الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸

👉👉ክፍል አንድ👈👈

👉ውድ እህቴ ለአላህ ብለሽ አምብቢው ምን አልባት አንቺ ከዚህ የሀራም ፍቅር ግኑኝነት እርቀሽ ሊሆን ይችላል ግን ብዙ እህቶችሽ ገብተውበታል
እናም ላንችም እውነታውን እውቂው እህቶችሽንም የማስታወስ ግዴታ አለብሽ።
👉መጥፎ ሲሰራ እያየን ዝም ካልን የአላህ ቁጣ ለኛም ይተርፋል።
ነገም በአላህ ፊት እንጠየቅበታለን።
በቀላሉ መልክቱን በቻልነው ሼር ለማድረግ እንሞክር የኛ ግዴታ ማስታወስ ነው የፈለገውን መምራት የፈለገውን ማጥመም የአላህ ስራ ነው።
☞ አንቺ ጠልተሽው እርቀሽው ላንቺ የጠላሽውን ለእህቶችሽም እስካልጠላሽ ድረስ ሙሉ አማኝ ልትባይ አትችይም እናም ፅፍሁፉን በውስጥ መስመርም ሼር በማድረግ ግዴታችንን እንወጣ።
መልክቱ አንገብጋቢና ወቅታዊ ችግር ነው በትግስት አምብበሽ ቆም ብለሽ ማገናዘብ ይኖርብናል።
ፅሁፉ ስለረዘመብኝ በክፍል አምስት ለመጨረስ ሞክሪያለው

👇የሀራም ፍቅር👇

ክፍል አንድ ①

ውድ እህቴ የሀራም ፍቅር ግኑኝነትን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ብዙ እህቶችሽ እየተፈተኑበት የሚገኙው ከባድና አስቸጋሪ ፊትና ነው አሁን ባለንበት ዘመን የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተበራክተዋል ለምሳሌ ዋሳፕ ፌስቡክ ኢሞ ቴሌግራም እና መሰል ሚዲያ አፖች በነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከሚመጡ ፊትና እራስሽን ማራቅ ይኖርብሻል።
ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ እህቶች በነዚህ ሶሻል ሚዲያዎች ከተለያዩ ወጣቶች ጋር የሀራም ፍቅር ግኑኝነት ፈጥረዋል
ለምን እህቶች ተብለው ሲጠየቁ ምን ችግር አለው ለቀልድ ለመዝናናት እና ጊዜ ለማሳለፍ ብቻ ነው ብለው ይመልሳሉ
ይሄንንስ የሀራም የቀልድ ግኑኝነት እንድትቀርቢው ማን ነው የፈቀደልሽ
ውድ እህቴ ይሄ ሀራም ነው ሀራም ነው።
እድግመዋለው ሀራም ነው አላህን ፍሪ።
እንዲህ አይነቱ የሀራም ፍቅር ግኑኝነት በጥብቅ የተከለከለ ነው እስከዛሬም ወደፊትም በሸሪዓው አልተፈቀደም።
እንደውም ከከባባድ ወንጀሎች ሊመደብ ይችላል ምክኛቱም እህቴ ያን ሚስኪን ወጣት በለስላሳው ድምፅሽና አንደበትሽ ተስፋን ሰጠሽ ፍተና ላይ ትጥይዋለሽ
በአላህ ይሁንብኝ ስንትና ስንት ወጣቶች ናቸው በሀራም ቆሻሻ ተግባራቶች ላይ የወደቁት ምክንያቱን ሲናገሩ እንደምንሰማው በእከሌ ምክንያት ተፈትኜ እከሌ ፊት ባትሰጠኝ እከሌ ባታማልለኝ ኖሮ እንዲህ አልሆንን ነበር ይላል
እና መሰል የፊትና ሰበቦች ከፊታቸው እያመጣሽባቸው ስለሆነ ነው።
ወድ እህቴ ከየትኛውም አይነት ወጣት ጋር የሶሻል ሚዲያ ሀራም ፍቅር ግኑኝነት ሚባለውን በጣም ልትጠነቀቂው ይገባል በጣም ተጠንቀቂ በቃ ፍቅር አይደለም ብለሽ ልታወሪም አይገባም መንገዱን ዝጊው።

