ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.46K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ለፈገግታ😂😂😂

አንዱ ቅድም ከሁዋላዬ ድንገት ደረሰና በሁለት እጆቹ አይኖቼን ሸፍኖ " ገምትስኪ ማነኝ!?
.....ክስ መስርቻለሁ!....
credit:- Fikre Z Bhere Ethiopia
#Stay_Home
#Stay_Safe
join us for more @Simetin_Begitim
ለፈገግታ😂😂😂


•ንስሃ ልገባ ሰፈር ያሉ ቄስ ጋ ሂጄ፡ ሁሏንም ጉድ ከሰሙ በኃላ...
.
.
.
.
.
#ቆይ_ለእናትህ
😥😢😭🙆

ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
#Stay_Home
#Stay_Safe
©ዝንቅ መዝናኛ

join For more @Simetin_Begitim
[በላይ በቀለ ወያ]


"እጄን ወደ ጡቷ ፣ ምን ፈልጌ ላኩት
ምንድን አስቤ ነው ፣ ከንፈሯን የሳምኩት?
ምንድን ነው ምክንያቱ ፣
ጡቷን ስነካካው ፣ ሰውነቷ ሚያልቀው
ከየት አምጥቶ ነው ፣
ከንፈሯን ስስመው ፣ አፏ ማር 'ሚያፈልቀው ?
ጡት እንደሚነካ ፣
ከንፈር እንደሚሳም ፣ ማን ነው ያስተማረኝ ?
ታውቃለች አውቃለሁ ፣
እሷ ከኔ በፊት ፣
ወንድ እንዳልነበራት ፣
እኔ ከሷ በፊት ፣ ሴት እንዳልነበረኝ።"
እያልሁ ስሟገት ፣ ስጠይቅ ራሴን
አወለኩት ልብሷን ፣ አወለቀች ልብሴን
ደግሞ 'ጠይቃለሁ ፣ ነፍሷን እና ነፍሴን።
።።።
ማን ነው ያስተማራት ፣ ማን ነው ያስተማረኝ
ምን እርቃን አስቀራት ፣ ምን እርቃን አስቀረኝ?
ምን እያረግን ነው ፣
ምንድን ያስጮሃታል ፣ ምንድን ነው ሚነዝረኝ?
ብዬ 'ጠይቃለሁ
እሷ ምን ታውቃለች ፣ እኔስ ምን አውቃለሁ!?
።።፣።።።
ደግሞ ግጥሙን አንብባችሁ አላስፈላጊ ቅርርብ ውስጥ ግቡ አሏችሁ ። ተ ራ ራ ቁ!!!


መልካም ምሽት
#Stay_Home
#Stay_Safe
ለውብ ቀን ....
☮️ሒሳብ አዋቂው ፈረስ ›

አሌክስ አብርሃም

☯️የሆነ ጊዜ አንድ የስነልቦና ሊቅ ፈረሱን እየጎተተ ወደአንድ ዩኒቨርስቲ ሄደና ‹‹ ፈረሴ አራቱን የሒሳብ ስሌት ከማወቅ አልፎ ውስብስብ የሂሳብ ስሌቶችን ውጤት እስከማወቅ ደርሷል ካላመናችሁ ፈትኑት›› አለ …በነገሩ የተገረሙ ሙሁራን ዳኛ ሰይመው ፈተና አዘጋጁ …እንግዲህ አፈታተኑ እንዲህ ነው ለምሳሌ 2 ሲደመር 2 ተብሎ ፈረሱ ይጠየቃል ….ከዛም የተለያዩ ሰዎች ቁጥር የተፃፈበት ሰሌዳ ይዘው ይቆማሉ ፈረሱ ቀጥ ብሎ 4 ቁጥር ወደያዘው ሰው ይሄድና በአፍንጫው ይጠቁማል(ምርጫ እንደማለት ነው) ….በቃ ማባዛት ነሽ ማካፈል መደመር ነሽ መቀነስ ውጤቱን በሰከንዶች ውስጥ ቁጭ ያደርገዋል ፈረሱ ….እናም ‹‹እውነትም ፈረሶች ከተማሩ ከሰው ልጆች እኩል ሂሳብ ማወቅ ይችላሉ›› ብለው ደመደሙ ምሁራኑ !!

