የ68 ተማሪዎች ውጤት ተሰርዟል!
🏷በአማራ፣ ደቡብ ፣ ቤኒሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች 846 ተማሪዎች ከፍተኛና ተመሳሳይ የውጤት መመሳሰል በማምጣታቸው ተጨማሪ #ማጣራት እንዲደረግባቸው ተወስኗል። በፈተናው ወቅት በተፈጸመ የደነብ ጥሰት 68 ተማሪዎች ውጤት #መሰረዙም ተገልጿል።
Via #ETHIOFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ለ200ሺህ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት!
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ 200 ሺህ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል፡፡ ሊ ዌይ ፕሮግራም የተሰኘዉ ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ ያለዉን የስራ አጥነት ችግር ይቀንሳል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ የሺወርቅ እንዳስታወቁት፤ ፕሮግራሙ ለቀጣይ 5 አመታት የሚቆይ ሲሆን ሴቶች እና ወጣቶች ወደ ንግድ እንዲገቡ ያስችላል ብለዋል፡፡
በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር የማኅበራዊ ዘርፍ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ በበኩላቸዉ የፕሮጀክቱ ዋነኛ ተጠቃሚዎቹ ሴቶች እና ወጣቶች መሆናቸዉን ገልፀዉ በተለይም የማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች ትኩረት እንደሚደረግባቸው ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የጎዳና ተዳዳሪዎችን በማንሳት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንሰራለንም ብለዋል፡፡ አሁን ላይ ለሀገሪቱ አሳሳቢ የሆነዉን ስራ አጥነት ለመቀነስም ከመንግስት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍም ሊረባረብ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
የሊ ዌይ ፕሮጀክት ለቀጣዮች 5 አመታት ተግባራዊ የሚሆን ሲሆን አሁን ላይ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ንግዱ ለማሳመራት 20 ሚሊዮን ዶላር መመደቡንም ተሰምቷል።