ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.37K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
💎💎💎ፍቅር💎💎💎:

"እምነት ፣ተስፋ ፣ፍቅር የሰው ልጅ ህልውና መሰረት ናቸው . . .
በህይወትህ ከሶስቱ አንዱን ያጣህ ሰአት ለመኖር ከባዱ ግዜ ይሆናል . . . ፍቅር ከሁሉም የፀና ነው፡፡"

❤️❤️❤️ፍቅር ይስጠን❤️❤️❤️
#መልካም_ቀን
@Simetin_Begitim
በትላንት መበሳጨት ለነገ መጨነቅ ዛሬን ማበላሸት ነው!
#መልካም_ቀን
#ከሙሉ_ጤና_ጋር
ተመኘንላችሁ፡፡
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ
ዕንባህን ባረገኝ

© ሰሊና

ከውስጥ ስሜትህ ከልብህ ፈልቄ
የአጉል ኩራትህን ሽፋኑን ፈልቅቄ
የዐይኖችህን ብሌን በዕንባ ሞልቼ
ቅል ባሳክላቸው በዕንባ አሳብጬ
ደም ባስመስላቸው ስሜትህን ገልጬ
ሲቃ ብሆንብህ ድምፅህን ዘግቼ
ጉንጮችህን ባርስ በመንታ ወርጄ
ከዛም...
ይህን ሁላ ሄጄ ሁሉን አቋርጬ
ብገኝ እመርጣለሁ ከንፈርህ ላይ ሞቼ

#መልካም_ቀን
ውብ ውሎ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ!!
ቲቸር ቦጋለ፡ ሒሳብ ሊያወሩልን ሲገቡ
" መጡ ደግሞ! ስራ ሊያስፈቱን " እንል ነበር።
ማንም አይሰማቸውምኮ፡ ብቻቸውን ያወራሉ
.............One man show!.............
" ውይ! ልጆች ይሄን ፎርሙላ አሳሳትኳችሁ ይቅርታ! "
......ተሳስተው ቢቀሩስ ምናለበት?.....
" ምንም አይደል ".....Who cares!?
ስድባቸውስ
" ትኋን ሁሉ! "
......የዘንድሮ ፈላ የቻይና እቃ መስሎታል ይሄኔ.....
ያኔ ትኋን እንደልብ የሚገኝ ተባይ ነበር! አዬ ግርማ ሞገስ! አዬ
እርጋታው!
ከነከሳችሁ በኋላኮ አይሸሽም! እንደ ድፍን ምስር ተጎልቶ
ይጠብቃችኋል! እናንተም ለመያዝ መጣደፍ አያስፈልጋችሁም፡
ጠዋት ከነከሳችሁ ንዴታችሁ ካልበረደ ማታ መጥቶ አንስቶ
መወርወር ነው!
ጣ! ይላል ሲወድቅ ( ወለምታው መሰለኝ! )
ከትኋን የተረፈችውን ደማችንን ቀይ መስቀል እየቀዳት ነውኮ
አይናችን ብቻ የቀረው! ( እንደ ጉጉት! )
እሱም አይን ሆኖ ቲቸር ቦጋለን ነው የምናይበት!
የፈተና ውጤታችንን አይሰጡንም። እኛም አንጠይቅማ!
" ቀጥሎ የማን ክላስ ነው? "
" የፓርላማ! "......የክላሳቸው ስም!
" አይታመሙምንዴ አንዳንዴ? "
" ሲሚንቶ ነገር "
ፊዚክስ ቲቸር ይግደለኝ! እሱ ሁሌም ያመዋል
" ተማሪዎች ነገ የለሁም! አርሾ እሄዳለሁ " ይላል ሁሌ
ያማረበት እየመሰለው በተሰበሰብንበት
" አርሾ ሰገራ ስጥ ብለውኝ..." ብሎ ያወራናል
......ይድፋህ አቦ!.......
ሁልጊዜ አርሾ ሄጄ ሰገራ ሰጥቼ መጣሁ ይላልንዴ?
" ባለገ! ይሄ ሰው " ይላል ጌቱ
" ወይ ሽንት ቤት የለው ይሆናል "
የአስተማሪዎቻችን ትዝታ ብዙ ነው።
ኢለመንተሪ ላይ ቲቸር ጸጋዬ ትዝ ይሉኛል
" የፈሳውን ካላጋለጣችሁ በመደዳ ትገረፋላችሁ "
ይታያችሁ! በአንድ አቃጣሪ ቂጥ፡ ስንጠፈጠፍ
ቲቸር ጸጋዬ የሚታሙት የተማሪ ምሳቃ በማጫረስ ነበር
.......ምሳ እቃ ሰባሪ በሏቸው.....
ምሳ ሰአት ላይ አፍንጫቸውን አስቀድመው ከች ይሉና፡
" ማነው ጎበዝ! አጉርሱኝስኪ " ይላሉ
አጉርሱኝ ይላሉ ግን በኋላ እሳቸው ናቸው የሚያጎርሱን!