#የመጀመሪያው እውነታ አድምጭኝ ውድ እህቴ አንችን ሊወድሽ ይችላል ግን ካንችም ውጭ አስር ሌሎች ሴቶችንም ይወዳል ይህ ማለት አንችም ላይ ይጫወታል ካንችም ውጭ ብዙ ሴቶች ጋር ግኑኝነትን ይፈጥራል።
ይህ የመጀመሪያው እውነታ ነው።

#ሁለተኛው ደግሞ ምንም ጋብቻ ሚባለውን ነገር አያስበውም አላማውም ግቡም የለውም ይህ ማለት ወደ ጋብቻ አይገፋፋሽም ሀሳቡም የለውም እንደውም ካንች ጀርባ ሁኖ ስላንች ብዙ ያወራል።
ከኔ ውጭ ሌላ ውንድ ጋር እያወራች ከሀዲ ናትኮ እያለ ስምሽን ያጠፈዋል ግን በተዘዋዋሪ እሱም አንችን ይከዳሻል።

#ይቀጥላል
ይቀጥላል

ለአላህ ብለን ሼር እናርገው ቢያንስ በውስጥ መስመር ለምናውቃቸው እንላክላቸው።

ሼር ሼር


💍::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
→ክፍል አንድ
🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸🩸
   ( ቦይ-ፍሬንድ  ገርል-ፍሬንድ )

    
       👇 የሀራም ፍቅር 👇
 
ወላሂ መነበብ ያለበት በጣም አስተማሪ ፁሁፍ ነው። አልሃምዱሊላህ ለብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል። ብዙዎችም ፁሁፍን አምበብው ጥንቃቄ እያደረጉ ነው።

ውድ እህቴ ለአላህ ብለሽ አምብቢው።


             ክፍል አንድ ①

ውድ እህቴ የሃራም ፍቅር ግኑኝነትን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ብዙ እህቶችሽ እየተፈተኑበት የሚገኙው ከባድና አስቸጋሪ ፊትና ነው አሁን ባለንበት ዘመን የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተበራክተዋል ለምሳሌ ዋሳፕ ፌስቡክ ኢሞ ቴሌግራም እና መሰል ሚዲያ አፖች አሉ በነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከሚመጡ ፊትና እራስሽን ማራቅ ይኖርብሻል።
ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ እህቶች በነዚህ ሶሻል ሚዲያዎች ከተለያዩ ወጣቶች ጋር የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ፈጥረዋል ለምን እህቶች ተብለው ሲጠየቁ ምን ችግር አለው ለቀልድ ለመዝናናት እና ጊዜ ለማሳለፍ ብቻ ነው ብለው ይመልሳሉ። ውድ እህቴ ይሄንንስ የሃራም የቀልድ ግኑኝነት እንድትቀርቢው ማን ነው የፈቀደልሽ  ውድ እህቴ ይሄ ሃራም ነው። አላህን ፍሪ!
እንዲህ አይነቱ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት በኢስላም በጥብቅ የተከለከለ ነው እስከዛሬም ወደፊትም በሸሪዓው አልተፈቀደም። እንደውም ከከባባድ ወንጀሎች ሊመደብ ይችላል ምክኛቱም እህቴ ያን ሚስኪን ወጣት በለስላሳው ድምፅሽና አንደበትሽ ተስፋን ሰጠሽ ፍተና ላይ ትጥይዋለሽ  በአላህ ይሁንብኝ ስንትና ስንት ወጣቶች ናቸው በሃራም ቆሻሻ ተግባራቶች ላይ የወደቁት ምክንያቱን ሲናገሩ እንደምንሰማው በእከሌ ምክንያት ተፈትኜ እከሌ ፊት ባትሰጠኝ እከሌ ባታማልለኝ ኖሮ እንዲህ አልሆንን ነበር ይላል።
እና መሰል የፊትና ሰበቦች እያመጣሽባቸው ስለሆነ ነው።
ወድ እህቴ ከየትኛውም አይነት ወጣት ጋር የሶሻል ሚዲያ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ሚባለውን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል በጣም ተጠንቀቂ ፍቅር አይደለም ብለሽ ልታወሪም አይገባም መንገዱን ዝጊው።
ትዳር ፈልገሽም ከሆነ በዚህ በሃራም ምንገድ መሆን የለበትም።ብዙዎች ትግስት እያጡ ወደ ሃራም ይሄዳሉ ማወቅ ያለብሽ ነገር በሃራም የጀመርሽው ግኑኝነት ልታገቢው ብትችይ እንኳ ለትዳርሽ ጥፍጥናን አታገኝም።

