ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ዕንባህን ባረገኝ

© ሰሊና

ከውስጥ ስሜትህ ከልብህ ፈልቄ
የአጉል ኩራትህን ሽፋኑን ፈልቅቄ
የዐይኖችህን ብሌን በዕንባ ሞልቼ
ቅል ባሳክላቸው በዕንባ አሳብጬ
ደም ባስመስላቸው ስሜትህን ገልጬ
ሲቃ ብሆንብህ ድምፅህን ዘግቼ
ጉንጮችህን ባርስ በመንታ ወርጄ
ከዛም...
ይህን ሁላ ሄጄ ሁሉን አቋርጬ
ብገኝ እመርጣለሁ ከንፈርህ ላይ ሞቼ

#መልካም_ቀን
ውብ ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ!!
ገላሽ ገላ አይመርጥም ፣ ከሁሉ ይጋደማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ከሴት ክብርሽ ይልቅ ፣ ስሜትሽ ይቀድማል።
።።።
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ጭን ከሰማይ ቢገዝፍ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢመስል...
ጡትም አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ....
ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን እንደሚስብ
የወንድ ልጅን ዐይን..
ከተበተነበት ፣ እንደሚሰበስብ
ነግሬሽ ነበረ...
ሴት ክብሯ የአምላክ ነው ፣ እንደ እናት ስታስብ!!!
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ክብረቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም
ሴት ልጅ ስታማርጥ ፣ ለራሷ ምራጭ ናት
በክብር ነው እንጂ.
በመውለድ አይደለም ፣ የሚኮነው እናት፡፡
።።።።።
ነግሬሽ ነበረ
እናትነት ስሟ
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ።
ሴት ክብሯን ስታጣ ፣ እድሜዋ ይሔዳል
የወንድ ልጅ ቤቱ...
የሴትልጅ ውበት ነው ፣ ካየበት ይለምዳል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ነግሬሽ ነበረ...
ጭንሽ ሴትነትን ፣ ከቶ እንደማይበልጠው
ቁንጅናም ይረክሳል!
ብቻውን እንዲቀር ፣ ሁሉም ከመረጠው!
።።።።
ነግሬሽ ነበረ
ብነግርሽ ብነግርሽ ፣ ባትሰሚኝም ቅሉ
"ሰደበኝ" በማለት ፣ ታወሪያለሽ አሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ስሜት ፊት ፣ ስድብ ይመሥላሉ።
።።።
ሞኝ ሰው ሲመክሩት
ሞኝ ሰው ሲነግሩት
የቀኑበት መስሎት ፣ በከንቱ ቢታበይ
ግን እነግርሻለሁ!
ነግሪያት ነበር ስል
ቀንቶ ተናገረኝ ፣ ወይም ሰደበኝ በይ።
።።።
ግን እነግርሻለሁ
ግን እመክርሻለሁ
ሴት ልጅ ክብሯ ሲጎድል ፣ ውበቷ አይመችም
ሁሉም ይተኛታል ፣ ከአንዱም ልብ የለችም!!!

