#የህይወት_ማዕዶት!
📝እግዚአብሄር አሁንም ይዞሃል📝
ግንቦት 22/2012
ቅዳሜ
@ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)
🖊እንደ ኢዮብ ሆነንም ደርሶብንም አያውቅም ! ግን ከኢዮብ በላይ የመረሳትና የመተው ስሜት የሚሰማን ነገር በጣም ግራ ይገባኛል።
ኢዮብ
- ተፈጥሮ ከድቶታል
- ሞት ቤቱ ላይ ተደራርቦበታል
- ጤንነት ከድቶታል
- ሚስቱ አፅናኝ ከመሆን አምላኩን እንዲረግም ጎትጓች ሆናለች። (ለእርሷ አምላክ የሙላት ጊዜ ተመላኪ የችግር ጊዜ ተረጋሚ አድርጋው አስባለች።)
- ወዳጅ ተብዬዎች ቁስሉ ላይ እንጨት ለመስደድ የማይፈሩ ደፋሮች ነበሩ።
🖊ቆይ አንተ/ቺ ይሄ ሁሉ ደርሶብሽ ይሆን ? አንዱ ወይ ሁለቱ ደርሶብህ በቃ አለቀልኝ ፣ እግዚአብሔር ረሳኝ ተወኝ የሚል መዝሙር ግጥምና ዜማ ሰርተህ ለምን እንደምትዘምር አላውቅም።
ጌታ አሁን በዚህ መልዕክት እየተናገረህ ነው። መቼም አልተውህም እያለህ ነው።
📖የእምነትህ ደረጃ የሚያሳድጉ አስቸጋሪ ሆኔታዎች አሉ። "ከፊታችን የተሰለፉ ረጅም ተራራዎች፣ የሚዳሰሱ ጨለማዎች፣ ሁሉ ገሸሽ ብሎ ብቻችንን የሆንን ሲሰማን ፣ ያለን በዜሮ ሲባዛ፣ ህይወት ምስቅልቅል ስትልና እግዚአብሄርን ፍፁም ልናገኘው እማንችልበት በሚመስለን ጊዜ እምነታችን ይፈተናል።"
🧑💻በሰላም በደስታ እና በምቾት ቀን ማን ይክዳል?
ኢዮብ የደርሰበትን ነገር ደግሜ ላስታውስህ ቤተሰቡን፣ ስራውን፣ ጤናውን፣ ልጆቹን ያለውን ነገር ሁሉ በአንድ ቀን ውስጥ አጣ። አንተ በአንድ ቀን ምን አጣህ ? ምንስ ተሰወረብህ ?
🧑💻እንደዚህ እንደመፃፍ እና እንደመስበክ ቀላል መሰለህ ? አይደለም። ከሙላት ከድሎት ፣ ደስ ከሚል ቤተሰብነት ፣ ከከበረ ብልፅግና ፣ ከነበረበት ከፍታ የነጋው ቀን እስኪመሽ ወደቀ ፣ ተከሰከሰ ፣ ተፈረካከሰ ፣ መኖርን ሳይሆንን ሞት አሁን ካለሁበት ይሻላል የሚልበት ሁኔታ ውስጥ ገባ።
🤦ይሄ ሲደንቀን 37 ምዕራፍ እና ለማይቆጠሩ ቀናት እግዚአብሄር ዝም አለው። ተናጋሪዎች በዝተው መካሪነን ባይ አቁሳዮች ፣ ያልሰራውን ኃጢያት ሰርቺያለሁ እንዲል እያስገደዱት ነው ፣ ኃጢያትህ ነው እንዲ አይነት መዓት ያዘነበብህ ብለው ሰማይ ስለ እርሱ የሚያወራውን የማያውቁ የሁኔታው ተንታኞች ፣ ኮሜንታተሮች የኢዮብን ስቃይ ሲያበዙት አሁንም ሰማይ ዝም ብሏል። ያማል ፣ በጣም ያስለቅሳል ፣ ልብን ይሰብራል
- ያልገባው ሁኔታ በህይወትህ እየሆነ ?
- ሰዎች ስለ እርሱ ብዙ እያሉ ሰማይ ዝም ብሎት ኢዮብዬ ያመሰግናል።
🧏♂ኢዮብን እንምሰለው ?
#1. ባለማጉረምረም ይልቅ በማመስገን!
" ኢዮብም ተነሣ .... የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን። " ኢዮብ 1፥20፦21
🧎ችግሩ በተከሰተበት በዚያው ቀን ፀጉሩን ቢላጭ አመድ ላይ ለሐዘኑ ቢቀመጥም።
በከንፈሩ ግን ማጉረምረምን ሳይሆን ምስጋናን ሞላው። በከንፈርህ አትበድል። በልቡ የማይበድል በከንፈሩ ሊበድል አይችልም። ሐዘን ላይ ነን ማለት አናመሰግንም ማለት አይደለም። አመስግን።
#2.የሚሰማህን ለሚሰማህ ለእግዚአብሔር ንገረው።
ኢዮብዬ! በውስጡ ያለውን ትኩሳት ለእግዚአብሔር መናገር ይችልበታል።
"ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ? ስለ ምን እኔን ለአንተ ዓላማ አደረግኸኝ? ስለ ምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?" ኢዮብ 7:20
🧎ኢዮብ ለእርሱ አላማ እንዳደረገው የገባው ያለ ነገር ይመስላል። ሰባተኛው ምዕራፍ በልቡ ውስጥ ያለውን ትኩሳት ፣ የውስጡን ግልብጥብጦሽ የመንፈሱን ጭንቀት ለሚገባው ፣ ሳይናገር ለሚያደምጠው ፣ ከእስትንፋሱ ቅርብ ለሆነው ነገረው። ንገረው ፣ ንገሪው !!
