Bilaluna Edris
543 subscribers
3.35K photos
275 videos
50 files
2.3K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጩኸቴን ቀሙኝ....😂

አሁን ማዘር ምን ማለት ፈልገው ነው? የተናገሩት ነገር ድጋሚ ቢሰሙት ራሳቸው አይገባቸውም....¡ ደሞ ቀጥሎ ያለው ሰው ማዋለድ አልቻልንም መጦሪያ አጣን ልጆች መማር ማጥናት አልቻሉም አላለም? 🥴የጥላቻ ጥግ ድንቁርና ውስጥ የከተተው ሰው ነው!!  #ኢትዮጵያ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

https://t.me/Xuqal
#Ethiopia #IMF

ኢትዮጵያ ከIMF ብድር ለማግኘት የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም ትስማማለች ? ሌላ አማራጭ የለም ?

የምጣኔ ሃብቱ ባለሞያ አቶ ያሬድ ኃይለመስቀል ፦

" devaluation የሚቀር አይመስለኝም። በምን ያህል ደረጃ devalue ይደረጋል የሚለው ጥያቄ ነው እንጂ devalue ሳይደረግ IMF / World Bank ገንዘብ ይሰጣል ብዬ እንደ ራሴ አልገምትም።

አማራጭ ፖሊስ በራሱ መጥፎ አልነበረም። ቅደም ተከተሉን አለማስተካከል ነው ትልቁ ስህተት። ለምሳሌ ከሌሎች መጀመር ይቻል ነበር።

liberalization ሊቀድም ይችል ነበር ከdevaluation ፤ liberalization ሲደረግ አዲስ ካፒታል ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይቻላል።

በዚህ ሂደት ካፒታል / ዶላር ይገኝ ነበር። ይህ ደግሞ የዶላርም ይሁን የሌላ ውጪ አሳሳቢ አይሆንም ነበር። እዳንም መቀነስ ይቻላል። አሁን ግን እዳ ይጨምራል።

ለምሳሌ ፦ የዛሬ 7 ዓመት ለባቡር ወይም ለሌላ የተበደርነው ዶላር ቢኖር መንግሥት ይጠበቅበት የነበረው 22 ብር ቀረጥ ሰብስቦ ወደ 21 ዶላር ቀይሮ መስጠት ነበር አሁን 56 እና 57 ታክስ መሰብሰብ አለበት።

የኑሮው ውድነት ?

ካለንበት ችግር በመነሳት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ቢወሰን በዋጋ ንረት ላይ በኑሮው መወደደ ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከባድ ነው።

ብዙ ነገር imported inflation የሚባለው ነዳጅ 39 ብር ነበር አሁን ከ70 በላይ ሆኗል ፤ ማዳበሪያውም ፣ ስንዴውም ፣ መኪናውም በብዛት 21 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት እቃ ወደ ሀገር ይገባል 3 - 4 ቢሊዮን የሚገመት export ታደርጋለች ይሄ ልዩነት ላይ ያለው 17 ቢሊዮን ብር የሚመጣውን እቃ ዋጋ ሊጨምረው ይችላል። ይሄ በእያንዳንዱ ቦታ ተበታትኖ በየሰዉ ኑሮ ላይ ተፅእኖ ያደርጋል።

inflation አሁን ትንሽ ረገብ አለ ቢባልም ከፍተኛ ነው። እንደገና ከፍ ሊል ይችላል።

ካፒታል ያላቸው ሰዎች ምንም ችግር የለባቸውም። ለምሳሌ ነጋዴ እቃ ቢወደድም ቢረክስም ችግር የለበትም የገዛበት ላይ ጨምሮ ነው የሚሸጠው ምናልባት ብዙ ላይሸጥ ይችላል ያ ሊጎዳው ይችላል።

