ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.46K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
Forwarded from ዝንቅ መዝናኛ (Mr. Nobody)
ሁልሽም ፕሮፋይልሽን ወደ ጥቁር ከመቀየርሽ በፊት እንጠንቀቅ!!

ብዙ እድል ተሰጥቶናል፤ በአግባቡ እንጠቀምበት። ይህ በሽታ በመንግስት አቅምና ጥንካሬ ሳይሆን በግለሰቦች ጥንቃቄ ስለሆነ የጉዳት መጠኑ የሚወሰነዉ እያንዳንዳችን የግላችንን ጥንቃቄ እናድርግ። በኃላ ማንም ተወቃሽ ማንም ወቃሽ መሆን አይችልም በዚህ ጉዳይ። ጣሊያን፣ ስፔን፣ አሜሪካና ኢራን ከኛ የተሻለ የጤና አጠባበቅ system አላቸዉ፤ ግን አልዳኑም። ጣሊያን ዛሬ ከቻይና የበለጠ ሞት በትንሽ ጊዜ አስመዝግባለች። ወገኖቼ የአየር መንገድ በራራ በማስቆም ቢሆን ጣሊያንን አሜሪካ እንኳን አልቀደመቻትም። ግን የሚሆነዉን እያየን ነዉ። ትላንት ጣሊያን የአለም ሪከርድ የሆነዉን የሞት መጠን አስመዝግባለች። ስለዚህ ለሁሉም ነገር ሰበብ መፈለጉንና ጣት መጠቋቀሙን ትተን በግል እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ ጥንቃቄ እናድርግ። ይህ በንዝህላልነት በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የመጣ ጋሬጣ ሳይሆን በአለማችን ላይ ዘር፣ ቀለም ሳይል የመጣ የሁላችንም ፈተና ነዉ። አንድ ላይ ከተባበርን፣ እያንዳንዳችን የየራሳችንን ኃላፊነት ከተወጣን ይህን ወረረሽኝ ብዙ እልቂት ሳያስከትል መቆጣጠር እንችላለን። ካልሆነ ግን ነገ ፕሮፋይል አይደለም ቆዳችንን ብንገለብጥ ምንም ለዉጥ አናመጣም። ዛሬም ያለንን ትንሽ ሰዓት ቁም ነገር እንስራበት።

የወረረሽኙን መጠንና ክብደት ያልተረዱ ብዙ ወገኖች ስላሉ ይህንን መልዕክት በሁሉም ሶሻል ሚድያ ላይ በማጋራት የበኩላችንን እንወጣ።

#Share
#Please
#BeSeriousCoronaIsSerious

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