#3.ትላንትና ያደረገለትን የማይረሳ ሰው ነው።
በፈተና ጊዜ ሊረዳው የማይችል አምላክ እንዳለው አያስብም። ሁኔታዎች እግዚአብሔር ከአንተ ርቋል ብለው ቢሰብኩትም እርሱ ግን ቅርቡ እንደሆነ ያውቃል።
“መንገዳቸውን መረጥሁ፤እንደ አለቃ ሆኜ ተቀመጥሁ ፤ ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር ፥ ኅዘነተኞችን እንደሚያጽናና ኖርሁ።” ኢዮ 29፥25
📕ኢዮብ 29 አሁን ብታነበው ኢዮብ የነበረበትን ከፍታ ነው የምታየው። ያንን ያደረገው እግዚአብሔር እንደሆነ ፈፅሞ አይረሳም።
- “ለዕውር ዓይን፥ ለአንካሳ እግር ነበርሁ።”
- “ለድሀው አባት ነበርሁ፤ የማላውቀውንም ሰው ሙግት መረመርሁ።”
- “የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረጂ የሌለውን አድኜ ነበርሁና።”
👌የትላንትናው ኢዮብ ሁኔታ እና የዛሬው ኢዮብ ሁኔታ ቢቀያየርም እግዚአብሔር ግን አይቀያየርም። የእኛ ሁኔታና እኛ እንጂ እግዚአብሔር አይቀየርም። አለ በዙፋኑ። አላማውን እየፈፀመ ነው። እየተሰራን እንጂ እየፈረስን አይደለንም። አሜን !!
እንዲህ ብለህ አውጅ :-
💛እግዚአብሄር መልካም ነው
💚እግዚአብሔር ያፈቅረኛል
💚እግዚአብሔር አይተወኝም።
💚እግዚአብሔር ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው
💙እግዚአብሔር ለእኔ ያለው ዕቅድ መልካም እና የሰላም ሐሳብ ነው።
👌ይሄንን ለራስህም ለሁኔታውም በደንብ ንገረው። የኖርከው በአንተ መልካምነት ሳይሆን በእርሱ መልካምነት ነው።
👉አንድ የእግዚአብሔር ሰው እንዲህ ብሎ አስፍሯል :- "እግዚአብሄር በብርሀን የነገረህን ነገር በጨለማ አትጠራጠረው ። የተቆለለውን ተራራ ሳይሆን ከተራራው ከጀርባ ያለውን ሜዳ ታያለህ፣ የሚዳሰሰውን ጨለማ ሳይሆን ወገግ ብሎ የወጣውን ብርሃን ትመለከታለህ፣ ብቻህን ያስቀሩህን ሰዎች ሳይሆን ብቻውን ጎልቶ የሚታይህን እግዚአብሄርን ታያለህ ይህ ሁሉ የሚሆነው ከፍ ወዳለ ደረጃ እያደረሰህ ስለሆነ ነው። ስለዚህ በችግርህ አትቸገር ሁኔታዎች የእግዚአብሄርን ባህሪ አይቀይሩትም። የእግዚአሄር ፀጋ አሁንም በሙሉ ብርታቱ አለ።" እኔም አሜን ብያለሁ !!
✉️ቡሩካን ናችሁ!!✉️
❤️እወዳችኋለሁ❤️
ይቀላቀሉንን 👇👇👇
👉👉👉 @workofgrace
👉👉👉 @workofgrace
👉👉👉 @workofgrace
Share and join

ውድ የworkofgrace ቤተሰቦች
ዛሬም እንደተለመደው በቤተክርስቲያኔ ገፅ ላይ የማስተምረውን የተሰሎንቄን ትምህርት ከ4:30 ጀምሮ አብራችሁን በመገኘት እንድታመልኩ እጋብዛችኋለሁ።
በየዕለቱ መልዕክቶችን በፅሁፍ ፣ በሳምንት ሁለት ቀን በድምፅ ለመገልገል ከፈለጋችሁ አብረውን ይቆዩ @workofgrace ሌሎችንም ወደ ቻናላችን ይጋብዙ።
@workofgrace

Forwarded from Ναηόμ נחומ
ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬም እግዚአብሔር ቸርነቱን አብዝቶልን አብረን እንድናመልከው ስለሆነ ስሙ የተባረከ ይሁን !!
እንግዲህ ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን!
እንግዲህ ፕሮግራማችንን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጀምራለን!
Forwarded from Ναηόμ נחומ
አሁን ቀጥለን በቀጥታ ወደ አምልኮ ነው የምንሄደው! ከናቲና ከፍሬ ጋር እናመልካለን
መልካም ቆይታ!
