الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌:::::::::::እውነተኛ ፍቅር:::::::::💌

ክፍል 2⃣

#የተከበረችው ኸድጃ በዝሆኖች አቆጣጠር ከ15 አመት ቀደም ብላ ከአባቷ ኩወይሊድ ኢብኑ አሰድ አብድልዑዛ ከእናቷ ፋጡማ ቢንቱ ዛኢዳ ተወለደች፡፡ #ከድጃ ስሩ ከጠለቀ ጫፉ ከዘለቀ ከተከበረ ነገድና ቤተሰብ የተገኘች ናት፡፡ #ከህፃንነቷ ጀምሮ የነገሮችን እውነታ የመከታተልና የማወቅ ጉጉቷ ከዕድሜዋ የላቀ ነበር፡፡ ስለ ንግድ አባቷ ከወንድሞቿ ጋር ሲወያዩ በአትኩሮት ትከታተል ነበር፡፡
ለአቅመ ሄዋን ስትደርስ ብዙ የጋብቻ ጥያቄ ይቀርብላት ጀመር፡፡ #እሷ #ግን በስሜት ተገፋፍታ ለምርጫ አልቸኮለችም፡፡ #ጉዳዩን በጥልቀትና በስፋት በመመርመር ለምትወስደው አቋም ሚዛናዊ መለኪያዎችን መፈለግ ተቀዳሚ ተግባሯ ነበር፡፡ በመጨረሻ ግን አቡሀላህ ኢብኑዚራራህን አገባች፡፡ #ከሱም ህንድና ሀላህ የተባሉ ልጆችን አገኘች፡፡ ከድጃ ከአቡሀላህ ጋር ጥቂት አመታት እንደቆየች በሞት ተለያት፡፡ ከዚያ አቲቅ ኢብኑል ኩዘይምን አገባች፡፡ ከሱም አንድ ልጅ ከወለደች በኋላ አቲቅ በሞት ተለያት፡፡ #ሀብትና #ንብረቱን ወርሳ ተቀመጠች፡፡
ከባሏ ሞት በኋላ የተለያዩ ሰዎች ለጋብቻ ቢጠይቋትም ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ የወንድ አይነት እየተግተለተለ በተለያየ አቀራረብ ደጅ ቢጠናትም ስሜት አልሰጣትም፡፡
#አላህ #በረቀቀ ጥበብና ማንም በማይደረስበት ሚስጥሩ የማንነት መለኪያ የትልቅነት መገለጫ ሆነው ከቀረቡት ነገሮች ሁሉ እጅግ ብልጫ ያለውን መልካም ነገርን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ሰው አዘጋጅቶላት እንደነበር አስባውም አታውቅም፡፡
#ከድጃ #ጣኦት አላመለከችም፡፡በጃህሊያ ከጣኦት አምልኮ እንድትቆጠብ ያደረጋት ለአጎቷ ወረቃ ያላት ቀረቤታ ነው፡፡ ወረቃ ኢብኑ ኑፈይል የነሳራዎች መፅሀፍ ከቅድመ አያቶቹ ስለተሰጠው ይህንን መከተል መርጦ ስለነበር ብዙ ዕውቀቶችን ወደተለያዩ አገሮች ሄዶ ተምሮ ብዙ እውቀት ስላገኘ ከድጃ የባዕድ አምልኮ እንዳትከተልና እንድትጠላ አድርጓታል፡፡ #የተረጋጋች በሳል ተፈጥሮዋ የሰከነ በመሆኑ ሰዎች "ጧሂራ"(ንፅህት) በሚል በልዩ የማዕረግ ስያሜ ይጠሯታል፡፡ #ይህን #ስያሜ ከእስልምና በፊት ያገኘችው ነው፡፡
#አንድ ወቅት ከቁረይሽ ሴቶች ጋር ሆና በጃህሊያ ጊዜ አመታዊ በዓል በሚያከብሩበት የክብር ቦታ ቁጭ ብላ ሳለ አንድ ሰው ሴቶቹ አጠገብ ሲደርስ "እናንተ የመካ ሴቶች በናንተ ከተማ ነቢይ ሊመጣ ነው #ስሙ #አህመድ ይባላል፡፡ ከናንተ የቻለ ያግባው " ሲል ይጮሀል፡፡ #ሴቶቹና ሌሎች ሰዎች ጭምር በድንጋይ እየደበደቡት አባረሩት፡፡ #የተከበረችው #ከድጃ #ስትቀር

❥ሀያት ቢንት ከድር❥

ይ...ቀ....ጥ.... ላ....ል

💌:::::::::Telegram:::::::::::💌


https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
#መልካም_ሚስት
#ሚስት ተጠየቀች ለምንድነው ባልሽ ይህን
ያክል የሚወድሽ?
ካንቺ ውጭ ሌላ ሴት የማያየው?
፦ እንደህ አለች ሚስት
* እርግጥም ይህን ያህል ቆንጆ ሴት አይደለሁም
፦ ነገር ግን ባሌ ባአንድች ነገር ካስከፋኝ ይቅር እለዋለሁ
#ወደኔ አዝኖና ተክዞ ሲመጣ የሆነውን ሁሉ
አይኑን እያየሁ በትኩረት አዳምጠዋለሁ
#ወደቤት ሲመጣ ፈገግ ብዬ ቆሚ
እጠብቀዋለሁ
#ብዙ ገንዘብ ከሰጠኝ በጣም አመሰግናለሁ
#ትንሽ ገንዘብ ከሰጠኝ ደግሞ እብቃቀዋለሁ
እንድህ ነው አላህ ና እረሱል ያዘዙኝ አለቻ
( ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)

🌷#እህቴ ሆይ አንቺም የሷ አይነት ሴት ሁኒ ። ዱኒያዊ ጀነትሽ ያምርልሽ ዘንድ።

#አላህ እኛንም ከመልካሞቹ ያድርገን

💌:::::::::::::::telegram::::::::::::::::💌
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
❥ ::::::ቆንጆ ሴት ማለት :::::::::❥

በዲኗ ጠንካራ የሆነች ፣በዲኖዋ ላይ የማትደራደር፣ ሁል ጊዜ #የአላህን እና #የመልእክተኛዉን ትእዛዝ ለማክበር የምትቻኮል፣

#አላህ ጋር በሚያቃርባት ነገር ሰው ምን ይለኛል ብላ የማትጨነቅ ፣በዲኗዋ በጥንካሬዋ በሲድቅነቷ በአለባበሷ ከኡመተል ሙእሚኒን ጋር የምትመሳሰል፣ የምዕራባወያን ስልጣኔ የማያስደንቃት፣ በሱና የተዋበችዋ ፣ከቀልዷ ቁም ነገሯ የበዛ፣

ዲኗን ለመገንዘብ እፍረት ኩራት የማይዛት #የአላህ ባሪያ የሆነች !!#አዎ ይህች #እንስት ለኔ በቃል የማልገልፃት #ቆንጆ ነች ።እች ለኔ የአኸረ እህቴ ነት

💍።።።።።ቴሌግራማችን👇።።።።።።💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
❥:::::::::ቆንጆ ሴት ማለት :::::::::❥

በዲኗ ጠንካራ የሆነች ፣በዲኖዋ ላይ የማትደራደር፣ ሁል ጊዜ #የአላህን እና #የመልእክተኛዉን ትእዛዝ ለማክበርየምትቻኮል፣ #አላህ ጋር በሚያቃርባት ነገር ሰው ምን ይለኛል ብላ የማትጨነቅ ፣
በዲኗዋ በጥንካሬዋ በሲድቅነቷ በአለባበሷ ከኡመተል ሙእሚኒን ጋር የምትመሳሰል፣ የምዕራባወያን ስልጣኔ የማያስደንቃት፣ በሱና የተዋበችዋ ፣ከቀልዷ ቁም ነገሯ የበዛ፣ዲኗን ለመገንዘብ እፍረት ኩራት የማይዛት #የአላህ ባሪያ የሆነች !!#አዎ ይህች #እንስት ለኔ በቃል የማልገልፃት #ቆንጆ ነች🌹...............እች ለኔ የአኸራ እህቴ ነት
#ሀያት_ቢንት_ኸዲር

💍።።።።።ቴሌግራማችን።።።።።።💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን😭😭😭
ለካ አንዳንዴ ለማፅናናትም የሚከብድ ሀዘን አለ😭
ከ100 በላይ ወገኖቹን በቋሚነት የሚደግፈው #ካሊድ_ናስር ይህንን ፅፎ አነበብኩና ከልቤ አዘንኩኝ😭

"እጅግ ከባድ ሀዘን ምን ብዬ እንደምጀምር አላቅም ብቻ አላህ ያመጣውን መቀበል ነው!ዛሬ ለኔም ለቤተሰቦቼም ለወዳጅ ጓደኞቼ ብቻ የሰው ልጅ ለተባለ ከባድ ሀዘን ነው ውድ እህቶቼ
1.አለም ናስር
2.ረሂም ናስር
3.ሙንተሀ ናስር
4.ዘቢባ ናስር እና ልጇን በመኪና አደጋ አጥቻለሁ።

እነዚህ እህቶቼ ለምሰራው በጎ አድራጎት እንቅስቃሴ በቻሉት ሁሉ በፀሎት ሳይቀር ከጎኔ 24ሰአት የነበሩ ለታናሽ እህቴ የጋብቻ ኒካ ወደ ወልቂጤ በመጓዝ ላይ ሳሉ በደረሰ የመኪና አደጋ 5 ቤተሰቦቼን አሳጥቶኛል😭
የእህቴ ልጅ ሪሀና አብዲም በከባድ ጉዳት ሆስፒታል ትገኛለች ወገኔ የመኪና አደጋ በኛ ይብቃ በኔ የደረሰ ለማንም አያሳየው!!!" ብሎናል😭 #አላህ_ያበርታህ!!
Kalid Nasir

ሁላቹም #ዱኣ_አድርጉለት ወንድማችን አላህ ሶብሩን ይወፍቀዉ በጣም ይከብደል

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
🚫:::::::::የሀራም ፍቅር:::::::::::🚫