በዚህ የሃራም ፍቅር ውስጥ የተደበቀውን እውነታ እነግርሻለሁ በደምብ አድምጪኝ

👉
#የመጀመሪያው_እውነታ  አንችን ሊወድሽ ይችላል ግን ካንችም ውጭ አስር ሌሎች ሴቶችንም ይወዳል ይህ ማለት አንችም ላይ ይጫወታል ካንችም ውጭ ብዙ ሴቶች ጋር ግኑኝነትን ይፈጥራል።
ይህ የመጀመሪያው እውነታ ነው።

👉
#ሁለተኛው_እውነታ ደግሞ ምንም ጋብቻ ሚባለውን ነገር አያስበውም አላማውም ግቡም የለውም ይህ ማለት ወደ ጋብቻ አይገፋፋሽም ሀሳቡም ግቡም የለውም እንደውም ካንች ጀርባ ሁኖ ስላንች ብዙ ያወራል። ከኔ ውጭ ሌላ ውንድ ጋር እያወራች ከሃዲ ናትኮ እያለ ስምሽን ያጠፈዋል ግን በተዘዋዋሪ እሱም አንችን ይከዳሻል።
 
👉
#ሥስተውኛ_እውነታ አንችን የሱ ባሪያ ወይም ምርኮኛ የሚያደርግብሽ በሁለት ከባባድ ምክንያቶች ነው።
↦አንድኛው ያንች ፎቶዎች ካሉት ይህ ወንድ ልጅ የሚያስፈራራብሽ የመጀመሪያው ከባድ ሰበብ ነው።
ይሄኔ አንች አቋምሽን እያለወጥሽ ትመጫለሽ ምክኛቱም ሌላ ነገር ለማድረግ አትደፍሪም እሱ የያዘብሽ ሚስጥራዊ ፎቶ ስላለ ትፈሪያለሽ።
እና እባካችሁ ተጠንቀቁ እህቶች ፎቶ መላላክ ይቅርባችሁ እባካችሁ ለማንም ፎቶ አትላኩ ሌላው ይቅርና የምትቀርቢያትና የምታምኛት ጓደኛሽ እንኳ ብትሆን ፎቶሽችን እንዳትልኪላት እስካሁን ከነበረም አስጠፊ ምክንያቱም በገዛ ፎቶሽ አሳልፋ ልትሰጥሽ ትችላለች።
በያዘችብሽ በገዛ ፎቶሽ ልታስፈራራሽ ትችላለች ፎቶ መላላክ ጭራሽ አስፈላጊ አይደለም በፍፁም ለማንም ፎቷችሁን መላክ የለባችሁም አንችን ከናፈቀችሽ ቤትሽ መጣ ትይሽ ከዛ ውጭ ፎቶ መላላክ አስፈላጊ አይደለም።
አሁኑኑ ማስጠፋት ይኖርብሻል አምናታለው ብለሽ አትሸወጂ ታማኝ ልትሆን ትችላለች ግን ጥሩ ነገር መስሏት ወይም እሷ ሳታውቅ ከሷ ስልክ ሌላ ሰው ሊወስደው ይችላል ለዚህ ደግሞ አንች እርግጠኛ መሆን አትችይም።  ስለዚህ ነገሩን በማስረዳት ማስጠፋት ይኖርብሻል።