መልካም ቆይታ!
Forwarded from 🔥🔥Pastor Bini 🔥🔥
📕የ1ኛ ተሰሎንቄ የመፅሐፍ ቅዱስ ተከታታይ ትምህርት📕
👉ክፍል ፭👈
✉️"ምስጉኗ ቤተክርስቲያን"✉️
💌ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው ?💌
🎤መልዕክት አቅራቢ :- መጋቢ ቢኒያም ኃይሉ🎤
🎧42:44🎧
ግንቦት 24/2012
⏱ዕሁድ ⏱
⏱ከ4:30 - 6:00⏱
🙏ቡሩካን ናችሁ!!🙏
❤️እወዳችኋለሁ❤
🤲መልካም ቆይታ!🤲
👉ክፍል ፭👈
✉️"ምስጉኗ ቤተክርስቲያን"✉️
💌ቤተክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው ?💌
🎤መልዕክት አቅራቢ :- መጋቢ ቢኒያም ኃይሉ🎤
🎧42:44🎧
ግንቦት 24/2012
⏱ዕሁድ ⏱
⏱ከ4:30 - 6:00⏱
🙏ቡሩካን ናችሁ!!🙏
❤️እወዳችኋለሁ❤
🤲መልካም ቆይታ!🤲
#የምሽቱ ባርኮቴ!
@workofgrace
@workofgrace
፨♥፨♥፨♥፨♥
ዘፍ 28:10-15
ያዕቆብ ከወንድሙ ዛቻ ና ማስፈራሪያ ባመለጠበት ምሽት ብቻውን በነበረ ሰዓት ምድረበዳ ላይ ሰው በማይደርሰበት በማይደርስለት ሁኔታ በነበረበት ሰዓት ፣ ነገር ሁሉ ጭልምልም ባለበት ሰዓት ፣ ባልጠበቀው ሰዓት ፀኃይ ስትጠልቅ ፣ የመለኮት ፀኃይ እንደወጣለት እኔ በኢየሱስ ስም እባርካችኋለሁ ፦
- ፨♥ፀኃይ በጠለቀችበት በጨለመው ፣ ማታ በሆነባችሁ ገዳይ ላይ እግዚአብሔር ብርሃኑን ይልቀቅላችሁ።
- ፨♥ብትጮኹ የሚሰማችሁ በሌለበት ወዳጅ ዘመድ ቤተሰብ በሌለበት እግዚአብሔር ይስማችሁ! መለኮት ይጠጋችሁ አለው ይበላችሁ።
- ፨♥ ሰው ሊገድለው ወንድሙ ሊገድለው ሲፈልገው እኔ እጠብቅሃለሁ ብሎ ህይወት እንደቀጠለለት ሞት እያሳደዳችሁ ፈርታችሁ በምትሸሹበት ምሽት በሆናችሁ ሌሊት ላይ የመለኮት ጥበቃ አለው ይበላችሁ።
- ፨♥ እሞታለው ሲል በአንተ ዘር አህዛብ ይባረካሉ እንዳለው እናንተ ያሰባችሁት ሞት ሳይሆን መለኮት ያሰበላችሁ ነገር በኢየሱስ ስም ይያዛችሁ።
-፨♥ የሰጠሁህን ተስፋ እስክፈፅምልህ ድረስ አልተውህም ብሎ በአስፈሪው ሌሊት የዛሬን ሌሊት ብቻ ሳይሆን ተስፋዬ እስከሚፈፀም ድረስ የትኛውም አስፈሪ ሌሊት ህይወትህን አይወስድህም ብሎ እድሜውን ከአስደናቂ ተስፋ ጋር እንዳስቀጠለለት እግዚአብሔር የመጨረሻ በምትሏት ሌሊት ላይ የመለኮት ጅማሬ በህይወታችሁ ይጀምር አስቸጋሪ የሚባሉ ሌሊቶችን ተሸክሞ የሚያሳልፍ የሚፈፀም ተስፋ ያግኛችሁ።
- ፨♥ እንደወጣችሁ አትቅሩ...እንደተኛችሁ አትቅሩ የተገባላችሁን ተስፋ እስክታገኙ በህይወት በእግዚአብሔር ጥበቃ ቆዩ!!
- ፨♥ የሸሻችሁት ሞት አያግኛችሁ...የእግዚአብሔር የዘመናት አጀንዳ ያግኛችሁ።
-፨♥ ህይወታችሁ ላይ አዲስ ጅማሬ የሚያደርግ የመለኮት ባርኮት ያግኛችሁ።
በኢየሱስ ስም አሜን አሜን አሜን! !
@workofgrace
@workofhrace
ብሩካን ናችሁ! !
እወዳችኋለሁ! !
ብርክርክ በሉልኝ።
መጋቢ ቢኒያም ኃይሉ!!
የተስማማ ብቻ አሜን ይበል!!
፨♥፨♥፨♥፨♥፨🙏🙏
Share and join
👇👇👇👇
❤️👉👉@workofgrace

📖 🍔የህይወት ማዕዶት 🍔
======================== "የመፅናናት እና የማፅናናት አምላክ"
ግንቦት 24/2012
ሰኞ!
