#ሌሎችን_በመውደድ_የትንሳኤውን_ትርጉም_በተግባር እንቀይር" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
በዛሬው እለት የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የትንሳኤ በአልን በአዲስ አበባ ስታዲዬም በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል ።
የወንጌል አማኞች ህብረት ፕሬዘዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ በበአሉ ላይ እንደተናገሩት ትንሳኤ መከራን፤ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታና ጨለማን ተሻግሮ ወደ አዲስና የሚደነቅ ብርሃን መግባትን፤ በአሸናፊነት መውጣትን የሚያመለክት የድል ብስራት ነው ያሉ ሲሆን ክርስቶስ አምላክ ሆኖ ሳለ: የሞተው ሃጥያት ወይም በደል ተገኝቶበት ሳይሆን ስለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅር ሲል ነው፡፤ በዚህ ታላቅ የፍቅር ተምሳሌትነቱን ማሰብ ና መቀጠል አለብን ብለዋል::
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የትንሳኤው ትርጉም በራሳችን ላይ ለውጥ እንዲያመጣ መፍቀድ አለብን ብለዋል።
በትንሹ ፍቅርን በማካፈል ፤ሁሉን ሰው ሳናዳላ በእኩል አይን በመመልከት በፍትሃዊነት በማገልገል፤ በይቅር ባይነት ብንበደል እንኳን በምህረት በማለፍ ፤ ሌሎችን በመውደድ የትንሳኤውን ትርጉም በተግባር እንቀይር ብለዋል::
አክለውም እኛ ኢትዮጵውያን በመካሰስና ጣት በመጠቋቆም : ተራርቀንና ተነጣጥለን ልናሸንፍ አንችልም፡፤ አንዱ ተጎድቶ ሌሎቻችን ልንጠቀም አንችልም ፤ አንዱ አዝኖ ሌሎቻችን ልንደሰት አንችልም:: ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ የጋራ ጉዳያችን ጥቅሞቻችን የተሳሰሩ ስለሆኑ ተከባብረን እየተሳሰብን ተከባብረን በጋራ እንስራ ብለዋል::
በመጨረሻም በዓሉ በዝማሬ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነስርዓቶች በድምቀት ተከብሯል።

#ወንጌል_ይቀጥላል።
ባሳለፊነዉ ማክሰኞ የዲመካ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ የማምለኪያ አዳራሹ ሙሉ በሙሉ መዉደቁ ይታወሳል።
የቤተክርስቲያኒቱ ምዕናን በዛሬዉ እለት የትንሳኤ በዓልን በዚህ መልክ በአምልኮ እና በተለያዩ መሰናዶዎች በዝናብ ውስጥ አክብረዉ የክርስቶስን ትንሳኤ አዉጀዉ አሳልፈዋል።
የወንጌል ስራ እንዲቀጥል ሁላችንም በማንኛውም መንገድ እርብርብ እንድናደርግ ጥሪ እናቀርባለን!!!
“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23
ወንጌል ለሁሉም !!
ሁሉም ለወንጌል !!
#አድራሻ፦ ዲመካ ከሆስቴ በስተጀርባ #Bank ACCOUNTS CBE-1000340167318
-Emmanuel United Church of Ethiopia Dimeka Local Church (Hamer)
Phone Number:- ☎️ +2519111575204 📱+251 912169165

#ቢሾፍቱ_ትንሳኤዉን_በአደባባይ_አዉጃለች🙏🙏🙏
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
#ክብር_ለአምላካችን_ይሁን
በቢሾፍቱ ወንጌላዉያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት አዘጋጅነት የትንሳኤ መታሰቢያ ልዩ መሰናዶ ቢሾፍቱ "ኢያሱ ሜዳ" በድምቀት ተከብሯል።
በፕሮግራሙ ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ቅዱሳን ትንሳኤዉን እያወጁ ወደ አደባባዩ ተሰብስበዉ በጋራ አምልከዋል።
የሕብረት ቦርዶች ፣ የ አጥቢያ መጋቢዎችና መሪዎች፣ ልቀኝ መንፈሳዊ ባንድ ፣ ከየ አጥቢያው ለተውጣጣችሁ የ ህብረቱ ኳየር(መዘምራን)፣ ዲያቆናት ፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ ድጋፍ በተለያየ መንገድ ላደረጋችሁ ወንድሞች፣ IEC ኳየር ፣ የከተማው መስተዳድር እና የፀጥታ አካላት እና በአንድም በሌላም ከዚህ ፕሮግራም ጀርባ ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ! የሕብረቱ መልዕክት ነዉ።
የፎቶ ምንጭ @ከተለያዩ ቅዱሳን