ተውሒድ የሁሉም ነብያቶች ጥሪ ነው።
7.44K subscribers
736 photos
274 videos
45 files
3.62K links
አላህ እኛን የፈጠረን እሱን በብቸኝነት እንድናመልክና በሱ ላይ ምንንም ላናጋራ ነው. መረጃዉም የሚከተለው የአላህ ንግግር ነው: “ጂንና የሰዉን ልጅ አልፈጠርኳቸዉም እኔን እንዲገዙኝ(እንዲያመልኩኝ) እንጂ።” ( ሱራህ አዝ-ዛሪያት 51:56).
ለሀሳብ አስተያየት
@Haymanot_Darsema
Download Telegram
ኡኽታዬ

ለመዘነጥ ሸርጥ አይደለም መገላለጥ!!
.. ከአሏህ ርቃችሁ ደስታ አጣን አትበሉ..


♻️በእስልምና ዉስጥ በምንኖረው ልክ ሕይወታች ያማረ፣ ስኬታችን የሰመረ፣ ደስታችን የጨመረ ይሆናል።

ወላሂ በእስልምና ውስጥ መኖር ከደስታ በላይ የላቀ ደስታ ነው።

➢አስቡት እስኪ ያጣቹህትን ነገር እያሰባቹህ ልትወድቁ ስትሉ የጌታቹህ ቃል መጥቶ ግርድ ይልና ቀጥ እንድትሉ የማይሰበር ምርኩዝ ይሆናቹሀል  ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ.........!!
አጅብብ እኔማ በመገረም ላይ ነኝ!

አወ አልሃምዱሊላህ አዛኙ ጌታችንኮ እርሱ በፈለገው  በተለያዩ ነገሮች እንደሚፈትነን ቀድሞ በተከበረው ቃሉ ነግሮናል!

ታድያ ዛሬ መፈተናችን ብርቅ ነው እንደ?
አይደለም እንደውም መታደል ነው!

ብቻ በጥቅሉ የምላቹህ ነገር ምድር ላይ ሲኖር ደስታ የራቀው ሰው
ከአሏህ ጋር ያለዉን ግንኙነት ይመርምር።


 https://t.me/UmuNuhBintdarsema
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِيَّاكُمْ وَالظَّنَّ ؛ فَإِنَّ الظَّنَّ أَكْذَبُ الْحَدِيثِ،﴾

“ጥርጣሬን ተጠንቀቁ። እሱ ከወሬ ሁሉ ቅጥፈት ነውና”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5143