@workofgrace
------- ------- ------
❗️" አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።" (ዮሐ.14:26)
❗️ " የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።"
(2ኛ ቆሮ 1:3-4)
#መፅናናት ፣ ማፅናናት
ትርጓሜ ፦
መፅናናት - "በሐዘን ውስጥ ላለ ሰው የሚሰጥ ማበረታቻ ነው።አማኞች ስለኢየሱስ መከራ ሲቀበሉ ይሄን መፅናናት ያገኛሉ። የተፅናና ደግሞ ሰውን ለማፅናናት ብርታቱን ያገኛል።"
- ማፅናናት ፦ "በችግር ጊዜ ለማበረታት እና ለመርዳት በአንድ ሰው አጠገብ መቆም ማለት ነው።"
እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ እና በግለሰብና በማህበረሰብ ህይወት ውስጥ የሰራቸው የማፅናናት ስራዎች አሉ። ዛሬም ይሰራል። ይህች ምድር እስክትጠቀለል እግዚአብሔር በማፅናናቱ ይሰራል።
#1.በግለሰብ ህይወት የታየ የመንፈስ ቅዱስ ማፅናናቱ!
✉️ሐዋሪያው ጳውሎስ ጭንቅላቱን ካሳበጠበት የዕውቀት ማህደር ገልፆ አይደለም የሚያወራን ፣ ከመፅሐፍት ላይ ያገኘውን ዕውቀት አይደለም ያካፈለን ያንን ማድረግ መጥፎ ባይሆንም ግን ከህይወቱ ካለፈበት ነገር ቆርሶ ነው ያካፈለን። ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል ብሎ መድረክ ላይ መፎከር እና በሚለይ ነገር ውስጥ እያለፍክ ማንም ሊለየን አይችልም በማለት የጌታን መፅናናት በህይወቱ እየተለማመደ ያለን ሰው መሆን ልዩነት አለው።
የቀመስከውን ነገር የጣዕሙን አይነት ታውቀዋለህ ጣፋጭ መራራ ጎምዛዛ ወዘተ ትላለህ አለዚያ ግን የቀመሱት ሲያወሩ "ዋው" እያልክ ትሰማለህ።
ጳውሎስ ለነገሩ ያለፈበትን ሲያወራ ለወንጌል የከፈልኩትን እዩልኝ እኔ እኮ ጀግና ነኝ በሚል የትዕቢት መንፈስ ተወጥሮ አይደለም ይልቁን ለሌሎች ብርታት ለመሆን እርሱን ያፅናናውን መንፈስ ለማጉላት ነው። ያለፍክበትን ስታወራ ስሜቱን ጭምር ታጋባለህ ደግሞ የተፅናናህበትን መንፈስ ደግሞ ታካፍላለህ።
2.ለህይወት ጉዞችን የሚያስፈልገው መፅናናቱ።
ህይወት በB እና በD መካከል ነች ይሏታል። (Birth - Death) በልደት እና በሞት (ያው በለ እና መ መካከል እንደማለት ነው።) አጭር ነች። ታይታ የምትጠፋ ነች። ግን ቁምነገር ሊሰራባት የማትችል አይደለችም። አሻራችንን ልናሳርፍባት የምንችል ዕድል ትሰጠናለች።ታዲያ መንፈስ ቅዱስ በዚህች አለም ላለን አጭር የጉዞ ቆይታ በጣም አስፈላጊያችን ነው።
የህይወት ጉዟችን ያለመንፈስ ቅዱስ እጅግ አድካሚ ልንወጣው የማንችል አሰልቺ ፣ ግባችንን ልንመታ የማንችል ደካሞች ነው የሚያደርገን ። ምንም ተፅዕኖ መፍጠር አያስችለንም። ለተፅዕኖ ፈጣሪነት ተፈጥረ ለምን ለቁጥር ማሟያነት ትኖራለህ። ህይወትህን በመንፈስ ቅዱስ ሙላት መምራት አለብህ።
ኢየሱስ ይሄንኑ ስለሚያውቅ "የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ሳትቀበሉ..." ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታድርጉ ብሏቸዋል። ያ የኃይል መንፈስ የተዓምራት ማድረግ ፣ የወንጌልን የመስበክ ጉልበት ብቻ ሳይሆን የመፅናናትም ኃይል ነው። ተዓምራት በማድረግ ጉዳና ብቻ ሳይሆን በመገረፍ ፣ በመታሰር ጎዳናም መሄድ አለ እና ነው ፣ ታዲያ ያው መንፈስ በባህሪያቱ ሊያፅናናቸው ካልቻለ ሰውማ እንዴት ያንን ሊቋቋመው ይችላል ?
#3.የፈተና ውስጥ ብርታት ነው። ድልም ነው።
እንደክርስቲያን በዚህች ምድር እስከ አለን ድረስ ልዩ ልዩ መከራ ሊያልፍብን እንደሚችል እናውቃለን። ዓመፅ ስለምንሰራ ብቻ ሳይሆን ሰይጣን ፣ አለምና ሐሰተኛ ወንድሞች ስላሉ ያልጠበቅናቸው ፈተናዎች ይገጥሙናል።
ግን እባክህን አንድ ጊዜ ስማኝ ፣ ይሄንን አድምጠኝ !