ቁርጥ ያለ ገቢ ያለው ሰው ሊጎዳ ይችላል። ለምሳሌ የዛሬ 7 ዓመት 22 ሺህ ብር ደመወዝ የሚከፈለው ሰው 1000 ዶላር አካባቢ ነው አሁን ግን 450 ነው የሚያገኘው ስለዚህ ደመወዙ 50% ቅናሽ አድርጓል። በሌላ በኩል የመኖሪያ፣ የምግብ ዋጋ ጨምሯል።

ብዙ አማራጭ ያለ አይመስለኝም ከ devalue አንጻር። ያለውን ብር መቀበል ነው። አልያም ብሩን አልፈልግም ብሎ ሌላ አማራጭ መፈለግ ነው። ወይም የሚባለውን አድርጎ የሚያስከትለውን ችግር መፍትሄ መፈለግ ነው። "

ይህ የምጣኔ ሃብት ባለሞያ አስተያየት የተወሰደው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይገልጻል።

@ https://t.me/Xuqal
Bilaluna Edris
Photo
የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን ሑጃጆች ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ

#Ethiopia |~ መጅሊስ ለተጓዦች ስለ ሐጅ አፈፃፀም የሚሰጠው ሥልጠና በዛሬው እለት ይጀምራል ።

ለ1445 ዓ.ሂ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ተጓዦች በረራ የሚያደርጉበት ቀን ታወቀ። “ሚንበር ቲቪ” ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) የሐጅ እና ዑምራ ዘርፍ እንደሰማው የመጀመሪዎቹ ተጓዦች በረራ የሚከናወነው ግንቦት 13፣ 2016 ነው።

ምክር ቤቱ ለዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ለመላክ በእቅድ የያዘው የምዕመናን ቁጥር መጠን 12 ሺሕ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። “ሚንበር ቲቪ” ከመጅሊስ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው በተያዘው ዓመት ለሐጅ ክንውን ወደ ሳዑዲ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ምዕመናን ቁጥር ከአምናው በ1 ሺሕ 62 ብልጫ ያለው ነው።

መጅሊስ ለጉዞው የመዘገባቸውን ምዕመናን ከዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 22/2016 አንስቶ ሥልጠና መስጠት እንደሚጀምር ታውቋል። ይህ ሥልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ነው።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2016 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። በመላው ዓለም የሚገኙ ወደ 2 ሚሊዮን ገደማ የሚቆጠሩ ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ያመለክታል።

ምንጭ  = ሚንበር ቲቪን
ኢላሂ እኛንም ወፍቀን 🥹 🤲
የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
▪️የኢራኑ ፕሬዝዳንት ራይሲ ከሄልኮፕተር አደጋው ጥቂት ቀደም ብሎ የነበሩበትን የሚያሳይ ቪዲዮ፤ እንዲሁም
    - ከአደጋው በኋላ ለአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የሄልኮፕተር ፍለጋ ስራቸውን አስቸጋሪ ያደረገው የአየር ሁኔታ

#Ethiopia #Raisi
#Iran #Helicoptercrash #SearchOperation
#RescueOperation

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
🇮🇷🇺🇸 የአሜሪካ አየር ኃይል ካርጎ የሆነው C-17 ግዙፍ ወታደራዊ አይሮፕላን ከዓመት በላይ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አዘርባጃን ባኩ በዛሬው ዕለት ማረፉ ተሰምቷል።

  የአሜሪካው ወታደራዊ ካርጎ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ራይሲ የተሳፈረበት ሄሊኮፕተር አዘርባጃንን ከመልቀቁ እና ከተከሰከሰበት ጊዜ ጋር መገጣጠሙ ጥያቄዎችን እየፈጠረ ይገኛል።

#Ethiopia #Raisi
#Iran #Helicoptercrash #SearchOperation
#RescueOperation

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
መጅሊስ በመካ መታወቂያ ማግኘት ያልቻሉ ሁጃጆችን በተመለከተ ምላሽ ሰጠ ።

#Ethiopia |~ መካ ላይ መንቀሳቀስ የሚያስችል መታወቂያ ካርድ ማግኘት ያልቻሉት በግላቸው ሐጅ ለማድረግ የሄዱ ናቸው ሲሉ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ምላሽ ሰጡ።