☯️ባለፈረሱ ግን እንዲህ አለ ‹‹ እናተ የማትረቡ ….ፈረስ መቸም ቢሆን ሒሳብ አይችልም …. ፈረሱ መልሱን የሚያውቀው በልብ ትርታችሁ ነው … ቁጥር ይዘው ከተደረደሩት ሰዎች መካከል ትክክለኛውን መልስ የያዘው ሰው የልብ ትርታ የተሳሳተ መልስ ይዘው ከቆሙት ሰዎች ጋር ሲነፃፀር የተረጋጋ ነው ...እንስሳት ደግሞ የሰውን ስሜት ጠረን በማሽተት ከፍተኛ በሆነ የማድመጥ ችሎታና የእንቅስቃን ፍጥነት በመመልከት የመረዳት ፈጣን ተሰጥኦ አላቸው።

በዚች ምድር እውነት ይዛችሁ በቆማችሁ ቁጥር እንኳን አእምሯቸውን የሚጠቀሙ ሰብአዊ ፍጥረቶች እንስሳት በደመነፍስ ይለዩዋችኋል … ፈረሱ የመረጠው የእናተን ዝባዝንኬ ቁጥር አይደለም … እውነት ያረጋጋው ልባችሁን እንጅ !! ወደመልሱም የመራው እውነት ያረጋጋው ልባችሁ ነው !!
ልባችሁ !!❤️

ሰናይ ቅዳሜ መልካም ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ

#Stay_Home
#Stay_Safe
ለውብ ቀን

ከ Fikre Z Bihere Ethiopia የFb ገፅ የተወሰደ
እቤት መዋል ከሰጠኝ እድሎች አንዱ ከአበራሽ ( የቤት
ሰራቸኛችን ) ጋር የነበረኝን ተግባቦት ማዳበር ነው።
አልተሳካምንጂ!
የምትናገረው በእርግጥ አማርኛ ነው። ግን አስተርጓሚ
ያስፈልገኛል።
" ወንዲይም! "
" አቤት አበራሽ "
" ኸባጧ ላይ ያለይ ብረት ለገመይ "
" ምን? "
" ሽቅብ! "
" ሽቅብ የሰፈረይ!? አንተና አንዲ ብላቴና ያበጃጃችኋት? "
ማታ ነው የገባኝ፡ ሳተላይት ዲሹ አይሰራም ማለቷ ነበር።
ያው ኸባጧ ማለት ከባጧ ነው፤ ባጥ ማለት ጣራ መሰለኝ።
ብረት ያለችው ደግሞ ዲሹን ነበር።
ለገመይ ለገመች ለማለት ነው። ወይ ፈጣሪ!
*
በቀደም ሲያንቀለቅለኝ፡
" አበሩ! እስኪ ከአገርሽ ለምን እንደወጣሽ አጫውቺኝ? " ብዬ
ጠየኳት። በረጅሙ ተነፈሰችና..." ኧህህ!!!!.........
" ሙጫ ሳለሁ..አበበይ እንዲየው ቁርጮ ዴሃ ነበር። መቼስ ወፈ
ግዝት መሆን አይጣል አንተው! አያቴንኳ የቂጥ ማረፊያ
ቢያኖሩለት በምን እዲል እቴ! ከነልዦቹ ይ'ፋሱ ብለው ሞቱ'ዪ። "
......ትርጉም?.....የደላችሁ! ( ወፍ የለም ).....
" ኋላማልህ...መኮርደዴን ያየ አበበይ ለአንድ እሪያ ጥርስ
ሊያቆናጥጠኝ ቲል እብስ ወዴ ኸተማ...."
መሳቅ ብፈልግም በምኑ ልሳቅ?
" እንዲያውኮ ከቀየው እንዴኔ ዴሟ የፈለቀም አትገኝ! መቼስ
ድረገብ ከመሆን አንዲያፉን ኸተማ ይሻል ብየ ነዉይ "
" ማለት? " አልኩ አምልጦኝ
" ዴፈነብህ? "
" ምን? "
" አይ የኸተማ ሰው!...ዴፈነብህ ወይ? "
.....እርፍ!
" በል እንግዲያው ዴመናው በሯል፡ ኸገበያው ልሂድ "
አሁን እኔ አማርኛን ችየዋለሁ?
ምንድነው ያለችው ግን?

