Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)
502 subscribers
3.25K photos
232 videos
46 files
2.18K links
♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ)

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ
                 ቁርኣን[ 3:104 ]


መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0
Download Telegram
ኑ! በጋራ በመሆን 500 ለሚሆኑ ወላጆቻቸው  በሞት ላጡ ህፃናት  የኢል ልብስ ለማልበስ የቻልንውን እንለግስ

አፋር/ሠመራ-ሎግያ
“ከመልካም ስራዎች በላጩ ተግባር በሙእሚን ወንድምህ ልቦና ውስጥ ደስታን ማስገባት ነው”
ረሱል ﷺ

https://t.me/Xuqal
﴿قُلْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَرِيبًا﴾

﴿وَنَرَاهُ قَرِيبًا﴾
ለምንድነው ሱሁር በረካ የሆነችው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1 ሱሁር መብላት መታዘዝ ነው, ሱናንም መከተል ነች
2 አህለል ኪታቦችንም መፃረር ነች
3 በኢባዳ ጠንካራ እንድትሆን ታደርጋለች
4 ለፆም ነሻጣን ትጨምራለች
5 ጾምን የመጨመር ፍላጎትን ስለሆነች
6 በረሀብ ምክንያት የሚመጣውን መጥፎ ባህሪ  ወይም ጉዳት ታስወግዳለች
7 በሱሁር ወቅት ላይ ለሰደቃ ሰበብ ልትሆን ትችላለችና
8 በሱሁር ወቅት ላይ ለዚክር(አላህን ሱብሀነ ወተዓላ) ለማስታወስ ሰበብ ትሆናለችና
9 ለፆም ኒያ ሳይነይት ለተዘናጋ ሰው እሷ ሱሁር ሰበብ ትሆናለችና
ሸርሁ ሙስሊም, ፈትሁ አልባሪ ኢብኑ ሀጀር አል አስቀላኒ
ሱሁር የሚበሉ ሰዎች ይህን ሁሉ ጥቅም ሲያገኙ የማይበሉ ሰዎች ይህ ሁሉ ጥቅም ያመልጣቸዋል ቢከብደንም አልበላም ቢለንም ቢያንስ ውሀ እንጠጣ ሱና ሀይ ለማድረግ

ሱሁር የማትበሉ መነሳት ይከብደኛል የምትሉ ምን ትላላቹ???

https://t.me/Xuqal
ረመዷን -11
***

የረመዷንን አሥር ቀን አነሳንለት፡፡ የወሩ አንድ ሦስተኛ ላይመለስ ሄደ፡፡ በምንም ይሂድ በምን ብቻ በቃ ሄደ፡፡
ያሳለፍናቸዉን የፆምና የዒባዳ ቀናት አላህ ይቀበለን፡፡ ያጎደልናቸዉን ነገሮች የሩሓችን ጌታ አምላካችን አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ይሙላለን፡፡ ማን ያላጎደለ አለ የኔ ጌታ!!!፡፡ በቀሩት ቀናት በተሻለ ሁኔታ ከሚበረቱት ያድርገን፡፡ 🤲

ረመዷን መልካም ነገር የተባለን ነገር ሁሉ በመሥራት፣ በዒባዳ በመበርታት ምንዳ የሚሸመትበት ገበያ ነው፡፡ በዚህ ገበያ የጌታዬ ረሕመት ሰፊ ነው፤ ምህረቱም በጣም ቅርብ ነው፡፡  ይህ ገበያ ለሚቀጥሉት ሀያ ወይም አሥራ ዘጠኝ ቀናትም ክፍት ነው፡፡ አላህ ልቦና ይስጠን፡፡ ነቅተው ከሚጠቀሙበትም ያድርገን፡፡
ያ ረብ!!🤲

https://t.me/Xuqal
አደራ ስንፍና እና መሰላቸት እንዳያጠቁህ! ዒባዳ ከተባለ ነገር ሁሉ የመራቅህ መንስኤ አትጠራጠር ስንፍናህ እና መሰላቸትህ ናቸው።
ሸይኽ ሰዒድ አል ከመሊ
«ድሃው ወንድምህ ሰደቃውን በመቀበል አኼራህን ሲያሳምረልህ አንተ ሰደቃውን በመስጠት ዱንያውን ነው ያስተካከልከው፡፡ ስለዚህ እርሱ ላንተ ባለውለታህ ነው፡፡»