ሐጅ ለማድረግ ሄደን መንቀሳቀሻ መታወቂያ ካርድ ስላልተሰጠን ከሆቴል መውጣት አልቻልንም በሚል ያቀረቡትን ቅሬታ ተከትሎ ጄይሉ ቲቪ በስልክ ያነጋገራቸው የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም ቤት የሐጅና ሁምራ ዘርፍ ኃላፊ ሐጅ አብድልፈታህ መሐመድ ናስር እንዳሉት ምክንያቶቹ ሁለት እንደሆኑና አንደኛው ሐጅ ለማድረግ በግላቸው የተጓዙ ሁጃጆች ሳውዲ ኤርፖርት ላይ ፖስፖርታቸውን አስቀምጠው ለመግባት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ማንነነታቸው ተለይቶ መታወቂያ ሊዘጋጅላቸው አልቻለም ብለዋል ።

ሌላው በመጅሊስ በኩል የሄዱትም ተመሳሳስ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸው በሳውዲ የሐጅ ስነስርት አስተባባሪዎች በወቅቱ ማድረስ ባለመቻላቸው እንደሆነ ይህኑ ለማስተካከል በስፍራው ያለው የመጅሊስ አስተባባሪ ቡድን ጥረት እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል ።

በዚህ ችግር ውስጥ ያሉ ሁጃጆችን ስለጉዳዩ በግልጽ የሚያስረዳቸውና በፍጥነት መፍትሄ እንዲያገኝ የሚጠይቁት የመጅሊስ አስተባባሪዎች በስፍራው አለመኖራቸውን መረጃው እንደደረሰው እና ምላሽ እንዲሰጡበት ለሐጂ አብዱልፈታህ የጠየቃቸው ጄይሉ ቲቪ በመካ የአስተባባሪዎች የሰው ኃይል እጥረት እንዳለባቸውና በፍጥነት እንደሚያስተካክሉ ቃል ገብተዋል ።

© Jeilumedia.

የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
@ https://t.me/Xuqal
በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ …

#Ethiopia | ሳኡዲ አረቢያ በሐጅ ወቅት የመጀመሪያዉን በሰማይ ላይ ማሽከርከር የአየር ታክሲ በይፋ በዛሬ ዕለት ይፋ አድርጋለች ።
የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናትን አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው የፀሓይ ንዳድ የሞት ዜና

#Ethiopia |~ ሳዑዲ ዐረቢያ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዓት ለመከወን ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ምዕመናንን አስተናግዳ ወደመጡበት መሸኘት ጀምራለች። በምዕመናን ዘንድ የዕድሜ ዘመን ናፍቆት ለሆነው የሐጅ ክንውን የተቀመጡ ቀናት አልፈው ምዕመናን ወደመጡበት መመለስ የጀመሩት ዛሬ ሐሙስ ነው።

የሳዑዲ ባለሥልጣናት ምዕመናን መካን መልቀቅ መጀመራቸውን ይፋ ሲያደርጉ፣ ጎን ጎን እየወጣ የሚገኘው ዜና አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው ይመስላል። ዜናው የሞት ነው፤ በፀሓይ ንዳድ ከምድር ሕይወት የተለዩ ምዕመናን ሞት።

በተለይ የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሲከወን እምብዛም ሽፋን በመስጠት በማይታወቁ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን እየተንሸራሸረ የሚገኘው ዜና፣ በሐጅ ሥነ ሥርዐት ወቅት በሳምንቱ መጀመሪያ ከሃምሳ ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የተመዘገበው ሙቀት ያስከተለው የጤና መቃወስ ቢያንስ የአንድ ሺሕ ምዕመናን ሕይወት ነጥቋል የሚል ነው።

