ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.45K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
(ልዑል ኃይሌ)
.
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
ከሠው መሐል እንግባ
አቀርቅረን መኖር ይብቃን፤
በዝምታ ፈጅተነው ነው
ጊዜ ንቆን ለዚህ ያበቃን፤
እንጮሃለን ላንታፈን፤
ይበቃናል
ዝምታችን ለዘመናት የገረፈን፤
.
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
እንደተዋደድን እንደተላመድን፤
ተጋባን ተዳርን አንድ ልጅ ወለድን፤
አርባ መዓልት ሲሆን
በጥምቀቱ አምነን ክርስትና አነሳን፤
ስም ማውጣቱ ላይ ግን
መስማማት አቃተን ለፍቺ ተነሳን፤
ልጃችን አደገ መጥሪያ ስም ሳይኖረው፤
ባሻነው ሰይመን ባሻነው ጠራነው፤
ሁሉም እየጠራው
ሁሉንም አቤት ሲል ልጃችን ስም ረሳ፤
ግራ እንደተጋባ
ከተቀመጠበት በቁጭት ተነሣ፤
.
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
በስም ጥል ተኳርፈን
ትዳራችንንም ልጃችንም አጣን፤
በጋብቻችን ላይ የተማማልንበት
መፅሐፍ ቅዱስ ጥለን ሌላ ህግ አወጣን፤
ፍቺ በሚል ድንበር ቤትና አልጋ ለየን፤
መስታወቱን ሰበርን እንዳያተያየን፤
እንዳልተዋደድን
በቅፅበት ጥላቻ በስም ተረሣሣን፤
ልንጋደልበት ጠብ-መንጃ አነሣን፤
ልጃችንም መጣ
ሳንጠራው "ወይ!" ብሎ፤
በኛ ስም ወጥቶለት
በተኮስነው ጥይት ስሙን ተቀብሎ፤
.
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
በጥይቶቹ ድምፅ ልጃችን አገኘን፤
ሁሌም አቤት እንዲል
ተኩሳችን እንዳይቆም መጋደል ተመኘን፤
ልጃችንም "ወይ!" ሲል
አጋማሹን ዕድሜ በከንቱ ጨረሠው፤
ቢወጣም ባይወጣም
ስም የሌለው ፍቅር ስያሜ አፈረሰው፤
.
ጮክ ብለን አብረን ጮክ እንበል!
ለምን እንታፈን
የምን መቆዘም ነው ለምን ነው ዝምታ፤
"መሐረነ!.." እንበለው
"እግዚኦ!" በሚለው ቃል አፋችን ይፈታ፤
"እግዚኦ!" ለልጃችን
"እግዚኦ!" ለተኩሳችን ለጥላችን ማረን፤
የሠውን ሕግ ጥሠህ
ያንተን ሕግ አስተምረን፤
.
"እግዚኦ! መሐረነ!..."
በጠብ-መንጃው ፈንታ መስቀልህ ያስታርቀን፤
በጥበብህ ዋጅተህ በፍቅር አጥምቀን፤
ልጃችንም ይዳን ካ'ፍህ ስም እናውጣ፤
"ፍቅር!!..." እንበለው
ፍቅራችን ፍፁም ነው ካንተ ዘንድ ከመጣ፤
.
"እግዚኦ!..መሐረነ!.."
አለመደማመጥ ትዕቢት ገደለነ፤
ከጉርሻችን ነጥቀን ጠመንጃ አጎረስነ፤
ፋኖሳችን ሰብረን እሳቱን ለኮስነ፤
ከምንም ተነስተን ከምንም ደረስነ፤
"እግዚኦ መሐረነ!.."
..
አትቁጠር ሐጢያቱን
አትቁጠር ቂም በቀል፤
ስራችንን ትተህ
የሚያኳርፈንን ዘመን ሠይጣን ንቀል፤
በጠብ-መንጃው ፈንታ መስቀልህ ያስታርቀን፤
በጥበብህ ዋጅተህ በፍቅር አጥምቀን፤
ልጃችንም ይዳን ካ'ፍህ ስም እናውጣ፤
"ፍቅር!!..." እንበለው
ፍቅራችን ፍፁም ነው ካንተ ዘንድ ከመጣ፤

©ግጥም ብቻ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ሰው ሲኖር 💚💛❤️

ሀገር ብቻዋን ምንም ናት ተራ ምድር ኢትየጵያን ኢትዮጵያ ያስባሏት ህዝቦቿ ሰዎቿ ናቸው ፡፡ እኛን እሚያባላን ሰውነት ስለ ረከሠ ነው ፡፡ ከምንም ነገር በላይ ለሠው ልጅ ክብር ይኑረን እራሳችንንም እናክብር ያኔ ቋንቋው መግባቢያ እንጅ መለያያ ዘር መቁጠርያ አይሆንም፡፡ ሰው ሲኖር አንድ ስንሆን ስንተባበር እንደ አለት እንጠነክራለን ስንለያይ በአሸዋ ላይ እንደታነፀ ቤት እንፈራርሳለን ፡፡ አንድ እንሁን ሠው እንሁን ...

መልካም ውሎ ሠናይ የስራ ቀን💚💛❤️

ሀይለመለኮት ነኝ!

@Simetin_Begitim
የቡና ቁርስ
-------

በእልፍኝሽ ደጃፍ ፥ እንዳገሬው ባሕል
አፍን ለማቦዘን ፥... ስትዘረጊ ፍንጃል
እንደ ጥንቱ ጊዜ...
ጥሞኝ እንድበላ ፥ እንደተለመደው
የቡና ቁርስሽን ፥ ዳቦ 'ካደረግሽው
እመጣለው እቱ…
ጀበናውን ጥደሽ ፥ አቦሉን አድርሽው
.
ሚኪ እንዳለ

for more join @mebacha
@Simetin_Begitim
ፋቂ
Jemal Seid (ድምፅ አልባ ገጣሚ)
ህዝቤ💚💛❤️
ቀለምን በመፋቅ ጊዜውን ከሚፈጀው
ችግሩን ቢፍቅ ነው ለኑሮው ሚበጀው!!
💚💛❤️
@Simetin_Begitim
. ተ ረ ት ተ ረ ት .
(ሜሮን ጌትነት)
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።

ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።

ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
@Simetin_Begitim
ይህን ምስኪን ህፃን ፊቱን እዩልኝማ 😭
ተስፋውን በጀርባው አዝሎ ወደ ፊቱን በድንጋይ ዘግተውበት በመሠቃቅ ሲራመድ ፣ ባልሠራው ሀጥያት ሲሰቃይ እዮልኝማ የስንቱን ተስፋ ደህንነት አደጋ ውስጥ እያስገባን እንዳለን ይበቃል እንበላቸው ለነገው ትውልድ ስንል ቦርቀው ላልጠገቡት ታናናሾቻችን ስንል
#ይበቃል
#ይበቃል
ስለ ሀገሬ እኔም ያሳስበኛል ልጅነቴን ያሳለፍኩባት ከተማ ላይ አንዳች እማልረሳው መልካም ትዝታዎች አሉኝ በንፁህ ኢትዮጵያዊነት ማን ብሄሩ ምን እንደሆነ ሳናውቅ ልጅነታችን ውብ ሁኖ አልፏል ያ አሁን ትዝታ ብቻ ሆኖ ቀርቷል ፡፡ ሁሉም በቡድን ተካፍሎ ይናቆራል ሠላምታው ከአንገት በላይ ነው ብቻ ሁሉም ነገር ያሳዝናል ፡፡ ሀገሬ ታማለች መድሀኒቷ ደግሞ በእኛ አጅ ነው እኛ ግን ደብቀን መድሀኒቱን ስቃዯን እያበዛን ነው ፡፡ ወጣትነት ዝም ብሎ በስሜት መነዳት ብቻ ሆኗል አንዱ ድንጋይ አንስቶ ከሮጠ ሌላውም ምክንያቱን ሣያጣራ መከተል ነው ፡፡ እምንከተለውን እንወቅ ወጣቶች ሀገር እምናፈርስም እምንገነባም እኛ ነን ፡፡ ከፖለቲከኞች እና ምግባቸውን የወጣቱን ስሜት በመቀስቀስ ከሚያበስሉ አክቲቪስቶች ወጣቱ እራሱን እና ኢትዮጵያን ይጠብቅ ፡፡ ሀገሬ ብዙ እሚሠራላት ወጣት እንጅ እሚያፈርሳት ወጣት አትሻም ፡፡
ወደድንም ጠላንም አማራጭ የሌለን አንድነት ብቻ እሚያዋጣን በሁሉ ነገር የተዛመድን አንድ ህዝቦች ነን ፡፡ አንድ እንሁን በፍቅር በመከባበር ኢትየጵያን በብሩህ ተስፋ እንሙላት ዱላ የጨበጡ መንገድ የዘጉ ሰው ያሠቃዩ እጆች ሳይሆን የኢትዮጵያ ቤዛዎች እሚሠሩላት እጆች ናቸው ፡፡

በኢትዮጵያ ተስፋ አለኝ ወደ ቀደመው ገናናነቷ ትመለሳለች ፡፡
ኢትየጵያ እና ህዝቦቿ ለዘለዓለም ተከብረው ይኑሩ💚💛❤️

ሀይለመለኮት ነኝ!!

@Simetin_Begitim
ጀግና ነኝ እያለ ሀገር ያስጨነቀው፣
ድንገት አንድ ምሽት ጥበቃ ቢነፍገው፣
ቄሮ ድረስ ብሎ ጩኸቱን ለቀቀው!!
😂😂😁😂😁😂😁

ጥበብ መናገር ጀምራለች!!
ምክንያታዊ ሁኑ!!
በስሜት አትደግፉ!!
በስሜት አትቃወሙ!!
ቆም ብሎ ማሰብ ሁሉንም መፈተን እና መጠርጠር ቢጠቅም እንጂ አይጎዳም!!

©ዝንቅ መዝናኛ
@Simetin_Begitim
* #በላይ_በቀለ_ወያ *

ሰው ሀገር ሆናችሁ
ሞቴን ባገሬ አርገው ፣
ምናምን ብላችሁ ፣ አታውሩልኝ ወሬ
ሬሳ ሰብሳቢ..
ጥንባንሳ አይደለችም ፣ ኢትዮጵያ ሀገሬ፡፡

ህይወታቹ እንጂ
እውቀታችሁ እንጂ ፣ የሚበጀው ላገር
ሞትማ ያው ሞት ነው!
የትም ቀባሪ አለ ፣ የትም አለ አፈር፡፡

@Simetin_Begitim
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ
--------------------------
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደሮሐ አለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሀይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ ፥ የማልገታ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ።
===============
📙 የማለዳ ድባብ
በዕውቀቱ ስዩም

@Simetin_Begitim
የአፍቃሪ ስንብት
<<>>
እሄዳለሁ ብለሽ፣ ሻንጣሽን ካነሳሽ
ትናንትናችንን፣ በዛሬ ከረሳሽ
አላስገድድሽም፣ መሄድ ካ’ ሻሽ ሂጂ
ባይሆን ተከትየሽ፣ እመጣለሁ እንጂ፡፡
የወፍ መንገድ
‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ተነስታ እንደ ዘበት
‹‹እንሂድ›› አለችኝ ፣ ወፍ ወደ ጮኸበት
‹‹እውነት?!
እንሂድ ምናሻኝ ፣ አሁኑ እንነሳ
ግን የምንደርበው ፣ ልብስ ብንይዝሳ?››
ይህችን ቃል ባወጣ
በቁጣ
‹‹ከመቼ ወዲህ ነው፣ ወፍ ልብስ የምታውቀው?
ይልቅ እሷን ምሰል፣ ልብስህን አውልቀው!››
ብላኝ ልብሷን ጥላ
ትታኝ ገሰገሰች ፣ ወፏን ተከትላ፡፡
‹‹እሽ ስንቅ እንያዝ?›› ልላት አሰብኩና
ተውኩት ሳልጀምረው
የትኛዋ ወፍ ነች፣ ስንቅ ይዛ ምትበረው?!
በቃ ተከተልኳት ፤
ጥብቅ አ’ረገችኝ ፣ ጥብቅ አደረኳት፡፡
አንደበቴ ሰላ ፣ ዝማሬ ጀመረው
ልቤ ክንፍ አወጣ ፣ መንሳፈፍ አማረው
ከመቼ ወዲህ ነው ፣ ወፍ የማትበረው?!

ምንጭ : Book For All Fb Page

ገጣሚ:-መዘክር ግርማ

@Simetin_Begitim
#ታሪክን የሗሊት!
(በእውቀቱ ስዩም)
ከእለታት አንድ ቀን፤ የሺዋ ሃያላን፤ ጭንቅ እማይችለውን
፤ሁሌም take it easy የሚለውን ፤ልጅ ኢያሱን በካልቾ
ብለው ፤ከስልጣን ካባረሩ በሗላ የምኒልክን ልጅ
ዘውዲቱን ዙፋን ላይ ዱቅ አደረጏት ! ተፈሪ መኮንን
የተባለውን ጎረምሳ መስፍን ደግሞ “አልጋወራሽ” ና
“እንደራሴ” የሚል ማእረግ ሸልመው፤ ወረፋ እንዲጠብቅ
አደረጉት፤ አይዞህ ቀስ ብለህ ትደርስበታለህ ብለው
ትከሻውን መታ መታ አድርገው አረጋጉት:: ተፈሪ ዘውዲቱ
እስክትሞትለት ሊታገስ አልቻለም፤ ተቅበጠበጠ!
በመንግስቱ ላይ አድራጊ ፈጣሪ ሆነ፤ ብዙ ሳይቆይ
በንግስቲቱ እና በአልጋወራሹ መካከል የስልጣን ፉክክር
ተጀመረ! መንግስት በዜድና በተፌ መሀል ተከፈለች፤
የኢትዮጵያ ህዝብ እንደፈረደበት በሁለቱ ጉልቤዎች
ብጥብጥ የሚመጣውን መዘዝ በስጋት እየጠበቀ
ተቀመጠ::
ዜድ እንደ እቴጌ ጣይቱ ብልጥ አልነበረችም፤በርግጥ
የምኒልክ ዘመዶች እና አርበኛዎች ከጎኑዋ ነበሩ፤በዚያ ላይ
የምኒልክ ቀጥተኛ ወራሽ ነኝ ፤ሰፊው ህዝብም ከኔ ጋር ነው
ብላ ተዘናግታለች፤
ተፌ በበኩሉ ቀጥተኛ ወራሽ አይደለም፤ ጉድለቱን
ያውቀዋል!! ስለዚህ እንቅልፉን ሰውቶ ጉልበት በመሰብሰብ
ተጠመደ፤ ካባቱ የወረሰውን ሀብት በመጠቀም የዘውዲቱን
ወራሾች ማስኮብለል ጀመረ፤የንግስቲቱን ብዙ አሽከሮች
ሰላይ አድርጎ መለመላቸው፤ ወጣቶችን አብዛኛው ሰራዊት
ከጎኑ ማሰለፍ ጀመረ፤
አልፎ አልፎ የዘውዲቱ አሸከሮች ተፈሪን ዋጋውን
ለመስጠት መሞከራቸው አልቀረም ፤ ተፌ ሙከራቸውን
በተደጋጋሚ አከሸፈ፤ ብዙ ሳይቆይ ተፈሪ የበላይ ሆኖ
ወጣ! የዘውዲቱን ቅንጥብጣቢ ስልጣኖች ሳይቀር
ቀማት፡፡
” ስልጣን፤(power ) በዙርያው ያለውን ካልጠቀለለ በቀር
አርፎ አይቀመጥም” ይላል የአልቦ- መንግስቱ ሊቅ
ሩዶልፍ ሮከር፤ የተፈሪ የፈረስ ስም ጠቅል መሆኑ
አለምክንያት አይደለም!
ቀሰ በቀስ የዘውዲቱ ስልጣን የይስሙላ ሆነ! ደግሶ
ከማብላት እና ቤተክስያን ከመሳም ውጭ የረባ ሞገስ
ያለው ተግባር የምታከናውንበት አቅም አጣች! ምንም
አይነት የመንግስት ስልጣን የሌለው ርእሰ መንግስት ሆና
ተቀመጠች፤ ይህንን የታዘበው የይድነቃቸው ተሰማ አባት
አዝማሪ ተሰማ እሸቴ በልቡ እየሳቀ ፤የሚከተለውን ነጠላ
ዜማ ለቀቀ!
“አዳራሽ ቁጭ ብላ፤ስታበላ ጮማ ስታጠጣ ጠጅ
ስእል ትመስላለች የምኒልክ ልጅ”
the morale of the story

#ስል እንጂ ስእል አትሁን!

©Book for All Fb Page

@Simetin_Begitim
💚💛❤️💚💛❤️
ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ
--------------------------
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደሮሐ አለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሀይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ፤

እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ ፥ የማልገታ

ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ኝ ።
===============
📙 የማለዳ ድባብ
በዕውቀቱ ስዩም
📖 📖 📖 📖 📖 📖

@Simetin_Begitim
#ኢትዮጵያ_ማለት
#እኛ
#እናንተ
#አንተ
#አንቺ ብሎም
#እኔ_ነኝ!
💚💛❤️
እኔ ሰው በመሆኔ ብቻ እኔ ላይ እንዲደርስ ማልፈልገውን ማንም ላይ አላደርስም ፡፡ እነኛነት ውስጥ እኔ ስላለው እኛ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ስለሆንን ኢትዮጵያ ስትታመም እኔም እታመማለው ፡፡ ለሰው ብለህ ሳይሆን ለራስህ ብለህ ኢትዮጵያን ጠብቅ ፡፡

#ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
Photo
ስለ ሀገሬ ያገባኛል---ሰላም ለሀገራችን፣ ሰላም ለሁላችን!
ሞት አያምም!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

@Simetin_Begitim