የሃራም ፍቅር ክፍል ሁለት
👉ይ ቀ ጥ ላ ል👈


ለብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
ብዙዎችም ፁሁፍን አምበብው ጥንቃቄ እያደረጉ ነው።

ለአላህ ብላችሁ ፁሁፉን በቻላችሁት ሼር አድርጉት
ፁሁፍ አጭር ክፍል ነው ያለው
በክፍል ሦስት ብቻ ያልቃል።


አዲሱን የቴሌግራም ቻናላችንን
ይቀላቀሉን ተጫባጭ በሆኑ አዳዲስ እርሶች አሉን ቤተሰብ ይሁኑን እንመካከር

Join us On
telegram channel
👇👇👇 👇👇👇

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w

https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜   ክፍል አስር/⑩    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 3/#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና       #በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ   በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል…
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜

 
#ክፍል
...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_
ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ ሰው ይቺ አንድ ሚስት የማትበቃው ከሆነ እና ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያልተፈደቀ ከሆነ አማራጩ አንድና አንድ ነው።እሱም ዲኑና ዱኒያውን የሚያበላሽበትን ፣የሚስቱን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥልበትን አስከፊና አጥፊ የሆነውን
#ዝሙትንና_በሀራም_ መንገድ_ስሜቱን_ማርካት ምርጫው ያደርጋል። አላህ ይጠብቀን የምንሰማውና የምንታዘበውም ነገር ይህንን ያረጋገጠ ነው።ከሚስቱ ውጭ በሀራም መንገድ ሲባልግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ወይም ለሰራተኝነት የያዛት ሴት ላይ ሀራም የሚፈፅም ወይም በሹክሹክታ የሚታማ ሰዎች ዘንድ ቁጥብ መስሎ የሚቀርብ ማንነቱን አዋቂው አላህ ብቻ ነው።በተለይማ ሚስቱ አቅመ ደካማ ወይም ረጅም የወር አበባ የምታይ ወይም ራስ በራስ የምትወልድ ከሆነች እና ለረጅም ጊዜ በወሊድ ደም ላይ የምትቆይ ከሆነች ይህ ሰው ስሜቱ ተቋቁሞ ማለፍ ለእርሱ ከባድ ፈተና ነው። አንዳንድ ጊዜ ካላገቡት ወንዶች የበለጠ በሸህዋ የሚሰቃይ ሊሆን ይችላል።እንደነዚህ አይነቶችን ችግሮች ለመፍታት ሲባል ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ለሰው ልጆች በዝሙት መንገድ ራሳቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደ።
#ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ„ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ትንሽ ምክር ልለግስሽ ወደድኩ፣ የባልሽን ሁኔታ እና ማንነት መገንዘብ ብዙ ይከብድሻል ብዬ አላስብም ባልሽ በአንቺ #በቂ_እርካታ አላገኘም ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ጉዳዩ በደንብ ሊያሳስብሽ ይገባል።ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር ሊያስፈራሽ ይገባል። በመጀመሪያ ባልሽን ለማርካትና ለማስደሰት ባልሽ የሚፈልጋትን ሴት ለመሆን ሞክሪ። ይህን አልፎ በቂ እርካታ የማያገኝ ከሆነ በአንቺ አነሳሽነት ከባልሽ ጋረወ በግልፅ ለመወያየት ሞክሪ ፣የሚፈልገውን ተረጂው ፣ስሜቱን እንዲደብቅሽ አታድርጊ፣የማትረጂው ከሆነ ባልሽ ከአንቺ እየራቀ ሌሎችን ማየት ይጀምራል። #በዝሙት አስቀያሚ መድረክ ታድሞ የዱኒያውንም የአኼራውንም ህይወቱን ከማበላሸቱ በፊት እንዲሁም ማንነታቸው ከማይታወቁ ሴቶች ጋር ተጨማልቆ የአንቺም የቤትሽም ህልውና አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት ልትነቂ ይገባል።
☞ባልሽን ስሜቱን ተረድተሽ ሁለተኛ የሚያስፈልገው ከሆነ ከአንቺ ጋር ተስማሚ፣ለአንቺም ለባልሽም አሳቢ ለዲኗ ተቆርቋሪ የሆነችውን ሴት እንዲያገባ ምከሪው ብቸኛው መፍትሄ
#የአንቺ_ቅንነት ነው። አንዳንድ ባሎች ሚስቶቻቸውን በግልፅ በስሜት እንደማያረኳቸውና ተጨማሪ ሚስተረ ማግባት እንደሚፈልጉ ሲያወያየረዋቸው በአብዛኞቹ ሚስቶች ላይ ቀናነት አይታይባቸውም።እንደውም #ሁለተኛ_የምታገባ_ከሆነ_እኔን_ፍታኝ የሚል ለመስማት የማያስደስት ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ።ለእንዲህ አይነቱ ችግር መፋታት መፍትሄ ያመጣል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፣ይቺ እህት በዚህ ምክንያት ከዚህኛው ባሏ ብትፋታ ቀጥላ ከምታገባው ባሏ ጋር ለመስማማቷ ምን ዋስትና አላት??ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም ምን አልባት ቤተሰብ ተመስርቶ ከሆነ ያን ቤተሰብ አፍርሶ ችግር ላይ መጣል እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል።የሚያሳዝነው አንዳንድ ሙስሊም ተብዬ ሴቶች ከካፊር ሴቶች የወረሱት ነገር ባሎቻቸው በሀላል መንገድ ሁለተኛ ከሚያገባባቸው ከፈለጋት ሴተኛ አዳሪ ጋር እንደፈለገ ቢሆን ደስታውን አይችሉትም።ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ይህ በአላህ ዲን አማኝ ከሆነች ሙስሊም ሴተወ አይጠበቅም፣ይህ ለዲን ተቆርቋሪ ከሆነች ሴት ሊሰማ አይገባም። ይህ የሱሀብይ ሴቶችን ፈለግ ከምትከተል ሴት የሚጠበቅ አይደለም።
7#የመጀመሪያዋ_ሚስት_መውለድ_አለመቻልባል የመውለድ ችሎታ እያለው ሚስቱ በተለያየ ምክንያት አለመውለዷ ቢረጋገጥና ባል ልጅ የመውለድ ፍላጎት ቢኖረው በእነዚህ ሁለቱ ባልና ሚስቶች መካከል ሊከሰት የሚችለው ነገር 2 አማራጭ ብቻ ነው።
ሀ/ ልጅ ወልዶ የሰውየው ዘሩ ወደኃላ ቅሪት እንዲኖረው የማትወልደውን ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት ማግባት
ለ/ የመጀመሪያዋን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ፣ከእነዚህ ሁለት አማራጮች ሊወጣ አይችልም።ነገር ግን የመጀመሪያውን ተግባራዊ ቢያደርጉት በአመዛኙ የተፈታችው ሴት ባል የማግኘት እድሏ የጠበበ ነው።ምክንያቱም የተፈታች እና መውለድ የማትችል ሴት የሚፈልግ ወንድን ፈልጎ ማግኘት በጣም ከባድ ነው እና በዚህም ምክንያት ይቺ ሴት ፈታኝ የህይወት ውጣ ውረድ ሊገጥማት ይችላል።