ክፍል 3⃣

ሁሉም ሴቶች ሊያነቡት ሚገባ ትልቅ ምክር

እህቶቸ በዚህ ሀራም ፍቅር ግኑኝነት የሚገኙ ወጣቶች ስለናንተ ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ ሴት ልጅኮ ከኛጋ ልክ እንደ ሲጋራ ናት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ታቂያለሽ እንደ ሲጋራ ማለት መጦ መጦ ሲጨርስሽ መሬት ላይ ጥሎ ይረግጥሻል በዚህም አያቆምም
ሌሎች እህቶችሽ ጋ ሂዶ አስቀያሚ ነገሮችን ስላንች ይነግራቸዋል
ይሄ ሁሉ ነገር አንች ላይ እንዲደረግብሽ ካልፈለግሽ ከዚህ የሀራም ፍቅር እራቂ።
የታለ ዲንሽ የታለ ሀያእሽ የታለ ስነ ምግባርሽ የታለ የቤተሰብሽ መልካም አስተዳደግ ሁሉንም ነው የሚያጠፋብን ይሄ ትልቅ ወንጀል ነው
ትንሽም ብትሆን በሀራም ግኑኝነት መጀመር የለባችሁም።

አንዳንድ እህቶች አታካብድ ይሄኮ ቀላል ግኑኝነት ነው ጨዋታና መዝናኛ ብቻ ነው ይላሉ። በፍፁም ቀላል አይደለም በአላህ ይሁንብኝ ይህችን ቀላል ነው የምትለዋን መጨረሻ ብትሰሙ ታዝናላችሁ
አንዷ ግኑኝነት የጀመረችው በቀላል የፌስቡክና የቴሌግራም የፍቅር ቃላቶች ልውውጥ ነበር የጨረሰችው ግን ክብረ ንፅህናዋን ጭራሽ በማጠብቅበት ቦታና ሰዓት ለዚያ ለፌስቡክ ወጣት ነበር ያስረከበችው።
#ሱብሀናላህ
ምክንያቱም ይህ ግኑኝነት የጀመረችው በሀራም ነው።
#አላህ ሱብሀነ ወተዓላ የሸትጧንን ዱካ አትከታተሉ ነው ያለን ለምን ይመስልሻል ምክኛቱም ሸይጧን የሚያዝሽ የቆሻሻና የጥመትን መንገድ ነው ውድ እህቴ ነብያች ሰለላሁዓለይሂ ወሰለም የተናገሩትን ላስታውስሽ ይህችኮ አይን ዝሙትን ትሰራለች ዝሙቷም ሀራምን ማየት ነው።
ይህችም ጀሮ ዝሙትን ትሰራለች ዝሙቷም መጥፎ ነገርን መስማት ነው።
ከዛም በመጨረሻው ሀዲስ ብልትም ወይ እውነት ነው ብሎ ይቀበላል አልያም ይዋሻል።
ውድ እህቶቸ በመጀመሪያ ደረጃ አላህን ልንፍራ ይገባል አላህን እንፍራ የሆነ ቀን ወደድንም ጠላንም ከአላህ ፊት እንቆማለን የሰራነውን እንደምንጠየቅ ማሰብ ይኖርብናል የሰው ልጅ ከሞተ ቂያማው በሱ ላይ እንደሚቆም ማውቅ አለብን ቀብር ደግሞ የመጀመሪያው ቤታችን ነው።
ወይ የጀነት ጮፌ ይነጠፍልናል አልያም የእሳት ስለዚህ ውድ እህቴ ዱንያ የፈለገ እረጅም ብትመስልሽ ባጭር ጊዜ ውስጥ እንደምትጠፋ ማወቅ ይኖርብሻል።
ውድ እህቴ አላህ ሱብሀነወተዓላ መጨረሻሽን አሁን ባለሽበት የሀራም ግኑኝነት እንዲያደርገው ትፈልጊያለሽ በፍፁም አትፈልጊም አይደል ስለዚህ ይሄን የውሽት ፍቅር በእውነተኛው የሀላል ፍቅር ቀይሪው
አንድ ማወቅ ያለብሽ ነገር በሀራም የመጣ ወንድ ልጅ የፈለገ ቢምል ይዋሻል ከመዋሸት ወደኋላ አይልም።
እውነተኛው ሀላልን ፍላጊ ወንድ ወደ ቤተሰቦችሽ ሂዶ ስላንች የሚመለከተው ሰው በሸሪአዊ መንገድ ያናግራል ይጠይቃል የጋብቻንም ጉዳይ በቶሎ ያስጀምራል ።
ነገር ግን በዚህ ሶሻል ሚዲያዎዎች በሜሴጅ በስልክ በፌስቡክ የሚመጣ ወንድ ከመዋሸት እና በራሱም ባንችም ላይ በመጫወት ወደኋላ አይልም
ስለዚህ ውድ እህቴ በደምብ ልታስቢበት ይገባል።
ይሄን ሁሉ የተናገርኩበት ምክንያት ሳታውቁ ትቀራላችሁ ብየ ሳይሆን ለማስታወስ ነው።

#ይቀጥላል
ይቀጥላል

የምትወጃት እህት ካለችሽ ሼር አድርጊላት

💍:::::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
→ክፍል ሁለት←

🍂🌼🍂🌸🍂🌺🍂

↝በሒጃብ ላይ ልዩ ማስታወሻ↜

«እህቴ ሆይ! አንቺ ምናልባትም አሁን በሕይወት እያለሽ የተሟላውን ሒጃብ
ለመልበስና በአግባቡ ለመሸፋፈን ላትፈልጊ ትችያለሽ፡፡ ያው በግልጽ እንደምናየው ሽቶ ተቀባብተሸ ከናፍርሽን ሊፒስቲክ አጥግበሽ፣ ጡትሽን እሹለሽ፣ ደረትሽ ከፍተሽ፣ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣ እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣ ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለብሰሽ የትም እየታየሽ ነው፡፡ ከሩቁ ድብን ብላሽ የሰው ዓይን ውስጥም እየገባሽ ነው፡፡ በእውነቱ ቀበጦቹ ሒጃቢስቶች ዓይነ-ግቡ ለመባል ከፍተኛ ጥረትን እያደረጉ ነው፡፡ ነገር ግን አስታውሺ❗️ አንድ ቀን ከራስ ፀጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ትለብሻለሁ፡፡
ግና የዛኔ ወደመቃብር ነው የምትወርጂው፡፡ ስለዚህ ያንን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ ሒጃብን የምትለብሽበት ዕለት አታድርጊው፡፡ እባክሽን አሁኑኑ ልበሺው ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት ሲባል አልሰማሽም? ገላ ፈራሽ ነው፤ ውበትም ጠፊ ነው፡፡ አዎ! ምንም ያህል ብታምሪ፣ የቱንም ያህል ድብን ብለሽ የወንዶች ዓይን ውስጥ ብትገቢ አንድ ቀን ሟች ነሽ፡፡ እናም ከወዲሁ የኣኼራ ሕይወትሽን ገንቢ። በዱንያ ሳለሽ ለቀበርሽ ስንቅ ያዥ፡፡

ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! ልክ እንደ ሉል ሁኚ፡፡ እንደሚታወቀው ሎል ውድ እና ብርቅ ነው፡፡ ለዚህም የበቃው የተቀመጠበት ቦታ ነው፡፡ ሉል ለፈላጊዎች እሩቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ውድ ሆኗል። አንቺም እንደዚያ መሆን አለብሽ፡፡ በሌላ በኩል እንደዘመኑ ቀበጥ ሒጃቢስቶች እዚያም እዚህ አትታይ፡፡ የትም የሚገኘው እኮ ድንጋይ ነው፡፡ እንደ አበባም እትሁኚ፤ ተጠቅመውብሽ ይወረውሩሻልና፡፡ እናም እንቺ ትክከለኛ ሒጃቢስት ሴት ሁኚ፡ በዚያን ጊዜ ሒጃብሽ መከበሪያሸ ይሆናል፡፡ ምንዳሽም ጀንት ይሆናል።

አስተንትኑ እናንተ የአዕምሮ ባለቤቶች ሞት የማትቀር እውነታ ነች።❗️
እህቴ ከዚህ ውድ መልዕክት እንድትጠቀሚበት ዱዓየ ነው።
ወላሂ እስኪ ቆም ብለሽ እራስሽን ተመልከች ፁሁፉንም በደምብ አስተንትኝው ፁሁፍ በልብሽ ላይ ምንም ተፅዕኖ ካልፈጠረ አሁንም ደግመሽ አምብቢ አሁንም ካልፈጠረ ልብሽ ላይ ችግር አለ ማለት ነው።
አዎ በርግጥ ሁላችንም ላይ ችግር አለ ግን ይሄ እንደቀላል ሊታይ ሚገባው መልዕክት አይደለም በደምብ ከተጠቀምሽበት ህይወትሽን ያሳምርልሻል። ሁላችንም ደስተኛ ለመሆን አይደል የምንለፋው ስለዚህ ወላሂ በዚህ መንገድ ደስተኛ ትሆኛለሽ ማለትም ሒጃብሽን አጥብቀሽ ከያሽ።
እናም እህቴ አደራሽን ተረጋግተሽ ፁሁፉን እያስተነተንሽ አስቢበት ።
እስኪ ራስሽን ጠይቂው ለምንድን ነው ትክክለኛ መስፈርቱን የማያሟላ ሒጃብ ማትለብሽው ከፁሁፍ መጀመሪያ እንደተጠቀሱት አይነት ሴት ሆነሽ አላህን መገናኘት ነው ምትፈልጊው
ማለትም ሽቶ ተቀባብተሸ ከናፍርሽን ሊፒስቲክ አጥግበሽ፣ ጡትሽን እሹለሽ፣ ደረትሽ ከፍተሽ፣ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣ እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣ ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለብሰሽ የትም እየታየሽ ከሩቁ ድብን ብለሽ የሰው ዓይን ውስጥ እየገባሽ። እህቴ እስኪ ንገሪኝ በዚህ ሁኔታሽ አላህን መገናኘት ነው ምትፈልጊው። በእርግጠኛ ነኝ መልስሽ አልፈልግም ነው።
ስለዚህ እህቴ መልስሽ አልፈልግም ከሆነ ተግባርም ጨምሪበት ግዜው አሁን ነው አራስሽን ጠንካራ አድርጊው እና
አላህ እንዳዘዘሽ ቀጥ በይ።
በርግጥ አላህን አጥብቀሽ ስትይዢ ፈተናው ሊበዛብሽ ይችላል ነገር ግን አላህን በፅናት አጥብቀሽ ከያሽ
አላህ ጥንካሬው ይሰጥሻል።
ክፍያሽም ጀነት ይሆናል በአላህ ፍቃድ።

