ተውሒድ የሁሉም ነብያቶች ጥሪ ነው።
7.21K subscribers
745 photos
275 videos
45 files
3.65K links
አላህ እኛን የፈጠረን እሱን በብቸኝነት እንድናመልክና በሱ ላይ ምንንም ላናጋራ ነው. መረጃዉም የሚከተለው የአላህ ንግግር ነው: “ጂንና የሰዉን ልጅ አልፈጠርኳቸዉም እኔን እንዲገዙኝ(እንዲያመልኩኝ) እንጂ።” ( ሱራህ አዝ-ዛሪያት 51:56).
ለሀሳብ አስተያየት
@Haymanot_Darsema
Download Telegram
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┄┈┈
│ሱነኑ አቢ ዳውድ سنن أبي داود

🎙የደርሱ አቅራቢ »
│⚊⚊
│» ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም
╰─────────────────╯
🏷በ5 አፕሊኬሽን ተዘጋጅቶ የቀረበ
╭𑁍──────────────
│➺ቁጥር 1 ከሐዲስ 01-1268
🖇 https://t.me/Yusuf_App1/509
├𑁍──────────────
│➺ቁጥር 2 ከሐዲስ 1269-2184
🖇 https://t.me/Yusuf_App1/510
├𑁍──────────────
│➺ቁጥር 3 ከሐዲስ 2185-3203
🖇 https://t.me/Yusuf_App1/511
├𑁍──────────────
│➺ቁጥር 4 ከሐዲስ 3204-4354
🖇 https://t.me/Yusuf_App1/512
├𑁍──────────────
│➺ቁጥር 5 ከሐዲስ 4355-መጨረሻው
🖇 https://t.me/Yusuf_App1/513
╰𑁍──────────────
⎙ አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
↻ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
⎘ ለመሰል ስራዎች ይቀላቀሉን
𑁍
http://t.me/Yusuf_App1
አብሽሩ
.
መርየም እጅግ አስጨናቂው ምጥ ላይ ሆና ‹ ብይ፣  ጠጪ፣ ተደሠቺም … ›  ተባለች፡፡ (መርየም ፡ 26) በጭንቅ ወቅት ምን ምግብ ይበልላል ! እንዴትስ ይጠጣል … ወላሂ ግርምት ነው፡፡
አብሽሪ አይዞሽ አላህ አለልሽ፣ እርሱ ካንቺ ጋር ነው አትፍሪ ማለት ይመስላል ነገሩ፡፡
~ የቱን ያህል በራሣችን ድንበር ብናልፍም፣ በወንጀል ብንጨማለቅም ወደራሱ አስጠግቶ ባሮቼ ሆይ ‹ከእዝነቴ ተሰፋ አትቁረጡ› ይለናል አላህ (ሱ.ወ.)፡፡ ‹ ላ ተቅነጡ ሚን ረሕመቲላህ፡፡›
~ አላህ (ሱ.ወ.) ባሮቹን ለችግርና ለመከራ የተወበት አንድም ጊዜ የለም፡፡ በዱንያ ላይ መከራ ያገኘው ሰው ቢያተርፍ እንጂ የሚከስር አይኖርም - ኢንሻአላህ፡፡
.
እናም ወዳጆቼ … ሕይወታችሁን ተረጋግታችሁ ኑሩ፣ አትፍሩ፣ አትሸበሩ፡፡ የአላህ ፈረጅም ቅርብ እንደሆነ አስቡ፡፡
.
ሰዎች ሲያስቡ እና ሲጨነቁ፣ ሲሸበሩና መላ ሲያጡ፣ መረጋጋት ሲያቅታቸውና መፍትሄ ሲጠፋቸው አይዟችሁ ማለትና በመልካም ነገር ማብሰር አምላካዊም ነቢያዊም መንገድ ነው ፡፡
.
ያልፋል አብሽሩ!
ከስጋት፣ ከፍርሃት፣ ከኪሣራ፣ ከድህነት ትወጣላችሁ … አብሽሩ ..

