ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.45K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
እንኳን ለነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሠቦቻችን !!

መልካም ቀን መልካም በዓል ይሁንላችሁ !

@Simetin_Begitim
"አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ያሳስበኛል፤ እኔ አሁን 86 ዓመት ሊሞላኝ ነው፤ ሌሊት እንቅልፍ የለኝም፤ ለ2 ሰዓታት ብተኛ ነው ቀሪውን አለቅስበታለሁ። ለምንድነው ብዙ ለማንቆይበት የምንጋደለው? ለምንስ ነው የምንጫረሰው? በጣም ያሳስበኛል ያስለቅሰኛል።"

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር እንድሪስ በሸገር ኤፍ ኤም በነበራቸው ቆይታ ከተናገሩት የተወሰደ

@Simetin_Begitim
ከሎሬቱ አንደበት 💚💛❤️

"ሰው አንድም ከፊደል ሀ ብሎ አንድም ከመከራ ዋ ብሎ ነው እሚማረው "

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

መከራ አያስተምረን ልቦናችን ይምራን በደቦ እና በመንጋ አንመራ ፡፡

መልካም ቀን!!💚💛❤️

@Simetin_Begitim
ከ አንዲት እንስት የቤተሰባችን ገጣሚ የተላከ ምርጥ ግጥም እንካቹ ብለናል👋
ሆድ አይሞላምና ይሄ ገንዘባቸው
ሰላም ይስጡንና አርሰን እናብላቸው!
#እጅጊት ሽባባው
©Book for All Fb Page

@Simetin_Begitim
#ሞቶ_ማሸነፍን
ፈሪ ሸሽቶ ሊድን — በአፉ ሊሾምበት
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል — ሺ ሟች በሌለበት
* * *
በየጦሩ ሜዳ — በየትግሉ አቀበት
ጀግናው ሞቶ አልቆ—ማን ይመስክርበት
* * *
‘ኃሊት ተኪዶ እንኳን — እሬሳ ቢቆጠር
የሞተ ካለ እንጂ — በቃላቱ ጠጠር
አንድም ሰው ላይገኝ—የእሱ ጦር የወጋው
አላዩም ብሎ ነው — ለቀሪው ‘ሚያወጋው
# እኛም # ሁልጊዜ
የተረፈ አግነን — የሞተ እየረሳን
ፈሪ በምላሱ — ሰላም ከሚነሳን
ገዳይ ብቻ ማድነቅ — እዳይሆንብን ሱስ
ሞቶ ማሸነፍን — እንማር ከእየሱስ
* * * * *
ከአርቲስት ቴውድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
######### # #########

ሠናይ ቀን ውብ ውሎ ይሁንላችሁ 💚💛❤️

@Simetin_Begitim
እንኳን ደስ ያላችሁ መላው የሲዳማ ህዝቦች !
የትግላችሁ ፍሬ እንሆ በድምፃችሁ ከጫፍ ደርሷል ፡፡ ሻፌታ የሲዳማ የድል አርማ ! ሲዳማም 10ኛው የኢትዮጵያ የክልል መንግስት ሆኗል ፡፡
ቀጣዮ የሲዳማ ህዝቦች የትግል መስክ የተገኘውን እድል በአግባቡ ተጠቅሞ የህዝቡን ሁለንተናዊ የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እና የሁል ጊዜ የህዝቡ ጥያቄ የሆነውን መልካም አስተዳደር መገንባት ነው፡፡
((ሰለሞን ሳህለ))

"እናትሽ..." ይሰኛል የግጥሜ ርእሱ
እናትሽ...
እናትሽ ምን ትሁን ?
ሶስት ነጥብ አለዉ ከእናትሽ ቀጥሎ
ቀጣዩን ሊነግርሽ ጅማሬዉን ጥሎ
እናትሽ . . .(ሶስት ነጥብ ያዉም በዝግታ)
እናትሽ ትባረክ ትዉለድ መንታ መንታ
አንዷን ትሞሽራት አንዷን አስጠቅታ
እናትሽ...(አሁንም ሶስት ነጥብ)
እናትሽ ትባረክ ትዉለድ ሁለት ቀና
አንዷ ለቁም ነገር አንዷ ለሽፍድና
እናትሽ...አሁንም ሶስት ነጥብ
ለፍቅር አይደለም ወይም ደግሞ ለጠብ
አንቺ ግን እንዴት ነሽ ከናትሽ ምናለኝ
ሰይጣን አፈር ይብላ እናትሽ ያስባለኝ
በነገራችን ላይ ሶስት ብየ አንድ አለኝ
ርእሴን ልጻፍ
ፍርሃት ከከበበሽ ጠብ ጠብ ከሸተተኝ
ርእስ
ይቅርታ
ፖራምፖ ድርጭታ
አሲምባ ወዲባ
ዱደቢት ደዲባ
ደዱዲ ዲዲዳ
ባገራችን እዳ
በሸንኮር አገዳ
በግድብ በግምቡ
ባሸሸዉ ፈረንካ ያበጠበት ልቡ
ባየር ላይ ጨዋታ
ባየር ላየር ንግዱ
አፍራሽ አስራ ሀንዱ
እድገት አስራ አንዱ
ወይ አንዱን አይጠሉ
ወይ አንዱን አይወዱ
ሸጋ ሰዉ ሸሽገዉ
ፉንጋ አያስወርዱ
እናትሽ ይግባቸዉ
እናትሽ ይረዱ
ሶስት ነጥብ አለኝ
ሶስት ግዜ ይዉለዱ

@Simetin_Begitim
*ምንም አልል *
(ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን)

እሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
በደቂቃ ዕድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ጊዜዬን እያሰላሰልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር፤ እየደገምኩ እያሰለሰልኩ
ሰልሰለች እየመላለስኩ ..........
እሺ እንግዲህ በጸጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለቸ እየደጋገምኩ
በእግረ ሕልና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አልመሰክርም
አልልም፡፡ ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም ............
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያስጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያደውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጅ ፤ ሌላ ምንም ምንም አልል


@Simetin_Begitim
አመውዴ(ልዑል ሀይሌ)

እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በግ ማይጠፋው ቤት
ዶሮም አልታረደ
ዘይት ዋጋው ንሮ
እህል ተወደደ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ኑሮ ቀርቶ
አንቺም ተወደሻል
………………………
እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
የቤታችን ቲቪ
ሪሞቱ ጠፍቶበት
የመኪናው መንገድ
አህያ ሄዶበት
ዕምነበረዳችን
ድንጋይ ተጠርቦበት
ያ ፅዱ ጎዳና
ተዝረክርኮልሻል
ለነገሩ ይሁን
አንቺም ሰው ጥለሻል
………………………
እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በአውቶቡስ ፌርማታ
ባቡር ተጠበቀ
ሌባው እየኮራ
ፖሊስ ተደበቀ
ጥርስ ያለው አይስቅም
ድዳሙ እየሳቀ
ለነገሩ ይሁን
ቀን ነግቶ ይመሻል
እንኳን ሌላው ቀርቶ
አንቺም የኔዋ ጉድ
የኔን ልብ ሰርቀሻል
………………………
እናምልሽ ውዴ…
አንቺን በመውደዴ
በዝግ ቤት ውስጥ ሆኜ
ብጠብቅሽ እንኳ
..
.

.
.
.

.
.
.
....
በራችን ተንኳኳ!!

@Simetin_Begitim
ለፈገግታ+አውነታ😂😂

ሁሉም ሰው ሊወድክ አይችልም ምክኒያቱም አንተ ብር💶 አይደለክም።

@Simetin_Begitim
@WalyasHood
#Repost
ፃፍ ፃፍ ይለኛል

ቃላቱን በተርታ
በውሉ ደርድረህ
ብእርህን ከወረቀት
በፍቅር ጥለህ
.
ፃፍ ፃፍ ይለኛል
ስለ ሴት ልጅ ውበት
እጅጉን አግዝፈህ
ውበቷን ከእርሰዎ
በጣሙን አብልጠህ
.
ፃፍ ፃፍ ይለኛል
.
እርሷን ብቻ አንስተህ
የፈጠራትን ረስተህ
እሷን ብቻ ስበክ
ውስብስብ አመሏን
በብዕርህ ተርክ።
.
ፃፍ ፃፍ ይለኛል
ደግሞም እንዲህ ብለህ
.
እንዴት ብትደፍር ነው
ፈጣሪዋን ረስተህ
ፍጡርዋን መስበክህ
ያውም የሄዋንን ዘር
ቃሉን ያሻረችህ
ዘላለማዊትነትን ነስታ
ሞትን ለቸረችህ??
.
ብቻ ፃፍ ፃፍ ይለኛል
መናኛ ሀሳቦቸ
ይተናነቁኛል፤
ፍጡር ከፈጣሪ
ይወዳደሩብኛል፡፡
.
.
.
ብቻ አሁንም ፃፍ ፃፍ ይለኛል !
19-08-10
ሀይለመለኮት፡ተ
@Simetin_Begitim join us
Cod 0️⃣1️⃣

✍️ሰለሞን ገረመዉ✍️

እኔ ምን አውቄ

ታውቂያለሽ አለሜ
አንዳንዴ ቁጭ ብዬ ብቻዬን ሳስበው
የማፍቀሬን ምክንያት ለማወቅ ሳስሰው
ጊዜ መግደል እንጅ መልሱን አላገኘው
ያ የሚያምረው አይንሽ እሱ ነው እንዳልል
አይናማ ለማግኘት ሩቅ ልሂድ ሳልል
በቅርብ አገኛለሁ ቆንጅዬ አይናማ
ካንች የምትበልጥ ልዩ የቀይ ዳማ
ጥርስሽ ነው እንዳልል እኔን ያሰመጠኝ
ብዙ ጥርስ አያለሁ በረዶ ሚመስለኝ
ካንቺ ጥርስ በልጦ የሚያስደነግጠኝ
ያ መልካምነትሽ ብዙ የተወራለት
እሱ ነው የረታት ልቤን የማረካት
ብዬ ልደመድም ውሳኔን ልሰጥ
ሄዋንን አያለሁ ካንቺ የምትበልጥ
ደግነቷ በዝቶ ለአለም የምትተርፍ
ተቸግሮ አይታ ጨክና የማታልፍ
ብቻ ግን አለሜ
ለዛች ለነገርኩሽ አይኗ ያምራል ላልኩሽ
ጥርሷ ይበልጥሻል በረዶ ነው ላልኩሽ
ደግነቷ ስቦኝ የታል ደግነትሽ
ብዬ ተናግሬ ቀናት ላስኮረፍኩሽ
ለሷ ልጅ አይደለም የተንገላታሁት
ፍቅርን እየጠራሁ እንባን ያፈሰስኩት
ካጠገቤ ሆነሽ በናፍቆት ታምሜ
አማላጅ ያስላኩኝ በፍቅርሽ ደክሜ
እየኖሩክ ያለሁት ልቤን ተሰርቄ
ባንቺ ነው አለሜ እኔ ምን አውቄ !!!!!!!!
@simetin_Begitm

@endenaendena
# ኤፍሬም_ስዩም እንደፃፈው
# ኑ_ግድግዳ_እናፍርስ_2008

# የማርያም_ንግስ_እለት ።
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረዋሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምሃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የኣንገት ሃብሌን::



@Simetin_Begitim
"ሲሳይ ነው"
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ይመስለኛል በህልሜ…
ሰው ህልሙን ሲነግረኝ ፣ እኔ አንቀላፍቼ
ህልም እየፈታሁ ነው ፣ ህልሜን ማለም ትቼ፡፡
……………………………………….
‹‹ይመስለኛል በህልሜ…
የተማረ ልጄ ፣ የተመራመረ
ባላዋቂዎች ፊት…
የሚያውቀውን ቋንቋ ፣ ስለተናገረ
"የጋራ ጠላት ነህ"
እያሉ አቃፊዎች ፣ ሲገፉት ሲገፉት
በድንጋይ ሲወግሩት ፣ በዱላ ሲገርፉት
‹‹ዝም››ያላቸው ጊዜ…
‹‹ንቆን ነው›› በማለት ፣ በቀን አርደው ደፉት፡፡››
ብላ ስትነግረኝ ፣አንዲት ምስኪን እናት
‹ሲሳይ ነው መገረፍ ፣ ሲሳይ ነው መደፋት››
በማለት ሸኘኋት ….
የታሰረ ህልሟን ፣ በህልሜ ፈትቼ
ሰው ህልሙን ሲነግረኝ…
ህልም እያየሁ ነበር ፣ ህልሜን ማለም ትቼ፡፡
………………………………………
‹‹ይመስለኛል በህልሜ….
የምወዳት ሀገር ፣ እሷም ምታፈቅረኝ
ካገር ተሰደደች ፣ መሄዷን ሳትነግረኝ
እኔም ሀገሬ ላይ ፣
መኖሪያ አጥቼ ፣ ሀገር እያማረኝ
ከመቃብሬ ላይ
"መግደል መሸነፍ ነው"
የሚል ጥቅስ ያኖራል፣ ሲገድሉኝ ሚቀብረኝ!"
፡፡››
እያለ ሲነግረኝ ፣ አንንድ ምስኪን ወጣት
‹‹ሲሳይ ነው መሠደድ ፣ ሀገር ለቆ መውጣት
ሲሳይ ነው ሀገር ላይ ፣ መኖሪያ ሀገር ማጣት››
በማለት ነገርኩት
የታሰረ ህልሙን ፣ በህልሜ ፈትቼ
ሰው ህልሙን ሲነግረኝ….
ህልም እያየሁ ነበር፣ ህልሜን ማለም ትቼ፡፡
………………………………………
ከነቃሁነ በኋላ….
ማንም ህልሙን ይዞ፣
‹‹ፍታልኝ›› አይበለኝ ፣ ካለሁበት ቦታ
መታሰርም ቢሆን ፤ ሲሳይ ነው ሲፈታ!!!
ህልሜን ልይበታ!!!

@Simetin_Begitim