Bilaluna Edris
544 subscribers
3.34K photos
275 videos
50 files
2.29K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ፦

'' ዑመር ሆይ፣ የሮምና የፋርስ ንጉሶች በዚህ ዓለም ይደሰቱ! ለኛ ግን የቀጣዩ ዓለም ደስታ በቂያችን ነው! ይህ አለም ለእኔ ከቶ ምን ያደርግልኛል?! የኔና የዚህች አለም ግንኙነት እንደ በጋ መንገደኛ ነው! ከዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ መልሶ እንደሚጓዘው።''

አለይሂ አፍደሉ ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ አለይህ

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
عليه افضل الصلاه والسلام اللهم صلي وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى اله وصحبه اجمعين

የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
መዳረሻዬ አንተ ከሆንክ… መንገዱ እንዴት ያለ ውብ ነው! ደጃፍህ እስክደርስ ክብደቱ ቢያንገዳግደኝም፣ የነፍስያ ጉትጎታ ቢያደናቅፈኝም ፍላጎቴ አንተ ነህና በመንገድህ እንድበረታ አግዘኝ ኢላሂ!! 🥹 🤲

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
የታሰሩ ነገሮች ሁሉ...አላህ በራህመቱ አንድ ቀን ይፈታቸዋል።
ባዶ እጃችንን ምንም ሳንይዝ ዱንያን ተቀላቀልን ፤ በዱንያም ላይ በሁሉም ነገሮች እና ጉዳዮች ላይ እየታገልን ቆየን ፤ ዱንያን ለቀን ስንሄድ ደግሞ እንደ አመጣጣችን ባዶ ሆነን ዱንያን ለቀን እንሄዳለን ፤ ከዛም በታላቁ ጌታ ፊት ቆመን ስለ ሁሉም ነገር ሂሳብ እንተሳሰባለን።

ጌታችን ሆይ ያማረ ኻቲማን ወፍቀን 🥹 🤲

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
"ዱዓዬ እጣፈንታዬን ለመቀየር በቂ አልነበረም ማለት ነው?" የሚሉ ከርታታ ልቦች አሉ። በህይወት ልዩ መልኮች እንቅፋት የተመቱ ልቦች። በህመም፣ በእዳ፣ በትዳር አለመሳካት፣ በሁኔታዎች መዘበራረቅና ግራመጋባት የሚዋኙ ስሜቶችም እንዲሁ። ምን ያህል ጌትዬን ተለማምጠናል? … ከአለሙ ሁሉ እስኪያስቀድመን፣ ከጠያቂዎች ሁሉ እስኪመርጠን። እርሱ የሚለማመጡትን ይወዳል። የሚወደውን ደግሞ ይመርጣል።

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal
ለ አላህ እንጅ የማይነገሩ ንግግሮች...
ወደ እሱ እንጅ የማይላኩ እሮሮዎች...
በእሱ ፊት እንጅ የማይወርዱ እንባዎች አሉ።.....ለርሱ እያንሾካሾካችሁ ያ......ረብ በሉ

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለፈገግታ

ድሮ ነው አሉ...አንዲት ግብፃዊት አዛውንት በሐጅ ላይ በሚደረገው የጠጠር መወርወር(ጀመራት) ስርዓት ላይ ጠጠር እየወረወሩ:-
"ያዝ አንተ ው*ሻ" ይላሉ።
ይህን ያየ አንድ ወጣት በተረጋጋ ድምፅ:-
"እናቴ እንዲህ መሳደብ አይፈቀድም!" ይላቸዋል።
እናትም ቀበል አድርገው :-"አንተን ይመለከትሃል? ወይስ ዝምድና አላቹህ?"😁

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ በህይወታቸው ለመጀመሪያ ግዜ አፕልን (🍎) ያዩበትን አጋጣሚ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
---------

እኔና የዒልም ጓደኞቼ ሆነን ሸይኽ ዐብድራህማን ኢብን ናስር አሰዕዲ ዘንድ የኢብኑ ረጀብን قواعد الفقهية  እንቀራ ነበር። ኪታቡ ትንሽ ጠጠር ይል ነበር! ቢሆንም  እርሳቸው ዘንድ ይሄንን ኪታብ ለመማር የጀመርነው ብዙ ተማሪዎች ነበርን ግን ከግዜ ወደ ግዜ የተማሪው ቁጥር በጣም እየቀነሰ መጥቶ ሸይኹ ዘንድ እኔ ብቻ እስክቀር ደረስኩ።  አልሃምዱሊላህ ኪታቡን እርሳቸው ዘንድ ጨረስኩት። በጨረስን በንጋታው ሸይኹን ካገኘኋቸው፣ ከዘየርኳቸውና ሰላም ካሉኝ በኋላ  እጃቸውን ወደ ኪሳቸው አስገብተው የሆነ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀውን የፍራፍሬ አይነት ሰጡኝ 🫴🏻 🍎

ያሸይኽ አልኳቸው ምን የሚደረግ ነው? ልጥበሰው? ልቀቅለው አልኳቸው እርሳቸውም "አይ ይሄ ቱፋህ (አፕል) ይባላል ዝም ብለህ ቆርጠህ ተመገበው"አሉኝ ይላሉ


ሁሉንም አላህ ይዘንላቸው፤ ነገም ያቺ ያማረችዋን የጀነት ፍራፍሬ ከሚበሉትና ከምንጯም ከሚጎነጩት ደጋግ ባሮቹ  ያድርጋቸው። አላህ እኛንም የነሱን መልካም ፈለግ ተከታዮች ያድርገን። 🤲

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
ለሰው ልጆች የደስታና የፈገግታ ሰበብ እንጂ ለአንድም ሰው የመከፋትና የማዘን ምንጭ አትሁን! ማስደሰትን እንኳ ባትችል ማንንም ለመጉዳት አታስብ!!
ከአፈር ተፈጥረን ፤ አፈር ላይ ስንረማመድ ኖረን ፤ ከዛ ሁላችንም ከ አፈር በታች እንገባለን። አንደኛው ከሌላኛው በምንም አይበልጠውም። ለአላህ ባለው ፍራቻ እና በመልካም ስራ ብቻ እንጂ።

የቴሌግራም ቻናሌን follow በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal