ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.48K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ፍትህ_ለጫልቱ!!
#JUSTICE_FOR_CHALTU!!

ሴት ሰው ናት!
ሴት ሀገር ናት!
ሴትን #መድፈር ሀገርን መድፈር ነው!

መንግስት የአሲድ መድፋት ወንጀልን ያስቁምልን!

📌የአሲድ ጥቃት አስመልክቶ ህግ ይውጣ።
📌አሲድ በቀላሉ እንዳይገኝ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ።

#ETHIOPIA
## ዓድዋ በባለቅኔው እይታ ###

ዋ! ..... ያቺ ዓድዋ

ዋ! ...
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ.....
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም በነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ ለት
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው በለው በለው በለው
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው በለው
ዋ! ...... ዓድዋ .....
ዓድዋ የትናንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና
....... ዋ! ........ ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ .......

© ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን
የካቲት - ፲፱፻፷፬ - ዓድዋ

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
የአድዋ አዋጅ እና እምዬ ምንሊክ ብልሀት

#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ

"የዳግማዊ ምኒልክ የክተት አዋጅ ከወራሪዎቹ እንቅስቃሴ አንፃር ከተጠበቀበት ወቅት ዘግይቷል፡፡ ይህም በአፍሪካና አውሮፓ ሀገሮች አይን ምንሊክን እንደ ፈሪ እንዲታዩ አድርጎ ነበር ይላል" ራይሞን ጆንስ የአድዋ ጦርነት በሚለው መፅሀፉ፡፡ ፀሀፊው ሲቀጥል "የመሪ ብልህነት የሚለካው ቸኩሎ በመወሰኑ ሳይሆንበወቅቱ ያሉትን አመቺ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ሲያሳልፍ ነው ይላል፡፡
የክተት አዋጁ በራሱ በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የፈተና ጊዜ ማለፍንና የመረጋጋት ዘመን መምጣቱን ገላጭ ከመሆኑም በላይ፤ ህዝቡ ከሃይማኖት፣ ከዘርና ግዛት ማስፋፋት ፍጭት በመውጣት ስለ አንድ ሀገሩ ደህንነት በጋራ የሚቆም እንደነበረ ያረጋግጣል።

" እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ፣ አገር አስፍቶ አኖረኝ" ሲሉ ከአድዋ በፊት ጠንካራ የውጭ ጠላት አልነበረምና ጦርነት በሌለበት ሀገር እርጋታ ላይ ሆና አስተዳደሯን እያደረጀች እንደነበረ ይነግረናል።

" አሁንም አገር የሚያጠፋ፥ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባህር አልፎ መጥቷል። እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር።"

ይህ ንግርት በወቅቱ ኢትዮጵያ የነበረችበትን የመከራ ዘመን "ክፉ ቀን" ደግመን እንድንመረምር ያደርገናል። በከ1881 ዓ.ም ጀምሮ የነበረው በኢጣሊያኖች አማካኝነት ወደ ሀገር የገባው የከብት በሽታ ለአራት አመታት ህዝቡን ከብቱን ጎድቶ ነበር። ረሀብ በመፅናቱ እናት ልጀቿን የበላችበት ክፉ ዘመን ነበር። እናም የዓድዋ ጦርነት ለምን ዘገየ ሲባል ራሱ አዋጁ ይነግረናል " የሰውን መድከም የከብቱን ማለቅ አይቼ እስካሁን ዝም ብለው" ይህ ሀሳብ ከላይ ራይሞን ጆንስ ከጠቀሰው ጋር የሚስማማ ነው፡፡

እምዬ በጥሪያቸው " ማርያምን አልምርህም! ለዚህ አማላጅ የለኝም " ብለዋል። ግን ሀገሬው በሙሉ ሃይማኖቱን አስቀድሞ በእምነቴ አልተጠራሁም ብሎ ሀገሩን ከመታደግ አልቀረም። ንጉሱን ተከትሎ ከንጉሱ ጋር ተዋደቀ እንጂ።

ለዛ ነው እምዬ ከምንም በላይ ሀገር እንደሚቀድም አሳይተው በአንድነት የመምራት ብቃት ነበራቸው የሚያሰኘው።

ክብር ይሁን!

#የጥቁር_ህዝብ_ኩራት
#ዓድዋ_123
#የኢትዮጵያውያን_ድል
#VictoryofAdwa
#Ethiopia

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
#Ethiopia
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Forwarded from @እንደኔ እይታ..... (Daree)
#ETHIOPIA | ~ ዳኒን ከቤተ መንግሥቱ ሳያስወጡት ከዐብይ አህመድም ሳያርቁት አይቀርም። ዳንኤል ክብረት ግን በተቻለህ መጠን ራስህን ጠብቅ። ሰልፉ ግን አይቀርም።

•••
በቤተ መንግሥት በተደረገው የዋዜማ ዝግጅት ላይ እኛ ኦሮሞዎችን ያሰደቡን ዳንኤል ክብረትና ዐቢይ አህመድ ናቸው እያለልህ ነው ጃዌ። እነ ጃ–War ን ያስነቀለው የገጣሚ ሕሊና በለጠ ግጥም በጥቂቱ እነሆ የሚከተለው ነው።

•••
በጭፍን ከመሮጥ አስቦ ማዝገም ነው፣ የመራመድ ውሉ፣
ሁሉም እንቅፋቶች እስኪጥሉን ድረስ ምርኩዝ ይመስላሉ።

•••
ከዕድሏ ጣራ ላይ ዘር የቀዳደደው ሽንቁሯ ቢበዛም፣
ያ ከንቱ ፎካሪ ባረጀ ቀርርቶ ሺህ ጉራ ቢነዛም፣
ሚሊዮን ዘር ቢሸጥ አንድ አገር አይገዛም።

•••
የዘመን እውነት ነን በደግነት ሰማይ በጥበብ የኖርን፣
ትእግስትም ልክ አለው ፈርተን እንዳይመስለው ስላቀረቀርን።
ማተብ አስሮን እንጂ ተጣልተን እንዳንቀር በክፍፍል ገደል፤
ካገር ፍቅር በልጦ ሞት ብርቃችን አይደል።

•••
በሞላ ጎዳና፥ ባልጠበበ መንደር፥ በዘር ገመድ ታግዳ
ነፃ ነኝ ትላለች፥ #መንጋነት ያሰረው፥ ባሪያ ትውልድ ወልዳ!

•••
እስኪ ልጠይቅህ? የጀግንነት #እብሪት፥ ልባችንን ደፍኖ፥ ማሰብ እየከዳን፣
እንዴት ነው #ነፃነት፥ እንዳበደ ፈረስ፥ ስሜት እየነዳን!
ገድሎ የመንገሥ ጥማት፥ ጩኸት ላገነነ፥ አመፅ ላጀገነው፣
ለዚህ ምስኪን ትውልድ፥ #በጅምላ_እየነዱት፥ በመንጋ እያሰበ፥ ነፃነት ምንድነው?!

•••
አሳር አደባይቶ መከራ የወለዳት ፤ ጀግና ናት አትክድም
በሸረኞች ድንጋይ፥ በሽንታሞች ተረት፥ ሃገር አትናድም።

•••
ንገሩት ለዚያ ሰው ኃይል እንደ ተራራ ገዝፎ ቢከመርም፣
ዓለም የሞተበት የጠላት ማርከሻ ጦር ቢደረድርም፣
በአንድ ዓይናችን ሰላም፣ በኢትዮጵያችን ክብር፣ አንደራደርም።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መስከረም 2/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
@endenaendena
በንቀት መጥቶ ሀገር ሊገዛ
ብዙም እልቆየ አደብ ሲገዛ
ይዞን የመጣ ሀገር ማርከሻ
እራሱ ጋተው በጦር በጋሻ
የአድዋ መሬት እንዴት ክፉ ነው
እሾህ የወጋው ጫማ ያረገን ነው

ግጥም አርቲስት Lij Michael Faf. (ማይክ)
#Ethiopia : መልካም የአድዋ በአል ምኒሊክ ጥቁር ሰው
©Natnael.mekonin
ቶሎ ስርአት የሚይዝ ህዝብ ያሸንፋል፤ ይሻገራል!

#Ethiopia : ኢትዮጵያ ያላት አማራጭ የኮሮና ወረርሽኝ ሳይሰራጭ በቶሎ መከላከል ነው። ለዚህ ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ማድረግ አለበት። መጪውን በዓል ቀጣይ ፋሲካ ቀጣይ የረመዳን አለ ቢቻል ሁሉም በየቤቱ ቢያከብር የተሻለ ይሆናል የሚል ሀሳብ አለኝ። አለበለዚያ ከገጠር ወደ ከተማ ለበአሉ የሚመጡ በሽታው በየቤቱ እንዲሰራጭ እድል ስለሚሰጡት ሁሉም በያለበት የማንወጣው አዘቅት ሊከተን ይችላል። ሁላችንም ጥንቃቄ ልናደርግ እና በጋራ ወረርሽኙን ልንከላከል ይገባል።"

አቶ የሺዋስ አሰፋ (የኢዜማ ሊቀመንበር)

እውነት ነው ሁሉም በያለበት ሁኖ እራሱን ቤተሰቡን ብሎም የሚወዳትን ሀገሩን መጠበቅ አለበት ፡፡

#Stay_Home
#Stay_Safe
#Ethiopia : እንኳን ለአርበኞች የድል መታሰብያ ቀን አደረሳችሁ!! ሚያዝያ 27 የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ በዓል ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ለሃገር ነጻነት አንድነትና ክብር የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን ያስጨነቀበት እና ድል ያደረገበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት «የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰብያ» ነው።

ጥንታዊ ጀግና አርበኞች የጣልያንን ጦር አምስት ዓመት ተጋድለዉ የሃገር ነፃነት አስከብረው አኩሪ ድል ተቀዳጅተዋል። መልካም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል መታሰብያ ቀን።
#Ethiopia : "የምናውቀው የመረመርነውን ነው ፤ የመረመርነው ደግሞ ትንሽ ነው። ትክክለኛ ትምህርትና እርምጃ ለመውሰድ በብዙ ቁጥር መያዝ ፣ በብዙ ቁጥር መሞት የለብንም”

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፤ የጤና ሚኒስቴር