https://t.me/UmuNuhBintdarsema
60ኛ. "የመልካም ሚስት ባህሪዎች صفات الزوجة"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.sifatzwjetusoliha
ጠንክሮ መሥራት
ለሁለቱም ዓለም ስኬት
.
እስልምና ሰነፍ ሰው አይወድም፡፡ ለስንፍናም ቦታ የለውም፡፡ ሁለቱም መልካም ቢሆኑም ጠንካራው አማኝ ከደካማው እንደሚበልጥ ያሰተምራል፡፡ ሰጭ እጅ ከተቀባዩ እንደሚሻልም ይናገራል፡፡ እስልምና ተግተው የማይሰሩ ኮሳሳ አማኞችን ያወግዛል፡፡ የአጓጉል ምኞት ተከታዮችን ያጥላላል፡፡
 ‹ብልህ ማለት ነፍሱን የመረመረና ከሞት በኋላ ላለው (ህይወት) የሰራ ነው፡፡ ደካማ ሰው ደመነፍሱን የተከተለና በአላህ ላይም አጓጉል ምኞት የተመኘ ነው፡፡› ብለዋል ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ፡፡
 - ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ ‹አላህ ሆይ! ከስንፍና ባንተ እጠበቃለሁ፡፡› ይላሉ፡፡
- ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ ረ.ዐ ‹ደከመኝ› ማለትን ይጠሉ ነበር፡፡
-  ታላቁ ኸሊፋ ዑመር ረ.ዐ ኮሳሳና ልፍስፍስ መስለው የሚታዩ ሰዎችን አይወዱም ነበር፡፡ ቀና፣ ቀልጠፍ እና ቆፍጠን ያለ ሙስሊም ያረካቸዋል፡፡ ሥራ ትተው መስጊድ ውስጥ የሚውሉትንም ይቆጡ ነበር፡፡ የርሳቸውን ሙሉ እንቅስቃሴ የተመለከተ እስልምናን ከሁኔታቸው ብቻ መማር ይችላል፡፡ ሲራመዱ እንደ ፏፏቴ ይወረወራሉ፡፡ ሲናገሩ እንደ ነጎድጓድ ያሰማሉ፡፡ ሲማቱ እንደ ዱላ ያሳምማሉ፡፡ ሲቆጡ እንደ ጀግና ይታገሳሉ፡፡ ሲራሩ እንደ እናት ልጅ ያዝናሉ፡፡
 አብነቶቻችን እነኚህንና እነኚህን የመሳሰሉ ጠንካሮቹ ሰዎች ናቸው፡፡ ‹ጥሩ ነው› የሚባለው ሙስሊም ጥሩና ጠንካራ የተባሉ ባህሪዎች ሁሉ የርሱ ናቸው፡፡ እኛስ ልፍስፍነትን ከየት አምጥተን ይሆን ጎበዝ?፡፡
.
እስልምና አባላቶቹ ዓላማ ያላቸው፤ ብቁና ንቁ እንዲሆኑ ይፈልጋል፡፡ በሁሉም ዘርፍ በላጭ የሆኑትን ያበረታታል፡፡ ታላቁ ነቢይ ሰ.ዐ.ወ ሙስሊሙ አማኝ ምርጥ የተባሉ ሥነምግባራት ባለቤት እንዲሆን ያበረታተቱ ነበር፡፡ በትምህርቶቻቸው እንዲህ ይላሉ _