ማገናዘብ የሚችሉት አብዛኛዎቹ ሴቶች ያለጥርጥር ሁለተኛውን አማራጭ ይከተላሉ። ምክንያቱም ከሞቀ ቤቷ፣የምትከበርበት ቀዬዋ እና ከሚያስብላትና ከሚንከባከባት ባሏ ትታ ወጥታ ያለተንከባካቢ ሜዳ ላይ መውደቅን አትፈልግም።ለእነዚህ መሰል ጥቅሞች ሲባል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ተደነገገ።
☞ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ፣የአላህ ተውፊቅ ሳይሆን ቀርቶ አንቺ ልጅ ለመውለድ ካልታደልሽ መውለድ የሚችለው ባልሽን አይዞህ ብለሽ ከጎኑ በመቆም ነገሮችን አመቻችተሽ በዲኗ ጠንካራ በአኽላቋ ምስጉን፣ልጆችን በተርቢያ ልታሳድግ የምትችል ሚስት እንዲያገባ እገዛ አድርጊለት፣ ይህ ታላቅ ተግባር ነው፣በዚህ ስራሽ ከሰው ጥሩ ነገር አትጠብቂ
#አላህ ግን አጅርሽን እጥፍ ድርብ አድርጎ እንደሚከፍልሽ አትጠራጠሪ።
8#ሚስቱ_ለረጅም_ጊዜ_የሚቆይ_ህመም_ታማሚ_የሆነችበት_ወን   የአላህ ውሳኔ ሆኖ ሚስቱ ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ የሆነችበት ሰው ያለው አማራጭ ከሶስት አንዱ ሊሆን ይችላል።
#አንደኛ_አማራጭ፣ በእድሜ ልኩ እንደሷው ታማሚ ሆኖ ስሜቱን አፍኖ ይዞ ልጅም እንኳን ባይወልድ መካን ሆኖ ዱኒያ በቃኝ ብሎ መኖር ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ በአብዛኛው ሰው ካለመኖሩ በተጨማሪ ኢስላም እንደዚህ ያለ ጭፍን ሰው አምላኪነትን ይቃወማል።አንድ ሰው ስለታመመ የሌላው ሰው ህይወት አላህ በማይወደው መንገድ ማበላሸት የተወገዘ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደዚች ምድር የመጣበት ዋነኛ አላማ አላህ በብቸኝነት መገዛት ነው ፣ህይወቱም ሞቱም እርዱም ስግደቱም ለአላህ ስለሆነ።
#ሁለተኛው_አማራጭ፣ ሚስቱ የረጅም ጊዜ ታማሚ ከሆነች እና ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ዝሙት ዎች የመውደቅ አደጋ ከተጋረጠበት የታመመች ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት አግብቶ የግሉን ህይወት መምራት ሊሆን ይችላል። ይህን ተግባር አንዳንድ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ።ነገር ግን ሌላ አማራጭ የሚኖር ከሆነ አብራው  የኖረችው ሚስቱን አሁን ስለታመመች አሁን መፍታቱ ታላቅ ግፍ ነው።ህ
#ሶስተኛው_አማራጭ፣ የታመመች ሚስቱ በቤቷ እያለች ሌላ ሚስት ፈልጎ በማግባት ሁለቱን በክብር ማስተዳደር ሊሆን ይችላል።ይህ አማራጭ ወደር የሌለው አማራጭ ነው ምክንያቱም ባልም ሚስትንም እኩል ፍትህ ይሰጣል።ባልም ሚስትህ ስለታመመች አብረህ  ተጎሳቆል ብሎ አያስገድድም።ሚስትንም ስለታመመሽና ባልሽን መንከባከብ ስላልቻልሽ ቤቱን ለቀሽ ውጭ ብሎ አያስገድዳትም።
☞ከአንድ በላይ በሸሪዓችን ባይፈቀድ ኖሮ ከላይ ያሳለፍናቸው  አንደኛው ወይም
ሁለተኛው አማራጭ ተግባራዊ መሆኑ የሚያጠራጥር አልነበረም።ከአንድ በላይ ባይፈቀድ ኖሮ የዚች ታማሚ ሴት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ነገር ግን #ሀያሉ
ጌታችን ጥበበኛ ስለሆነ ለወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደላቸው።
#ስለ_ሻዕባን_ወር_አጫጭር_ጥቆማዎች ☜

☞ በሸይኽ ሙሐመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን
#ሙስሊሞች_ሆይ_ያለነው_በሻዕባን ወር ላይ ነውና በዚህ ወር ዙርያ አንድ ስድስት ነጥቦችን በማውሳት ልንከተለው ስለሚገባን ግዴታችን እናብራራለን።

1)☞
#የመጀመርያው_ነጥብ
የሻዕባን ወር ከሌሎች ወራት በተለየ ሁኔታ በፆም ይለያልን? አዎን ይለያል ። ምክንያቱም ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በዚህ ወር ፆም ያበዛሉ። ከወሩ ጥቂት ቀናት እስኪቀራቸው ወሩን ይፆሙት ነበርና።»
በዚህም ሱና መሰረት የአላህ መልእክተኛን [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] በመከተል በዚህ በሻዕባን ወር ፆም ማብዛት አለብን።

2)☞
#ሁለተኛው_ነጥብ
የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ፆምን የተመለከተው ነው። ይህንን ቀን ለይቶ መፆምን የሚመለከቱ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኙና ትክክለኛ ያልሆኑ ደካማ ሀዲሶች ተነግረዋል። በነዚህ ተመርኩዞ ይህንን ዒባዳ መፈፀም ደግሞ አይቻልም። ከነቢዩ ለመተላለፉ ባልተረጋገጠ ማንኛውም ነገር አላህን ማምለክ አይፈቀድም። በመሆኑም የሻዕባን አስራ አምስተኛው ቀንን ለይቶ መፆም የሌለ ነገር ነው። ከመልእክተኛው ለመገኘቱ መረጃ ከሌለ ደግሞ ቢደዐ ነው።

3)☞
#ሶስተኛው_ነጥብ፤ የሻዕባን ወር አስራ አምስተኛው ቀን ሌሊት ትሩፋትን ይመለከታል።
ልክ ቀኑን መፆም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለው ሁሉ ለሌሊቱም ከሌሎች ሌሊቶች በላጭ ነው ተብለው የተነገሩት ሀዲሶች ከነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለመነገራቸው ትክክለኛ መረጃ የሌላቸው ደካማዎች ናቸው።
ስለሆነም የሻእባን አጋማሽ ሌሊት ልክ እንደ ረቢዕ ወር ሌሊት፣ እንደ ረጀብ ወር ሌሊት እንጂ የተለየ ነገር የለውም። ተነገረ የተባለውም መረጃ ቀድሜ እንደገለፅኩት ደካማዎች ናቸው።

4)☞
#አራተኛው_ነጥብ
ይህችን የአስራ አምስተኛዋን ሌሊት ለየት አድርጎ ዝግጅት ፈጥሮ ማሳለፍ ቢደዐ ነው። ነቢዩ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ለየት አድርገው ያሳዩን፣ ሌሊቱን የሚሰገድ አምልኮትም ዝግጅትም የለምና። ስለዚህ ምሽቷ ልክ እንደ ሌሎች ምሽት ናት። አንድ ሰው ከዚያች ሌሊት በፊትም የለይል ሰላት መስገድ ልምዱ ከነበረ በዚያች ሌሊትም ተነስቶ መስገዱ ልክ እንደበፊቱ ነውና ችግር የለውም። ካልሆነና በፊት የማይሰግድ ከነበረ ዛሬ በሻዕባን "ለይለቱ ኒስፍን" ለየት አድርጎ መስገድ የለበትም። ምክንያቱም ከአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያልተገኘ ተግባር ነውና። ከዚህም የከፋው ደግሞ አንዳንዱ ሰው የሆነ ያህል ረከዓ በዚህ ምሽት ይሰገዳል በሚል ለየት ያደርገዋል። ይሁንና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን ምሽት ነጥሎ ለየት ማድረግ ስላልተገኘ ይህችን ምሽት በሰላት ልዩ አናደርግም።

☞5)☞
#አምስተኛው_ነጥብ
የአላህ ሱብሃነሁ ለነገሮች የሚያደርገው ውሳኔ በሻዕባን አስራ አምስተኛዋ (አጋማሽ) ምሽት ነውን

ምላሹም አይደለም ሲሆን፤ ምሽቷም የመወሰኛይቱ ሌሊት [ለይለቱል ቀድር] አይደለችምና ነው። ምክንያቱም "ለይለቱል ቀድር" በረመዳን ውስጥ የምትገኝ ምሽት ናት። ሃያሉ አላህ እንዳለው፤
”إنا انزلناه“
☞እኛ አወረድነው" ማለትም ቁርኣንን ለመጀመርያ ግዜ ያወረድነው ማለቱ ነው። ይህም ሙሉ ምዕራፉ ሲነበብ እንዲህ ይላል፤

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ ﴿١﴾ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ ﴿٢﴾ لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ ﴿٣﴾ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ ﴿٤﴾ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ ﴿٥﴾
Al-Qadr☞ القدر:- [1-5]

☞እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡ (1)መወሰኛይቱም ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? (2)መወሰኛይቱ ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ (3) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ (4) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡(5)]
ይህ ክስተትና ምሽቱም መቼ እንደሆነ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤

(شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖوَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّـهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّـهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ) البقرة:- 185

(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት፡፡ አላህ በእናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፡፡ በእናንተም ችግሩን አይሻም፡፡ ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ ታከብሩትና ታመሰግኑት ዘንድ (ይህን ደነገግንላችሁ)፡፡ (185)]

በዚህም መረጃ መሰረት ለይለቱል ቀድር ማለትም ፈጣሪያችን አላህ ለማንኛውም ነገር ሁሉ አመታዊ ውሳኔ የሚሰጥበት ምሽት በረመዳን ወር ውስጥ የምትገኝ አንዲት ሌሊት መሆኗን እንረዳለን። ምክንያቱም ሌሊቷ ቁርኣን የወረደባት ሌሊት ነች ። ቁርኣን ደግሞ የወረደው በረመዳን ወር ነውና የመወሰኛይቱ ምሽትም የምትገኘው በረመዳን እንጂ በሌላ ወር አይደለም። ስለሆነም የሻዕባን አጋማሽ ሌሊት  "ለይለቱል ቀድር" የመወሰኛይቱ ምሽት አይደለችም። በዚያች ሌሊትም ለአመቱ የሚሆን ምንም የሚወሰን ነገር የለም።

6)☞
#ስድስተኛው_ነጥብ፦ የሻዕባን ወር አጋማሽ ቀን ላይ አንዳንዶች ምግብ አዘጋጅተው ለድሆች በሚል የሚያከፋፍሉትና የእናት እራት፣ የአባት እራት ወይም የወላጆች እራት የሚሉት [እንዲሁም ባገራችን የእህል ዘሮችን ባንድ ላይ ሰብስቦ በመቀቀልና ከዚያም መጀመርያ ግቢ ውስጥና ውጪም በመበተን አመቱ የጥጋብ የርጋታ ይሁንልን የሚሉት] ሁሉ ከነቢዩ ያልተላለፈልን ከሰሃቦችም ሪድዋኑላሂ አለይሂም ያልተገኘ መጤ የሆነ ቢድዐ ነው።

#እነዚህን_ስድስት_ነጥቦች ጠቅሼ ብቆጥራቸውም ሌሎች ላብራራቸው የሚገቡ ሆነው ያለፍኳቸው እንዳሉ ግልፅ ነው።  አላህ እኛንም እናንተንም ሱናን የሚያሰራጩ፣ ቢድዐን የሚያስጠነቅቁና ተመርተው የሚመሩ (ቅን ሆነው የሚያቀኑ) ያድርገን። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በጁምዓ ኩጥባቸው ወቅት እንደገለፁት ከምሪቶች ሁሉ በላጩ የሳቸው ምሪት ነውና ቅኑን መንገድ የሚከተሉ፣ በሳቸው አመራርም የሚመሩ ያድርገን። «በማስከተል፤ ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው። ከአመራሮች ሁሉ በላጩም የሙሀመድ ምሪት ነው። መጥፎ ጉዳይ ማለት መጤዎቹ ናቸው። ሁሉም ፈጠራዎች ጥመት ናቸውና።»ብለዋል።
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam