ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.47K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ሠላም_ይስጠን!

ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
#ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

እንደው አንዳንዴ ይገርማል
አረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
ራስን መውደድ አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካ'ፋችን
ስናይ እየተጠማ ልባችን

አንቃን...

ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን

የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ #ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
.
.
ሠላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለሁ እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል ባ'ይኔ

በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም
ዘላ'ለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን

አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሠላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቀን ወዳጅ አ'ርገህ አንቀን
አንቃን
የት ይደረሳል
ምን ይወረሳል
ይብቃን
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን ከዚህ ፈተና
አፉ ቅዱስ ሰው ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን እግዚኦ ማርና
አቤቱ ..... አቤቱ
አውጣን ከመአቱ
#እግዚኦ
ማረን ..... ማረን
ከክፉ አድነን

ድምፃዊ #ጎሳዬ_ተስፋዬ
#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተረት መሠረት
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
አባቶች እናቶች
በፍቅር ተጋግዘው ፣ ያቆሙልን እውነት
በዘመን ጠልሽቶ...
ለእኛ ለልጆች ፣ ይመስለናል ተረት፡፡
።።።።።።
የኛ ትልቅ ችግር ፣ የኛ ትልቅ ህመም
መሰረት ሳንይዝ.
"የመሰረት" ብሎ ፣" እሺ" እያሉ ማዝገም፡፡
።።።።።።፣
ተረት ተረት
"የመሰረት"
አንድ ሀገር ነበረች
"እሺ"
እምነትን ከፍቅር ፣ ገምዳ ያስተማረች፡፡
"እሺ"
አናም በዚች ሀገር...
ሙስሊሞች በእምነት ፣ መስጅድ ሲገነቡ
ክርስቲያኖች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ምሶሶ ሲያቀርቡ፡፡
"እሺ"
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እናም በዚች ሀገር...
ክርስቲያኖች በምነት ፣ ቤተስኪያን ሲያንፁ
ሙስሊሞች በፍቅር...
ይታዩ ነበረ ፣ ጉልላት ሲቀርፁ፡፡
"እሺ"
እናም በዚ መልኩ ፣ ሲኖሩ ሰኖሩ
እንደተዋደዱ እንደተፋቀሩ
እንደተጋገዙ እንደተባበሩ
መሰረት እንድናይ...
አንዋር ከራጉኤል ፣ ተጎራብተው ቀሩ
"እሺ"
"እሺ" ማለት ጥሩ
መሰረት ሳይዙ ...
የመሰረት ብሎ ፣ መኖር ነው ችግሩ!!!
።።።።።
።።።።።
በኮልፌ ጠሮ የሚገኝ የኡስማን በስጅድ እና የስላሴ ቤተ ክርስቲያን ጉርብትና።
#ሼር ለሁሉም!!!

@Simetin_Begitim
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ሼር #SHARE

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፦

COVID-19 በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አለው?

ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው።
ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው?

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከትሉትን እንዲያደርጉ ይመክርዎታል፦

- እጅዎን ይታጠቡ- ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች

- በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ፤ በእጅዎ ዓይን፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።

- ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ። ቢያንስ የ1 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።

- ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ - ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ። ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ፦ እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ። 8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መደናገጥ እና አጉል ፍራቻ፣ ከበሽታው እኩል አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ!

ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
የፊት ማስክ አጠቃቀም እና አወጋገድ

- የፊት ማስኮን ከማድረግ በፊት እጅም በሳሙና መታጠብ።

- በማስኩ አፍና አፍንጫን መሸፈን ምንም ክፍተት ሳይኖረው።

- ማስኩ አፍንጫዎ ላይ እንደተመጠ እንዲቆይ የአፍና የአፊንጫዎን ጠርዝ በጣቶ መጫን።

- ማስኩን በሚያወልቁበት ወቅት ክዳን ባለው ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጣሉት ወይንም ያቃጥሉት።

- ማስኩን አድርገው እያለ ማስኩን በእጆ ባይነኩ ይመረጣል። ለመንካት ከፈለጉም እጆን በሳሙና ታጥበው መሆን አለበት


#ሼር ያድርጉ
#Share it
ጠቃሚ መልዕክት!

🧼 እጃችሁን በሳሙና እና በውሃ በደንብ ታጠቡ

👋🏾 አትጨባበጡ/አትሳሳሙ

🙅🏽‍♀️ ማህበራዊ መስተጋብርን በጣም ቀንሱ!

አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ከቤት አትውጡ

☎️ ትኩሳት ፣ ሳል እና ትንፋሽ ማጠር...ምልክት ከታየባችሁ በቅድሚያ ከዚህ በታች ባሉት ነፃ የስልክ መስመሮች ይደውሉ ፦

አዲስ አበባ - 8335 /952 ፣ ትግራይ ክልል - 6244 ፣ አፋር ክልል - 6220 ፣አማራ ክልል - 6981 ፣ ኦሮሚያ ክልል - 6955 ፣ ሱማሌ ክልል - 6599 ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል - 6016፣ ደቡብ ክልል - 6929 ፣ ሀረሪ ክልል - 6864 ፣ ጋምቤላ ክልል - 6184፣ ድሬዳዋ ከተማ - 6407

#SHARE #ሼር

#HaymanotGirma