The Christian News
5.32K subscribers
3.06K photos
27 videos
720 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ቤተክርስቲያኒቱ_ለ800_አቅመ_ደካሞች_ድጋፍ_አደረገች
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

አራራ ዋቃዮ አለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ800 አቅመ ደካማ ሰዎች የምግብ እህል ድጋፍ አደረገች።

በነብይ መሰረት ታዬ አማካኝነት የተቋቋመችው ቤተ ክርስቲያኒቱ 500 ሺህ ብር የሚገመት ብር ወጪ አድርጋ ለ800 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪ.ግ የእህል ዱቄት ነው የለገሰችው።

ከዚህ ቀደም በግጭት ምክኒያት ለተፈናቀሉ, በረሃብ ምክኒያት ለተቸገሩ ሰዎች ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች።

የነቀምት ከተማ አስተዳደር ሃላፊ ቤተክርስቲያኒቱ በነቀምት ለድሆች ባደረገው ድጋፍ አመስግነው ድሃ ቤተሰብን መርዳት የእግዚአብሄርን እና እግዚአብሔርን የሚወዱትን ስራ መስራት ነው ብለዋል።

በእለቱም ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ቤተርስቲያኒቱን አመስግነዋል ሲል የነቀምት ኮሙኒኬሽን ቢሮን ጠቅሶ ያስነበበው OBN ነው።
#እንኳን_ደስ_አላችሁ!!!

ገሊላ ኢንተርናሽናል ሴሚናሪየም ከ100 በላይ የመጀመሪያ ድግሪ እና ሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸዉን ተማሪዎች በአዲስአበባ ምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እያስመረቀ ነዉ።

የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የታደምን ሲሆን ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#የማይቀርበት_ቀጥሎ
#ቢሾፍቱ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በቢሾፍቱ ከተማ ለምትገኙ ቅዱሳን በሙሉ መልካም ዜና እነሆ🙏🙏🙏

ዛሬ እና ነገ በኢያሱ ሜዳ ከተወዳጅ አገልጋዬች ጋር ልዩ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በቢሾፍቱ ወንጌላዉያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ተዘጋጅቷል።

ዛሬ ቅዳሜ ከ11:ዐዐ ጀምሮ
ነገ በትንሳኤው ቀን ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ የክርስቶስን ትንሳኤ በአደባባይ የሚታወጅበት ሰዓት ነዉና ሁላችሁም እንድትገኙ እና አብረን እንድናመልክ ግብዥችንን እናቀርባለን።
ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ዘላለማዊ ፍቅሩና ምህረቱ ለሰው ልጆች ሁሉ የተገለጠበት ታላቅ በዓል ነው።

በመሆኑም መላው ክርስቲያኖች ይህንን በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ሥርዓት በድምቀት ያከብሩታል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላቸው እየተመኘ በዓሉ የሰላም ፤ የደስታ ፤ የመከባበር እና የአብሮነት እንዲሁም ለተቸገሩ እና ለታረዙ፣ ወገኖቻችን የምንናካፍልበት የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን ይመኛል።

ይህ በዓል ከሌሎች በዓላት የሚለይበት የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ ነብሱን ለሰው ልጆች ሁሉ የሰጠበት እና አለምን በአንድ ልጁ ያዳነበት በመሆኑ ምሳሌነቱን ተከትለን አንዳችን ለአንዳችን የምንቆረስበት የመተሳሰብና የመተጋገዝ በዓል ነው።

የዘንድሮው በዓላችን ሀገራችንን ጨምሮ መላው ዓለማችን የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች፣ የእርስ በእርስ ግጭት፣ በሽታ የኑሮ ውድነት ፈተና የበዛበት ቢሆንም ዓለማትን በፈጠረው ሞትን በሕይወት ፣ ጨለማን በብርሃን ፍርሃትንና ድንጋጤን ወደ ሙሉ ደስታ በለወጠው በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ተስፋ ተሞልተን በዓሉን በመተሳሰብና በመተጋገዝ እንድናከብር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በተጨማሪም በሀገራችንም ይሁን በመላው አለም የሚታየው፣ መቅሰፍት፤ ሞት የእርስ በእርስ ግጭት ጠፍቶ በወንድማማቾችና በእህትማማቾች ዘንድ ሰላም፣ ፍቅር ፣መተባበርና መከባበር እንዲሰፍን ስናካሂድ የነበረውን የጸሎትና የንስሐ ልመና አምላካችን እንደቸርነቱ ብዛት ይቅር እንዲለን አጠንክረን ልንፀልይ ይገባል።

እኛ ኢትዮጵያውያን ቀድሞ የነበረን እና የምንታወቅበት አብሮ የመኖር ፤ የመተሳሰብ ፤ የመከባበር እና አንዱ ለአንዱ የመድረስ ቀደምት ባህላችንን ከምን ጊዜም በላይ ልናሳድገው እና ልናጎለብትበት የሚገባ ወቅት ላይ እንገኛለን።

ክርስቶስ በምድር በነበረበት ወቅት ለደቀመዛሙርቱ መታዘዝን እና ትህትናን ይቅርታን እንዳስተማረ ሁሉ ዛሬም የሃይማኖት ቤተሰቦች ከሰው ሁሉም ጋር በሰላም ኑሩ የተቸገሩትንም እሩዱአቸው የሚለውን አምላካዊ ቃል በመፈጸም አንዱ ከአንዱ ጋር በሰላም እና በመከባበር ለሀገር ሠላምና አንድነት ከምንጊዜውም በላይ በጋራ ሊንሰራ ይገባል።

በመጨረሻም በዓሉን ሲናከብር በስደት ላይ ያሉትን ኢትዮጵያን ወንድሞች እና እህቶቻችንን የአገርን ድንበር ለማስከበር በየጠረፉ የምገኙ የመከላከያ ሠራዊትና የጸጥታ አባላትን፣ በየማረሚያ ቤቶች በህግ ጥላ ስር የምገኙ የሕግ ታራሚዎች፣ በየሆስፒታሉ የምገኙ ህሙማን፣ በጸሎት እያሰብን ፤ በጦርነት እና በእርስ በእርስ ግጭት ከቀያቸው ተፈናቅለው የሚገኙትን ወገኖቻችንን ሁሉ በምንችለው ሁሉ እያገዝን እና በጸሎታችን ሁሉ እያሰብናቸው እንድናከብር እናሳስባለን።

በድጋሚ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2014 ዓ.ም እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ በዓሉ የሰላም የደስታ የፍቅር እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ሚያዚያ 12 2014ዓ.ም
አዲስ አበባ
#የነገዉ ልዩ የትንሳኤ ፕሮግራም ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ነወ።
#በአዲስ_አበባ_እስታዲየም
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ2014 ዓ.ም የትንሣኤ በዓል ምክንያት በማድረግ የምልጃና የጸሎት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል።

ለአገራችን በሚደረገው በዚህ የምልጃና የጸሎት ፕሮግራም ላይ እሑድ ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በስፍራው በመገኘት አብረን የእግዚአብሔርን ፊት እንድንፈልግ ኅብረቱ ጥሪ ያደርጋል።

በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ዝግጅቱ በመጠናቀቀ ላይ ሲሆን በነገዉ እለት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#በድምቀት_ተከብሯል
#አዲስአበባ_እስታዲየም

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ መታሰቢያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የጸሎትና የምልጃ መርሃግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ተካሂዷል።

በመርሀግብሩ ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት ጸሎት፣ ትንሣኤውን የሚያወድሱ ዝማሬዎች እና የእግዚአብሔር ቃል ተሰብኳል።

በአደባባይ የክርስቶስን ትንሳኤ ታዉጇል።