#አላህ_የበለጠ_ያውቃል
በዱዓችሁ አትርሱኝ
አላህ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።
በሃይማኞታችን የሚያስከብረን መሪ
አላህ ይስጠን።
اللهم صل وسلم علي سيدنا محمد
━━━━━✦✿✦━━━━━
👉ይቀጥላል 👉ይቀጥላል

ኢንሻ
አላህ በቀጣይ የሒጃቢስት ሴት ማስታወሻ የሚል አጭር በጣም ደስ የሚል በቁም ነገር የተሞላ ፁሁፍ ይዤላችሁ እመጣለሁ።


ወላሂ አሁን ይሄን መልክት ሼር ሳያደርግ የሚያል ሰው ይኖር ይሆን
ምን አልባት በእምነቱ የሚያፍር ሰው ካልሆነ በቀር ዝም ብሎ ሼር ሳያደርግ ያልፋል ብየ አላስብም።
እስኪ ማነው እኔ በእምነቴ አላፍርም ሃላፊነት ይሰማኛል የሚል
ይሄን መልዕክት በሁለት ግሩፕ ወይም ከዛ በላይ ሼር የሚያደርግ እና በውስጥ መስመር ለ10 ጓደኞቿ የምትልክ።

Co๓๓ent⇢
@Jezakellah &
@Jezakellah

ቀጣዩንና ያለፈው ሌሎችንም አዳዲስ በቁም ነገር የታጀቡ ማስታወሻዎችን ለማምበብ ባጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያገኘውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/latekrebu_zina
Join us on
Telegram channel

👇 👇 👇 👇 👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
👆 👆 👍 👆
→ ክፍል ሦስት ←

💐🍁🍂🌷🍂🍁💐
↝የሒጃቢ ሴት ማስታወሻ↜

ያቺ ትክክለኛ መስፈርቱን አሟልታ የምትለብሰዋ ባለ ሒጃቧ እህቴ ማስታዎሻ ነው። እስኪ አድምጧት ስለለበሰችው ሒጃብ ያስተላለፈችውን መልዕክት
ለለበሱትም ጥንካሬ ይሆናል ላለበሱትም እንዲለብሱ ማስታዎሻ ይሆናል። በአላህ ፍቃድ።

🥀🌾🥀🌾🥀🌾🥀🌾
እናንተ ወደኔ ትመለከቱና እኔን የተጨቆነች ናት ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፤ የዚህ ቀላሉ ምክንያትም እኔ የለበስኩበት መንገድ ነው፡፡ እዝናለሁ፤ እናንተ እኔን የምታውቁኝ ውስጣዊ ለሆነው ማንነቴ አይደለም ይልቁንም እኔ በራስ መተማመን በለበስኩት አለባበሴ ዳኛቸሁኝ ብታውቁ ኖሮ ገላዬ የናንተን ዓይን ለመያዝ ለእኩይ ዕይታችሁ ማረፊያና ወሲብ ቀስቃሽ ሆኖ እንዳልተፈጠረ በተገነዘባቸው ነበር፡፡እውነተኞች ብትሆኑ ኖሮ ለኔ እንስታዊ ቅርፅ ሳይሆን ለአዕምሮዬ ትናገሩ ነበር እኔ አንድ ነፃ ግለሰብ ነኝ፤ የማንም ሰው ባሪያ አይደለሁም ሴት የአላህ ባሪያ ነኝ፤ እኔም አብዝቼ ምጓጓው ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው እኔ ድምጽ አለኝ፤ እናም ልደመጥ እገባለሁ ምክንያቱም በልቤ ውስጥ የርሱን ቃላት ተሸክሚያለሁና፤ እንዴት መልበስ እንዳለብኝም አውቄያለሁ እናም ወንዱ ለኔ በዚህ መንገድ ልበሺ ብሎ ሊነግረኝ አይገባውም ምከንያቱም እኔ የምታዘዘው ከአላህ ለሆነው ሕግ ነውና ጭቆና ፈጽሞ እኔ ያልሆንኩት አንዳች ነገር ነው፣ ነፃነት ከሆነ እኔ ያገኘሁት ነገር ነው እርሱም ለኔ የተሰጠኝ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው እንክብካቤን ከማግኘት መብት ጋር፣ ከማደግ መብት ጋር እኔ ጋራዎቸን ልወጣና ባህሮችን ላቋርጥ እችላለሁ አዕምሮዬን በሁሉም አቅጣጫዎች ማስፋት እችላለሁ፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን እስካልተከተልኩ፤ ተሳስቼ እስካላሳሳትኩ፤ ጠፍቼ እስካላጠፋሁ፡፡ ዓይኖቼን እገልጣለሁ፤ ልቤን ለዕውቀት እከፍታለሁ፤ ገላዬን ደግሞ በሒጃብ እሸፍናለሁ፤ እራሴን አላራቁትም፤ እናንተም አራቁታችሁኝ ልትዝናኑብኝ አልሻም፡፡
💐 💐 💐 💐 💐

አላሁ አክበር❗️
አላህ እንዴት ደስ የሚል ማስታዎሻ ነው።
ይሄ መልዕክት ትክክለኛ ሒጃባቸውን
ለሚለብሱ እህቶች ማስታዎሻ ነው።
ላለበሱትም እንዲለብሱ ትልቅ ማስታዎሻ ይሆናል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።
ሒጃብ ማንኛውንም አይነት ስራ ለመስራት አይከለክልም እንደውም ጥንካሬ ይሰጣል።❗️
ማንኛዋንም መስፈርቱን አሟልታ ሒጃቧን የምትለብስ ሴት ካያችሁ ይሄን ውድ ቃል ተግብራ ነው ማለት ነው።
እና ክብር አይገባቸውም ለነዚህ ውድ እህቶች።
አላህ ፅናቱን ይስጣችሁ።
ወላሂ ይሄ እድለኝነት ነው
አላህ ያዘነላቸው ካልሆኑ አያገኙትም።❗️

ተማሪበት ውድ እህቴ እንደነዚህ ውድ እንቁዎች የመሆኑ እድሉ አሁንም አለሽ ከመሞትሽ በፊት ቀድመሽ ተጠቀሚበት።
እስካሁን ጌታሽን ያመፅሸው ይበቃሻል።
ወላሂ
አላህ ደግሞ ወደርሱ ሚጠጉትን በደስታ ነው ሚቀበላቸው ወንጀልሽን ይምርልሻል።
አብሽሪ ወላሂ ያለፈው ወንጀልሽ ሒጃብ ከመልበስ አይከልክልሽ ትክክለኛ ተውበት አድርገሽ የወደፊቱን ህይወትሽን አሳምሪው ካልሆነ ግን ባለፈውን በቀረውም
አላህ ይጠይቅሻል።

ካለፉት እንማር እህቶቼ ስንቶች አሉ ትክክለኛ ሒጃብ የለበሱ ነገር ግን ያ የለበሱበት ሁኔታ ወደ ቀብር ሲወርዱ ነው።
እህቴ ወደ ቀብር ስትገቢ ተገደሽ ሒጃብ መልበስሽ አይቀርም ነገር ግን በህይወት እያለሽ ለብሰሽው የአላህን ውዴታ አትርፊበት።


#አላህ_የበለጠ_ያውቃል
ባረከላሁ ፊኩም

ያረቢ ከመሞታችን በፊት ንፁህ የሆነችን ተውበት ወፈቀን።
#አላሁመ_አሚን
Co๓๓ent⇢
@Jezakellah

#ኢንሻ_አላህ በቀጣይ የሒጃብ ድንጋጌዎች በሚል እርዕስ በጣም ደስ የሚል በቁም ነገር የተሞላ ፁሁፍ ይዤላችሁ እመጣለሁ።

ሼር እናድርገው አይታወቅም ለእህቶቻችን ለመመለስ ሰበብ ልንሆን እንችላለን ።ከኛ ሚጠበቀው ማድረስ ነው የፈለገውን ሚመራው የፈለገውን ሚያጠመው
አላህ ብቻ ነው።

እስኪ ማነው እኔ በእምነቴ አላፍርም ሃላፊነት ይሰማኛል የሚል ይሄን መልዕክት በግሩፖች እና በውስጥ መስመር ለ10 ጓደኞቿ የምትልክ።

ለመልካም ነገር እንሽቀዳደም በአላህ ፍቃድ በጀነትም ቀዳሚዎች እንድንሆን።❗️
https://t.me/latekrebu_zina

ያለፈውንም የቀረውንም የማይጠገቡ መልዕክቶቻችንን ለማንበብ ቤተሰብ ይሁኑን።

Share SHARE share
ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
Join us on
telgram channel
👇N 👇 O 👇 W

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
→ክፍል አራት←

🌻🥀🍁🌹🍁🥀🌻
↝የሒጃብ ድንጋጌዎች↜

አላህ(ﷻ)ሒጃብን በበርካታ የቁርኣን አንቀጾች አዟል፡፡ የዚህም
ዋናው ምክንያቱ ሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለብሰው ወንዶችን እንዳይፈታተኑ ነው፡፡ ከነዚህም አንቀጾች መካከል ቀዳሚዎቹ በወንዶች የሚጀምሩትና ሱረቱን ኑር ላይ ያሉት ሁለት ተከታታይ አንቀጾች ናቸው፡፡
አላህ(ﷻ)እንዲህ ይላል፡-

↝Surah An-Nur (النّور), verses: 30 ⇩

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا۟ مِنْ أَبْصَٰرِهِمْ وَيَحْفَظُوا۟ فُرُوجَهُمْ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا يَصْنَعُونَ

ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤
አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡

↝Surah An-Nur (النّور), verses: 31 ⇩

ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡(የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት(ባሪያ)ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ
አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡

↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 33 ↷

وَقَرْنَ فِى بُيُوتِكُنَّ وَلَا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ ٱلْأُولَىٰ

በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፡፡ እንደ ፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ፡፡

↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 53 ↷
وَإِذَا سَأَلْتُمُوهُنَّ مَتَٰعًا فَسْـَٔلُوهُنَّ مِن وَرَآءِ حِجَابٍ ذَٰلِكُمْ أَطْهَرُ لِقُلُوبِكُمْ وَقُلُوبِهِنَّ

ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው፡፡ ይህ ለልቦቻችሁ፤ ለልቦቻቸውም የበለጠ ንጽሕና ነው፡፡