- ‹በላጫችሁ ለቤተሰቡ በላጭ የሆነው ነው፡፡›
- ‹በላጫችሁ ቁርኣንን የተማረና ያስተማረ ነው፡፡›
- ‹ከሰዎች መካከል በላጩ ለሰዎች ጠቃሚ የሆነው ነው፡፡›
.
ነገም ሆነ ዛሬ ሁሉም የሰው ልጅ የሥራ ውጤቱን ነው የሚያገኘው፡፡
- ሐምዛ ረ.ዐ ‹አሰዱሏህ/ የአላህ አንበሳ› የተባለው ያለ ውሎው አይደለም፡፡
- ዐብዱረህማን ኢብኑ ዐውፍ ረ.ዐ ሀብታም የሆነው ነግዶ ነው፡፡
- ሙዓዝ የሐላል እና ሐራም ኤክስፐርት ለመሆን የበቃው ተምሮ ነው፡፡
- ኻሊድ ‹ሰይፉላህ አልመስሉል› ከአፎቱ የተመዘዘ የአላህ ሰይፍ› የሚል ስያሜ የተሰጠው ጀግኖ ነው፡፡ - አቡበከር ረ.ዐ በስምንቱ የጀነት በሮች ሊጠራ የቻለው ንብረቱን በሙሉ በአላህ ሱ.ወ መንገድ ሰጥቶ ነው፡፡
-  በጀነት የተበሰሩት አስሩ ሰሃቦች ደክመው ለፍተው ነው፡፡
 እኔና አንተ አንቺ ምን ሰራን?፡፡ እነርሱ ‹ሰርተን ነው! የላባችንን ነው! የለፋንበት ነው!› ቢሉ ያምርባቸዋል፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ አለ
وَتِلْكَ الْجَنَّةُ الَّتِي أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ [٤٣:٧٢]
‹ይህችም ያቺ ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የተሰጣችኋት ገነት ናት፡፡› (አዝ ዙኽሩፍ፡ 72)
مَّنْ عَمِلَ صَالِحًا فَلِنَفْسِهِ ۖ وَمَنْ أَسَاءَ فَعَلَيْهَا ۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّامٍ لِّلْعَبِيدِ [٤١:٤٦]
‹መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም፡፡› (ፉሲለት፡ 46)
.
ስለሆነም.. በምድር ላይ እስካለን ድረስ እንስራ፡፡  የሥራን ዋጋም እንወቅ፡፡ ሰራተኛና ሰነፍ ሰው ደረጃቸው የተለያያ መሆኑን እንገንዘብ፡፡ ለመኖር ብቻ ሣይሆን ለመጥቀም እንኑር፡፡ ለህይወት ጨማሪዎች እንጂ ጭማሪ አንሁንባት፡፡
- ባርነት ስንፍና ሲሆን ሥራ ነፃነት ነው፡፡
-  መለመን ውርደት ሲሆን መለገስ ክብር ነው፡፡ 
- ድሃ፣ ሰነፍ፣ ደካማ …የሚለው መጠሪያ የሚውለው ወደኋላ ለቀሩት ነው፡፡
- ሀብታም፣ ጎበዝ፣ ጠንካራ ..የሚለው ደግሞ ለቀደሙት ነው፡፡
 ታዲያ ለምን ከፊት አንሆንም?
ድህነት ቅንቅን ነው፡፡ ሆኖም ግን እንደ ዶሮ ላባን በማራገፍ አይደለም የሚረግፈው፡፡ መሃይምነት ጨለማ ነው፡፡ ሆኖም ግን አምፖል በማብራት አይደለም የሚጠፋው፡፡ ስንፍና በሽታ ነው ነገርግን ዳማከሴ በመታጠን አይደለም የሚለቀው፡፡ የድህነት ተራራ ሊናድ የሚችለው በሥራ ነው፡፡ የመሃይምነት ጨለማም የሚገፈፈው በመማር ነው፡፡ ተቀምጦ አሊያም ተኝቶ ጎበዝ መሆን አይችልም፡፡    
የሙስሊም ባህሪ ወደላይ ነው፡፡ የሚመኘውም ሆነ የሚያልመው ምርጥ ነገር ነው፡፡ ሁሌም ተሸሎ ለመገኘት ይጥራል፡፡  ምኞቶቹ ትላልቅ፤ ህልሞቹም ውድ ናቸው፡፡ መዋያዎቹ ፅዱ፤ እኩዮቹም ምርጥ ነገሮች ናቸው፡፡ ለተራ ነገር እጅ አይሠጥም፡፡ ለርካሽና ውዳቂ ነገሮች አይሸነፍም፡፡
 በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ዳዒ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአንድ ሙስሊም የውጤት ደረጃ ምን ሊሆን እንደሚገባው በግቢው ቋንቋ ሲያስረዱ እንዲህ ነበር ያሉት፡፡ ‹ኤ› ዋጅብ/ግዴታ ነው፡፡ ‹ቢ› ሙስተሐብ/ይወደዳል፡፡ ‹ሲ› ሙባሕ/የተፈቀደ ነው፡፡ ‹ዲ› ከራሃ/የተጠላ/ ነው፡፡  ‹ኤፍ› ሐራም ነው፡፡ 
ይህ የውጤት ደረጃ ምደባ በህይወት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለምንኖረው ለኔና ላንተም ጠቃሚ መመሪያ ይመስለኛል፡፡
"ህልም አለኝ" ከተሠኘው መጽሐፌ
ኮፒ
Forwarded from DARU-TEWHID [ዳሩ-ተውሒድ] (Muhammed Ibnu Fedlu [Abu Nuh])
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ርቀትህን ለካ
.