መሬት በዘር ወቅት ትልቅ ፈተና ውስጥ ያልፋል ፣ ይቆፈራል ፣ ይጎለጎላል ፣ ይከሰከሳል ፣ ደግሞ መጨረሻ ይለማል ከዚያ ይዘራበታል ያፈራል። ግን መቆፈር ፣ መጎልጎል ፣ መከስከስ እኮ ደስ አይልም። አየህው አንዳንድ ፈተናዎች ልባችንን ሲቆፍሩት ፣ ውስጣችንን ሲከሰክሱት አረም ሊዘራበት አይደለም ትህትናን ሊያስተምሩን ፣ ፍሬያማ ሊያደርጉን የእግዚአብሔር ሰራተኞች ፣ የመንፈስ ቅዱስን መፅናናት ማጣጣሚያዎች እንደሆኑስ ታውቅ ይሆንን ?
ፈተናዎች እየሰሩን እንጂ እያጠፋን አለመሆኑን ተረዳ። ቆይ እሳት ውስጥ የገባ ወርቅ ሲለበለብ አለቀልኝ ፣ በቃ ጠፋው ምን አባቴ ልሆን ነውን ? ይላል አይልም። ካለም የሚለው እየነጠርኩ ነው ፣ እሳቱ ደስ ባይልም እየጠራሁ ነው ፣ ደምቄ እንደወጣ ቆሻሻው እየተራገፈ ነው ነው ሊል የሚችለው። የምናልፍበትን ፈተና ሁሉ መጥፊያቸን እንደሆነ የሚነግረን እርሱ ዲያቢሎስ እኛም የተጣባነው አሉታዊ አስተሳሰብ ነው።
ጌታ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ብዙ ጊዜ አፅናንቷችኋል። በባህር ላይ ወጀቡን ፀጥ በማድረግ ፣ በእጥረት ጊዜ ሙላት በመሆን ፣ በውጥረት ጊዜ መረጋገትን በመስጠት ፣ በጠላቶቻቸው ተቃውሞ በሚደርስባቸው ጊዜ የልብ ጥንካሬን እና የመንፈስ መፅናናትን አልፎ መሄድን በመስጠት አፅናንቷቸዋል ደግሞም አፅንቷቸዋል።
አሁን መፅናናት ለሚሻ ሰው መንፈስ ቅዱስ አፅናኙ አለለት። አፅናኝ እልክላችኋለሁ ያለው ያለእርሱ በዚህች አለም ላይ ያለንን ጉዞ ልንወጣው ስለማንችል ነው። እግዚአብሔር የመፅናናት አምላክ ነው።
#በመንፈሱ የሆነ መፅናናት!!
" እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።" (ዮሐንስ 16:7)
የመንፈስ ቅዱስ ሲያፅናና አይምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም በመስጠት ነው የሚያፅናናው።
አንዳንድ ጊዜ ለቅሶ ቤት የሚመጡ አፅናኞች የበለጠ አስለቃሾች ናቸው። ካፅናኑም ብዙዎቹ ከንፈር መጣጮች ናቸው።
መንፈስ ቅዱስ ከንፈር መጣጭ ፣ ውጫዊም አፅናኝ አይደለም። በምናልፍበት ነገር እግዚአብሔር ልክ እና አዋቂ ነው ብለን እንድናልፍ የሚያደርገን ፣ የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን የሚያሰኝ ነው። አዎ እርሱ የልብን የሚረዳ አፅናኝ ነው። ማፅናናቱ ጉልበት አለው። ወደላይ የሚያስፈነጥር ፣ ከተያዝንበት የሚያወጣ ፣ የሚያስኬድ ነው።
በመንፈስ ቅዱስ መፅናናት ውስጥህ ሲጠበቅ ልክ እንደ ሐዋሪያት ስለወንጌል ብዙ ዋጋ እየከፈልክ ፣ እየታሰርክ፣ እየተደበደብክ ፣ አንዳንዶቹ እየሞቱብንም የወንጌልን እሳት እያነደድን እንቀጥላለን።
ዛሬም አፅናኙ የመፅናናት አምላክ አለ። እርሱም ማደሪያው አንተ ውስጥ ነው። የሚያጠራ እንጂ የሚያጠፋ ፈተና የለም። ፈተና የገደለው ሰው የለም። ጊዜውን ጨርሶ የሄደ እንጂ። ሳትጨርስ አትሄድም ግን እግዚአብሔር በመፈታተን መንገድ ግን አትሄድ ምክንያቱም አይገለኝም ብለህ መርዝን ብትጠጣ የተፈጥሮን ህግ ጥሰሃልና በወተትም ላትተርፍ ትችላለህ ትሄዳታለህ። ራስህን ጠብቅ ፣ ርቀትህን ጠብቅ ፣ ማስክህን አድርግ ፣ ለጊዜው ከቤት የምትወጣበት ጉዳይ ከሌለ አትውጣ የሚለውን መልካም ምክር ንቀህ ጠባቂና አፅናኝ አለኝ ብለህ የመፈታተን መንገድ ብትገባ ባትሞት እንኳን ለምትከፍለው ዋጋ ግን ኃላፊነቱን ትወስዳለህ ብዬ ምክር ለግሼ ፅሁፌን ዘጋሁኝ።
አፅናኙ አለ።
ቡሩካን ናችሁ!