ሒጃብ ያስፈለገው ሴቷ ለመሠረታዊ ጉዳዮች ከቤቷ ስትወጣ እንድትታወቅበት፣ ገላዋን እንድትሸፍነት፣ ከወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ እንድትርቅ፣ ውበቷንና ጌጣጌጦቿን ከባዳ ወንዶች እንድትደብቅበት፣ ጨዋነቷን እንድታስመሰክርበት፣ ለባዳ ወንዶች
የተከለከለች መሆኗን እንድታሳይበትና ከባለጌዎች ተንኮል እንድትጠበቅበት ነው፡፡
ይህንኑ አስመልክቶ
አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፡-
↝Surah Al-Ahzab (الْأحزاب), verses: 59 ↷
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّأَزْوَٰجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَآءِ ٱلْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَٰبِيبِهِنَّ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰٓ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና(በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ (ረድየላሁ አንሀ) «ምርጥ ሴት ማለት ያቺ ወንዶችን የማታይና ወንዶችም እርሷን እንዲያዩዋት የማታደርግ ናት» ብላለች፡፡ ይህም ማለት ወንዱ ዓይነስውር ቢሆን እንኳን፣ ልከ እርሱ እንደማያያት ሁሉ እርሷም እርሱን ማየት የለባትም ማለት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ ዓእሻ እና ሀፍሳ (ረድየላሁ አንሁማ) ከነብዩ (ﷺ) ጋር ተቀምጠው ሳሉ ዓይነስውሩ ዐብደሏህ ኡም መክቱም (ረድየላሁ አንሁ)መጣ፡፡
ከዚያም ነብዩ (ﷺ) ለሚስቶቻቸውም፡-
እራሳችሁን ከርሱ ሸፍኑ አሏቸው፡፡ እነርሱም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ታዘናል አሉና (ግን) እርሱ ዓይነስውር ነው፡፡ እናም እኛን ለይቶ ሊያውቀን አይችልም እኮ› በማለት ጠየቋቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ነብዩ(ﷺ እናንተ ግን ዓይነስውሮች አይደላችሁም፤ እናም እርሱን ማየት ትችላላችሁ» አሏቸው፡፡»
(ቲርሚዚ፣ አሕመድና አቡ ዳዉድ)
🍁 🍁 🍁
ያ ኡኽቲ እነዚህ የአላህ ቃላቶች ለኛ ናቸው አጥብቀን ከያዝናቸው በአላህ ፍቃድ ውዷን ጀነትን እንወርስበታለን።
ግን አብዛሃኞቻችን እውነታውን እያወቅን ተዘናግተናል በዚች ዝቅተኛ በሆች ዱንያ ተታለናል ቂያማንም እሩቅ አድርግን አስበናል ይችን አጭር ህይወትም ረጅም አድርገን እያሰብናት አብዛሃኞቻችን ተዘናግተናል።
አላህ ካዘነላቸው ውጭ።

ያ ኡኽቲ የህይወት ዋጋው ምንድን ነው አላህን በመታዘዝና እርሱን ለማግኜት መዘጋጀት ላይ ካልሆነ እ
↝የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) አላሉምንዕ ከናንተ በላጩ አድሜው የረዘመና ስራው ያማረ ነው ከናንተ መጥፎው እድሜው የረዘመና ስራው የከፋ ነው።

እናስተንትን እንጂ ወላሂ ይህች ህይወት ረጅም ብትመስለንም አጭር ናት ባጭር ጊዜ ውስጥ ትጠፋለች።

የምተነፍሽው ትንፋሽም ሊወጣና ላይመለስ ይችላል አይንሽም ትርገበገባለች ዳግም
አላህ ፊት ካልሆነ ላትርገበገብ ትችላለች።
ምንአለ ካንቺ በፊት የሞቱትን ብታስታውሽና ከነሱ ትምህርት ብትወስጂ።
ውድ እህቴ ቀድሞ ከሞተው ትምህርት ያልወሰደ ሌላ በምን ትምህርት ሊወስድ ይችላል። ኧረ እንቃ እህቶቼ ይመሻል ይነጋል ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ናት እስከመቼ ነው? ጊዜው ቆሞ ይጠብቀናል እንዴ ወደ ሞት እየተቃረብንኮ ነው።
አትፈሪም በዚህ ሁኔታሽ መሞት።❗️

እንመለስ ወደ
አላህ ባረከላሁ ፊኩም።

#አላህ_የበለጠ_ያውቃል
አላህ እኔንም እናንተንም በሰማነው ይጥቀመን።
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد
በዱዓችሁ አትርሱኝ
አላህ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን።
☞ኢንሻ
አላህ በቀጣይ↓ #የትክክለኛ_ሒጃብ_መስፈርቶች በሚል ርዕስ አጭር በጣም አስተማሪ በሆነ ፁሁፍ እንገናኛለን።

መልዕክቱን ሼር እንድታደርጉት ማስታወስ ሚጠበቅብኝ አይመስለኝም ምክንያቱም ሃላፊነት እንደሚሰማችሁ አምናለሁ።
እና ለአላህ ብላችሁ ሼር አድርጉት።
የኡመትሽ ሒጃብ አለመልበስ ካሳሰበሽ/ካሳሰበህ፣ የኡመትሽ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስ መልበስ ካመመህ ካመመሽ፣ የኡመታችን ወደ ዚና አብዝቶ መሳብ ካስጨነቀን አሁኑኑ ሼር እናድርገው። ❗️
#ሼር_ሼር_ሼር_ሼር

ማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ ጀዛከላህ በሚለው ሊንክ አናግሩኝ።
@Jezakellah @Jezakellah

https://t.me/latekrebu_zina
የማይጠገበውን ምክሮቻችንን ይግቡና ያምብቡ
አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑን
Join JOIN join
👇 👇 👇 👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
👍 👆 👍
→ክፍል አምስት←

🌹🥀🌼🌺🌸🥀🌹
↝የትክክለኛ ሒጃብ መስፈርቶች↜

አንዲት የተሟላ ሒጃብን የለበሰች ወይም መልበስ የፈለገች እህት በትንሹ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች አሟልታ ሒጃቡን ልትለብሰው ይገባታል።

→①/ ወንዱ ከእምብርቱ እስከ ጉልበቶቹ ያለውን የሰውነቱን ክፍል መሸፈን አለበት፡፡ ለሴቷ ደግሞ መላ ሰውነቷ መሸፈን አለበት፡፡ ሊታይ የሚፈቀደው የሰውነት ክፍሏ ፊቷና እጆቿን ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህንም መሸፈን ከፈለገች መሸፈን ትችላለች፡፡ በተለይ አሁን ፊትናው እንዲህ በተስፋፋበት ጊዜ መሸፈኗ የበለጠ ይበረታታል፡፡

→②/ የምትለብሰው ልብስ ጠባብና የሚያጣብቅ ሆኖ የሰውነቷን ቅርፅ የሚያሳይ መሆን የለበትም፡፡ ከምንም በላይ ልብሷ ወሲብ ቀስቃሽ መሆን የለበትም፡፡

→③/ ልብሱ ብርሃንን የሚያሳልፍና ወደውስጥ የሚያሳይ መሆን የለበትም፡፡

→④/ ልብሱ አብረቅራቂና ተቃራኒ ፆታን የሚስብ መሆን የለበትም፡፡

→⑤/ የምትለብሰው ወይም የሚለብሰው ልብስ ከተቃራኒ ፆታዎች ጋር የሚያመሳስላቸው መሆን የለበትም፡፡

→⑥/ ልብሱ ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር የሚያመሳስል መሆን የለበትም፡፡
🍂 🍂 🍂

ውዷ ባለ ሒጃቧ እህቴ ሆይ የምትለብሽውን ሒጃብ ለአላህ ብለሽ የአላህ ትዕዛዝ መሆኑን አውቀሽ የአላህን ውዴታ ፈልገሽበት ከአላህም ቅጣት ለመዳን ፈልገሽ ከሆነ ከላይ ያስታወስኩሽን የሒጃብ ልብስ መስፈርት አጥብቀሽ ልተገብሪያቸው ግድ ይልሻል።
━━━━━✦✿✦━━━━━
#አላህ_የበለጠ_ያውቃል
اللهم صل وسلم على سيدنا محمد

ኢንሻ
አላህ በቀጣይ #ከሒጃቢስት_ሴት_የሚጠበቁ_ነገሮችን በሚል እርዕስ
በጣም አስተማሪና ብዙዎቻችን የተዘናጋንበትን ደስ የሚል ፁሁፍ ይዤላችሁ እመጣለሁ።

#በምርጡ_በዱዓችሁ_አትርሱኝ

ልታግዙኝና ልታበረታቱኝ ለምትፈልጉ በዱዓና ፁሁፍን ሼር በማድረግ አግዙኝ።
ሼር ማድረግ ግዴታችሁም መሆኑን አትርሱ ስለዚህ ሃላፊነት ሚሰማችሁ ከሆነ አሁኑኑ ባሉሽ ግሩፖችና በውስጥ መስመርም ለምታውቂያቸው እህቶችሽ ሼር አድርጊላቸው።

Co๓๓ent⇢
@Jezakellah

https://t.me/latekrebu_zina
ቤተሰብ ይሁኑን ያለፈውንና የቀረውንም ሌሎችንም የማይጠገቡ ምክሮቻችንን ያምብቡ።

Join us on
telegram channal
⇣ NOW JOIN ⇣

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
→ክፍል ሁለት
🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸
      ( ቦይ-ፍሬንድ  ገርል-ፍሬንድ )

    
       👇 የሀራም ፍቅር 👇
 
             ክፍል ሁለት

↦ሁለተኛው ከባድ ምክንያት ደግሞ ምን ግዜም በሚያወራሽ ነገር ልብሽን ያደክመዋል አንችን የሱ ለማድረግ ቀላል በሆኑ ነገራቶች ያሳምንሻል በፍቅር ስሜታዊ በሆኑ የውሽት የእዝነት ቃላቶችና ፅሁፎች ባጭሩ ያታልልሻል።
ወዳዘጋጀልሽ ወጥመድ ያስገባሻል ያኔ ወደሱ ወጥመድ በገባሽ ግዜም የፈለገውን ነገር ያዝሻል አንችም በፍቅር ስለከነፍሽ ያዘዘሽን ቆሻሻ ነገር ትፈፅሚያለሽ አላህ ይጠብቀን ይሄኔ የሰውም የጅንም ሸይጧን ይጫወትብሻል።