መረጃው ከሲኤንኤን እስከ ሲቢኤስ፤ ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እስከ ሬውተርስ እየተዘዋወረ ይገኛል። ማክሰኞ እለት ቀድሞ 550 ምዕመናን ሞተዋል ያለው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ዛሬ ሐሙስ አመሻሽ የሟቾቹን አሐዝ 1 ሺሕ 81 አድርሶታል። የዜና ወኪሉ ከሟቾቹ ውስጥ ከፍተኛው ቁጥር የግብጻዊያን ነው ያለ ሲሆን፣ የተመዘገበው ቁጥር 658 ነው።

ከእነዚህ ውስጥ 630 ምዕመናን በሐጅ ክንውኑ ላይ ሲሳተፉ የነበረው ለሥነ ሥርዐቱ በተዘጋጀው ቪዛ ሳይሆን በሌላ ዐይነት ቪዛ ቅድስቲቱ መካ ከተማ ተገኝተው ነው። የዜና ወኪሉ በሳዑዲ ባለሥልጣናት ሕገ ወጥ በሚል የተለዩት እነዚህ ምዕመናን፣ ከፖሊስ ለመደበቅ በሚያደርጉት ጥረት የአየር ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸው ሥፍራዎች መግባት ስለማይችሉ ለፀሓይ ንዳድ ተጋላጭ ሆነዋል ሲል ለኅልፈታቸው ሰበብ መላ ምት አስቀምጧል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው፣ እስካሁን የሞቱት ከአንድ ሺሕ በላይ ምዕመናን ከአስር ሀገራት የተውጣጡ መሆናቸውን ዲፕሎማቶች እንደነገሩት ነው የጠቀሰው። የዜና ወኪሉ ይህን ቢልም ምዕመናን ራሳቸውን ከፀሓይ ንዳድ ለመከላከል አዘውትረው ዣንጥላ እንዲጠቀሙ ሲመክሩ የቆዩ የሳዑዲ ዐረቢያ ባለሥልጣናት የየትኛውም ሀገር ዜጋ ስለመሞቱ ማረጋገጫ ሲሰጡ አልታዩም።

ሬውተርስ የዜና ወኪል በአንፃሩ አንድ የሳዑዲ ጤና ሚኒስቴር ኃላፊ ሰኞ እለት በምዕመናን ላይ እስካሁን ድረስ ከሌላ ጊዜው የተለየ የሞት ምጣኔ እንዳልተመዘገበ ነግረውኛል ብሎ ዘግቦ ነበር። ኃላፊው የሳዑዲ ጤና ባለሞያዎች በፀሓይ ንዳድ ለተመቱ 2 ሺሕ 700 ምዕመናን የሕክምና ድጋፍ መስጠታቸውን እንደገለፁም አስፍሯል።

የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን የሑጃጅን የሞት ዜና ሲሸፍኑ በዋሉበት ዛሬ ሐሙስ፣ 12 ሺሕ ምዕመናንን የላከው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በተቃራኒው ለሐጅ ክንውን ከተጓዙ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በፀሓዩ ንዳድ ሳቢያ ሕይወቱ ያለፈ ምዕመን አለመኖሩን አስታውቋል፡፡ ምክር ቤቱ በንዳዱ የሞተ እንደሌለ ቢጠቅስም አምስት ኢትዮጵያውያን በሌላ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ግን በመረጃው አሥፍሯል፡፡ ከምዕመናኑ መካከል አንደኛው የሞቱት በተሽከርካሪ አደጋ መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ፣ ለቀሪዎቹ የሞት መንስዔ ብሎ የጠቀሰው ሕመም ነው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሟቾቹ ኢትዮጵያውያን ሕመም ድንገተኛ ይሁን አልያም ቀድሞ የተለየ የጠቀሰው ነገር የለም። (ሚንበር ቲቪ)

የፎቶ ምንጭ፡ ኤኤፍፒ
© Minber TV

ለተጨማሪ መረጃ ፣ የቴሌግራም ቻናሌን follow ያድርጉ
@ https://t.me/Xuqal