በላይ በቀለ ወያ
ቲቸር ቦጋለ፡ ሒሳብ ሊያወሩልን ሲገቡ
" መጡ ደግሞ! ስራ ሊያስፈቱን " እንል ነበር።
ማንም አይሰማቸውምኮ፡ ብቻቸውን ያወራሉ
.............One man show!.............
" ውይ! ልጆች ይሄን ፎርሙላ አሳሳትኳችሁ ይቅርታ! "
......ተሳስተው ቢቀሩስ ምናለበት?.....
" ምንም አይደል ".....Who cares!?
ስድባቸውስ
" ትኋን ሁሉ! "
......የዘንድሮ ፈላ የቻይና እቃ መስሎታል ይሄኔ.....
ያኔ ትኋን እንደልብ የሚገኝ ተባይ ነበር! አዬ ግርማ ሞገስ! አዬ
እርጋታው!
ከነከሳችሁ በኋላኮ አይሸሽም! እንደ ድፍን ምስር ተጎልቶ
ይጠብቃችኋል! እናንተም ለመያዝ መጣደፍ አያስፈልጋችሁም፡
ጠዋት ከነከሳችሁ ንዴታችሁ ካልበረደ ማታ መጥቶ አንስቶ
መወርወር ነው!
ጣ! ይላል ሲወድቅ ( ወለምታው መሰለኝ! )
ከትኋን የተረፈችውን ደማችንን ቀይ መስቀል እየቀዳት ነውኮ
አይናችን ብቻ የቀረው! ( እንደ ጉጉት! )
እሱም አይን ሆኖ ቲቸር ቦጋለን ነው የምናይበት!
የፈተና ውጤታችንን አይሰጡንም። እኛም አንጠይቅማ!
" ቀጥሎ የማን ክላስ ነው? "
" የፓርላማ! "......የክላሳቸው ስም!
" አይታመሙምንዴ አንዳንዴ? "
" ሲሚንቶ ነገር "
ፊዚክስ ቲቸር ይግደለኝ! እሱ ሁሌም ያመዋል
" ተማሪዎች ነገ የለሁም! አርሾ እሄዳለሁ " ይላል ሁሌ
ያማረበት እየመሰለው በተሰበሰብንበት
" አርሾ ሰገራ ስጥ ብለውኝ..." ብሎ ያወራናል
......ይድፋህ አቦ!.......
ሁልጊዜ አርሾ ሄጄ ሰገራ ሰጥቼ መጣሁ ይላልንዴ?
" ባለገ! ይሄ ሰው " ይላል ጌቱ
" ወይ ሽንት ቤት የለው ይሆናል "
የአስተማሪዎቻችን ትዝታ ብዙ ነው።
ኢለመንተሪ ላይ ቲቸር ጸጋዬ ትዝ ይሉኛል
" የፈሳውን ካላጋለጣችሁ በመደዳ ትገረፋላችሁ "
ይታያችሁ! በአንድ አቃጣሪ ቂጥ፡ ስንጠፈጠፍ
ቲቸር ጸጋዬ የሚታሙት የተማሪ ምሳቃ በማጫረስ ነበር
.......ምሳ እቃ ሰባሪ በሏቸው.....
ምሳ ሰአት ላይ አፍንጫቸውን አስቀድመው ከች ይሉና፡
" ማነው ጎበዝ! አጉርሱኝስኪ " ይላሉ
አጉርሱኝ ይላሉ ግን በኋላ እሳቸው ናቸው የሚያጎርሱን!

Fikre Z Bhere Ethiopia

#መልካም_ቀን_ሠናይ_ውሎ
መጠንቀቁ አይከፋም የወሬ ምንጭ የሆነው Ethio_Leaks| የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ እእዲህ ሲል ዘግቧል
በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ምኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተናገሩ!

ምኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል።

ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል። በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል።

የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ምኒስትሩ አስረድተዋል።
ከ Covid 19 በላይ ስቃይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞ እየመጣ ያለው የሀገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ነው ይህ ምርጫ ዘንድሮ ይካሄድ አይካሄድ እናንተ ምን ታስባለችሁ የሽግግር መንግስትስ ያዋጣል ?
public poll