@መጋቢ ቢኒያም ኃይሉ።
መልእክቶቼን ማግኘት ከፈለጋችሁ
👇👇👇👇
ይ🀄️ላ🀄️ሉን

ዕሮብ
ግንቦት 26/2012
#አትሂጅብን!
#አትሂድብን!
❤💖❤💖
በሰው ዘንድ የምትሰራቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ሰዎች አንተን እንዲፈልጉህ ከማድረጉ በላይ እንድትሄድባቸው አይፈቅዱልህም።
መፅሐፍ ቅዱሴን ሳጠና በጣም ካስገረሙኝ ሰዎች መካከል ጣቢታ የተባለችው ሴት ነች። ወይም ዶርቃ !
ይህቺ ሴት መልካም ነገር የሞላባት ፣ መፅዋች ፣ ለመበለቶች የሚሆን ልብስ ሰርታ በነፃ የምታከፋፍል ሴት ነች።
ይህቺ ሴት መቁረስን ብቻ ሳይሆን መቆረስን ጭምር የምታውቅ ለሰዎች ህይወት መትረፍን የለመደች ሴት ነች። መልካምነቷ ጉንጯ ላይ ብቻ ያልቀረ ይልቁንም በተግባር ሰው ሁሉ የሚመሰክረው ነበረ።
ድንገት ታማ ሞተች ይለናል መፅሐፍ ቅዱስ። ሰዎቹ ግን ተስፋ አልቆረጡባትም ። ተስፋ በሚቆረጥበት ሞት ውስጥ ሆና ሳለች ...! እነርሱ ግን ሬሳ ሳጥን ከመግዛት ይልቅ እንደተኛ ሰው አጥበው ሰገነት ላይ አኖሯት።
ስማኝ በሰዎች ዘንድ አትሂድብን የምትባል አይነት ሰው ስትሆን ሞተህ እንኳን ተስፋ አይቆረጥብህም።
ዶርቃ ለቀብር መሰናዳት ሲኖርባት እንድትሄድ አንፈቅድላትም ብለው መበለቶቹ በሙሉ ጴጥሮስን አስጠሩት።
ያለመሰሰት ሰጠች ! ያለመሰሰት ኖረች። ያለመሰሰት አካፈለች። ያለመሰሰት ...!
ምሰጠው የለኝም አትበል ብዙ የምትሰጠው ነገር አለህ። ዕውቀትህን ፣ ጉልበትህን ፣ ታለንትህን ፣ ገንዘብህን ወዘተ መስጠት ትችላለህ።
በዚህ ህይወት ሰው ንፋግ የሚሆነው የሚሰጠው ስለሌለው ሳይሆን መስጠት ገንዘብ ብቻ እንደሆነ ስለሚያስብ ነው።
ዶርቃዎች የትናችሁ ? 👐👐
ጴጥሮስም መጥቶ ከእንቅልፍ እንደሚቀሰቅስ ሰው አስነሳት።
አትሂድብን
አትሂጂብኝ
እንባላለን ወይስ እረ እንኳን እርሷ ሄደችልን እንኳን እርሱ ሄደልን ተብሎ ይነገርብን ይሆን።
እኔ ግን ልባርካችሁ ምድር ሁሉ አትሂድብን ብሎ የሚናፍቃችሁ አይነት ሰው ያድርጋችሁ።
ተናፋቂ ሰው እንጂ ምነው እርሱን/ እርሷን የሚገላግለን በመጣ አይባልባችሁ።
#አትሂድብን
#አትሂጅብን
ሐዋ 9:37-42
ኖራም መልካምነት የሞላባት ነች ከሞት ስትነሳ ደግሞ ብዙዎች ወደ ጌታ እንዲመጡ ምክንያት ናት!
ኑሮችሁ ብቻ ሳይሆን ሞታችሁ ጌታችሁን ያክብርላችሁ።
በሰው ዘንድ የምትፈለጉ የምትናፈቁ ሰዎች ያድርጋችሁ።
አሜን
ብሩካን ናችሁ!
@ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)
#አትሂጅብን!