ይህችን የፈተና ምድር አልፈን ከጀነቱ እንደርሳለን አብሽሩ...
ኮፒ
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
ድንቄም ሰለፍ!
============
ፎቶዋን ለጥፋ በሚድያ ሰፈር፡
ሰለፍ ነኝ  ትላለች አወይ አለማፈር፡
ፎቶ በመለጠፍ ከመንሀጁ አልወጣም፡
ሰለፍ አያደርግም ቀሚሥና ጥምጣም፡

      ጮኸች ውይ እያለች፡
      በእምነቷ ቀለደች፡

እኔም ይህን አልኩኝ፡
በእህቴ እያፈርኩኝ፡

አወ ትክክል ነሽ አንች አልተሣሣትሽም፡
ምክንያቱም አንች መንሀጂ አልተማርሽም፡
በፎቶ ጉዳይም ፈተዋ ሰጥተሻል፡
ከመንሀጂ አትወጭም ኡዝር ይሰጥሻል፡

ግን ይገርማል

ፎቶ መለጠፉ ንቃት ከመሰለሽ፡
የት አወቅሽው እና መንሀጂ መቸ ተማርሽ፡

አንድት ሙሥሊም እንሥት ፎቶ ከለጠፈች፡
መከናነብ ትታ ከተገላለጠች፡
ከነዚያ ከሀድያን በምን ትለያለች ፡
የዋህ ወንድምሽን ለፈተና ዳርገሽ፡
ለብሰው ያለበሱ ነብዩ እንዳላሉሽ፡
ይባሥ ብለሽ ደግሞ ይህ ሣያሣፍርሽ፡
የደረቅ ክርክር ሰለፍ ነኝ ማለትሽ፡
በኢሥላም አለኝታ በድኑ ጠበቆች ፡
ሱና ባነፃቸው በነቢ ሦሀቦች፡
በምድር  ብርሀን በሰማይ ከውከቦች፡

" ጉድ እኮ ነው አሉ ሸሆቹ!

መቸ ገባሽና መቸ ትወጫለሽ፡
መቸ ተማርሽና ሰለፍ ነኝ ትያለሽ፡
በሰለፍዮች ሥም ፊትናን አታሥፋፊ፡
ሰለፍይ ከሆንሽ ፎቶ አትለጥፊ፡

ወይ አንዳንድ  ሴቶች!!

ነገር እንደ አክርማ እየሰነጠቁ፡
ሰለፍ ነኝ ይላሉ መንሀጁን ሣያውቁ፡
አንዳንዶቹ ደግሞ አጥባቂ ሆነዋል፡
ሰለፍ ነን እያሉ ሣይገቡ ወጥተዋል፡
እህቶች በሰለፍ መነገድ ሊያቆሙ ይገባል፡
እንደት በዚህ ተረት መንሀጂ ይገነባል፡
ተገላልጠሽ ቆመሽ ሰውን እየፈተንሽ፡
ሰለፍይ ነኝ ብለሽ ትከራከሪያለሽ?

ከዚሁ መንደር የተገኘ
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
🌧ከምርጥ ሴቶች!!

🇸🇦 ዛቱ ኒጧቀይን(ባለ ሁለት መቀነቷ ) በመባል የምትታወቀዉ አስማእ ቢንት አቡበክር፦ ነብያችንን( ﷺ) አቡበክር ረዲየሏሁ ዓንሁ ከቁረይሾች ሽሽት ዋሻ ዉስጥ በተደበቁ ጊዜ መቀነቷን ለሁለት ከፍላ ስንቅ አስራበት ታመላልስላቸዉ ስለነበር "ዛቱ ኒጧቀይኒ" የሚል መጠሪያ ነበራት።

🇸🇦 አስ ስዲቃ ቢንት አስ ስዲቅ(እዉነተኛይቱ የእዉነተኛዉ ልጅ) ዓኢሻ ቢን አቡበክር አባቷና እሷ እዉነትን በመናገር የታወቁ በመሆናቸዉ የተሰጣት መጠሪያ