#Stay_Home
#Stay_Safe

በነገራችሁ ምን እንዳለች ሚነግረን ካለ
@Simetin_Begitimbot Or በ @Haile_melekot ይላኩልን መልሰን ወደ እናንተው እናደርሳለን

Join us and invite Your friends to our channel

@Simetin_Begitim
ቶሎ ስርአት የሚይዝ ህዝብ ያሸንፋል፤ ይሻገራል!

#Ethiopia : ኢትዮጵያ ያላት አማራጭ የኮሮና ወረርሽኝ ሳይሰራጭ በቶሎ መከላከል ነው። ለዚህ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። መጪውን በዓል ቀጣይ ፋሲካ ቀጣይ የረመዳን አለ ቢቻል ሁሉም በየቤቱ ቢያከብር የተሻለ ይሆናል የሚል ሀሳብ አለኝ። አለበለዚያ ከገጠር ወደ ከተማ ለበአሉ የሚመጡ በሽታው በየቤቱ እንዲሰራጭ እድል ስለሚሰጡት ሁሉም በያለበት የማንወጣው አዘቅት ሊከተን ይችላል። ሁላችንም ጥንቃቄ ልናደርግ እና በጋራ ወረርሽኙን ልንከላከል ይገባል።"

አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊቀመንበር)

እውነት ነው ሁሉም በያለበት ሁኖ እራሱን ቤተሰቡን ብሎም የሚወዳትን ሀገሩን መጠበቅ አለበት ፡፡

#Stay_Home
#Stay_Safe
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
(ልዑል ሀይሌ)
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
መንገድ ጥረጊልኝ
ይህቺን ብቻ አርጊልኝ!
.
ስምሽን እያነሱ
እንዳያስታውሱኝ
በሞተው ትዝታ
እንዳይቀሰቅሱኝ
ያንቺ አለመሆኔን
ዛሬ እንዳሳያቸው
ጨረቃን ፀሐይን
ምድር አውርጂያቸው
ውቅያኖስ ባህሩን
ሰማይ ስቀያቸው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
የረገጥነው አስፋልት
የሄድንበት መንገድ
ያ ያለፈው ፍቅር
ያ ያለፈው መውደድ
ፍፁም ውሸት ብዬ
እንድሸመጥጠው
ተፈጥሮን አዛቢ
መውደዴን እንድተው
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ገደሉን ሙዪና
ተራራውን ናጂው
ደመናን አውርደሽ
አፈሩን ውሰጂው
የረገጥሽው መሬት
አምሮ እንድታይበት
በአበባው ፋንታ
ሳማ ትከይበት
.
እ-ን-ድ-ረ-ሳ-ሽ
ያ ሁላ ቃል ኪዳን
ተበትኖ እንዲቀር
አይጥ ሀይቅ ትዋኝ
ዓሳ ሰማይ ይብረር
በህይወት ባሉት ምትክ
ሙታኖች ይነሱ
ነገስታት ይውረዱ
ባርያዎች ይንገሱ
.
ይሄን ካረግሽልኝ
መውደዴን ይቅርና
መኖር አቆማለሁ
በመኖር ብረሳሽ
ባለመኖርም ውስጥ
አስታውስሻለሁ

#Stay_Home
#Stay_Safe
Fikre Z Bhere Ethiopia©ፈገግ ብላችሁ ዋሉ
የፋሲካ ትዝታ!
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ
ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን
በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር
እንደ ሊስትሮ.....
መቼም ያ በሬ ሳር ቢያገኝንኳ እንደዛ አይጎመጅም!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን
ይመስል ነበር።
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው
ውስጥ ጨመራቸው!( እንደታዘዘ )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "

#Stay_Home
#Stay_Safe
#DrTsionFirew

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ፦

በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።

ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።

በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።

መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።

በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ።

#Stay_Home
#Stay_Safe
ጁመዓ ሙባረክ

መልካም ስግደት🙏

የሁላችንንም ልመና ፈጣሪ ይስማን ፡፡

መልካም ቀን

#Stay_Home
#Stay_Safe
#ተነስቷል

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ? ተነሥቶአል
እንጂ በዚህ የለም። ሉቃ 24፥5

የኃያላኑ ኃያል የጌቶቹ ጌታ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ የሞት እዳችንን ከፍሎ በትንሳኤው ሞታችንን እርሱ ሙቶ ሽሮልናል ፡፡ መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንልን፡፡ ትንሳኤው የምህረት የድህነት እንዲሁም የይቅርታ ይሁንልን አሜን!