በፊትም በኋላም በግራም በቀኝም አስበህ
ሞክረህ በነገርህ ሁሉ ጥረህ ካልተሳካ፣
ሙሲባህ ከበዛ ኪሣራህ ካየለ
በድርብርብ ችግር ዉስጥህ ከተነካ ፣
እራስህን መርምር  ችግሩ ካንተ
ነው ከፈጠረህ አምላክ ምን ያህል
እንደራቅክ ክፍተትህን ለካ! 
.
ተውሒድ የሁሉም ነብያቶች ጥሪ ነው።
Photo
ጓደኛህ ማነው?
~
ጓደኛህ ወደ ተሻለ የምትወስደው ወይም ወደተሻለ የሚወስድህ ይሁን። ካልሆነ ግን ወይ ያጠፋሀል። ወይ ታጠፋዋለህ። ወይ ተያይዛችሁ ትጠፋላችሁ።
ሰው ውሎውን ይመስላል። ውሎህ የት ነው? ከማን ጋር? ሰዎች ጠጪ የሚሆኑት በጓደኛ ሰበብ ነው። ቃሚ፣ አጫሽ የሚሆኑትም በጓደኛ ተፅእኖ ነው። ያለ ምክንያት አይደለም "ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን ልንገርህ" የሚባለው።
ከመጥፎ ሱስ መውጣት፣ ባህሪህን መግራት ትፈልጋለህ? ከልብህ ከሆነ ውሎህን አስተካክል። ልጅህ ከመጥፎ አዝማሚያ እንዲመለስ፣ መስመር እንዲይዝልህ ትፈልጋለህ? ሰበብ ሳታደርስ ጠዋት ማታ አትጨቃጨቅ። ይልቁንም ውሎው ላይ አጥብቀህ ስራ። ካልሆኑ ጓደኞች ጋር ገጥሞ ከሆነ የምትችለውን ሁሉ መስዋእትነት ከፍለህ ለየው።
ለብዙዎች በዲንም ይሁን በዱንያ መቃናት መልካም ጓደኛ ትልቅ ድርሻ አለው። እስኪ በህይወት ጉዟችሁ ላይ አነሰም በዛ ላገኛችሁ ስኬት ወይም መልካም ለውጥ አስተዋፅኦ ያላቸውን ጓደኞቻችሁን ለአፍታ አስቧቸው። በተቻለ መጠን ውለታ መላሽ ሁኑ። እሱ ቢቀር አመስጋኝ ሁኑ። ከዚያም በላይ በዱዓእ አስታውሷቸው።
ጓደኝነት ኣኺራን ከነጭራሹ ሊያጨልም፣ ኩ. ፍ. ር ላይ ሊጥል ይችላል። በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ለተረዱት እውነት እጅ መስጠት አቅቷቸዋል?! በጓደኛ ሰበብ ስንቶች ውስጣቸው እያወቀ እምነት ቀይረዋል? ስንት ወንዶች ሴት ተከትለው፤ ስንት ሴቶችም ወንድ ተከትለው ዘላለማዊ ህይወታቸውን አጨልመዋል?! የተሰጠን እድል ከእጃችን ሳያፈተልክ፣ ነፍሳችን ሳትሾልክ በፊት ሳይመሽ እናስብበት። እንወስን በጊዜ። ነገ ፀፀት እንዳይበላን። ጌታችን እንዲህ ይላል:-
{ وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا (27) یَـٰوَیۡلَتَىٰ لَیۡتَنِی لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِیلࣰا (28) لَّقَدۡ أَضَلَّنِی عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَاۤءَنِیۗ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِلۡإِنسَـٰنِ خَذُولࣰا (29) }
{በዳይም፡ «ምነው ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)። «ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ። (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ» (ይላል)። ሰይጣንም ለሰው በጣም ለውርደት አጋላጭ ነው።} [አልፉርቃን፡ 27-29]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 2/2016)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
አሠላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ውድና የተከበራችሁ እህት ወንድሞች ይች እህታችን ስሟ ተምሬ አራጋው ጎቸል ትባላለች ከፓስፖርቱላይ እንዳለው በጠለብ ከአራትና አምስት ወር በፊት ሳኡድ ጂዳ ከተማ ገብታ ነበር እናም አሰሪዋ መንገድ ላይ ጥላታለች አሉን። አእምሮዋም ትክክል አይደለም ቪዶወውላይ እንደምታዩት።የቀረጿትም ልጆች ልንወስዳት ስንል ሴትየዋ እምቢአለችን አሉ በሰአቱ ዘወር ብለው ሲመለሱም ከቦታው እንዳላገኙዋት ነው የተናገሩት እና ጂዳ አካባቢ ያላችሁ በተለይ እባካችሁ ይችን እህታችንን ያያት ካለ እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