የዛሬ አመት አከባቢ ፌስቡክ ገፄ ላይ ለጥፌው ከነበረ የተወሰደ።
Share and Join
👉👉 @workofgrace
👉👉 @workofgrace
👉👉👉 @workofgrace
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

አንድ ከአስር ላይ በቤተክርስቲያኔ እያካፈልኩ ያለውትን "የመጨረሻ ዘመን እና ኗሪዎች " በሚል የማስተምረውን ትምህርት ልለቀው ነው ዝግጁ ናችሁ።
የ @workofgrace ቤተሰቦች ሁሌም አብራችሁን ሁኑ ትባረኩበታላችሁ👍👍

#የህይወት_ማዕዶት
26/9/2012
ሐሙስ
#መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ
አስተማሪ ታሪክ
#አንድ_ምሽት_ላይ ልክ ባለሱቁ ሱቁን ከመዝጋቱ በፊት አንድ ውሻ ወደ ሱቁ ይገባል።
ውሻው በአፉ ዘምቢል ይዟል። ዘምቢሉ ውስጥ የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር እና ገንዘብ ተቀምጧል።
#ባለሱቁ_ገንዘቡን_ወስዶ እቃዎቹን በዘምቢሉ ውስጥ ያኖረዋል።
ወዲያውኑ ውሻው ዘምቢሉን ይዞ ይሄዳል።
#ባለሱቁ_ስለገረመው የውሻው ባለቤት ማን እንደሆነ ለማወቅ ውሻውን ይከተለዋል።ውሻው አውቶብስ ፌርሜታ ቆሞ ይጠብቃል።
ከትንሽ ጊዜ በኋላ አንድ አውቶብስ ሲመጣ ውሻው አውቶብሱ ውስጥ ይገባል።
#ትኬት_ቆራጩ እንደመጣ ወደፊት ጠጋ አለ የአንገት ቀበቶው ላይ ያለውን ገንዘብና አድራሻ ለማሳየት።
ትኬት ቆራጩም ገንዘቡን ወስዶ ትኬቱን በአንገት ቀበቶው ውስጥ ያኖርለታል። የሚወርድበት ቦታ ሲደርስ ወደፊት ቀረብ ብሎ ጭራውን ያወዛውዛል መውረድ እንደሚፈልግ ለማመልከት መሆኑ ነው።
#አውቶብሱ እንደቆመለትም ይወርዳል። ባለሱቁ አስከአሁን እየተከተለው ነበር። ውሻው ከአንድ ቤት ደርሶ በሩን በእግሮቹ ያንኳኳል።
#ባለቤቱ_ከውስጥ ወጥቶ ውሻውን በዱላ ይመታዋል። በዚህ ጊዜ ባለሱቁ ተናዶ " ውሻውን ለምንድነው የምትመታው?" ብሎ ይጠይቀዋል። ባለቤቱም እንዲህ ብሎ ይመልስለታል። "ከእንልፌ ቀስቅሶኛል።
ቁልፉን ይዞ መሄድ ነበረበት።"
#ይህ_የህይወት_እውነት_ነው! ሰዎች ለአንተ የሚሰጡት ግምት ማብቂያ የለውም።
ከዚህ በፊት የሰራሃቸው ጥሩ ነገሮች ሁሉ ይረሳሉ። ትንሿ ስህተትህ ጎልታ ትወጣለች። ይህ የዚህ ቁሳዊ ዓለም ተፈጥሯዊ ገጽታ ነው! በዚህ ምድር ቆይታችን የከፈልነውን ዋጋ ማንም ባይረዳን እንኳን ከማንም ምንም አይነት ምላሽ ሳንጠብቅ ለመልካም ነገር መትጋታችንን እንቀጥል!
አጋራዋችሁ!
ቡሩካን ናችሁ
#pest
ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ

#ከንባብ_ሽርሽሬ_የተቀዳ!
ግንቦት 28/2012
አርብ !
#አስተማሪ ታሪክ!
💖❤💖❤❤💖❤
#በአንድ_ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡
#አባቷ_የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡
#በድስቶቹ_ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡
#ከሀያ_ደቂቃ በኋላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡
"#ልጄ_አሁን_ምን_ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ "በቁጣ ስሜት ሁና ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡
"#በደንብ_ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡
"#እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡
በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡
"አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡
አባት ማብራራት ጀመረ፡፡ "#ድንቹ፣ #እንቁላሉ እንዱሁም #የቡናው_ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡
#ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡
#እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡
#ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡
#አንቺ_የትኛው_ነሽ?" ችግር ስገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?"
✍#በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!"
የትኛው ነህ? ነሽ?
ቡሩካን ናችሁ!!
@ቢኒያም ኃይሉ(መጋቢ)
#pest!

###እሰር ###
1ኛ ዮሐ 3:-8
ስለዚህ የዲያብሎስ ስራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ
👉ዲያብሎስ ስራ አለው ስራፈት አይደለም ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠበት አንደኛው ምክንያት የዲያብሎስ ስራ ሊያፈርስ ነው።
👉ከዲያብሎስ ስራ አንደኛው ና ዋነኛው የወንጌል እውነት ለአለም እንዳይደርስ ለማድረግ ወይም ቤተክርስቲያን የተሰጣትን ተልዕኮ እንዳትፈፅም ለመገደብ ሰዋች ከዘላለም ሞት እንዳይድኑ ነው።
✍ አሁንም በዚህም ጊዜ አላማው ወንጌል ለፍጥረት እንዳይደርስ ሰዋችን ደግሞ ወደ ዘላለም ጥፋት ለመውሰድ ነው።
ሐዋ 13:-7-11
ይህም በርናባስና ሳውልን ወደ እርሱ ጠርቶ የእግዚአብሔር ቃል ሊሰማ ፈልገ ጠንቋዩ ግን ኤልማስ ስሙ እንዲሁ ይተረጉማልና አገረ ገዢው ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው ጳውሎስ የተባለ ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ትኩር ብሎ ሲመለከተው አንተ ተንኮል ሁሉ የሞላብህ የዲያብሎስ ልጅ የፅድቅ ሁሉ ጠላት የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን አነሆ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት ዕውርም ትሆናለህ...