አይካሄድ – 29
👍👍👍👍👍👍👍 48%

ይካሄድ – 24
👍👍👍👍👍👍 40%

የሽ/መንግስት ይመስረት – 7
👍👍 12%

👥 60 people voted so far.
ታጋቹ ማስታወሻ
( በእውቀቱ ስዩም)
ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ
ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ
እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት
ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን
ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስና
የተረፈውን በረንዳው ላይ ተቀምጨ እጨርሰዋለሁ፤
ሩዝ ጠዋት ማታ ከመብላቴ የተነሳ ወደ ማጅራቴ ሲሸሽ የነበረው
ፀጉሬ ተመልሶ ቅንድቤ ድረስ ግጥ—ም አለ ፤ የህንድ አክተር
ለመምሰል የቀረኝ በሱሪ ላይ ቀሚስ መደረብና ባየር ላይ የሚበር
ሞተር ሳይክል መንዳት ነው፡ ፡
የሆነ ግልገል ጉንዳን ጠረጴዛየ እምብርት ላይ ከተበተኑት የሩዝ
ቅንጣቶች መካከል አንዲቱን መርጦ ተሸክሞ ሲያዘግም
ተመለከትኩ ፤ኩንታል መሸከሙ ነው፤ አይ ጉንዳን! አሁን ጉንዳንን
የመሰለ ታታሪ ፍጡር በሚኖርበት አለም የሰው ልጅ የላባደሮችን
ቀን ያከብራል ? ልይዘው ሞከርኩ ፤የጣቶቼን ጥላ ሲያይ
ኩንታሉን እንደተሸከመ መሮጥ ጀመረ፤ አምልጠህ ሞተህል
ባክህ! !ባውራ ጣቴና በነገረኛ ጣቴ መካከል አጣብቄ ያዝኩት ፤
የሞተ መስሎ ፀጥ አለ፤ ለካ አስመሳይነት የሰው ልጆች ባህርይ
ብቻ አይደለም፤ ትወናውን አድንቄ በተሸከመው የሩዝ ቅንጣት ላይ
አንዲት የቲማቲም ፍሬ መርቄለት ለቀቅሁት፤
ባለፈው ለለውጥ ያክል የሱካር ድንች ለመቀቀል ሞከርኩ፤
የአሜሪካ የሱካር ድንች አንዱ ፍሬ የድሮ ካውያ ያህላል ፤ ችግሩ
በቀላሉ አይበስልም፤ እንዲያውም ካሜሪካ ሱካር ድንች፤
የኢትዮጵያ በሬ ሸኮና ቀድሞ ይበስላል፤ ቤት ጠርጌ ፤ምንጣፍ
ቀይሬ፤ ኮርኔስ ራሱ ቀይሬ ተመልሼ መጥቼ ሳየው፤ አልበሰለም፤
ምን ጉድ ነው! ከዛ ገላየን ተታጥቤ፤ ብብቴንና በስተራስጌ
የሚገኘውን ሁሉ ተላጭቼ ለባብሼ ሳበቃ ብረትድስቱን ከፈትኩት፤
ድንቼ መብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካየ ወጋ አደረግሁት፤
እንዴየየየየ! የሹካው ጥርስ ተጣመመ፤ በጣም ተናደድሁና
አውጥቼ በመስኮት በኩል ወረወርኩት፤ ድው! የሆነ ሰውየ oh
Fuck! ብሎ ሲወድቅ አየሁት፤ ልጅ እያለሁ እናቴ “ ምግብ
መወርወር ጡር ነው “ ትለኝ ነበር፤ እረ ጦርም ነው እማየ ፤
ይሄው አንድ ምስኪን ፖስታ አመላላሽ ፈረንጅ ለትንሽ ገድየ ነበር!
በክቡር ዳኛ Frank Caprio ፊት ቀርቤ ፤የፈነከትኩት ሰውየ
እስኪሻለው ድረስ አልጋው አጠገብ ተቀምጨ በእንግሊዝኛ
እንዳስታምመው ፈረዱብኝ! ሁለት ወር ሙሉ ተጎድቼ
እንደከረምኩ ያወቅሁት በሆስፒታሉ ውስጥ የሚቀርበልኝን መኖ
ሳይ ነው-ቆስጣ፤ የወይን ዘለላ፤ በማር የተጠበሰ ዳቦ! ግሪክ
ሳላድ! እረ ወገን! ላስታማሚው እንዲህ አይነት ምግብ ከቀረበ
ለታማሚው ምን እንደሚቀርብ ኢማጂን እንግዲህ!
ባልተያያዘ ዜና ፤
እንደ ዶክተር አቢይ አህመድ ያለ ብልጥ ሰው ግን አለ? ፤
ሰልስትና (ከሶስት ቀን በፊት) ተቃዋሚዎችን ፓርላማ ውስጥ
ሰብስቦ ሲያወራ ማስኩን ካፍንጫው ሸርተት አድርጎ ከንፈሩ ላይ
አስቀምጦት አየሁ ፤ ብዙ ሰው ስትራቴጂ መሆኑ የገባው
አልመሰለኝም ፤የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመንበሮች " አንተ ብቻ ነህ
እንዴ አፍንጫህን የማናፈስ ነፃነት ያለህ ?ብለው በእልህ
ማሳካቸውን ገለቡት ፤ አብቹየም ሁሉም አፍንጫውን ማጋለጡን
ከተመለከተ በሁዋላ ፈገግ ብሎ በልቡ፤ “ጎበዝ! እንግዲህ ይቺን
ቫይረስ እንቃመሳታ ፤ እኔ ጎልማሳ ስለሆንኩ አገግሜ እነሳለሁ ፤
ለእናንተም ደግሞ አካላዊ ርቀቱን ያስጠበቀ ቀብር አስከባሪ
ይዘጋጃል” ካለ በሁዋላ የምትከተለዋን ዘለሰኛ ማስታወሻው ላይ
አሰፈረ፤
ጎልማሶች ከመከራ ስንማር ፤
ለሼባዎች ነፍስ ይማር