#Stay_Home
#Stay_Safe
#Happy_Easter
Fikre Z Bhere Ethiopia©
ይህቺን ነገር የሚሻማን ልጅ ነበር። ብሬ! በየቤቱ እየዞረ ስልቅጥ
ነው!
ለነገሩ ያኔ በግ የቤት እንስሳ ነበር! ቢያንስ በሰፈራችን አብዛኛው
ሰው ስለሚያርድ።
የበጎች ድምጽ ከጠፋ ታርደዋል ማለት ነው....
ያንኳኳል.......
" ምነው በደህና ነው ልጅ ብርሃኑ? "
" ጋሼ! እንኳን አደረሳችሁ! " ይላል ወደግቢው እያጮለቀ።
በሰፈሩ ሁሉም ስለሚያውቀው ያዘጋጅለታል። ገና አብስለው
ሲሰጡት እንደ ድመት አይኑን ጨፍኖ ያነክተዋል....
" ፍቅርሻ! "
" አቤት "
" ተዘጋጀልኝ?"...( እንዳስቀመጠ )
" ያውልህ! "
የሰፈሩ አባቶች ልጆቻቸውን ( በተለይ ወንዶቹን ) ለማብላት
ይሞክራሉ
" ልጅ ብርሃኑኮ ጀግና ነው! "
" እንዴት? "
" የበግ ቆ** ይበላል ቢያንስ!..አንተ እሳት ዳር ቁጭ ብለህ ጉበት
ጥበስ ረኸጥ! "
"...ወንድ ልጅ የበግ ቆ** ሲበላነውንጂ!!!....." ይባላል።
ጥቅሙን ሲያስረዱ.....
" በተለይ አንተ ( እኔን ነው ) ይሄ ውሻና ሸረሪት ስታይ
የምትበረግገው ነገር ይለቀሃል ".....እርፍ!
አንድ ቀን እትዬ ሻሼ ቤት ሄደ ብሬ....
.....በጉኮ አልታረደም! ድምጹ ስለጠፋ ብርሻ ከች!...
" ሳይታረድ እንደ ቲማቲም ከላዩ ላይ ልትቀነጥስበት ነውንዴ? "
አሉ እትዬ ሻሼ
" ሲታረድ ልምጣ? "
" ሳር አብላውማ! ጎሽ..."
በጉ አመጸኛ ነገር ነበር። ብሬ ጠጋ ሲለው ሊወጋው
ተንደረደረ!.....ብሬ እንደዛ ተፈናጥራ አታውቅም!
እማማ ሻሼ.....
" ያን ኩሉ የበግ ቆ** ሰልቅጠህ እንደ ፌንጣ መዝለል?
ሆ!ሆ!ሆ...እኛው እንበላዋለን ከዛሬ ጀምሮ "
" ለሴት አይሆንምኮ እትዬ ሻሼ "
" ለምን ሲባል!? ምን እንዳይቀንስብኝ ነው? "
...እውነታቸውን ነው..
ብሬ ታዲያ ከፍ እንዳለ ቀበሌያችንን ወክሎ ቦክሰኛ ሆኖ ነበር።
የሁላችንም ውጤት አይደል?
የሚያሳዝነው ሁሌም ይሸነፋል!
እሱ በዝረራ በተፈነደሰ ቁጥር ቤቱ ሄዶ መጠየቁ ታከተን!
አንድ ቀን እትዬ ሻሼ ሊጠይቁት ሄዱ
" ተረፍክ ልጄ? "
" ደህና ነኝ እትዬ "
" አቤት.. አቤት.. አቤት! ጭካኔ! አንተ ለነገሩ ለምደኸው ነውንጂ
ሌላ ሰውማ ይሞታል! "
እያዘኑ ቆዩና...ጠጋ ብለው
" ያኔ እየዞርሽ ሃሞት ጠጥተሽ ቢሆን....."

#መልካም_ትንሳዔ
#Stay_Home
#Stay_Safe