Fikre Z Bhere Ethiopia

#መልካም_ቀን_ሠናይ_ውሎ
አይፍታህ!..(ልዑል ኃይሌ)

የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት ተሳላሚ አያጣም፤
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ
አልፈታህም ብለው ፈፅሞ አልቀጣም፤
.
ካላፊ ካ'ግዳሚው
እልፍ ሠው መካከል ቢሠለፍ ለፍትሃት፤
በነፍሰ ስጋዬ
ገለባ ልብ እንጂ መች አደለኝ ብልሐት፤
ከእንግዲህ በቅቶኛል
ፍታኝ ላለኝ ሁሉ አይፍታህ ነው መልሴ፤
እስር ቋጠሮውን
እንዴት እፈታለሁ ሳልፈ'ታ ራሴ፤
.
ማሕሌት ያልቆመ ልብ
አርምሞ አልባ ምኞት ሱባኤ-ቢስ ሐሳብ፤
ከደመና አያልፍም
በሠማይነቴ በሠውነት ቢሳብ፤
አ'ለምድም ከእንግዲህ
ከነ ሰባራ ሕልም ከኑሮ ጥምጣም ጋር፤
አሳልሜ አልፋለሁ
ላልተማረ ቀልቤ ክህደትና ችጋር፤
ተምሮ ይለፈው
ድኩም ማንነቴ የኔ ምዕመን ስጋ፤
አገኘሁኝ ብሎ
ፍፁም እምነት ይዞ ሠው እንዳይጠጋ፤
.
[ቅስና ለሌለው
'ሠው ነው!' የሚል ማዕረግ ምን ቢጠመጥሙ፤
ነፍስስ ምን ይረባል
ከወዳጅ ክህደት ጋር ልብ እያጣመሙ፤]
.
ለነፍሴ ውዳሴ
ለነፍሴ ቅዳሴ ቆሜ ማደርስበት፤
መቅደስ 'ሠውነቴ!'
እግዜር ያነፀልኝ የኔ ሕልም አለበት፤
.
ይሄ ፅኑ መቅደስ
የሠው ክብሪት ሐሳብ እንዳያቃጥለው፤
ክፋቱን ክህደቱን
ውስጤ ሳይደርስ ነው አርቄ 'ምጥለው፤
.
የሌላው መፈታት
ለሕልሜ ማሠሪያ እንዳያበጅለት፤
ነፍሴን እየመገብኩ
ራ'ቡን እንዲያስታግስ ስጋ ልጣልለት፤
.
የኑሮዬ መስቀል የኑሮዬ ጥምጣም፤
የቄስ ማዕረግ ነጥቆት 'ሚሳለም ባላጣም፤
ሕልሜን ለተጠማ
'ይፍታህ!' ብዬ አልፌ ራሴን አልቀጣም፤
23ኛው ሚያዚያ, 2012ኛው

#መልካም ቀን ውብ ውሎ ተመኘንላችሁ፡፡
ያነበብኩትን ላካፍላችሁ

*ቅናት*

ፍቅሬን ሜዳላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።

ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት።
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት።
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፈርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት

እያልኩ እረግማታለሁ ።

ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።

እያልኩ እረግማታለሁ።

የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።

አበባው መላኩ

#መልካም ቀን ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ፡፡
""" "እናቴ"" """
ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።
እማ ዛሬ ፍቅርሽ ገባኝ!!!

#መልካም ቀን
ግብዣ
{በዕውቀቱ ሥዩም}
_________________________
እትዬ ፀሐይ ቤት ከተከራየሁ ከሁለት ሳምንት በኃላ የገና ዋዜማ
ሆነ ።
''አንተ ልጅ ብቻ መሆን ጥሩ አደለም ተጎረቤቶችህ ጋር
ተቀላቀል!'' አሉኝ እትዬ ፀሐይ ።
እሺ ብዬ ተከተልኳቸው።
ቤታቸው በእንግዶች ተጨናንቋል። ያስተዋውቁኝ ጀመር ። ''ይሄ
ከግራ ጎንህ ያለው ዶክተር ምትኬ ነው ።
ይሄን ቤት ከተከራየው አራት ዓመት ሆኖታል ። ባሁኑ ጊዜ እጅግ
የተከበረ ሐኪም ከመሆኑም ባሻገር ወደ ውጭ ሀገር አሁንም
አሁንም ይመላለሳል። ውጭ ሀገር ማለት ለእሱ ሶደሬ ሄዶ
እንደመመለስ ነው። ለነገሩ ሶደሬ ብርቅ የሆነባቸው ሰዎች እንዳሉ
ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም ። ለምሳሌ አንተ ሶደሬን ታውቃለህ ?''
''አውቀዋለሁ''
''ማወቅማ...ያው በስም ሲጠሩት መስማትህ የት
ይቀራል ?....ሄደህ ታውቃለህ ወይ ማለቴ ነው ?''
''ሄጄ አላውቅም!''
'' እኮ ! ....አየህ ሄድሁ ብትለኝ ማን ወሰደህ ብዬ ላፋጥጥህ
ነበር!!...ይሄ ጎረቤትህ ግን ውጭ ሀገር ይመላለሳል ።
አውሮፕላን ለሱ አንተ የምትመላለስበት 64 ቁጥር አውቶብስ
ማለት ነው ። ታዲያ ሄዶ ሲመለስ በእጅ አንድ ነገር
ሳያንጠለጥልልኝ አይመለስም። መከራየት ማለት ሺህ ብር
ከፍለው በሰው ቤት መፈንጨት ብቻ አለመሆኑን የተረዳሁት በእሱ
ነው እንግዲህ ....'' አሉኝ ።
ዶክተር ምትኬ ራሱን አወዛወዘልኝ። { እኔ ነኝ እወቀኝ እንግዲህ
እንደማለት }
''ይህች ደግሞ !...'' አሉኝ ''ሶፋው ላይ ከፊት ለፊቴ
የተቀመጠችዋን ማለፊያ ሴት በአገጫቸው እየጠቆሙኝ ''ይቺ
ደግሞ በቀኝህ በኩል ያለችው ተከራይ ናት ። ቆንጆ መሆኗ
የማይካድ ቢሆንም እጮኛ ግን አላት ። ለዚህ ነው ዕቃ ለመዋስ
ስትፈልግ እኔን ጠይቀኝ እያልኩ የምጨቀጭቅህ። የወንዶችን
አመል እኔ መች አጣሁት....ነገር የሚጀምሩት ስኒ በመዋስ ነው
።ትንሽ ቆይተው ቢራ ልጋብዝሽ ይላሉ። ስኒ ሳይኖርህ እንዴት ቢራ
ልትጋብዝ ትችላለህ ? የማይመስል ነገር እኮ ነው ....ሆሆ
....የወንዶችን አመል እኮ አብጠርጥሬ ነው የማውቀው ።
እንግዲህ ስኒ በመዋስ ይገቡና በኃላ የሚፈልጉትን ሲያገኙ ጀበና
ይሰብራሉ። ለማንኛውም ይች ውብ መዓዛ ነሽ ትባላለች ።
እንደነገርኩህ ምን የመሰለ በደምግባቱም በሀብቱም የተሳካላት
እጮኛ አላት። አይ ፀባይ ! አይ ልግስና ....ኑሮው ፊልድ
መውጣት ነው። ከዚያ ሲመለስ ሽንኩርቱን፣ ከሰሉን፣ ፍራፍሬውን፣
ማሩን አስጭኖ ይዞልኝ ይመጣል...አይኔ ይፍሰስ...አይ የሰው
መለያየት !....ሰው ዝጉርጉር ነው ። አንዳንዱ እጁን ኪሱ ጋር
ሰፍቶ ይፈጥረዋል ። አንዳንዱን እንዲያውም ወይ ከኪሱ ወይ
ከእጅ አንዱ የጎደለበት ነው ። ሌላው እንደመአዛነሽ እጮኛ ያለው
ደግሞ ..."
''ይሄ ደግሞ '' አሉ ወደኔ እየጠቆሙ ምን ብለው ሊያስተዋውቁ
እንደሆነ በመጠበቅ አንገቴን ደፋሁ። ''ይሄ ደግሞ ...''ብለው
ቆሙ ። ቀና ብዬ አየኋቸው። ''ይሄ ደግሞ ...ያው ተከራይ ነው
...!'' አሉና ወደ መስተንግዶው ሄዱ ።
ብፌ ነው ።
ብፌውን እየዞርን እህል ማንሳት ጀመርን ።
የእትዬ ፀሐይን ንግግር እያብሰለሰልኩ ድብል እንጀራውን ሳነሳ፣
ክትፎውን ፣ቆስጣውን፣ ስጋውን ፣አይቡን ሳነሳ ሳላስበው ሰሃኔ
ትንሽ ጉድባ መስሎ ኑሯል ።''
ወደ ቦታዬ ስመለስ የሁሉም ዓይን ወደኔ መጣ ። እንዴት ያለ ነገር
ነው ? ...አልኩና ቶሎ ቶሎ ንጄ ልቀንሰው እጄን ስሰድ....የእትዬ
ፀሐይ ትንሽ ልጅ ቱር ብሎ ከጓዳ መጣ ።
''እማማ እራቴን!'' አለ ።
'' ሂድና አንሳ!'' አሉና ሰሃን ሰጡት ።
ልጅ ግን የማይረሳ ነገር ተናገረ ።
'' ከዚህ ነው ከዚያኛው ? ከየትኛው ላንሳ?'' አለ የኔን ሰሃን እና
የብፌውን ጠረጴዛ እያፈራረቀ እያየ ።

#መልካም ቀን