Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
474 subscribers
3.13K photos
208 videos
46 files
2.15K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ኢብኑል-ቀይም "በዳኢዕ አልፈዋኢድ" በተሰኘው ኪታባቸው ከኢማም ኢብኑ ዐቂል የተያዘ ወርቃማ ንግግርን አስፍረዋል:-
"አንድ ሰው "የነቢዩ አካል ያረፈበት ስፍራ(ሑጅራህ) ይበልጣል ወይንስ ከዕባ? ሲል ጠየቀኝ።እኔም እንዲህ መለስኩ:-
"በጥያቄህ ለማወዳደር የፈለከው ካዕባን እንዲሁ ከቀብራቸው ስፍራ(ሑጅራ) ጋር ከሆነ ካዕባ ይበልጣል።ነገር ግን በሑጅራው የእሳቸውﷺ አካል እያለ ከሆነ ግን በፍፁም ወላህ።ዐርሽና ተሸካሚዎቹ፤አደም የኖሩባት ኤደን ጀነት፤ተሽካርካሪ ፈለኮችም ጭምር ከሑጅራው ጋር አይወዳደሩም።ምክኒያቱም በሑጅራው ከፍጥረተ ዓለሙ ጋር ቢለካ የሚመዝን አካል አርፏል።"

عليه افضل الصلاه والسلام اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى اله وصحبه اجمعين

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Video
ቁርአን ለሰይዳችንﷺ ክብርና ልቅና ለመሳል በሚከብድ መልኩ የተለየ ቦታ ሰጥቶ እናገኛለን።ይህንም በአንድ ታሪካዊ ምሳሌ እንግለፀው:-

ሰይዳችንﷺ ማር በጣም ይወዱ ነበር።በለት ተለት ተግባራቸው ከሚፈፅሟቸው ተግባሮች አንዱ ከዐስር ሰላት በኃላ ባለቤቶቻቸውን እየተዟዟሩ መዘየር ነበር።ልክ ሲመሽም ወደ አንዷ ባለቤታቸው በመሄድ ያድራሉ።

ታዲያ የምዕምናን እናት የሆኑት ዓኢሻህ እና ሐፍሳህ አንድን ነገር ያስተውላሉ።ሰይዳችንﷺ ከዐስር ሰላት በኃላ እየተዟዟሩ ሲዘይሯቸው ከሌሎቹ በተለየ መልኩ እናታችን ዘይነብ ቤት ይቆዩ ነበር።ሲያጣሩም ዘይነብ ጋር ሲቀመጡ እናታችን ዘይነብ ሁሌ ማር እንደምትሰጣቸው አወቁ።የዚህ ጊዜም በጋራ አንድ ውጥን ወጠኑ።ሁለታቸውም ቤት ሲመጡ "መጋፊር" የተሰኘ ጣፋጭና ጠረኑ መጥፎ የሆነን ፈሳሽ የሚያወጣ አትክልት እንደበሉ ለመንገር ተስማሙ።
ሰይዳችንﷺ የሐፍሳና የዓኢሻህ ቤት በገቡበት ሰዓት ሁለቱም "የመጋፊር" አትክልት እንደበላ ሰው አይነት ጠረን እንደተሰማቸው ገለፁ።
ሰይዳችንምﷺ:-"አይደለም! ዘይነብ ማር አጠጥታኝ ነው።"ሲሉ ገለፁ።ነገር ግን ነገሩ ከአንድም ሁለት ሰው ስላነሳው ጥርጣሬ ገባቸው።
በቀጣዩ ቀንም ዘይነብ ቢንቱ ጀሐሽ ቤት ከገቡ በኃላ ማር እንደማይበሉ በመግለፅ ራሳቸውን ቆጠቡ።

ይህ ክስተት ከሴቶች ተፈጥሯዊ የቅናት ባህሪ አንፃር ሲታይ ተራ ነገር ነው።በሺህ ቤቶችም የሚከሰት የተለመደ ተግባር ነው።ነገር ግን ቁርአን ይህን ጉዳይ እንደ ተራ ነገር አልተወውም።ይህ እና መሰል ተግባር ከሰይዳችንﷺ  ጋር ፈፅሞ መደረግ የሌለበት መሆኑን አጥብቆ ገለፀ።የምዕምናን እናት የሆኑትን ዓኢሻህና ሐፍሳህን የሚወቅስ አንቀፆችም ወረዱ።በአንቀፆቹም ከዚህ ተግባራቸው የማይመለሱ ከሆነ አሏህ፣ጂብሪል፣ሌሎች መልአክት እንዲሁም ደጋግ ምዕመናን ረዳቱ ከሆኑት ሰው ጋር ፀብ እንደገቡ ገለፀ።

إِن تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ

ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና (ትስማማላችሁ)፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡

ይህን ክስተት በደምብ አስተውል።የሁሉ በቂ የሆነው የፍጡራን ሁሉ አምላክ የሆነው አሏህ፤እንዲሁም የመልአክት አለቃ የሆነው ጂብሪልና ደጋግ የአሏህ ባሪያዎች በአንድ ጎን፤ዓኢሻህ እና ሐፍሳህ ደግሞ በሌላ ጎን እንደሚያደርግ የተገለፀው ይህ ክስተት በብዙሐን ቤቶች የሚከሰትና እንደተራ የሚታይ ክስተት ነው።

ይህ ጥብቅና ዛቻን ያዘለ መለኮታዊ መልእክት የርሳቸው ክብርና ልቅና ምን ያክል የከበደ እንደሆነ የሚገልፅ ነው።የሳቸው ስብእና ድምበር ለማድረግ በሚከብድ መልኩ እጅጉን የተለየ መሆኑ በዚህ አንቀፅ ይታያል።ለርሳቸው ክብር የሰማያት ግርዶሽ ተገልጦ ጅብሪልን ያንቀሳቀሰና እስከ እለተ ትንሳኤ ድረስ የሚነበብን አናቅፅት ወርደዋል።ትንሽ አድርገን ያየናት "የማር ጠብታ" ይህን ከፈጠረ፤የእሳቸውን ትዕዛዝ የሚያጣጥል፤ክበራቸውን የሚዳፈር እንዲሁም አባትና እናቱ ቢገለፁበት በሚከፋው እጅግ የወረደ ቃላት የሚገልፅ ሰው ቦታው የት ይሆን?

ኢማም አዝ-ዘመኽሸሪይ አንቀፁን ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ።
" ኃያሉ አምላካችን አሏህ ብቻውን በቂ ከመሆኑ ጋር ከርሱ በኃላ፤ጂብሪልና ደጋግ አማኞች እንዲሁም  የቁጥራቸው ብዛት፤ሰማያትን ያጣበቡ መልአክት እርሱን በጠላ ሰው ላይ አንድ ሆነዋል።ታዲያ ይህ ሁሉ ረዳት ያለው ሰው የሁለት እንስቶች በሐሳብ ማበር ምን ሊያደርገው ይችላል?"

محمد بشر وليس كالبشر
بل هو ياقوتة والناس كالحجر

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ጥሩ የሩሕ ጓደኛ መፈለግ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ጥሩ ጓደኛ መሆን ደግሞ ግዴታ ነው።
"ለወላጆች በጎ መዋል ትላልቅ ወንጀሎችን ያስምራል"

ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀንበል ቀደሰላሁ ሩሁሁ
"እውቀት ሁሉም ሊያገኘው ማይችል የአላህ ስጦታ ነው "
ኢማሙ አህመድ
"በድህነት ላይ ሰብር ማረግ ታላላቆች እንጂ ማያገኙዋት ደረጃ ነች"

ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀንበል
"በሰደቃ ላይ መመፃደቅ ሀራም ነው
ምንዳውንም ያበላሻል"

ኢብኑ ነቂብ አል ሻፍዒይ ረሂመሁሏህ
وَمَا تَدۡرِی نَفۡسُۢ بِأَیِّ أَرۡضࣲ تَمُوتُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِیمٌ خَبِیرُۢ


ማንኛይቱ ነፍስም በየትኛው ምድር እንደምትሞት አታውቅም፡፡ {ቁርአን)

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
فَإِن تَنَـٰزَعۡتُمۡ فِی شَیۡءࣲ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمۡ تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلۡیَوۡمِ ٱلۡـَٔاخِرِۚ ذَ ٰ⁠لِكَ خَیۡرࣱ وَأَحۡسَنُ تَأۡوِیلًا }

በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
"ዑመር ሆይ ይች ቀናት ብቻ ነች ታልፋለች አትዘን"

አቡ ደርዳእ ረ.ዐ

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
Photo
ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
10 ኢትዮጵያዊያን ሐጃጆች ሕይታቸው አለፈ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ውስጥ በድምሩ 10 ሐጃጆች ሕይታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ አሺቢ ተናገሩ።

አሥሩ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሙሉ በመካ፣ መስጂደል ሀረም ላይ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው የቀብር ሥርዓታቸው እንደተፈፀመ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ ተናግረዋል።

የአምስቱ ሐጃጆች ሕይወት የሐጅ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት  ማለፉን ያስታወሱት ሸይኽ አል-መርዲ የሌሎቹ ሕይወት ያለፈው በአረፋ ወቅት መኾኑን ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል በተለይ ሁለቱ እናቶች በሐጅ ሥርዓተ ክንዋኔ ወቅት ጠፍተው ከነበሩት አምስት ሰዎች መካከል መኾናቸውና 'ሚና' ላይ ሕይወታቸው ማለፉ እንደታወቀ ተነግሯል።

በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሐጃጆችን ደኅንነት ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተለው ኤጀንሲ፣ ስድስቱ ሐጃጆች በድንገተኛ ህመም፣ ሁለቱ በክፍላቸው ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲኾን፣ አንድ ሐጃጅ በመኪና አደጋ፣ አንድ በካንሰር፣ እንዲሁም ሌላ አንድ ሐጃጅ በህመም ምክንያት እንደሞቱ የሆስፒታሉን ውጤት አያይዞ ይፋዊ መረጃ ሰጥቷል።

የሐጃጆቹ  የቀብር ሥርዓት የተፈፀመው በሀገሪቱ ደንብ መሠረት በሦስት ሰዓታት ውስጥ የሟች ቤተሰብ፣ የቅርብ ዘመድ አልያም ምስክር የሚኾን ጎረቤት በተገኘበት እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።

በዚሁ መሠረት የዘጠኙ ሟቾች ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በዚሁ ደንብ መሠረት ሲኾን፣ ሚና ላይ ሞተው ከተገኙት የአንዷ እህት በተባለው ጊዜ ውስጥ መገኘት ባለመቻሏ  ሕይወቷ ማለፉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል መርዲ አብዱላሂ፣ የ1445 ዓ.ሒ. የአርረህማን እንግዶች ሆነው መጥተው ሞት ቢቀድማቸውም ኒያቸው ከፍ ያለ በመኾኑ፣ ሞታቸውን የሸሂድ (የሰማዕት) ደረጃ የሚያደርሱት አሉ ብለዋል።

"ሞት የማይቀር ተፈጥሯዊ ሕግ በመኾኑ፣ በእንዲህ ዓይነት ሂደት መሞት ትልቅ ፀጋ ነው" ብለዋል ሸይኽ አል መርዲ።

"ሀረም ላይ የዓለም ሙስሊም የአርረህማን እንግዶች ሆነው በመጡበት አጋጣሚ፣ ጀናዛቸው ላይ ተሰግዶ መካ ላይ መቀበር ትልቅ ፀጋ በመሆኑ፣ ቤተሰቦቻቸው ሊሶብሩ እና ሊፅናኑ ይገባል" ብለዋል።

via mujib

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
.

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ قُل لِّأَزۡوَ ٰ⁠جِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاۤءِ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ یُدۡنِینَ عَلَیۡهِنَّ مِن جَلَـٰبِیبِهِنَّۚ ذَ ٰ⁠لِكَ أَدۡنَىٰۤ أَن یُعۡرَفۡنَ فَلَا یُؤۡذَیۡنَۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمࣰا }
[Surah Al-Aḥzāb: 59]

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ሰላምህን አላህዬ 🤲
ቤተሰባችንን፣ አካባቢያችንን ፣ አገራችንን ፣ ዓለማችንን ሁሉ ሰላም አድርግ። ጥላቻ፣ መጨካከንና መገፋፋትን ከመካከላችን አስወግድ። 🤲
ሰላማችሁ ይብዛ።

ቲስበሑ 😍

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal