣን የወረደልን  ድምፅ በማሰማት ባማረ ጉሮሮ ማንበብ፣እና ስናዳምጠውም በተመስጦ ልናዳምጠው ብቻ አይደለም....
ነገር ግን የሞተውን ህሊናችንን ለመቀስቀስ....የደነደነውን ልባችንን ለማስባነን.... እና ውስጣችንን ለማረጋጋትም ጭምር ነው ።

በእያንዳንዷ ቁርአን አያ ውስጥ ምክር.... በእያንዳንዱ ሀዘን ውስጥ መጽናኛ...እና  እና በእያንዳንዱ ምሳሌ ውስጥ ትምህርት አለ .... አላህ በተደቡር ከሚያነቡት ቀሊል ኢባዶቹ ያርገን ! 🤲

@ https://t.me/Xuqal
ነገ የቂያማ ቀን ሰዎች በሀገራቸው ባንዲራዎች ስር አይሰበሰቡም ፤ ይልቁንም ይከተሉት በነበረው እምነት ስር ይሰበሰባሉ።

  " ነገ የቂያም ቀን ሲሆን ተጣሪ ይጣራል " ሁሉም ኡማ ታመልካት በነበረችው ስር ትሰብስብ " ይባላል።  ቡኻሪና ሙስሊም

በዘራቸው በከለራቸው በአህጉራቸው አይቀሰቀሱም።

" መጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ ሆናችሁ የሰጠናችሁን ሁሉ በጀርባዎቻችሁ ኃላ የተዋችሁ ስትሆኑ ለየብቻችሁ ስትሆኑ በእርግጥ ወደኛ መጣችሁን " አል'አንዓም 94

ዱንያ ላይ ደሀን በመፀየፍ ሀብታም ከሀብታም እንደሚሰበሰበውም አኺራ ላይ አይሰባሰቡም።

" ገንዘቤ ከእኔ አላብቃቃኝ ( አልጠቀመኝ) ፤ ሀይሌ ከእኔ ላይ ጠፋ ይላል" አል'ሐቃ 28-29

ያን ቀን የጥሩ አንደበት ባለቤት መሆን ወይም ንግግር የማይገራለት መሆን ለውጥ ወይም ልዩነት የለውም።

  " ያች ቀን ስትመጣ ሁሏም ነፍስ በእሱ ፈቃድ እንጅ አትናገርም " ሁድ 105

 ብቻ ያኔ የተውሂድ ሰዎች ሲልቁና ሲከብሩ የሽርክና የኩርፍ ባለቤቶች ያፍራሉ።

@ https://t.me/Xuqal
(يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي)
" «ዋ እኔ! ምነው ለሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል ፡፡"
[ፈጅር 24]
እስራኤል ኢስፋሀን የሚገኘውን የኢራን የጦር ሰፈር ለማጥቃት የላከቻቼው ድሮኖች በኢራን አየር መከላከያ በቀላሉ ተመቶ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ ተጥለዋል ። ኢራን የአየር ክልሏ የሚጠብቁ ፀረሚሳኤል ሚሳኤሎችን በተጠንቁቅ አቁማለች ።

@ https://t.me/Xuqal
ሰበር
እስራኤል :- አፀፋዊ ጥቃት በኢራን ኢስፋሃን ላይ ፈፀመች

ነገርግን የኢራን ጄኔራል ስለ ጥቃቱ

"በኢስፋሃንም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ምንም አይነት የአየር ጥቃት አልደረሰም እስራኤል ኳድኮፕተር ድሮኖችን በማብረር እና ጥቃት ለማድረስ ያልተሳካ እና አሳፋሪ ሙከራ አድርጋ ሁሉም በአየር መቃወሚያ ተመተዋል"
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ🖤
“ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሰደቃ ይሆንለታል”

ረሱል ﷺ
"የተቅዋ ምልክት ምን እንደሆነ ታቃላቹ? ሙዕሚን ሀራምን መመገብ(መፍጨት) አይችልም ይሄ ወሳኝ ጉዳይ ነው አማኝ ለዒባዳ የተገነባ ሰውነቱን መመገብ ያለበት በሀላል ብቻ ነው"

ሸይኽ ሙሃመድ ሰዐድ ከንደህለቪ