ውድ እህቴ አንችኮ በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ የተቀመጥሽ ንፁህ ነበርሽኮ ለምን እንዲህ ያለ መከራና ስቃይ ውስጥ ትገቢያለሽ ለምን!? ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው በዚህ ሰዓት በእንደዚህ አይነት መከራ ውስጥ የሚገኙ ስንስትና ስንት ሴቶች ናቸው በዛቻ ማስፈራሪያ ውስጥ የሚገኙ ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው ሚስጥራቸው አደባባይ ላይ የወጣባቸው
ስንትና ስንት ሰቶች ናቸው ክብረ ንፅህናቸውንና ማንነታቸውን ያረከሱ
ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው በፀፀትና በቁጭት የሚገኙ ታዲያ ከነዚህ ሁሉ እህቶቻችሁ ትምህርት መውሰድ አትችይም ከነዚህ ሁሉ እህቶች ታሪክ መማር ማገናዘብና ማስተንተን አለብሽ።

እህቶቸ በዚህ ሀራም ፍቅር ግኑኝነት የሚገኙ ወጣቶች ስለናንተ ምን እንደሚሉ ታውቃላችሁ ሴት ልጅኮ ከኛጋ ልክ እንደ ሲጋራ ናት ትርጉሙ ምን እንደሆነ ታቂያለሽ እንደ ሲጋራ ማለት መጦ መጦ ሲጨርስሽ መሬት ላይ ጥሎ ይረግጥሻል በዚህም አያቆምም ሌሎች እህቶችሽ ጋ ሂዶ አስቀያሚ ነገሮችን ስላንች ይነግራቸዋል ይሄ ሁሉ ነገር አንች ላይ እንዲደረግብሽ ካልፈለግሽ ከዚህ የሀራም ፍቅር እራቂ። የታለ ዲንሽ የታለ ሀያእሽ የታለ ስነ ምግባርሽ የታለ የቤተሰብሽ መልካም አስተዳደግ ሁሉንም ነው የሚያጠፋብን ይሄ ትልቅ ወንጀል ነው ትንሽም ብትሆን በሀራም ግኑኝነት መጀመር የለባችሁም።

አንዳንድ እህቶች አታካብድ ይሄኮ ቀላል ግኑኝነት ነው ጨዋታና መዝናኛ ብቻ ነው ይላሉ። በፍፁም ቀላል አይደለም በአላህ ይሁንብኝ ይህችን ቀላል ነው የምትለዋን መጨረሻ ብትሰሙ ታዝናላችሁ አንዷ ግኑኝነት የጀመረችው በቀላል የፌስቡክና የቴሌግራም የፍቅር ቃላቶች ልውውጥ ነበር የጨረሰችው ግን ክብረ ንፅህናዋን ጭራሽ በማጠብቅበት ቦታና ሰዓት ለዚያ ለፌስቡክ ወጣት ነበር ያስረከበችው።
# ሱብሀናላህ ምክንያቱም ይህ ግኑኝነት የጀመረችው በሀራም ነው።
#አላህ_ሱብሀነ_ወተዓላ የሸትጧንን ዱካ አትከታተሉ  ነው ያለን ለምን ይመስልሻል ምክኛቱም ሸይጧን የሚያዝሽ የቆሻሻና የጥመትን መንገድ ነው።
ውድ እህቴ ነብዩ(ﷺ ) ያሉትን ላስታውስሽ
↝አንድ ሰው ወደ ባዳ (እንግዳ/አጅ ነቢ) ሴት (ወንድ) በሚመለከትበት ጊዜ በዓይኖቹ ዝሙትን ይፈጽማል፡፡ የጆሮዎች ዝሙት ወሲባዊ ውይይቶችን ማዳመጥ ነው፡፡ የምላስ ዝሙት ስለወሲብ ማውራት ነው:: የእጅ ዝሙት ያን ያልተፈቀደን መንካት ነው፡፡ እንዲሁም የእግር ዝሙት ወደ አጅነቢ ሴት መጓዝ ነው:: ልብ ዝሙተኝነትን በኃይለኛው ይመኛል፤ እንዲሁም የወሲብ አካላት ድርጊቱን ያጽድቃሉ ወይም ይቃረናሉ፡፡» (ቡኻሪና ሙስሊም)
☞ከባዳ ወንድ ጋር የምትፃፃፊውም ከእጅ ዚና ይቆጠራል።
ከባዳ ወንድ ጋር በስልክ ምታወሪውም ከጆሮና ከምላስ ዚና ይቆጠራል በዚህ ሁሉ ነገር ነገ በቀብራችን ውስጥ እንጠየቅበታለን።
ውድ እህቴ እራስሽን ቀድመሽ ሂሳብ አድርጊ።

የሃራም ፍቅር ክፍል ሦስት
👉ይ ቀ ጥ ላ ል👈

ቻናሉን ተቀላቅላችሁ አምብቡት
ወላሂ መነበብ ያለበት በጣም አስተማሪ ፁሁፍ ነው።
ለብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
ብዙዎችም ፁሁፍን አምበብው ጥንቃቄ እያደረጉ ነው።

ለአላህ ብላችሁ ፁሁፉን በቻላችሁት ሼር አድርጉት
ፁሁፍ አጭር ክፍል ነው ያለው
በክፍል ሦስት ብቻ ያልቃል።


አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን
ይቀላቀሉን ተጫባጭ በሆኑ አዳዲስ እርሶች አሉን ቤተሰብ ይሁኑን እንመካከር

Join us On
telegram channel
https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
👇👆👇👆👇👆👇👇👆
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ

ውድ የቻናላችን ተከታታዩች እንኳን ለኢድ አል-አድሃ /አረፋ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የፍቅር የሠላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

#አላህ_ኢባዳችንን_ሁሉ_ይቀበለን

🌙🌙🌙🌙🌙
عيد مبارك
ኢድ ሙባረክ
Eid mubarek

🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
❥:::::::::ቆንጆ ሴት ማለት :::::::::❥

በዲኗ ጠንካራ የሆነች ፣በዲኖዋ ላይ የማትደራደር፣ ሁል ጊዜ #የአላህን እና #የመልእክተኛዉን ትእዛዝ ለማክበር የምትቻኮል፣

#አላህ ጋር በሚያቃርባት ነገር ሰው ምን ይለኛል ብላ የማትጨነቅ ፣በዲኗዋ በጥንካሬዋ በሲድቅነቷ በአለባበሷ ከኡመተል ሙእሚኒን ጋር የምትመሳሰል፣ የምዕራባወያን ስልጣኔ የማያስደንቃት፣

በሱና የተዋበችዋ ፣ከቀልዷ ቁም ነገሯ የበዛ፣ዲኗን ለመገንዘብ እፍረት ኩራት የማይዛት #የአላህ ባሪያ የሆነች !!#አዎ ይህች #እንስት ለኔ በቃል የማልገልፃት #ቆንጆ ነች.

እች ለኔ የአኸረ እህቴ ነት

💍።።።።።ቴሌግራማችን።።።።💍

t.me/Tidar_Be_Islam
t.me/Tidar_Be_Islam
#አላህ_ሆይ_አንተ_መሐሪ_ነህ፣ ማርታንም_ትወዳልህና_አንተው_ማረን አሚን 🤲🤲

Oh lord Oh Allah please forgive us.

💍::::::ቴሌግራማችን::::::💍

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam🌸🍃
🌊  በባህር የሰጠመችዋ  #ጀግና ሴት ልጅ

     አስገራሚ
#ታሪክ_ነው_ሼር_አድርጉ 👇

ጥብቅ ጨዋ የሆነችው ሙስሊሟ ሴት ገላዋን በአደባባይ አታሳይም ስብእናዋን አታቆሸሽም ክብሯን አታሰደፍርም ለምን የህይወት መስዋእትነት ጭምር አያስከፍላትም በክብር አትደራደርም

#አል_ኸጣብ ዑዳለት አስሰማእ በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እንዳሰፈሩት ከአርባ አመት በፊት በባግዳድ እንሰሳት እያረደ ሥጋ በመሸጥ የሚተዳደር አንድ ሰው ነበር ገና ሳይነጋ በፊት ወደ ሱቅ ይሄድና የሚሸጠውን በግ አርዶ በማዘጋጀት ወደ ቤቱ ይመለሳል ፀሐይ ከወጣች በኋላ ደግሞ ተመልሶ በመውጣት ሱቁን ይከፍታል ያዘጋጀውን ሥጋ ለመሸጥ  #ከዕለታት አንድ ቀን ሌሊት ላይ ሥጋውን አርዶ ሲመለስ በድቅድቅ ጨለማ በመመለስ ላይ እያለ በመንገዱ ላይ ከጨለማ ውስጥ የጨኸት ድምጽ ሰማ ባረደው የበግ ደም ልብሱ ተበላሽቶ ነበር ፈጠን ብሎ ድምፁን ወደ ሰማበት አቅጣጫ አመራ ወዲያውኑ በተደጋጋሚ በጩቤ የተወጋ አንድ ሰው ላይ ወደቀ ሰውዬው ደሙ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሰው ነበር ጩቤውም ሰውነቱ ላይ እንደተተከለ ነው ጩቤውን ነቅሎለት በእጁ ይዞ ሰውዬውን ለመርዳት ብሎ ሊሸከመው ተንደረደረ የስውዬው ደም ልብሱን አጠበው በዚሁ ሁኔታ ላይ እያለ ጨኸት የሰሙ ሰዎች ከያቅጣጫው ተሰባሰቡ ጩቤውን በእጁ ሲያዩና ልብሱ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን በደም የተጨማለቀ መሆኑን ሲመለከቱ እንዲሁም ሰውዬውም የደነገጠ መሆኑን ሲያስተውሉ ሰውዬውን የገደለው እሱሰለመሆኑ እርግጠኛ ሆኑ ከዚያም እንዲገደል ወሰኑበት ግዲያው ወደሚፈፀምበት ቦታም ወሰዱት እንደሚገደል እርግጠኛ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ድምፁንሸ ከፍ አድርጎ ጮኸ #ሰዎች_ሆይ ‼️ወላሂ ይህንን ሰውዬ እኔ አልገደልኩም ነገር ግን ከሀያ አመት በፊት ሰው ገድዬ ነበር በዚህ ወንጀል ምክንያት ዛሬ ቅጣት እየተፈፀመበኝ እንደሆነ ይገባኛል አላቸውና #ታሪኩን ማውጋት ጀመረ