🔜ሁለቱም የአንበሳዉ አቡበክር ልጆች ናቸዉ ።ረዲየሏሁ ዓንሁም

https://t.me/UmuNuhBintdarsema
*ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦*

*እኔ የማቀውን ብታቁ ኖሮ ጥቂት ስቃችሁ*
*ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር*


https://t.me/UmuNuhBintdarsema
አብደላህ ኢብኑ ኡመር አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና

ቀዝቃዛ ውሃ ጠጥቶ በጣም የበረታን ማልቀስ አለቀሰ

ለእርሱም ምንድን ነው የሚያስለቅስህ ተባለ
ላቅ ያለውን የአሏህ ሱብሀነሁ ወተአላን አንቀፅ አስታወስኩ አለ
( ----በእነርሱና በሚፈልጉት መካከል ተጋረደ )

የእሳት ሰውች ቀዝቃዛ ውሃን እንጅ ሌላን ነገር እንደማይፈልጉ አወኩ አለ

በርግጥም የተከበርው ጌታችን እንድህ ብሏል َ

(የእሳትም ሰዎች የጀነትን ሰዎች በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ (ጣሉልን) ብለው ይጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል ይሏቸዋል )

አላህ እኔንም እናንተንም ከጀሀነም እሳት ይጠብቀን።

https://t.me/UmuNuhBintdarsema
ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ!

ሰሞኑን ከየመን የተላኩ ጥቂት ኪታቦች ደረሱኝ ። አላህ የዒልም እና የጀነትን መንገድ ያግራለትና አንድ የሱና ወንድሜ ነበር ኪታቦቹን የላከልኝ ።
ከነዚህ ኪታቦች ውስጥ አይኔ አጠር ያለች አንዲት አጭር ሪሳላ ላይ አረፈ ። ርእሱ ልቤን ሳበው ! ሪሳላዋን ላነብ አለቅጥ ጓጓሁ ... ርእሱ በዘመናችን የተንሰራፉ ሁለት የልብ ነቀርሳዎችን መሰረት ያደረገ ነው - ዝናን ማንፍነፍ ! መሪነትን ማሰስ! !

حب الرئاسة والظهور يورث الشقاق والشرور
ይላል ... ፀሃፊው ከየመን መሻይኽ ዉስጥ አንዱ የሆኑት
الشيخ أنيس بن صالح المهندس اليافعي
ናቸው ... ሪሳላዋ ውስጥ በርእሱ ዙሪያ ጠቃሚ እና ልብን የሚያክሙ ገሳጭ ምክሮችን በሰፊው  እናገኛለን

ወላሂ!
ነገሩ ያሳስባል ! ርእሱ እጅጉን ያስጨንቃል !
ለመሆኑ ...
ስንቶቻችን እንሆን እንዲህ አይነቱን በሽታ በልባችን አምቀን ከመልካሞች የምንታሰብ !?

ስንቶቻችን እንሆን ... በመልካም ስራዎቻችን እና ንግግሮቻችን  ዝናን እያነፈነፍን ውለን የምናድር?

ስንቶቻችን እንሆን  እነዚህን ሁለት የኢኽላስ ጠላቶች ተሸክመን ስለ ኢኽላስ የምንሰብከው ? !

ስንቶቻችን እንሆን  ዝናን በማሰስና ፣   መሪነትን በማሰብ ሌሎች ወንድሞች በእኛ ቦታ  የአላህ ቤቶች ውስጥ እንዳያስተምሩ እንቅፋት የምንሆነው ?!!

ስንቶቻችን እንሆን ዝናን እና የበላይነትን  ፍለጋ ሊትተቹ የማይገባቸው አማኞችን አለአግባብ የተቸን ?!

ስንቶቻችን ...

አላህ ይመልሰን

ጀነት በሚፈለግባቸው ስራዎች ከንቱ ዝናን እና መሪነትን መፈለግ ይብቃ!