#ኡስታዝ_በድሩ_ሁሴን

https://t.me/Xuqal
ፈታዋ ኑሩን ዐለ ደርብ ሙጀለድ 7 ኪታቡ ሲየም
.
ጠያቂ፦ ፃመኛ ሙዐዚኑ ላኢላሀ ኢለላህ እስከሚል ድረስ መብላት ይችላል ሲባል እንሰማለን ይሄ ትክክል ነው ወይ?
.
ሸይኽ ዑሰይሚን ቀደሰሏሁ ሩሀሁ፦ አይደለም ይሄ ትክክል አይደለም እንደውም ሙዐዚኑ ፈጅር ሳይወጣ አዛን እንደማይል ካወቅን አዛን ሲል ከመብላት ከመጠጣት መቆጠብ አለብን.... ወሏሁ አዕለም

https://t.me/Xuqal
በጀነት አትክልቶች ውስጥ 
እየተዝናናህ  ድንገት… ……
ረሱልን (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)
ፈገግ ብለው እየጠበቁህ ብታገኛቸው? ...አስበኸዋል

ኢላሃና ያንን እድል ከሚያገኙት መካከል አድርገን ፤ በዱንያ ላይ ያላየነውን ፊታቸውን በጀነት የምናየው አድርገን 🥹 🤲

{ فداك أبي و أمي و روحي يا رسول الله
اللهم أني أسألك أن تجمعنا برسول الله في الجنه
فنحن أمته نحبه كما يحبنا و نفديه بأرواحنا و بكل ما نملك
يارب صلِّ وسلم وزد وبارك على الحبيب المصطفى محمد صل الله عليه وسلّم تسليما كثيراً 💚 }

https://t.me/Xuqal
ረሱሉል አሚን عليه افضل صلوات الله وسلامه عليه እንዲህ አሉ

❝ ከ ሌሊቱ ክፍል አንድ ሶስተኛው ሲቀር በሁሉም ሌሊቶች ላይ ጌታችን አላህ  ﷻ ሰጥቶ ማያልቅበት ሀያሉ ጌታችን ሀጃችንን ሊሰማ ወደ ቅርቡ ሰማይ ይወርዳል... ከዛም እጆቹን ዘርግቶ..

"ማን ነው ሚጠይቀኝ ምሰጠው ፣ ሚለምነኝ
ምቀበለው ፣ ከልብ ተፀፅቶ ምህረቴን ሚፈልግስ ማነው?" ብሎ ይጠይቃል ❞

ወንጀልህ አውስተህ ድክመትህን ጠቅሰህ ተናንሰህ ተሰብረህ ምህረቱን ጠይቀው 

ረመዷን ላይ በጣም ትኩረት ሰጥተን ማዘውተርና ማብዛት ካለብን ዒባዳዎች አንዱ ይህ ዱአ ነው (አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ቸር የሆንክ ጌታ ነህ!! ይቅር ማለትንም ትወዳለህ!! ወንጀሌን ሁሉ ይቅር በለኝ)

https://t.me/Xuqal
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጩኸቴን ቀሙኝ....😂

አሁን ማዘር ምን ማለት ፈልገው ነው? የተናገሩት ነገር ድጋሚ ቢሰሙት ራሳቸው አይገባቸውም....¡ ደሞ ቀጥሎ ያለው ሰው ማዋለድ አልቻልንም መጦሪያ አጣን ልጆች መማር ማጥናት አልቻሉም አላለም? 🥴የጥላቻ ጥግ ድንቁርና ውስጥ የከተተው ሰው ነው!!  #ኢትዮጵያ #Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

https://t.me/Xuqal
ምግብ ኃይልና አቅም የሚሰጠው በብዛቱ ሳይሆን በበረካው ነው።🙌

ሱሁር ደርሷል ተሳሀሩ ለማለት ያህል ነው። አህባቢ 🤗 🥰

https://t.me/Xuqal
ረመዷን -12
***

ረመዷን የቁርኣን ወር ነው ይባላል፡፡ ቁርኣን የወረደበት ወርም ነው፡፡ በቁርኣን በወረደበት ወር ቁርኣን መቅራት ማብዛት ትልቅ ምንዳ አለው፡፡

ቁርኣን በረካ አለው፡፡ ቁርኣን የገባበት ነገር ሁሉ ረድኤት አለው፡፡ ቁርኣን ወደ አንድ ነገር የገባ እንደሆነ ጨለማው ብርሃን ይሆናል፣  ጥቂቱ ይበዛል፣ ትንሹ ይተልቃል ፣ ጠባቡ ይሰፋል፡፡

በረመዷን የቁርኣንን በረከት አብዝታችሁ ተቋደሱ፡፡ ማንበብ ባትችሉም ከፍታችሁ እዩት፡፡ ትረካላችሁ፣  ታድጋላችሁ፣ ትለወጣላችሁ፡፡ ቀደምት ደጋግ የአላህ ባሮች ሌሎች ትምህርቶችን በመተው ቁርኣን ላይ ብቻ ያተኩሩ ነበር፡፡ የቁርኣን ሰዎች አላህ ሰዎች ናቸው፡፡ አላህ ወዳጆች ናቸው፡፡ ቁርኣንን የሚወዱትን አላህ ይወዳል፡፡ 

https://t.me/Xuqal