👉ጳውሎስና በርናባስ የሚይስተምሩትን ቃል ለመስማት ቢፈልግም የወንጌል ጠላት ግን አይፈልግም ዛሬም ይህንን የወንጌል እውነት መስማት የሚፈልግ አለ ነገር ግን የዲያብሎስ ልጅ ይሄን አይፈልግም ስለዚህ የቀናው የጌታ መንገድ ሊያጣምም ይፈልጋል
👉አገረ ገዢው ወንጌል መስማት እየፈለገ የከለከለውን ነገር ጳውሎስ በመንፈስ ቅድስ ተሞልቶ ትምህርቱ ከማስተማሩ በፊት ይሔን የወንጌል ጠላት እንደገሰፀው ዛሬም በመንፈስ ሙላት የወንጌሉን ጠላት ስራን እናፍርሰው
👉ነገር ግን አስቀድሞ ኀይለኛውን ሳያስር ወደ ኀይለኛው ቤት ገብቶ ዕቃውን ሊበዘብዝ የሚችል የለም። አስሮ ግን ቤቱን ይበዘብዛል ዛሬም ከዲያብሎስ ሰዋችን ለማዳን ቅድሚያ እንሰር ካላሰርን መበዝበዝ አንችልም አስረን ግን ብዙ ትውልድ እንናጠቃለን።
👉ጳውሎስ አጋንቱን ማሰሩ( የተሰጠውን የልጅነት ስልጣን) ና በጌታ ትምህርቱ የተነሳ ተገርሞ አመነ። በአግባቡ ስልጣናችን መጠቀም ላልዳኑት መገረሚያ ነው ቃሉ ደግሞ መዳኛ ነው
✍ወንጌልን ለመስማት የሚፈልግ ትውልድ አለ ግን በአጠገብ ሆኖ ወንጌል የሚያጣምም አለና ነቅተን እንቃወም ወንጌል መስማት ለተገባው ትውልድ እንዲደርስ
1ኛ ጴጥ 5:-7
በመጠን ኑሩ ንቁም ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራል በአለም ያሉትን ወንድሞቻችሁን ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ፀንታችሁ ተቃወሙት
👉ወንድሞቻችን ሊውጥ የሚፈልግ አለና እንንቃ የጠላትን ሀሳብን እንሳተው ፀንተን እንቃወም
👉በአጋንት ሁሉ ላይ ስልጣን አለን ስለዚህ የተሰጠንን ስልጣን እንጠቀምበት። ስልጣን የሌላቸው ወንድሞቻችን አሉና ስልጣኑን እስኪያገኙ ድረስ በእምነት ፀንተን እንቃወም ሌሎችን እንታደግ ድሉ የእኛ ነው
👉👉የሰው ጠላት የለንም እንጂ ጠላት አለብን መቼም ቢሆን የማንወዳጀው
👉👉እንቃወመው ከእኛ ይሸሻል
ማቲ 16:-18 በዚች አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሰራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሏትም የመንግስተ ሰማይ መክፈቻ እሰጥሃለሁ በምድር የምታስተምረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል
👉👉ጠላታችንን እንሰር በምድር ያሰርነው በሰማይ የታሰረ ይሆናል
👉👉በአጋንንት እስራት ያሉትን እንፍታ የተፈቱ ይሆናሉ። ማንም ለምን ትፈታላችሁ ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጋሉ በሉ።
👉👉👉👉✍ አስተውሉ ግን በኤፌሶን 6:-11 እንደሚናገረው የዲያብሎስ ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔር ዕቃ ጣር ልበሱ።ውጊያ ከመግባታችን በፊት ልብሳችንን መልበሳችንን እርግጠኛ እንሁን። ወታደር ምንንም ይህል ጎበዝ ቢሆን ወደ ውጊያ ቦታ ከመግባቱ በፊት ትጥቁን እንደሚይሟላ እኛ ትጥቃችንን አሟልተን ወደ ውጊያ እንግባ።ሰይጣን ወደ ዘላለም ጥፋት ሊወስድ ያለውን ሰው እንናጠቀው ሰው እየጠፋ ዝም አንበል እኛ ስልጣን ተሰጥቶን እንጠቀምበት እናትርፍበት አንደብቀው በአግባቡ እንጠቀምበት ግድ ይበለን ኀላፊነት ያሰማን
የእግዚአብሔር ዕቃ ጦር በመልበስ ውጊይችሁን ቀጥሉ ድሉ የእኛ ነው አዲስ ስይጣን የለም የተቸነፈ ነው
አትርሳ##### እሰር#####
የኃይለኛውን ቤት በመበዝበዝ ተባረኩ
❤️❤️❤️
Join and share

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእውነት በጣም ነው የሳቅኩት ....ዘና ማለት ጥሩ ነው። ሳቅ በሉ...