🖋 ኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ

https://t.me/Muhammedsirage
قال الشيخ ‎عبدالرزاق البدر -حفظه الله- :
★በእኛ ላይ ሀሳቦች አልበዙም።ትካዜዎችና ጭንቀቶችም አልተሰራጩም።ከቁርኣን በመራቃችን ምክንያት ቢሆን እንጂ።

★ እንጂማ"ቁርኣንን በትክክል የያዝን ብንሆን ኖሮ"ወደሱም(ቁርኣን) ቅርብ ብንሆንና ትክክለኛ ማንበብን(ከማስተንተን) ጋር ብናነበው ኖሮ ከሰዎች ሁሉ እድለኞቹ(ስኬታማዎቹ) እንሆን ነበር።

جامع للمؤلفات والرسائل: [297/14]
          

https://t.me/UmuNuhBintdarsema
ወንድሜ

የትም ሆነህ አላህን ፍራው!

በቀን፡በማታ በጫካ፡በገደል በየትም ሁኔታ  ላይ ሁን ጌታህ ያይሀል እና አላህን ከመፍራት ወደ ኀላ አትበል፡፡

አላህን  በትክክል ከፈራሀው

☞ የእውተኛ መለያ ብርሀን ያደርግልሀል
☞ወንጀልህን ያብስልሀል
☞  ይምርሀል

ሰለዚህ ወዳጄ አላህን በመፍራት ላይ ጠንከር በል አደራ !

አላህ  (ﷻ)  አንዲህ  ይለናል 

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن تَتَّقُوا اللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
=>አላህ ይዘንላቸውና ቀታዳ እንዲህ ይላሉ፦

ቁርአን በሽታችሁንም ይሁን መድሃኒቱን ይጠቁማችኋል።

*በሽታው=ወንጀል ሲሆን*
*መድሃኒቱ ደግሞ=ካሳለፉት ወንጅል አላህን ይቅርታ መጠየቅ ነው።*

📚ሹዓቡ_ል ኢማን 9/347

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida

🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
የዱንያ ቀናት መለዋወጥ
.
ቀን አንድም ከፍ፣ አንድም ዝቅ ነውና ነገሮች አስቸጋሪና ከአቅም በላይ ሲሆኑብህ ይህች ዱንያ ከዕለታት በአንዱ ቀን ወስዳ ሰው ፊት ልታቆምህ ትችላለች፡፡ አንተ አልፈልግም ከነችግሬ ልሙት ብትልም ሁኔታህን የሚያውቁና ገቢያችው ከዕለት ጉርሣቸው ያልተረፈ ወዳጆችህ  ከዚህ በላይ መታገስ አንችልም በማለት ገፍተው ወደ አደባባይ ይዘውህ ይወጣሉ፡፡ ስላንተም ሌት ተቀን ይሮጣሉ፡፡
.
ወዳጄ...ገንዘብ የቱን ያህል ቢሆንም፤ በሰው ፊት የመገረፍን ካሳ ፈፅሞ ሊክስ አይችልም፡፡ ‹ እኛ ነን የረዳነው› ከሚለው አሳማሚ ቃል ጀምሮ ‹ ብዙ ተዋጥቶለታል› እስከሚለው በዳይ ንግግር ድረስ የአብግን ሰው ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡
.
አንዳንዴ ፊትህንም ስምህንም አስረክበህ ይሁን ብለህ እጅ በሠጠህ ጊዜ በተደረገልህ ትብብር ችግርህ ሳይቀረፍልህ ሲቀር ካንተ በፊት እጅጉን የሚያዝኑት አስተባባሪዎቹ ይሆናሉ፡፡ ‹ምነው በቀረብን› ሊሉ ሁሉ ይችላሉ፡፡ ብዙ እንቅስቃሴዎች ላይ የዚህ ዓይነት ነገር ገጥሞናል፡፡
.

ኮፒ ከ ABX ቤት
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
በስፖርት ስም የካፊሮችን የበላይነት ለሚመኝ እና ባዳ ሴቶችን እርቃናቸውን ለሚመለከቱ ሁሉ ይድረስ!!
———
ለሙስሊም ወጣቶች አደጋ ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ የተተረጎመ ፈትዋ!!