ከሀያ ዓመት በፊት በባህር ላይ ጀልባ ሰዎችን የማመላልስ ወጣት ነበርኩኝ ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሀብታም ወጣት ከእናቷ ጋር ሆነው ወደ ባህር ማዶ ለመሻገር መጡ እኔም አሻገርኳቸው በሁለተኛው ቀንም መጡና ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ አሻገርኳቸው ቀናት አለፉ ልቤ በዚህች ወጣት ላይ ተንጠለጠለ ወደድኳት እሷም ወደደችኝ እንዲድሩልኝ ብዬ ለአባቷ ሽማግሌ ብልክም በድህነቴ ምክንያት ጥያቄዬን ውድቅ አደረጉት ከዚህ እሷም ምን እንደገጠማት አላውቅም ብቻ ቀረች ተጠፋፋን እሷንም ሆነ እናቷን ለረጅም ጊዜ ማግኘት አልቻልኩም ልቤ ግን እንዳፈቀራት ኖረ
#ከሁለት_ወይም_ከሶስት ዓመታት ቆይታ በኋላ ነበር አንድ ቀን ጀልባዬን ይዥ ተሳፋሪዎችን በመጠበቅ ላይ እያለሁ አንዲት ሴት ትንሽ ልጅ ይዛ መጣችና ወደ ዚያኛው ማዶ እንዳሻግራት ጠየቀችኝ ተሳፍራ መሃል ባህር ላይ በደረሰች ጊዜ ተመለከትኳት ያቺ አባቷ የለያየን ሴት መሆኗንም አወቅኩኝ ሰለገኘኋት ደስ አለኝ ያለፈውን ጊዜ አስታወስኳት #ፍቅር መቼስ የማይሸር እዳ ነው እሷ ግን ሰርዓት ባለው መልኩ አናገረችኝ እንዳገባችና የያዘችውም #ህፃን  መሆኑን አስረዳችኝ ቀስ በቀስ ሸይጣን በኔ ውስጥ ሥራውን ይሰራ ጀመር መጥፎ ነገርም አሳሰበኝ ተጠጋኋት ጮኸችብኝ #አላህን እንድፈራ አስታወሰችኝ ሆኖም ግን ማስጠንቀቂያዋ ምንም ግድ አልነበረኝም  እሷ የቻለችውን ያህል ትከላከል ትገፋኝ ጀመር ህፃን ልጇ ያለቅሳል ይህንን ባስተዋልኩ ጊዜ ይበልጥ እልህ ያዘኝ ልጇን ወሰድኩና ወደ ውሃው አስጠጋሁት ፈቃደኝነቷን ካልገለፀችልኝ አሰመጥዋለሁ ብዬ አስፈራራኋት አለቀሰች ለመነችኝ ተማፀነችኝ አልሰማኋትም የልጁን ጭንቅላት ይዥ ውሃ ውስጥ እየነከርኩ እየመለስኩ አስፈራራታለሁ እሷ ታለቅሳለች ትማፀናለች አልራራሁላት ልጁን አጥብቄ ውሃው ውስጥ ነከርኩት ትንሽምአቆየሁት እሷ ታያለች ክስተቱን ላለማየት #ዐይኗን ትሸፍናለች ልጁ ተንፈራፈረ ተልፈሰፈሰ ከውሃ ውስጥ ሳወጣው በድን ሆኗል #ሞቷል በድኑን ውሀሰ ውስጥ ወረወርኩት ከዚያም ተነሳሁና ወደሷ ሄድኩኝ በቻለችው ሁሉ ተከላከለችኝ ጮሃ አለቀሰች ፀጉሯን ይዠ በመጎተት ወደ ውሃ አሰጠጋኋት አየነከርኩ አስወጣታለሁ ደጋግሜ ባደርግም በእንቢተኝነቷ ፀናች በፍፁም አላደርገውም አለች እጄን ሲደክመኝ ነክሬ አቆየኋት እሷም እንደ ልጇ ሁሉ ተንፈራፈረች ከዚያም ፀጥ አለች ሞተች ውሃው ውስጥ ወረወርኳትና ተመለስኩኝ ይህንን ወንጀሌን አንድም ሰው ሳያውቅ ለዓመታት ኖርኩኝ ቢያቆይ እንጂ የማይረሳ የሆነው ጌታ ዛሬ ያለ ወንጀሌ ያዘኝ አላቸው ሰዎች ታሪኩን ሲሰሙ አለቀሱ አንገቱ ተቆርጦ እንዲገደልም አዘዙ #አላህ በዳዮች የሚፈጽሙትን ወንጀል የሚረሳ አይደለም እስቲ የዚህችን ወጣት #እናስተውል ዐይኗ እያየ ልጇ ለፊቷ ተገደለ እሷም ሞተች ይህ ሁሉ ለምን ሆነ #ክብሯን  ከማስደፈርና በዝሙት ከመዋረድ በሞት መገላገልን መረጠች ይህ ከጨዋ ሴቶች ታሪክ መጠነኛ ማሳያ ነው ብዙ ትምህርትም  እናገኝበታለን ።

#አደራ_እህት_ወንድሞቼ
እሄንን ድንቅ አስገራሚ የፀናት ታሪክ ሼር አደርጉ
     ለሙስሊም እህት ወንድሞች እናድርስ

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam🌸🍃
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር በኢስላም´☜   ክፍል ሁለት/ ②ት ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት    ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በነብዩ የተጀመረ እና ኢስላም ብቻ እንደሚፈቅድ አድርገው የጥላቻ ወሬን ለሚነዙ አይሁድና ነሷራ ነን ለሚሉ ሰዎች የንቃት ደወል እንዲሆናቸው በመሻት ያለፉት ነብያት ከአንድ በላይ ያገቡ እንደነበር #ኦሪት እና ወንጌል እያጣቀስን ለማስረዳት እንሞክራለን።ከአባታችን ነብዩላህ ኢብራሂም ዘመን…
☞ትዳር በኢስላም☜

ክፍል ሶስት/ ③

=>ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት..

     ....በዚህም ምክንያት ሳራም ነብዩላህ ኢብራሂም አሰ ልጅ ይወልዱ ዘንድ
#ሀጀርን ዳረቻቸው።ሀጀርን አግብተው ነብዩላህ ኢስማኢልን አሰ ከወለዱ በኃላ #ሳራ የቅናት_መንፈስ አደረባት። ኢብራሂም አሰ ሚስታቸውን ሀጀርን እና ልጃቸውን ኢስማኢልን ከአጠገቧ እንዲያርቁላት ሳራ ጠየቀች። ይግን ጉዳይ ኢብራሂም አሰ ወደ #አላህ አቤት አሉ።
አላህም ወደ አረብ በርሃ ወስደው እዛ እንዲያስቀምጧቸው ፈቃድ ሰጣቸው። ኢብራሂም አሰ ሀጀርን እና ኢስማኢልን ማንም በሌለበት በርሃ አስቀምጠዋቸው ለመመለስ ወሰኑ፣ ለተወሰነ ቀን ከሚሆን ስንቅ ውጭ ጥለዋቸው ሲመለሱ የሚበላም የሚጠጣም በቦታው አልነበረም። ስንቃቸው በማለቁ ምክንያት በተለይ የሀጀር ልጅ ኢስማኢል በውሃ ጥም በመያዛቸው መሬት ላይ እየተንፈራፈሩ እሱ እናታቸው ሀጀር ልጇ ውሃ ጥም ይዞት ሲሰቃይ ላለማየት የምትሆነው ቅጡ ጠፍቷት
#የሚረዳት እና ልጇን_የሚታደግላት አካል ለመፈለግ በሶፋና መርዋ ተራሮች መካከል ሶምሶማ እየሮጠች ሰባት ጊዜ ተመላለሰች
:አንድም አካል ልታገኝ አልቻለችም፣ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች የሆነ ድምፅ ሰማች እሱም ከአላህ ዘንድ የተላከላት መላኢካው ነበር። በአላህ ፈቃድ መላኢካው የዘኝዘም ውሃን በእርሷ እና በልጇ ምክንያት እንዲፈልቅ አደረገው። የሙስሊሞች በሶፋ እና መርዋ መካከል ማረትረታቸው ከዛ የተያዘ ነው።በምድር ላይ ለሰው ልጆች ከተሰጡት ታላላቅ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የዘምዘም ውሃ የመፍለቁ ሰበብ ይቺ
#ሁለተኛ ሆና የተገባች ሀጀር ነበረች
…እንደ መፅሀፍ ቅዱስ አባባል ኢብራሂም ሳራን አግብተው ነብዩ ኢስሃቅን ወለዱ (ዘፍጥረት ምእራፍ  18 አንቀፅ 10)

… …ሀጀርን አግብተው ኢስማኢልን ወለዱ
(ዘፍጥረት ምእራፍ 16 አንቀፅ 4)

……ኬጡራን አግብተው ስድስት ልጅ ወልደዋል
(ዘፍጥረት ምእራፍ 25 አንቀፅ 1)

☞ በአንዳንድ ዘገባዎች እንደሚወራው ነብዩ ኢብራሂም ያገቡት 4 ሴቶችን ሲሆን  ሳራ እና ሀጀር በስም የተጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህ ሁለቱ ሚስቶቻቸው በተጨማሪ ሌሎች ሁለት አግብተው ከአንዷ 6 ወንዶች ከሌላዋ 5 ወንዶች ወልደዋል የሚልም ተወርቷል ነገር ግን
#ኢስላም ስለነዚህ ሁለት ሚስቶች ማረጋገጫ ስላልሰጠን እኛ ሙስሊሞች_አምነን አንቀበለውም ።

⇡መፅሀፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረውና የእምነቱ አስተማሪ ነን ባይዎች በደንብ ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ ይህ ሆኖ ሳለ የእምነቱ ተከታይ ነን የሚሉ ወገኖች የነብዩ ኢብራሂም አሰ የትዳር ህይወት እንደ ሞዴል በመቁጠር ሲያሞካሹት እና ሲያደንቁት ማየት ለማንም አዲስ አይደለም። ሁለት ባል እና ሚስት አዲስ ሲጋቡ ትዳራችሁን የአብሃም እና የሳራ ያድርገው የሚለውን ቃል ከእነዚህ ወገኖች አንደበት ሰምቶ የማያውቅ ጥቂት ሰው ብቻ ነው፣ ታዲያ ይህን ሲያንፀባርቁ ከአንድ በላይ ማግባታቸው በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍሮ እያለ እሱንም እንደዚህኛው ማንፀባረቅ እና ማስተዋወቅ ለምን ከባድ ሆነባቸው???ለምንስ ኢስላም ላይ ጣት መቀሰር አስፈለገ???መልሱን እነሱ ይመልሱ።

……… በእርግጥ የነብያት አባት የሆኑት የነብዩ ኢብራሂም የትዳር ህይወት ከእነሱ የበለጠ ለእኛ ለሙስሊሞች ሞዴል ነው ነገር ግን እኛ ሙስሊሞች  እንደ ሌሎች ወገኖች አንዱንጥለን_አንዱን_አንጠልጥለን ሳይሆን ሁሉንም በኢስላም መነፅር አይተን እንቀበላለን።እንተገብራለንም

     ☞ የነብዩላህ ኢብራሂም አሰ የትዳር ህይወት ለኢስላም ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፣ ሁለተኛ በማግባታቸው በረከት
አላህ ታላላቅ በረከቶችን ለሙስሊሞች ለግሷል።ለማስታወስ ያክል በሶፋ እና መርዋ መካከል 7 ጊዜ ማረትረት፣ የዘምዘም ውሃ መፍለቅ፣ የበይቱላህ መገንባት፣ እና የመሳሰሉት ታላላቅ ታምራቶች የተከሰቱት ነብዩላህ ኢብራሂም ሀጀርንበሳራ ላይ ሁለተኛ በማግባታቸው የመጣ በረከት ነው
ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ነብያት ነብዩላህ ያዕቁብ እና ሌሎችም...

ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜   ክፍል አስር/⑩    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 3/#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና       #በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ   በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል…
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜

 
#ክፍል
...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_
ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ ሰው ይቺ አንድ ሚስት የማትበቃው ከሆነ እና ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያልተፈደቀ ከሆነ አማራጩ አንድና አንድ ነው።እሱም ዲኑና ዱኒያውን የሚያበላሽበትን ፣የሚስቱን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥልበትን አስከፊና አጥፊ የሆነውን
#ዝሙትንና_በሀራም_ መንገድ_ስሜቱን_ማርካት ምርጫው ያደርጋል። አላህ ይጠብቀን የምንሰማውና የምንታዘበውም ነገር ይህንን ያረጋገጠ ነው።ከሚስቱ ውጭ በሀራም መንገድ ሲባልግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ወይም ለሰራተኝነት የያዛት ሴት ላይ ሀራም የሚፈፅም ወይም በሹክሹክታ የሚታማ ሰዎች ዘንድ ቁጥብ መስሎ የሚቀርብ ማንነቱን አዋቂው አላህ ብቻ ነው።በተለይማ ሚስቱ አቅመ ደካማ ወይም ረጅም የወር አበባ የምታይ ወይም ራስ በራስ የምትወልድ ከሆነች እና ለረጅም ጊዜ በወሊድ ደም ላይ የምትቆይ ከሆነች ይህ ሰው ስሜቱ ተቋቁሞ ማለፍ ለእርሱ ከባድ ፈተና ነው። አንዳንድ ጊዜ ካላገቡት ወንዶች የበለጠ በሸህዋ የሚሰቃይ ሊሆን ይችላል።እንደነዚህ አይነቶችን ችግሮች ለመፍታት ሲባል ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ለሰው ልጆች በዝሙት መንገድ ራሳቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደ።
#ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ„ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ትንሽ ምክር ልለግስሽ ወደድኩ፣ የባልሽን ሁኔታ እና ማንነት መገንዘብ ብዙ ይከብድሻል ብዬ አላስብም ባልሽ በአንቺ #በቂ_እርካታ አላገኘም ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ጉዳዩ በደንብ ሊያሳስብሽ ይገባል።ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር ሊያስፈራሽ ይገባል። በመጀመሪያ ባልሽን ለማርካትና ለማስደሰት ባልሽ የሚፈልጋትን ሴት ለመሆን ሞክሪ። ይህን አልፎ በቂ እርካታ የማያገኝ ከሆነ በአንቺ አነሳሽነት ከባልሽ ጋረወ በግልፅ ለመወያየት ሞክሪ ፣የሚፈልገውን ተረጂው ፣ስሜቱን እንዲደብቅሽ አታድርጊ፣የማትረጂው ከሆነ ባልሽ ከአንቺ እየራቀ ሌሎችን ማየት ይጀምራል። #በዝሙት አስቀያሚ መድረክ ታድሞ የዱኒያውንም የአኼራውንም ህይወቱን ከማበላሸቱ በፊት እንዲሁም ማንነታቸው ከማይታወቁ ሴቶች ጋር ተጨማልቆ የአንቺም የቤትሽም ህልውና አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት ልትነቂ ይገባል።
☞ባልሽን ስሜቱን ተረድተሽ ሁለተኛ የሚያስፈልገው ከሆነ ከአንቺ ጋር ተስማሚ፣ለአንቺም ለባልሽም አሳቢ ለዲኗ ተቆርቋሪ የሆነችውን ሴት እንዲያገባ ምከሪው ብቸኛው መፍትሄ
#የአንቺ_ቅንነት ነው። አንዳንድ ባሎች ሚስቶቻቸውን በግልፅ በስሜት እንደማያረኳቸውና ተጨማሪ ሚስተረ ማግባት እንደሚፈልጉ ሲያወያየረዋቸው በአብዛኞቹ ሚስቶች ላይ ቀናነት አይታይባቸውም።እንደውም #ሁለተኛ_የምታገባ_ከሆነ_እኔን_ፍታኝ የሚል ለመስማት የማያስደስት ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ።ለእንዲህ አይነቱ ችግር መፋታት መፍትሄ ያመጣል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፣ይቺ እህት በዚህ ምክንያት ከዚህኛው ባሏ ብትፋታ ቀጥላ ከምታገባው ባሏ ጋር ለመስማማቷ ምን ዋስትና አላት??ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም ምን አልባት ቤተሰብ ተመስርቶ ከሆነ ያን ቤተሰብ አፍርሶ ችግር ላይ መጣል እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል።የሚያሳዝነው አንዳንድ ሙስሊም ተብዬ ሴቶች ከካፊር ሴቶች የወረሱት ነገር ባሎቻቸው በሀላል መንገድ ሁለተኛ ከሚያገባባቸው ከፈለጋት ሴተኛ አዳሪ ጋር እንደፈለገ ቢሆን ደስታውን አይችሉትም።ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ይህ በአላህ ዲን አማኝ ከሆነች ሙስሊም ሴተወ አይጠበቅም፣ይህ ለዲን ተቆርቋሪ ከሆነች ሴት ሊሰማ አይገባም። ይህ የሱሀብይ ሴቶችን ፈለግ ከምትከተል ሴት የሚጠበቅ አይደለም።
7#የመጀመሪያዋ_ሚስት_መውለድ_አለመቻልባል የመውለድ ችሎታ እያለው ሚስቱ በተለያየ ምክንያት አለመውለዷ ቢረጋገጥና ባል ልጅ የመውለድ ፍላጎት ቢኖረው በእነዚህ ሁለቱ ባልና ሚስቶች መካከል ሊከሰት የሚችለው ነገር 2 አማራጭ ብቻ ነው።
ሀ/ ልጅ ወልዶ የሰውየው ዘሩ ወደኃላ ቅሪት እንዲኖረው የማትወልደውን ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት ማግባት
ለ/ የመጀመሪያዋን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ፣ከእነዚህ ሁለት አማራጮች ሊወጣ አይችልም።ነገር ግን የመጀመሪያውን ተግባራዊ ቢያደርጉት በአመዛኙ የተፈታችው ሴት ባል የማግኘት እድሏ የጠበበ ነው።ምክንያቱም የተፈታች እና መውለድ የማትችል ሴት የሚፈልግ ወንድን ፈልጎ ማግኘት በጣም ከባድ ነው እና በዚህም ምክንያት ይቺ ሴት ፈታኝ የህይወት ውጣ ውረድ ሊገጥማት ይችላል።
ማገናዘብ የሚችሉት አብዛኛዎቹ ሴቶች ያለጥርጥር ሁለተኛውን አማራጭ ይከተላሉ። ምክንያቱም ከሞቀ ቤቷ፣የምትከበርበት ቀዬዋ እና ከሚያስብላትና ከሚንከባከባት ባሏ ትታ ወጥታ ያለተንከባካቢ ሜዳ ላይ መውደቅን አትፈልግም።ለእነዚህ መሰል ጥቅሞች ሲባል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ተደነገገ።
☞ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ፣የአላህ ተውፊቅ ሳይሆን ቀርቶ አንቺ ልጅ ለመውለድ ካልታደልሽ መውለድ የሚችለው ባልሽን አይዞህ ብለሽ ከጎኑ በመቆም ነገሮችን አመቻችተሽ በዲኗ ጠንካራ በአኽላቋ ምስጉን፣ልጆችን በተርቢያ ልታሳድግ የምትችል ሚስት እንዲያገባ እገዛ አድርጊለት፣ ይህ ታላቅ ተግባር ነው፣በዚህ ስራሽ ከሰው ጥሩ ነገር አትጠብቂ
#አላህ ግን አጅርሽን እጥፍ ድርብ አድርጎ እንደሚከፍልሽ አትጠራጠሪ።
8#ሚስቱ_ለረጅም_ጊዜ_የሚቆይ_ህመም_ታማሚ_የሆነችበት_ወን   የአላህ ውሳኔ ሆኖ ሚስቱ ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ የሆነችበት ሰው ያለው አማራጭ ከሶስት አንዱ ሊሆን ይችላል።
#አንደኛ_አማራጭ፣ በእድሜ ልኩ እንደሷው ታማሚ ሆኖ ስሜቱን አፍኖ ይዞ ልጅም እንኳን ባይወልድ መካን ሆኖ ዱኒያ በቃኝ ብሎ መኖር ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ በአብዛኛው ሰው ካለመኖሩ በተጨማሪ ኢስላም እንደዚህ ያለ ጭፍን ሰው አምላኪነትን ይቃወማል።አንድ ሰው ስለታመመ የሌላው ሰው ህይወት አላህ በማይወደው መንገድ ማበላሸት የተወገዘ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደዚች ምድር የመጣበት ዋነኛ አላማ አላህ በብቸኝነት መገዛት ነው ፣ህይወቱም ሞቱም እርዱም ስግደቱም ለአላህ ስለሆነ።
#ሁለተኛው_አማራጭ፣ ሚስቱ የረጅም ጊዜ ታማሚ ከሆነች እና ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ዝሙት ዎች የመውደቅ አደጋ ከተጋረጠበት የታመመች ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት አግብቶ የግሉን ህይወት መምራት ሊሆን ይችላል። ይህን ተግባር አንዳንድ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ።ነገር ግን ሌላ አማራጭ የሚኖር ከሆነ አብራው  የኖረችው ሚስቱን አሁን ስለታመመች አሁን መፍታቱ ታላቅ ግፍ ነው።ህ
#ሶስተኛው_አማራጭ፣ የታመመች ሚስቱ በቤቷ እያለች ሌላ ሚስት ፈልጎ በማግባት ሁለቱን በክብር ማስተዳደር ሊሆን ይችላል።ይህ አማራጭ ወደር የሌለው አማራጭ ነው ምክንያቱም ባልም ሚስትንም እኩል ፍትህ ይሰጣል።ባልም ሚስትህ ስለታመመች አብረህ  ተጎሳቆል ብሎ አያስገድድም።ሚስትንም ስለታመመሽና ባልሽን መንከባከብ ስላልቻልሽ ቤቱን ለቀሽ ውጭ ብሎ አያስገድዳትም።
☞ከአንድ በላይ በሸሪዓችን ባይፈቀድ ኖሮ ከላይ ያሳለፍናቸው  አንደኛው ወይም ሁለተኛው አማራጭ ተግባራዊ መሆኑ የሚያጠራጥር አልነበረም።ከአንድ በላይ ባይፈቀድ ኖሮ የዚች ታማሚ ሴት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ነገር ግን
#ሀያሉ
ጌታችን ጥበበኛ ስለሆነ ለወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደላቸው።
#ረመዷን_እና_ቁርኣን_ወይስ_ረመዷን_እና_ነሺዳ