#መልካም ዕሁድ
በላይ በቀለ ወያ

በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..
አንቺን ለመርሳት ስል ፤
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው በቀደም ለት…..
ሳቅሽን የሚመስል ፤
ሳቋን የምትስቅ ፤ አንዲት ሴት ወድጄ
ሳቋን ለማፅናት ስል..
አንቺን ባሳቅሁሽ ቀልድ፤ እንድትስቅ ቀልጄ
ቀልዴ አላስቅ ብሏት ...
ያንቺን የሚመስለው ፤ ያ ሳቋ ቢጠፋ
በቅፅበት ጠላኋት…
አንቺን ባሳቀሽ ቀልድ፤ ሳያት እሷ አኩርፋ፡፡
።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።፣።።
ባለፈው ለት ደሞ…
ያንቺን የሚመስል፤
ኩርፊያ ካኮረፈች፤ ከአንዲት ሴት ጋራ
ላንች የነገርሁሽን...
አስኮራፊ ታሪክ ፣
ኩርፊያዋን ለማፅናት፤ አኩርፌ ሳወራ
ያንቺን የሚመስል ፣
ኩርፊያዋ እስኪጠፋ ፣ ሳቋን ብትለቀው
ድንገት አስጠላችኝ….
እሷ ማን ሆና ነው?
አንቺን ባስኮረፈሽ ፤ ታሪክ የምትስቀው!?
።፣፣፣፣፣።።።።፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣።።።፣፣፣፣
ሰሞኑን ደግሞ አንዷን…
የዋናውን መንገድ፤ ትንሽ ገባ ብላ
አራቴ ወደ ቀኝ...
ሶስቴ ወደ ግራ፤ ከታጠፈች ኋላ
ወደ ሌላ ሚወስድ
ሌላ ዋና መንገድ
ከማግኘቷ በፊት...
ያለው ድልድይ ጋር ፣ እንገናኝ ስላት
አንቺ ከምትወጂው...
አንቺ ከምትቀጥሪኝ፤ ቦታ ላይ ስቀጥራት
‹‹እንዲህ ያለ ቦታ...
በጭራሽ አላውቅም›› ፣ የሚል ነበር መልሷ፤
ዘልዓለም ጠላኀት!
አንቺ ምትወጂውን
ቦታ የማታውቀው ፤ ማን ሆና ነው እሷ?!
፣፣፣፣፣፣።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ብቻ ምን ልበልሽ….
በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..
አንቺን ለመርሳት ስል ፤
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው ደሞ ዛሬ…
የሌላ እንዳልሆን ፤በልክሽ ሰርተሸኝ
ከተውሽኝ በኋላ…….
ምትወርጂውን መንገድ ፣
እኔ እወጣሁት፤ ድንገት አግኝተሸኝ
‹‹እንዴት ነህ? ››ስስትዪኝ ...
እንዴትም እስክሆን ፣ ግራ አጋባሽኝ
አንቺ ነሽ? እኔን ነው? እንዴት አናገርሽኝ?
እንዴት ነኝ ልበልሽ?
እንደዚያው ነኝ በቃ!
እንደዚህ አድርገሽ ፣ያኔው እንደተውሽኝ፡፡
አንቺ ግን እንዴት ነሽ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

#ውብ ቀን
አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ
ጎበናን ተሸዋ አሉላን ተትግሬ
አሉላን ለጥይት ጎበናን ለጭሬ
አሉላ ሴት ልጁን ጥይት ቲያስተኩስ
ጎበና ሴት ልጁን ቲያስተምር ፈረስ
አገሬ ተባብራ ... ካረገጠች እርካብ
ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ።
....


ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian pinned «ከ Covid 19 በላይ ስቃይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞ እየመጣ ያለው የሀገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ነው ይህ ምርጫ ዘንድሮ ይካሄድ አይካሄድ እናንተ ምን ታስባለችሁ የሽግግር መንግስትስ ያዋጣል ? public poll አይካሄድ – 29 👍👍👍👍👍👍👍 48% ይካሄድ – 24 👍👍👍👍👍👍 40% የሽ/መንግስት ይመስረት – 7 👍👍 12% 👥 60 people voted so far.»
ከ Covid 19 በላይ ስቃይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞ እየመጣ ያለው የሀገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ነው ይህ ምርጫ ዘንድሮ ይካሄድ አይካሄድ እናንተ ምን ታስባለችሁ የሽግግር መንግስትስ ያዋጣል ?
public poll