በዚህን ጊዜ ሴቱም ወንዱም የተዘፈቀበት ትልቁ አደጋ በስፖርት ስም የሚደግፉትን ካፊር ስፖርተኛ እንዲያሸንፍ መመኘትና ካፊር ስፖርተኞችን መውደድ፣ እንዲሁም እርቃናቸውን (በፓንትና ፓካውት) የሚወዳደሩ ሴቶችን መመልከት ነው!!

ለታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ ፈውዛን አል-ፈውዛን አላህ (ይጠብቃቸውና) እንደሚከተለው ጥያቄ ቀረበላቸው:-

የትልቅ ደረጃ ባለቤት የሆኑ ሸይኽ አላህ መልካም ነገርን ይመንዳዎትና ጠያቂው እንዲህ ይላል:-
«በዚህን ጊዜ ብዙ ሰዎች የስፖርት ሚዲያዎችን በመመልከት የተፈተኑበት ነገር ነው፣ ስፖርት ለመመልከት በመሰባሰብና (የሚደግፉት አካል) የበላይ እንዲሆን በመመኘት (በጉጉት ይሰባሰባሉ ይመለከታሉ) በስፖርተኞች መካከል ከሀዲዎችም ይኖራሉ፣ ይህ ከሀዲዎችን ከመውደድ/ከመወዳጀት ውስጥ ይካተታልን?

መልስ:- በስፖርትም ቢሆን እንኳን ከሀዲ የበላይነት እንዲያገኝ ከወደደ  ይህ እነሱን መውደድ ነው። በስፖርት እንኳን ቢሆን ድል እንዲያገኙ ከወደደ ይህቺ ለነሱ ዉዴታ ናት።» ከድምፅ የተተረጎመው መልሳቸው እዚህጋ አበቃ።

ከሀዲን መውደድ ደግሞ አደጋው ከላ! ኢላሀ ኢለላህ (ከእስልምና) አፍራሾች አንዱ ክፍል ለመሆኑ ጥርጥር የለውም!!።

ከሀዲዎችን ከመውደድ አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ በማለት አማኞችን ከልክሏል:-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼንና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡» አል-ሙምተሂና 1

👉🏾 ልብ ይበሉ እኛ ሙስሊሞች ነን ስሜታችንን የሚገጥመንን ነገር ብቻ ፊት ለፊት እያየን ልባችን ሊታወር አይገባውም!!። በማንኛውም ጉዟችን ላይ ይህ ሸሪዓን ይገጥማል ወይስ ይቃረናል ብለን ልናስተውል ግድ ይለናል!!።
በስፖርት ሰበብ (አጅነቢይ) ባዳ ሴትንና ሀፍረተ ገላን ማየቱ ሌላው አደጋ ነው!!
منقول
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
🛑'ነሺዳ ይወዳሉ"?!📛

{ቁርኣንን ከመስማት ይልቅ ግጥሞችን
የመስማት ፍላጎትና ጉጉት ያለው ሰው
የአሏህና የንግግሩ (የቁርኣን)ውዴታ
ልቡ ውስጥ ያለመኖር ትልቅ ምልክት
ነው!} አል-ኢማሞ ኢብኑ ቀይሚል
ጀውዚያ [አል-ጀዋቡልካፊ ገፅ ٢٣٦]

➷ሸይኹ ይህንን ንግግር የተናገሩት
ከስድስት መቶ ዓመት በፊት ነው:-
ዛሬ ሙስሊሙ ወጣት ያለበትን ሁኔታ
ቢመለከቱ ምን ሊሉ ነበር!?

📒ቁርኣን ሲሰሙ ምንም የማይመስላቸው
በነሺዳ ግን የሚያነቡና ኢማናቸው የጨመረ
የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው!