አላህ ሁላችንም ይጠብቀን እሷንም ያስገኛት!!

እኔ የሰፈሯ ልጂ ነኝ ካገኛችኋት

0532053175 Bint Mohammed በዚህ ቁጥር በዋሳብም ወይም በመስመር ያገገኙኛል ይደውሉ የሠማችሁም አደራ ሸር አድርጉልኝ
👑መደበቅ ለሴት ልጅ ትልቅ ክብር ነው
በየ ቦታው መገኘት ዝቅጠት ነው !!!
በየ ቦታው አትገኚ  ትረክሻለሽ!!

♕የሰለፍያ እንስት የውዶች ውድ ናቸው።♕

  يَآ آخِتٌيَ کْوٌنِيَ غُآلَيَهّ
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በሱፊያው ዓለም በርካታ የሚመለኩ ቀብሮች አሉ። ቀብሮቹ ዘንድ በመሄድ ልጅ፣ ዝናብ እና የተለያዩ ሐጃዎችን ይማፀናሉ። የሞተ ሰው እንኳን የነሱን ጉዳይ ሊፈፅም ከራሱ፣ ከተሰራለት ዶሪሕ እንኳ መከላከል አይችልም። ይሄው ይሄ "ወሃቢ" የሆነ ጎርፍ ዶሪሑን ነቅሎ እየወሰደው ነው።
{ أَیُشۡرِكُونَ مَا لَا یَخۡلُقُ شَیۡـࣰٔا وَهُمۡ یُخۡلَقُونَ (191) وَلَا یَسۡتَطِیعُونَ لَهُمۡ نَصۡرࣰا وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ (192) }
"ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን)?" [አልአዕራፍ፡ 191-192]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
#My_sister
🌺ኡኽታዬ‼️ጓደኛሽ ማን ናት⁉️
🌺እህትዬ‼️ወዳጅሽ ማን ናት⁉️


ያቺ የፋሽን ዓይነት እያመጣች የምታስለብስሽ
ያቺ በተገናኛችሁ ቁጥር ፎቶ ምትቀርፅሽ
ያቺ በዬ ካፌው እንዝናና የምትልሽ
ያቺ ከዒልም ቦታ
የምታዘናጋሽ
ያቺ اللهን ከማስታወስ የምታርቅሽ
ያቺ ሀያዕሽን አስጠፍታ ፈጣጣነትን የምታስተምርሽ
ያቺ በየመንገዱ walk እንብላ   የምትልሽ
ወይስ ያቺ........ የቷ ነች ያንቺ ጓደኛ እ እህት እ የቷ‼️

♨️ይቺ ከሆነች ጓደኛሽ♨️
   ♨️ እህቴ ተበላሽ♨️
♨️ እህት ንቂ ተመለሽ♨️

🚫 ዛሬ በባጢል ቦታ በባጢል ነገር ላይ የመሰረሽው ጓደኝነት አይደለም ነገ #በአኼራ_ይቅር_እና_ዛሬው_ዱንያ_ላይ_ሳይቀር_ምነው ጓደኛዬ ባትሆን ኖሮ እያልሽ ትፀፀችበታለሽ።

♨️ ስንት እና ስንት ምርጥ ምርጥ እህቶች ነበሩ #በማይሆኑ_ጓደኞች_ተስበው_ከዒልም_መንደር_ባልታሰበ_መንገድ_የጠፉት فكم‼️ والله‼️فكم

    ♨️ ምን ነበር አባባሉ " አህያ ጋር የዋለች ጊደር....... ጨርሽው


ሰምተሽው ይሆን‼️👇👇

ياويلتى ليتني لم أتخذ فلانا خليلا
ወዮልኝ እከሌን ጓደኛ ባላደረኩ ኑሮ

لا حول ولا قوة الا بالله العلي العظيم‼️‼️

🌺 እከሌን ጓደኛ አድርጌ ባልያዝኩ ኑሮ እያሉ መፀፀት እንዳለ ታውቂ ነበር⁉️አዎ እህቴ ዛሬ ላይ አቀማማጭሽን ጓደኛሽን ተመልከቺ❗️

ይልቅ እህትዬ ይቺ ትሁን
ጓደኛሽ👇

ሒጃብን የምታመላክትሽ❗️
ስትር እንድትሆኚ የምታስተምርሽ❗️
ወደ ቂርዓት የምትጎተጉትሽ
ሀያዕን የምታስተምርሽ
መጥፎ የሆነ አመለካከት ስታመጪ አይ አይሆንምይህ ክልክል ነው እንዲህ አይደረግም የምትልሽ❗️
ዲንሽን እንድታውቂ፤እንድትማሪ፤ከባጢል ቦታ ርቀሽ ልታይሽ የምትከጅለው
ባጠቃላይ ከመጥፎ ከልክላ ወደ ኸይር የምታመላክትሽ
ለالله ብላ የምትወድሽ በالله መንገድ ላይ የተገናኘሻት የሆነችዋ

🌺ይቺ ትሁን እህትሽ👆👆

ይቺ ነች አንቺን በالله ፍቃድ የምትጠቅምሽ ፤አኼራን አስታዋሽ፤ሲጠፋሽ አስተማሪሽ፤ስትጣበቢ መካሪሽ፤ሀሳብ ሲጠፋብሽ ሀሳብ ሰጪሽ፤ይቺ ትሁን እህት
ጓደኛሽ‼️

📣 ካልሆነ ግን ውዷ እህቴ👇
#ወዮልኝኝኝኝኝ_ትያለሽ!!

ياويلتى ليتني لم أتخذ فلانا خليلا،لقد أضلنى عن الذكر بعد إذا جآءنى وكان شيطان للإنسان خذولا.

የሴቶች መስተካከል ለቤተሰብ መስተካከል ወሳኝ ነው‼️

የልጅ ትምህርት ቤት እናት ነች‼️

قال الإمام مالك رحمه الله كانت #أمي_تعمموني_وتقول_لي: إذهب إلى ربعة فتعلم من عدبه قبل علمه

قال الشيخ مقبل الوادعي رحمه الله نحن محتاجون إلى #النساء
#الصالحات يقمن الدعوة في أوساط النساء

ሴት ልጅ الله ነፃነትን አውጆላታል!የታወጀላትን ታውቀው ዘንድ ቁርዓን እና ሐዲስን በሰለፎች አረዳድ ትማር ያኔ ነፃነቷን ታውቃለች፤ባጭበርባሪዎችም አትታለልም‼️
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
يرجى الإشتراك بالقناة وإرسال الإعجاب من كل إخوتي وأخواتي في أنحاء العالم لتعم الفائدة بإذن رب العالمين👇👇👇👇
https://youtube.com/@EdrisAwol?si=gNmT2JT_xbWl5OIM


المقصد الوحيد من عبد الضعيف هو إبلاغ التوحيد في جميع أقطاب الأرض شرقا وغربا ـ بواسطة اللغة العربية ولغة الأم الأمهرية ـ بتوفيق رب العرش والسماوات

وبالله التوفيق

أخوكم؛ أبو رسلان من أرض الحبشة
በሸሪዐ ላይ አዳዲስ ኢስጢላሕ እየፈበረኩ በቢድዐህ የሚፈራረጁና ራሳቸውን ወደ ደጋጎቹ ሰለፎች የሚያስጠጉ ቡድኖች መንሀጃቸው ባጢል መሆኑን የምታውቀው እነርሱ ዘንድ ቢድዐህ ከኩፍር ገዝፎ ኩፍርና ካፊሮች ላይ ድምፅ አልባ መሆናቸውን ስታይ ነው።

አላህ ከቢድዐ በላይ መጀመሪያ ያስጠነቀቀው ኩፍርን ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ቢድዐህ ላይ –ለዚያውም ባብዛኛው ቢድዐ ባልሆነ ነገር–  እገሌ ሙመይዕ እገሌ ሙብተዲዕ እያሉ ሲለባለቡ ይውላሉ።

ድሮ ላይ ይሻል ነበር አሁን ላይ እንደ ሰፈር ጉሊት በየመንደሩ ፈልተዋል።በካፊሮች ላይ ግን  አንዳቸውንም ብርቱ ተናጋሪ ሆነው አታገኛቸውም! በድምፅም ይሁን በፅሁፍ ብይናቸውን አይተነፍሱም!

ቢድዐህ ከሌሎች ወንጀሎች የከፋ መሆኑ ግልፅ ነው።ነገር ግን አንድም ሰለፍም ሆነ ኸለፍ ዓሊም ቢድዐህ ከኩፍር ይበልጣል ያለ የለም።

መሰረታዊ የተውሒድ እውቀት የሚያስፈልገው የገጠር ማህበረሰብ ድረስ ሄደው ስለ «ሙመይዕ» ሲያብራሩ ይውላሉ ። መሰረታዊ የዐቂዳ፣ የወላእና የበራእ ርእስ ላይ  ስትጠይቃቸው ግን ሜዳውም ፈረሱም ይጠፋቸዋል።

ፈኢለላሂል ሙሽተካ!

መንቁል!!
#ስራ ክቡር ነው ግን...

ከጥገኝነት ወጥቶ ራስን ችሎ
ለመኖር ደፋ ቀና ማለት በጣም
የሚያስደስትና የሚያኮራ ተግባር
ነው።ሆኖም ግን የምንሰራው ስራ
ሐላል (በዲናችን የሚፈቀድ) እና
ክብራችንን የማይነካ መሆኑን ቀድመን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል!በዚህ ረገድ ሁለት ነገሮች ብዙ ጊዜ ያሰጋሉ

1⃣ ሙስሊም ሴት ፥ በየመንገዱ እና በየሱቆች  ጥግ  ላይ  ቡና  እያፈላች የተለያዩ  አደብ የሌላቸውና አልፎ ሁሉ ግልጽ  የብልግና  ቃላትን  የሚናገር ወንዶችን ቁጭ ብላ ማስተናገድ በጣም ይቀፋል!  ስለዚህ  እህቴ  ሆይ ሌላ ስራ ሞክሪ ዲንና ክብርሽን ጠብቂ!

2⃣ጫት.... ብዙዎችን ከዲን
ያራቀውን የሌሎችን ደግሞ ትዳር
ያፈረሰውን ወይም ያቀዘቅውዘውን
አደንዛዥ እጽ በመሸጥ የሚተዳደሩ ወንድሞች (እንዲሁም ጥቂት የማይባሉ እህትና እናቶች) ጫት ከጎጂነቱ አንጻር  ሐራም (በዲናችን የተከለከለ) ስለሆነ በጫት መተዳደር ለራስም ይሁን ለቤተ-ሰብ ከዲንም ከዱኒያም አንጻር ጥሩ ባለ መሆኑ ሌላ ሐላልነቱ የማያጠራጥር ስራ ልትሰሩ ይገባል።

🔸ሐራም እና ሐላልነቱ አጠራጣሪ
ስራ መቼም በረካ አይኖረውም!የራስንም ይሁን የሌሎችን ዲን ወይም ጤና የሚጎዳ ነገር ሲሆን ደግሞ ከበረካ ማጣቱም ባሻገር
አሏህ ዘንድ ተጠያቂ ያደርጋል!

🔹ከዱኒያ  አንጻር  ከኛ  በታች  ያሉትን እያየን  ልንጽናና  እና  በሐላል  ለማደግ ልንሞክር   ይገባናል  እንጂ  ዲናችንን እየጎዳን  ለመበልጸግ  ልንሞክር አይገባም።

🤲አሏህ ለሁላችንም በረካ ያለው ሐላል ከስብ ያድለን ከሐራም ይጠብቀን "ኣሚን"
https://t.me/UmuNuhBintdarsema