አይካሄድ – 29
👍👍👍👍👍👍👍 48%

ይካሄድ – 24
👍👍👍👍👍👍 40%

የሽ/መንግስት ይመስረት – 7
👍👍 12%

👥 60 people voted so far.
አይፍታህ!..(ልዑል ኃይሌ)

የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት ተሳላሚ አያጣም፤
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ
አልፈታህም ብለው ፈፅሞ አልቀጣም፤
.
ካላፊ ካ'ግዳሚው
እልፍ ሠው መካከል ቢሠለፍ ለፍትሃት፤
በነፍሰ ስጋዬ
ገለባ ልብ እንጂ መች አደለኝ ብልሐት፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ አይፍታህ ነው መልሴ፤
እስር ቋጠሮውን
እንዴት እፈታለሁ ሳልፈ'ታ ራሴ፤
.
ማሕሌት ያልቆመ ልብ
አርምሞ አልባ ምኞት ሱባኤ-ቢስ ሐሳብ፤
ከደመና አያልፍም
በሠማይነቴ በሠውነት ቢሳብ፤
አ'ለምድም ከእንግዲህ
ከነ ሰባራ ሕልም ከኑሮ ጥምጣም ጋር፤
አሳልሜ አልፋለሁ
ላልተማረ ቀልቤ ክህደትና ችጋር፤
ተምሮ ይለፈው
ድኩም ማንነቴ የኔ ምዕመን ስጋ፤
አገኘሁኝ ብሎ
ፍፁም እምነት ይዞ ሠው እንዳይጠጋ፤
.
[ቅስና ለሌለው
'ሠው ነው!' የሚል ማዕረግ ምን ቢጠመጥሙ፤
ነፍስስ ምን ይረባል
ከወዳጅ ክህደት ጋር ልብ እያጣመሙ፤]
.
ለነፍሴ ውዳሴ
ለነፍሴ ቅዳሴ ቆሜ ማደርስበት፤
መቅደስ 'ሠውነቴ!'
እግዜር ያነፀልኝ የኔ ሕልም አለበት፤
.
ይሄ ፅኑ መቅደስ
የሠው ክብሪት ሐሳብ እንዳያቃጥለው፤
ክፋቱን ክህደቱን
ውስጤ ሳይደርስ ነው አርቄ 'ምጥለው፤
.
የሌላው መፈታት
ለሕልሜ ማሠሪያ እንዳያበጅለት፤
ነፍሴን እየመገብኩ
ራ'ቡን እንዲያስታግስ ስጋ ልጣልለት፤
.
የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት 'ሚሳለም ባላጣም፤
ሕልሜን ለተጠማ
'ይፍታህ!' ብዬ አልፌ ራሴን አልቀጣም፤
23ኛው ሚያዚያ, 2012ኛው

#መልካም ቀን ውብ ውሎ ተመኘንላችሁ፡፡
በምድራዊ ጉዞና ርምጃ ውስጥ ፍጽምናን የሚጠብቁ ካሉ
እነርሱ የሥራን ጠባይ የማያውቁ ናቸው። ሥራ ወደ ፍጹምነት
ይሄዳል እንጁ ፍጹም ሆኖ አይጀመርም። ፍጹምነት አንጻራዊ
ነው። እየተሟላም የሚሄድ ነው፡፡ ሁሌም ዕድገትና መሻሻል
ባላለቀ ሥዕል፣ ባልተጠናቀቀ ዜማ ፣ ባላለቀ ክርክር ውስጥ
የሚገኝ ነው ፡፡ ከታሪክ እንማር ፡፡ ልዩነታችን የምንሳሳልበት
እንጂ የምንጠፋፋበት አይሁን፡፡

D/r Abiy Ahmed ዛሬ በfb ገፃቸው ላይ የለጠፉት ድንቅ ንግግር
79ኛው አርበኞች የድል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

( አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ )

ቀደምት አባቶች ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት የመጣውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 79ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን እየተከበረ ነው:: በዓሉ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው የድል ሀውልት በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ እና የአርበኞች ተወካዮች በሃውልቱ ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

#መልካም_የአርበኞች_ቀን
የሰው ልጅ የሚለካው በአለባበሱ ሳይሆን
.
.
.
.
በሜትር ነው፤ የሚመዘነው ደግሞ በሀብት ሳይሆን በሚዛን ነው😜

#ተግባባን
#Ethiopia : እንኳን ለአርበኞች የድል መታሰብያ ቀን አደረሳችሁ!! ሚያዝያ 27 የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ በዓል ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ለሃገር ነጻነት አንድነትና ክብር የኢጣልያ ፋሽስት ወራሪ ሃይልን በመመከት ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመጉረፍ ጠላትን ያስጨነቀበት እና ድል ያደረገበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት «የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰብያ» ነው።

ጥንታዊ ጀግና አርበኞች የጣልያንን ጦር አምስት ዓመት ተጋድለዉ የሃገር ነፃነት አስከብረው አኩሪ ድል ተቀዳጅተዋል። መልካም የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል መታሰብያ ቀን።
ተላልፎ ከሞተ አርበኛ ላገሩ፣
ነፃነት ያገኛል እስከነዘር ዘሩ፣
ነፃነት እንዲያብብ ያገራችን ምድሩ፣
እናንት ገበሬዎች ደማችሁን ዝሩ፣
እኔ ይህን መከርሁ እናንተም ምከሩ፣
ይሄ ብቻ ነው መዳኛ ነገሩ!
( ብላታ ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ- 1927 ዓ/ም)
ስምሽን ቄስ ይጥራው!
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
በምድር ያሰሩት....
በሰማይ ሊታሰር
በምድር የፈቱት ፣ በሰማይ ሊፈታ
ለካህናት ስልጣን ፣ ሰ'ቷል እና ጌታ
ቃሉን እንደ መርገም ፣ ሲቆጥረው አዳሜ
"አሜን " በይኝ ፍቅሬ...
"ስምሽን ቄስ ይጥራው" ፣ ስልሽ ደጋግሜ።
...........................................
ምክንያቱም የኔ ውድ....
ከእርግማን ቃል ላይ ፣ ፅድቅሽን ስቀምም
በቄስ አፍ ሲጠራ ፣ "ወንጌል" ነው ያንቺ ስም!!!
"ኢትዮጵያን ለመጎብኝት የነበረኝ ጉጉት እንግሊዝን ፣ ፈረንሳይና
አሜሪካንን በአንድ ላይ ጎብኝ ብባል ከሚኖረኝ ጉጉት እጅግ
የላቀ ነበር።
ከአፄ ሀይለሥላሴ ጋር ተገናኝቶ መጨባበጥን ደግሞ ከታሪክ
ከራሱ ጋር ተገናኝቶ እንደመጨባበጥ እቆጥረው ነበር ። "
# ኔልሰን_ማንዴላ

መልካም ቀን ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር ፡፡
" ስለ ፍቅሯ ሞተ "
.
//ምንተስኖት_ዋቆ//

ገና አፍላ ሳለሁ ፣በሙሉ አይኔ ላይሽ ፣ እሳሳልሻለሁ ፡፡
እኔም _ _ _
አፍቃሪሽ ሳልሆን ፣ ሎሌሽን መስዬ ፣
በአንቺነትሽ ታዛ ፣ ስኖር ተጠልዬ ፡፡
በፍቅርሽ ታመምኩኝ ፣
ሞቼ ተቀበርኩኝ ፣
"ስሞት እንዳትረሺኝ" ፣ ብዬ ተናዘዝኩኝ ፡፡
ግና እንዲህ ሆኖ ፣
ነፍሴ በ'አንቺ ችሎት ፡ ላይፀድቅ ተኮንኖ ፤
ቀብሬ ላይ ቆመዉ ፣ አፅሜ ላይ ተረቱ ፣
'ስለፍቅሯ ሞተ' ፣ ብለዉ ተዛበቱ ፡፡
# ተፈጠመ
በምድጃዬ
.........
በዓይኔ ምድጃ ውስጥ-
ፍም እሳት ይዣለሁ
ፍቅር ይሞቀኛል
በዓይኔ ምድጃ ውስጥ-
በረዶ ይዤ አድራለሁ
ሀዘን ይበርደኛል
ዓይኔ ላይ ድስት አለ -
ነገር ላብስል ብዬ
እሳት አነድዳለሁ
ሆድ የባሰኝ እንደሁ-
በፈላው ዕንባዬ
ተስፋን ጥጄ አድራለሁ፡፡

© ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ


#ሠናይ_ምሽት