🛑ሸይጣን  አመሳስሎባቸው  እንጂ
በዜማና  በዘፈን  ኢማን  አይጨምርም!
ይልቁንስ  ቀልብ  ይደርቃል  ከቁርኣንም
ይሸሻል‼️

#የዲን_ዕውቀት_የሌላቸው

ባለባበሳቸውም ይሁን በሌሎች ነገሮች
➷ የነቢዩን  صلى الله عليه وسلم

🔺ሱንና የማይከተሉ ባቀራረባቸውም
ከከሃዲያንና ከፋሲቅ ዘፋኞችጋር የሚመሳሰሉና
ልክ እንደነሱም ወንድና ሴት ተቀላቅሎ
በተቀመጡባቸው መድረኮች ላይ እየቀረቡ
በኢስላም ስም ኢስላምን የሚያደፈርሱ
በደዕዋ ስም ወደሌላ ነገር የሚጣሩ
ወገኖች አሏህን ሊፈሩ ይገባል‼️

➴ዲኑን መኻደምፈልገው ከሆነም ቁርኣንና
ሐዲሥን መሰረት ባደረገ መልኩ ሊሆን ይገባዋል!

🛑ዲኑን የማንም መጫወቻ አናድርገው‼️

➷ስሜታችንንም አንከተል ስሜት በዱኒያ
ለጥመት በአኼራ ለእሳት ይዳርጋልና።

اللهم ارزقنا حلاوة كتابك وتلاوته آناء الليل وأطراف النهار

🔷አሏህ ሆይ፦ የቁርኣንን ጥፍጥና ስጠን

➷ቀን  ከሌሊት  በአግባቡ  ከሚያነቡት
       ባሪያዎችህም አድርገን

🔺#ልብ_ይበሉ: ደጋግ ቀደምቶች (ቁርኣንና ዘፈን የአንድ ግለሰብ ልብ ውስጥ አይሰበሰቡም) ይሉ ነበር

📛የዘመኑን  ነሺዳዎች  ከዘፈን መለየት
          በጣም እየከበደ ነው!

ነሺዳን ዘወትር በማድመጥ የተፈተናችሁ
     #ወንድምናእህቶቼሆይ

🛑ነሺዳ  በማድመጥ ለጊዜው ስሜታዊ
ከመሆን ውጪ ያገኛችሁት ጥቅም አለ?!

🔷ቶብቱ ወደ ቁርኣን ተመለሱ
🔷ቁርኣንን በማድመጥ ብቻ ቀልብ ይረጥባል!

🔸ወንጀል ይራገፋል ኢማን ይጨምራል
🔸የአሏህ ውዴታም ይሸመታል።

🍃አሏህ ቀልብ ይስጠን "  ኣሚን !!
          .........................
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥያቄአንድ ሰው ቁርአን ቀርቶ ሲጨርስ አሏህ አዕለም ቢል ችግር አለውን?

  🎙 U𝚜𝚝𝚊𝚣 K𝚎𝚍𝚒𝚛 A𝚑𝚖𝚎𝚍
                            -حَفِظَهُ اللهُ تَعَالَى    

       🌐 T.me/Ustaz_Kedir_ahmed_2
መከራ ያልፈታው ነቢያዊ ሕይወት
እኛና አላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም!

በምድር ላይ እያለን ጉዳት ደርሶብናል፤ ብዙ መከራ አይተናል የምንል ሰዎች እስቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማስተዋል የኛን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሁኔታ እናነፃፅር፡፡ ምን እንደረሰባቸውና ምን እንደደረሰብን እናመዛዝን …

~እናት አባትህ አሉ?
እርሣቸው እኮ ያለ እናትና አባት ነው ያደጉት፡፡ አባታቸው ሳይወለዱ፣ እናታቸው ደግሞ ገና የአምስት እና ስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የሞቱባቸው፡፡
~ ልጆችህን አጥተሃል?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሁሉም ስድስት ልጆቻቸው እርሣቸው በህይወት እያሉ  ሞተዉባቸዋል፡፡ ከሴት ልጃቸው ፋጢማ በስተቀር፡፡
~ሥምህ ጠፍቷል አሊያም ተሰድበሃል፣ ተደብድበሃል?
እርሣቸው እኮ ተሰድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ገጣሚ፣ መተተኛ/ደጋሚ ተብለዋል፡፡ የመካና የጣኢፍ ምድሮችም የሚመሰክሩት ይህንኑ ነው፡፡
~ በቤተሰብህ የመጣብህ ችግር አለ? ባለቤታቸው በመናፍቃን በዝሙት ሥማቸው ጠፍቷል፡፡ በዚህም የእርሣቸውም  የታላቁ ነቢይ ክብር ተነክቷል፡፡
~ዕዳ አለብህ?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሲሞቱ ዕዳ ነበረባቸው፡፡ የጦር ልብሳቸው አንድ አይሁዲ ዘንድ በዕዳ ተይዞ ነበር፡፡
~ ተቸግረህ፣ ተርበህ ታውቃለህ?
ረሱሉ እኮ ከርሃብ የተነሳ ሁለት ሶስት ድንጋዮችን በሆዳቸው ላይ ያስሩ ነበር፡፡ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን እሣት በቤታቸው ሳይቀጣጠል ተምርና ውሃ ብቻ እየተመገቡ ወራትን ያሳልፉ ነበር፡፡
~ ልጅህ ወይም የቅርብ ዘመድህ ተፈታ በሷ ሥነልቦና ተጎድተህ ታውቃለህ? የአላህ መልዕክተኛ እስልምናን በመስበካቸውና የአላህን የሐቅ መንገድ በማሳየታቸው ብቻ ተጠልተው  ሁለት ሴት ልጆቻቸው በባሎቻቸው ተፈተዋል፡፡
~ሳትወድ በግድ ከምትወደው የትውልድ ሀገርህ ተሰደህ ታውቃለህ?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ተከታዮቻውን ይዘው እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ  ተሰደዋል፡፡ ለዓመታትም የስደት ሕይወት ገፍተዋል፡፡ 
~ የግድያ ሙከራ ተደርጎብህ ያውቃል? ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ከአንድና ሁለት ሶስት ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡
~ በአደባባይ ቆሻሻ ተጥሎብህና ተስቆብህ ያውቃል?
ነቢዩ እኮ ሰላት በመስገድ ላይ እያሉ ሱጁድ ላይ ሆነው ቆሻሻ ተጥሎባቸዋል፡፡
~የእምነት ነፃነትህን ተነፍገሃል?
የአላህ መልዕክተኛ ለሶስት አመታት እምነታቸውን ደብቀው ኖረዋል፡፡
~ ማዕቀብ ተጥሎብህ ያውቃል?
ረሱሉ እኮ ለሦስት አመታት ያህል ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ ተደርገዋል፡፡
~ አካልህ ላይ ጉዳት ደርሶ ያውቃል? ነቢያችን እኮ ተፈንክተዋል፣ ጥርሣቸው ተሰብሯል፡፡
.
ምናልባት አንተን እና እኔን አንድ ችግር አግኝቶን ያንኑ ችግር መቋቋም ተስኖን ይሆናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ግን ከነኚህና መሰል ብዙ ችግሮች ጋር  ምንም እንዳልሆኑ ሆነው እያመሰገኑ ደስተኛ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡
ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይሂ
https://t.me/UmuNuhBintdarsema
🛑 livestream 💎

የመጀመሪያው ፕሮግራም  ተጀመረ

ርዕስ
               በጋብቻ ላይ ማነሳሳት!
👇
🎙</ኡስታዝ አቡ ዚክራ>

🌹
    🌹
        🌹
            🌹
                 🌹
ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም ተከታተሉ
ሼር አድርጉት
:

https://t.me/tdarna_islam?livestream
https://t.me/tdarna_islam?livestream
#በትዳር ዉስጥ መናናቅ ካለ መቸም ቤትዉስጥ
ሰላምአይኖርም።
ጡሩእና ብልህ ሚስት  ባሏን አክባሪነች

ይህነየምታደርገዉ እራሷን ስለምታከብርነዉ
#ባለቤቷ ደካማ ቢሆንም ለእርሷ ሞገሷነዉ

አብዝታ ታስብለትአለች ትሳሳለትአለች
በሰለምዉለህግባ ትለዉአለች
#ደክሞ ሲገባ ማረፊያዉነች #ከፍቶት ሲመጣ
ታፅናናዉአለች
#ጡሩ ሚስት እንደ ነብዩ ሶለላሁአለይሂ ወሰለም
ሚስት እንደ ከድጃነች።
#ባሏን በችግር እና  በመከራ ወቅት ታፀናለች።
#አይዞህ በርታ ያልፋልለከይርነዉ ትልህአለች አኩየ! መልካም ሚስት ለባሏ ዘዉድነች የተባለዉ
ለዚህነዉ ።
#እሷም የቤቱ ንግስትነች

#አኩየ መተሳሰብ መቻቻል መተዛዘን  ካለ መናናቅ
አይኖርም ቤትዉስጥ ሰላም ይኖራል

#ስለዚህ ከራስም አልፎ ለልጅች ማሰብ ነዉ

ልጅ ያየዉን ይሰራል አባት ወይንም እናት ሲደርጉ
ሲያይ እነሱን ለመምሰል ይሞክራል።
ይህነገር እዳይፈጠር  ማሰብትልቅነገርነዉ
#እኮን ለትዳርጓደኝ አንድ ሙስሊም አንድ
ሙስሊም ወንድሙን መናቅ  ለክፋትበቂነዉ::
#ብለዉአል የአሏህ መለክተኛ #ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም። ስለዚህ አሏህ ሱበሀነሁ ታእላ ያስተካክለን ።ይ ቀ ጥ ላ ል
https://t.me/tdarna_islam
እህቴ ሆይ፡

  ጊዜያዊ ደሥታ ብለሽ ወንዶችን ወደ ዝሙት የሚጣሩ የማይረባ ልብሥ አትልበሺ
ዛሬ ለትንሽ ደቂቃ የሚያልፍ ሥሜት ብለሽ ነገ የሠው ልጆች አምሣ ሺ አመት ያለ ምግብ ያለ መጠጥ የሚቆሙት ቀን አሥታውሺ የዚህ ቀን መከራ የዚህ ቀን ፈተና መውጣት የምትችዩ የጌታሽን ትዛዝ በዱንያ ላይ ሠምቻለሁ ታዝዣለሁ በማለትሽ እና በመተግበርሽ ነው ምትወጩ
እንጂ
          የአላህን ትዛዝ ጥለሽ ከሩቁ የሚጣሩ አልባሣት እና ና እያለ የሚጣራው የፈረንሣይ ሽቶ በመቀባት አይደለም ያን እናት ልጅዋን ጥላ ነፍሤ ነፍሤ በምትልበት በዛች ቀውጢ ቀን የምትድኙ ዛሬ ላይ ለአሄራ ብለሽ  ባሥቀመጥሽው ሥራሽ ነው።

ወንድሜ ሆይ!
  ምነካህ ሥልጣኔ ነው እያለች የሚያማልሉ ልብሦች ለብሣ ሽቶች እንደ እጣን ታጥና ታኮ ጫማ አርጋ ሸይጣን እየነዳት ምትወጣው እኮ የአንተ ደካማ ጎንህን አይታ ነው ።ታዳ እንዴት ትሸወዳለህ ለዚች የሠው ሸይጣ ከቻልክ መንገድ መቀየር ካልቻልክ አንገትህ ሠብረህ ሂድ ኢንሻላህ በዚህ ተግባርህ እሡዋ አሣማሚ ቅጣት ሥትቀምሥ አንተ የጌታህ ትሩፋት ትታደላለህ ።
አሥተያት አትሥጣት እሥዋ ያሁሉ መሥታወት እና ያሁሉ ቀለሞች ተቀብታ ዝንጀሮ የመሠለችው  የአንተ አሥተያየት ፈልጋ ነው እና አትልከፍ ይህ ከዝሙት ውሥጥ የድርሻህ እየወሠድክ ነው
ጌታችን ሆይ እዘንልን
ጌታችን ሆይ እዘንልን!!
🍃🍃🍃🍃🍃🍃
https://t.me/UmuNuhBintdarsema