#በትዕግስትና_በእርጋታ_ያንብቡት

ከጥንት ጀምሮ ደጋግ ቀደምቶችና አሏህን ፈሪ ዑለማዎች:-ረመዳን ሲገባ ጥቅልል ብለው ወደ ቁርኣን ይዞሩ ነበር
ኡመቱንም በዚሁ ይመክሩ ነበር፣
አሁን አሁን ግን በኢስላማዊ ነሺዳና መንዙማ ስም ሰዎችን ከደጋግ ቀደምቶች ፈለግ፣ ከሰላሙ የጀነት ጎዳና የሚጠልፉ፣ የዓሊሞችንና የዲን ሰዎችን ልብስ ለብሰው ወደ ዲን ተጣሪ የሚመስሉ በረመዷን ስም እየነግዱ ሰዎችን ከቁርኣን የሚያርቁና የምእምናንን ቀልብ የሚያደርቁ ሰዎች የበዙበት ዘመን ላይ ደርሰናል!

❗️ረመዷን የቁርኣን ወር መሆኑን ከማወቃቸውና በተደጋጋሚም
ከመስማታቸው ጋር አንዴ እንኳ የማያኸትሙ ነገር ግን አዳዲስ
የሚታተሙ ነሺዳ፣ መንዙማ፣
የሱዳን፣ የሶማሌና የዓረብኛ
ዘፈን እየገዙ የሚያደምጡ አላዋቂዎች እጅግ  በጣም ብዙ ናቸው

☞አሁን አሁን ጭራሽ ይባስ
ብለው ታዳጊ ወጣቶችን በጉሩፕና በቡድን እያደረጉ ኢስላማዊ ነሺዳ በሚል ሽፋን (ዘፈን) በየመድረኩ ልክ ዘፋኞች እንደሚሆኑት እየሆኑ ( ጺሙን ላጭቶ ሱሪውን ጎትቶ)የአሏህን እና የመልእክተኛውን ስም ወይም ቁርኣንና ሐዲስ እየጠቀሱ ሲዘፍኑ ማየትና መስማት ጀምረናል

❗️ሴቷም ኢስላም በሐያእና ድምጽን በመቀነስ ላይ እንዳላዘዛት ሁሉ ነሺዳና ግጥም እያለች ድምጿን  እያስዋበችና እየተቅለሰለሰች
የቤተ-ክርስቲያን ዘማሪ/ት ትመስል ድምጿን ለዓለም እየለቀቀች ጌታዋን ታምጻለች
ይህም አንሷት  ወንጀልን በተላመደ አንደበቷ የቁርኣንና ሐዲስ
ጥቅሶችን እየቀነጭበች ትዘፍንባቸዋለች ( ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)
ይህ ተግባሯ አሏህን ከማስደሰት ይልቅ
ሸይጧንን የሚያኮራ መሆኑን ዘንግታለች ወይም የጥመት ጎዳና ላይ በርቺ የሚሏት ኢብሊስ የተጫወተባቸው ሀቅን እያወቁ በመደበቃቸውና የዚህችን ምድር ደስታና ተድላ ከጀነት በማስበለጣቸው ምክንያት ለባጢል ዘበኛ የሆኑ ዓሊም እና ዳዒ ተብዬዎችን ተመክታለች
እንዲህ ዓይነቱን ዘመን ወለድና የጅህልና ውጤት የሆነን ስራ ለህዝብ የሚያደርሱ ሚዲያዎችም ህዝቡን ከቁርኣን በማራቅና ጊዜና ገንዘቡን በማይረባ ነገር በማቃጠሉ ወንጀል ተጋሪዎችና ተጠያቂዎች ናቸው!

❗️ከመቼ ጀምሮ ነው ዘፈን ዒባዳና
   የዳዕዋ መንገድ የተደረገው?!
❗️ለዚህስ ማነው እውቅና የሰጠው?!
❗️ማንስ ነው ነሺዳን የዘፈን ምትክ ያደረገው?!

❗️ዘፈን ትቼ ነሺዳ አደምጣለሁ የሚል ሰው ምሳሌው ነጃሳን በሽንት አጥባለሁ እንደሚል ሰው ነው "
(ሸይኽ ዶ/ ሳሊሕ አልፈውዛን )
📚ሸርሕ ኢጛሰቱልለህፋን

እናንተ ሙስሊሞች ሆይ፥
አሏህን ፍሩ ጭቃ ቤት ለማሰራት
አናጺና ባለሙያ እንደምታማክሩት ሁሉ የጀነት ቤት ለማግኘት የሚያበቃችሁን እምነትና ዐቂዳችሁን በተመለከተ ሞኞችና ግዴለሾች አትሁኑ

#ዓይን#ጆሮ☞ልብ ወዘተ አሏህ እናንተ ዘንድ አደራ ያስቀመጣቸው ጊዜያዊ መጠቃቀሚያዎች ናቸው
ነገ አሏህ ዘንድ የሚያስጠይቅን ነገር አትስሩባቸው

ነሺዳና መንዙማ ከስሜት ጋር ስለሚሄዱና የካፊሮችን ሙዚቃና ዘፈን ስለሚተኩ ጥሩ ነው እያልክ/ሽ አታድምጥ/ጪ❗️

☞እንደቁርኣን ልብን   
  የሚያረጥብ ነገር በጭራሽ የለም

☞ኢብኑ ተይሚያና ኢብኑል ቀይም የሚከተለውን ብለዋል
("በግጥም/በአንጉርጉሮ ልቤን አረጥባለው ማለት ልብ ላይ የአላህ ውዴታ ያለመኖሩ ምልክት ነው ")

ልቡ ላይ የጌታው ትክክለኛ ውዴታ ያለ ሰው ቁርኣንን ትቶ በሰው ንግግር ልቡን ማከም አያስብም

☞ቁርኣን ያላቃነው ምንም አያቃናውም
☞ከቁርኣንና ሐዲስ ውጪ ያሉ ነገሮች በሙሉ ጥመት ናቸው!
ጥመትን ማስዋብና የዲን አካል አድርጎ ማሳያት የሸይጣን ስራ ነው!

❗️
#ሙነሺዶች_ሆይ:- አላህን ፍሩት በሰጣችሁ ጊዜና ድምጽም ነገ የማያስወቅሳችሁን ነገር ስሩበት
በዲን አትነግዱ የወጣቱን ጉልበት በማይረባ ነገር አታቃጥሉት ከቁርኣንም አታርቁት
ለዲኑ በትክክለኛው መንገድ የሆነን  ነገር ማበርከት ካልቻላችሁ ጥግ ይዛችሁ የግላችሁን ኑሮ ኑሩ ሐላል ከስብ ፈልጋችሁ ነግዱ፣
ዲኑን እየተጻረራችሁ ለዲን እንሰራለን አትበሉ
ከምንም በላይ ለናንተ የሚያሰጋኝ ነገር ቢኖር (ሱረቱ ሁድ ቁጥር 18 እና 19 )ላይ የተጠቀሰው ውግዘትና እርግማን እንዳይደርስባችሁ ነው

❗️ንቁ/ አዋጅ የአላህ እርግማን በደለኞች ላይ ይሁን እነዚያ ሰዎችን ከአላህ መንገድ  የሚያዞሩት ላይ }
ሰዎችን ከቁርኣን ማራቅ ከአላህ መንገድ ማረቅ መሆኑ መንም ጥርጥር የለውም

❗️ቁርኣና ነሺዳም የአንድ ሙእሚን ልብ ላይ እንደማይሰበሰቡ አዋቂዎች ዘንድ ምንም ጥርጥር የለውም!

❗️የጥንት የጠዋቱን እጅግ ጠቃሚውን"ሺዕር/ የዓረብኛ ግጥም" ከዘመኑ ነሺዳ ጋር የምታመሳስሉና ሺዕር ስለሚቻል ነሺዳም ይቻላል የምትሉ አስተማሪዎች ሆይ፥ የሁለቱን ልዩነት አስተውሉ! የማይመሳሰለውን አታመሳስሉ ሐቅንም ከባጢል ጋር አታቀላቅሉ!

በዘመኑ ነሺዳ ዙሪያም ታላላቅ የዲን መሪዎች ምን እንዳሉ ዝቅ ብላችሁ አጥኑ!

#አላህ_ሁላችንንም_ቀናውን_መንገድ_ይምራን! የሐቅን ውዴታም ይለግሰን!አሚን🤲🤲

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
ብዙ ጊዜ ሴቷም አላህ ሷሊህ ባል እንዲሰጣት ትፈልጋለችም ትለምነዋለችም!!!! ወንዱም ሷሊህ ሚስት አላህ እንዲሰጠው ይፈልጋልም ይለምነዋልም!!!! ግን ሁለቱም ጋ የተዘነጋ አንድ ምስጢር አለ እሱም:- "ሁለቱም አስቀድመው በውጫቸውም በውስጣቸውም፣ በአንደበታቸውም በተግባራቸውም
ሷሊህ ሆኖ መገኘት" ዋናው ነገር ይህ ነው!!።
#አላህ በሁለመናችን ሷሊህ ያድርገን!!!አሚን

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam