Seid Social
10.2K subscribers
2.5K photos
418 videos
6 files
1.61K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
ባለፈው ሳምንት በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ የምርጫ ቅስቀሳ ፅዮናዊው ትራምፕ ፅዮናዊውን ባይደንን " ባይደን መጥፎ ፍልስጤማዊ ነው እስራኤልን ከድቷታል ለሀማስ ጥቃት እንድትጋለጥ አድርጓታል እኔ ፕሬዚዳንት ብሆን ኖሮ እስራኤል እንደዚህ አትጠቃም ነበር " በማለት ባይደንን ሲወቅስ ሲሳደብ ነበር።

እንግድህ አሜሪካ በባይደን ዘመን ሁሉንም አይነት እገዛ ለእስራኤል በማድረግ ፍልስጤማዊያን እያስጨፈጨፈች ትገኛለች።

ትራምፕ ከዚህ በላይ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ከንግግሩ መረዳት ይቻላል። ይህ ነውጠኛ እ*ብ*ድ መሪ ጋዛን በኑክሌር እንድትጠፋ እንደማይፈቅድ መገመት ሞኝነት አይደለም። ምናል ማታ ለጋዛዊያን የተመኘውን ለራሱ አግኝቶ በነበር !

ጨካኞች ምድርን እንደፈለጋቸው እንዲያደርጉ የተፈቀደበት ሸእን ግን ይጠናኛል !

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፍረሀትን ጥግ ተመልከቱ !

እነዚህ ጭራቆቹ የእስራኤል ወታደሮች ናቸው ። የሆነ ህንፃ ውስጥ ከአፍ እስካፍንጫቸው ታጥቀው እየገቡ ነው በጣም ፈርተዋል እና በጥንቃቄ እየተጓዙ ሳለ ከላይ አይጥ ወደቀቺባቸው ። እንግድህ ቀጥሎ የሆነውን ተመልከቱና ፍረዱ !
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ጎርጎራ ሀላላ ኬላን የመሳሰሉ ብጥስጣሽ ሪዞርቶችን ይቅርና ቡርጂ ኸሊፋን የሚያክል አስደናቂ ግንባታን እንኳ ኢትዮጵያ ላይ ቢያቆም የነዚህ ግፉአን እንባ ፈሶ እስከቀረ ድረስ ወላሂ ወቢላሂ መቼም ደስ ሊለኝ አይችልም!
አብረቅራቂ ግንባታዎችን አይቼ የምደሰተው ደስታ ግፉአን ሲያለቅሱ አይቼ የማዝነውን 0.00001% እንኳ ሊያፅናናኝ አይችልም !!! በጭራሽ !

የብልፅግና ባለስልጣናት አሸሸ ገዳሜ እያሉ አምባገነናዊ ላይፋቸውን የሚቀጩባቸው የመዝናኛ ሪዞርቶች በእንባ እየታጠበ አንገቱን ደፍቶ ለሚኖረው ምስኪኑ ህዝቤ ምኑ ነው ? ለእኔስ ምኔ ነው ??

ዛሬ ጥጋባቸው ሸፍኖባቸው የድሀን ህይወት አፍረሰው የናጠጠ መዝናኛ ሲገነቡ የማይጠየቁ ቢመስላቸውም ቀን ተገለባባጭ ነውና ለሰሯት ግፍ ሁሉ ቢሆን በዚቹ ዱኒያ ባይሆን ነገ በአኼራ ይከፍሏታል !

ግን በስንቱ ልዘን 😢
ሳዳም ሁሰይን ማን ነው ?
እጅግ አጓጊው የሀያሉ መሪ ታሪክ ከልጅነት እስከ ሀያል አንቀጥቃጭ መሪነት !
የታሪክ መዝገብን አሰናድቼ አቅርቤላችሟላ ትአታተሉትም ዘንዳ በአክብሮት እጠይቃለሁ !

https://youtu.be/VsUN0sKfzkU?si=0P1bnXe_Rw6PH3bx
አርጀንቲና ሀማስን በሽብርተኝነት ፈርጃ በአሸባሪዎች መዝገቧ ውስጥ አስፍራዋለች ።

በፅንፈኛውና ነውጠኛው ጃቪየ ሚሊየ አገዛዝ ስር የገባቺው አርጀንቲና የእስራኤል ቀንደኛ ወዳጅ ሆና ብቅ ብላለች። እናም ይሄ የትራምፕ አምሳያ የሆነና ትራምፕና ኔታኒያሁን አድንቆ የማይጠግበው ቀኝ ዘመም ፅንፈኛውና አወዛጋቢው ሰው አርጀንቲናን በመሪነት ከተረከበ ጀምሮ ወደ ቅራቅር እየወረወራት ይገኛል።
ፅንፈኛው መሪ ካቶሊክ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ የካቶሊክ ሀይማኖትን የሚያናናቅ ከዚያም አልፎ የሀገሩ ልጅ የሆኑትን የካቶሊኩን ርእሰ ሊቃነጳጳስ አቡነ ፍራንቺዝ ኩዝን ጭምር የሚሳደብ ጋጠወጥ መሪ ነው። ከእስፔይን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ጋር አፍ የሚካፈት ከብራዚሉ ሉላ ዳሲልቫ ጋር በቃላት የሚወራወር የመሪነት ግርማም ክብርም የሌለው ሰው ነው። ቦልሶናሪዮ አሁን ላይ ካቶሊክን የማይቀበል ሲሆን ሀይማኖቱንም ወደ አይሁድነት እንደቀየረ ይነገራል። ይሁን እንጅ ከአርጀንቲናዊያን የሚደርስበትን ተቃውሞ በመፍራት ሀይማኖቱን ደብቆ ይገኛል።

ላቲን አሜሪካ ላይ የእርሱን አይነት መሪ የነበረው የብራዚል ጂየር ቦልሶናሪዮ የነበረ ሲሆን ይህኛው መሪ ብራዚል ኢየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን እውቅና እድትሰጥ ያስደረገ መሪ ነበረ። ይሁን እንጅ ብራዚላዊያን ይህንን መሪ ጥለው ሉላ ዳ ሲልቫን ሲመርጡ ብራዚል የፍልስጤማውያን ዋነኛ ወዳጅ ሆናለች።
የአርጀንቲና ሁኔታም በተመሳሳይ መልኩ እንደሚቀየር ተስፋ አደርጋለሁ ።

አርጀንቲና በጃቪየር ሚሊየ አስተዳደር የዋጋ ንረቷ 270% የደረሰ ሲሆን አርጀንቲና የብሪክስ አባል ለመሆን ያቀረበቺውን ጥያቄም ነውጠኛው መሪ አቋርጦታል። ጃቪየር ሚሊዮ የግብረሰዶማዊነትና የአደንዛዥ እፅከፍተኛ አቀንቃኝ ሲሆን እስካሁን ምንም አይነት ትዳር የሌለው ስድ ሰው ነው።
ከርበላእ

መልዕክተኛው ሰዐወ ከተቀመጡበት ክፍል ውስጥ ሁነው አንድ እንግዳ መልዐክ ሊግባ ፈቃድ ይጠይቃል። መልዕክተኛም መልዓኩ እንዲገባ ፈቅደውለት ሌላ ሰው እንዳይረብሽ በሩ እንዲዘጋ አዘዙ።

መልዕክተኛው ሰዐወ ከመልዓኩ ጋር በፅሞና ላይ ሳሉ የልጅ ልጃቸው ሁሰይን በህፃን እርምጃው እየተንገዳገደ ወደሳቸው መጣ። ህፃኑ የአያቱ ትከሻ ላይ መጫወት ለምዷል'ና ልክ እንደመጣ ከትከሻቸው ላይ ወጥቶ መጫወት ጀመረ።

መልዐኩ ወደ ነቢ ሰዐወ ወሰለም ተመለከተ፦‹‹ይህን ልጅ ይወዱታል?›› ብሎ ጠየቃቸው።
‹‹እንዴታ! የአብራኬን ክፋይ!›› አሉት።
‹‹ወደፊት ህዝቦችህ ሲገድሉት ባየህ! ከፈለግክም ከሚገደልበት ስፍራ አፈር ዘግኜ ላምጣልህ? ›› አላቸው።

ብዙም ሳይቆይ መልዓኩ በእጁ የዘገነውን አፈር ለመልዕክተኛ አሳያቸው።ልጅ አልበረክት ያላቸው መል�ዕክተኛውም አፈሩን እያሸተቱ ያለቅሱ ጀመር።

ግዜያት ነጎዱ። ይህ ህፃን ከጨቅላነት እድሜ ክልል ሳይወጣ አያቱ ሰዐወ ሞት አፋፍ ላይ ደረሱ። ህዝባቸውን ሰብስበው፦‹‹ህዝቤ ሆይ! ቤተሰቤን አደራ! ቤተሰቤን አደራ!›› ብለው ተናዘዙ።

ነቢ ሰዐወ አረፉ። በርካታ አመታት ብዙ ክስተቶችን እያስከተሉ ነጎዱ። በመጨረሻም የመልዓኩ ትንቢት ሊፈፀም የነቢ ሰዐወ ልጅ ልጅ የሆነ ሁሰይን ልጆቹን እና ነቢያዊ ቤተሰቦችን ይዞ ከዝያች ከ "ከርበላእ" ምድር ተከሰተ።

በዘመኑ የሙስሊሞች መሪ ተብሎ በሚጠራው የዚድ አማካይነት የተላኩት ወታደሮችም የነቢ ዘር የተባሉ ህፃናትን በአንቀልባ እቅፍ ሳሉ በቀስት ፍላፃዎች ይጨፈጭፏቸው ጀመር።

ሁሰይን ረዐ ህፃናቱ ላይ ሚዘንበውን ቀስት እና የነቢያዊ ቤተሰብ ላይ ሚወርደውን ውርጅብኝ መቋቋም ቢያቅተው የጨበጣ ውግያ ሊያደርግ ትጥቁን ታጥቆ ሲወጣ ለስንብት የያዘውን ልጁን ሳይስመው ከሩቅ የተወነጨፈ ቀስት ህፃኑን ወጋበት።

ህፃኑም፦‹‹አባቴ...! አባቴ...!›› እያለ ህይወቱ አለፈች።
ሁሰይን ረዐ ነገሮች ከአቅሙ በላይ ሁኑበት። አያቱ ትዝ አሉት፦‹‹ልጄ ሆይ! አብሽር ከአያቶችህ ትገናኛለህ›› ብሎ ወደ ትግሉ ገባ።

ብዙም አልቆየም ያ የነቢ ሰዐወ የአብራክ ክፋይ በበዳይ ወታደሮች ተከበበ። አንዱ በሰይፍ ሌላው በቀስት ቀሪው በጦር ይጨፈጭፉት ጀመር። ይህን ሁሉ መከራ ከተቀበለ በኋላ መቋቋም ሲያቅተው ከመሬት ተደፍቶ ማጣጣር ጀመረ።

የነቢን ሰዐወ ዘር ያስቀጥላሉ የተባሉ ሴቶች እና ወንዶች ሁላ ነቢያዊ ውለታን በረሳ ጭፍራ ደማቸው በከርበላእ ሜዳ እንደ ጎርፍ ሲፈስ ዋለ።

ሁሰይንም ረዐ ከወደቀበት የከርበላእ ምድር ሊሞት በማጣጣር ላይ ሳለ ሲናን የተሰኘ የገዢው ወታደር የሁሰይንን አንገት ቆርጦ ጣለው።

ያኔ ነቢያዊው ቤተሰብ በአሳዛኝ ሁኔታ በገዢው ትዕዛዝ በበረሃ ተጨፍጭፈው ጥቂት ህፃናት እና ሴቶች ብቻ ቀሩ።

ሁሰይንን ረዐ የገደሉት የሰራዊቱ አካላት የነቢን ልጅ ልጆች ስንቅ እና አልባሳትን ተቀራመቱባቸው።

ነቢ ትከሻ ላይ ይጫወት የነበረው ሁሰይን ዛሬ ገላው በደም ተላውሶ ከበረሃ አሸዋ ላይ ወድቋል። ሙስሊም ነን ብለው የሚያስቡት እኚህ የገዢው ወታደሮችም አስር ፈረሶችን መድበው በዚህ ክቡር ገላ ላይ እየተመላለሱ በግልብያ ይረግጡት ጀመር።

በመጨረሻም ሰራዊቱ የሁሰይንን የተቆረጠ ጭንቅላቱን እና የተቀሩትን የነቢ ሰዐወ ቤተሰቦች አስረው ወደ ገዢው (አስተዳዳሪው) ቤተመንግስት አመሩ።

የሁሰይንን ረዐ ጭንቅላት በከረጢት ይዞ የነበረው ሲናን ወደ ቤተመንግስቱ ሲያመራ ቤተመንግስቱ ዝግ ሁኖ ያገኘው'ና ያን የተከበረ ራስ ቅል አንጠልጥሎ ሲናን ከቤቱ ገባ።

ለሚስቱም እንደ ትልቅ ጀብድ፦‹‹የዘመናትን ድል ይዤልሽ መጣሁ›› አላት።
‹‹ምን ተገኘ?›› አለችው።
‹‹የሁሰይንን ራስ ቅል አመጣሁ›› አላት።
‹‹ጦረኛ ወርቅ እና አልማዝ ማርኮ ይገባል፤ አንተ የነቢን ልጅ ራስ ቅል ይዘህ መጣህ? ወላሂ ከንተ ጋር ላልኖር ቃል ገባሁ›› ብላ ትታው ወጣች።

ይህ ሰው ሌላኛዋን ሚስቱን አ�ስመጥቶ ሌሊቱን ከሷ ጋር አነጋ። ጠዋት ሲነቃም ሴቲቱ፦‹‹እዝያ ጋር ምንድነው ያለው! ሌሊቱን ሙሉ ብርሀን እያየሁ አነጋሁ እኮ›› አለችው።

ሲናንም እሷን ትቷት የሁሰይንን ጭንቅላት ይዞ ወደ አስተደዳሪው ቤተመንግስት ማልዶ ሲገባ ቤተመንግስት ውስጥ በርካታ የነቢ ልጅ ልጆች የራስ ቅሎችን በጓደኞቹ አማካይነት ገብተው ተመለከተ።

የከፍለ ግዛት ገዢው(አስተዳዳሪ) ኢብን ዚያድ ይሰኛል። የሁሰይንን ረዐ ራስ ቅል ከመሬት ተቀምጦ ሲመለከት በያዘው በትር ከርቀት ሁኖ ከንፈሮቹን ነካካቸው።

ይህን ትዕይንት ከቤተመንግስት ውስጥ ሲከታተል የነበረ አንድ ሽማግሌ በሀሳብ ወደ ነቢ ሰ�ዐወ ዘመን ተጓዘ። በትዝታ እንባዎቹ ከጉንጮቹ እየፈሰሱ፦‹‹እባክህ በትርህን ከዚህ ክቡር አፍ ላይ አንሳ! ወላሂ እኚህን ውብ ከንፈሮች ነቢ ሰዐወ ሲስሟቸው በአይኔ ተመልክቻለሁ›› ብሎ ይንሰቀሰቅ ጀመር።

የክፈለ ግዛት ገዢውም ይህን አዛውንት እየገላመጠው፦‹‹ወላሂ የጃጀህ ሽማግሌ ባትሆን እገልህ ነበር›› አለው።

አዛውንቱም፦‹‹የዐረብ ነገዶች ሆይ! ዋ ክስረታችሁ! የነቢን ዓሰ ልጆች ገድላችሁ እርኩሳንን ሾማችሁ? ውርደትን የተጎናፀፋችሁ ህዝቦች ዘራችሁ ይጥፋ›› እያሉ በማጉረምረም ወጡ።

ይህ መሪም የሁሰይንን ራስ አንጠልጥሎ መስጅድ በመግባት ህዝብ እንዲሰበሰብ ካደረገ በኋላ የሁሰይንን ራስ ቅል ቆርጦ ድል መጎናፀፉን ይፎክር ጀመር።

ከህዝቡ መሀል ኢብኑ ዐፊፍ ብድግ ብሎ፦‹‹ዋ ጥፋትችሁ! የነቢያትን ልጆች ጨፍጭፋችሁ እንደ ፃድቃን ትመፃደቃላችሁን!›› ሲል ወድያው ገደሉት።

ከዝያም የራስ ቅሎቹን በከተማዋ አዟዙረው ያለ ከልካይ ለህዝቡ ካሳዩ በኋላ ወደ ጠቅላይ ገዢው ወደ የዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ(ንጉስ) ላኳቸው።

የዚድ ከንግስና መንበሩ ላይ ሳለ የነቢ ልጅ ልጆች የራስ ቅሎች ተደረደሩለት።

‹‹ምንድነው?›› አለ።

የጦር መሪውም፦‹‹ባዶ ሜዳ ላይ አገኘናቸው። ከሰይፉም ከጦሩም እየዋዛን ከበብናቸው። መሸሻ አጥተው እማይሸሽ ሽሽትን ሞከሩ፤ አይለምኑ አለማመንን እየለመኑን በሰይፎቻችን ከታተፍናቸው። በቀስቶቻችንም ለበለብናቸው፤ ከሜዳው ላይ ደማቸውን አፍስሰን የራስ ቅሎቻቸውን ይዘንልህም መጣን›› አሉት።

ጠቅላይ ገዢው የሙዐዊያ ልጅ ከደሙ ነፃ ለመሆን እየሞከረ፦‹‹አላህ ይርገማችሁ! ሳትገድሉት ብታመጡት ጥሩ ነበር። እኔ በናንተ ቦታ ብሆን አልገድለውም ነበር›› ብሎ እንደማስተባበል አለ።

የንጉሱ ዘመድ ይህን ሲመለከት እንዲህ ሲል ገጠመ፦

‹‹ባርያ ልጅ ወልዳ፤ ዘሯ በርክቶላት
የነቢን ዘር ሀረግ ክሯን ቆራረጧት››

ይህን ሲል ንጉሱ የሙአውያ ልጅ ገጣሚውን ተቆጣው።

ሌላም ሰው ከበዳዩ ቤተመንግስት አንድ ድምፅ አስተጋባ፦‹‹ነገ ነቢ ሰዐወ ለልጃቸው አማላጅ ሁነው ሲመጡ ላንተ ማን ሊያማልድልህ ነው?›› ብሎ ሸሸ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተቀሩት የነቢ ልጅ ልጆች ከእስር ቤት ወደ ጠቅላይ ገዢ አልተላኩም ነበር'ና ወደ ጠቅላዩ ለመላክ ቅድሚያ ወደ ክፍለ ግዛት ግዢው(አስተዳዳሪው) ላኳቸው። የወታደር ቡድን አጅቧቸው ወደ ኢብኒ ዚያድ (ክፍለ ግዛት ገዢ/አስተዳዳሪ) ተሸኙ።

እኚህ የነቢ ሰዐወ ቀሪ ቤተሰቦች ሁሉም ሴቶች የነበሩ ሲሆን 2 ህፃናት ወንድ ልጆች ብቻ ነበሩ ከመኃከላቸው።

በጉዞአቸው ላይም ሁሰይን እና ሌሎች ቤተሰቦቻቸው የተገደሉበትን ስፍራ ደረሱ። ስፍራው ላይ ወድቆ የቀረው የነቢ ልጅ ልጅ ሁሰይን እና ሌሎችም አስክሬናቸው እዚህም እዝያ ተበታትኖ ሲያዩት ሴቶቹ ያለቅሱ ጀመር።
ዘይነብ የሁሰይን እህት ናት። የነቢ ልጆች ሜዳ ላይ እንዲህ ያለ ከልካይ ወድቀው ስትመለከት እንዲህ ስትል ታነባ ጀመር።

‹‹ዋ! ሙሀመድ፤ ዋ! ሙሀመድ። የአላህ እና የመላዕክቱ ሰላም በርሶ ላይ ይሁን። ሁሰይን በሜዳ ላይ አሸዋ ለብሶ አዩት ወይ! ነቢ ሆይ! ሁሰይን ገላው ተቆራርጦ ሜዳ ላይ ደሙ ሲፈስ አዩት ወይ!... ዋ ነቢ ሴት ልጆችሆ ምርኮ ሁነን ወንድ ልጆችሆ የአውሬ መጫወቻ ሲሆኑ አዩ ወይ! ›› ብላ እዬዬ ስትል ወዳጅ ጠላትን አስለቀሰች።

ክብር እሚገባው ቤተሰብ በውርደት አንገታቸውን ደፍተው ወደ አስተዳዳሪው ዘንድ ገቡ። ከመካከላቸው ትልቋ እና መከራን የተሸከመችው ዘይነብ ልብሷ በትብያ ቆሽሾ እና ተጎሰቃቅላ አስተዳዳሪው ፊት ህፃናት እህት ወንድሞቿን ይዛ ቆመች።

አስተዳዳሪው በንቀት እየተመለከታት፦‹‹ይቺ ማን ናት›› ብሎ ሲጠይቅ ዝም አለች የነቢ ልጅ።
አብሯት የነበሩት ሴቶችም፦‹‹ዘይነብ ናት›› ብለው መለሱለት።

‹‹ያዋረዳችሁ፣ የገደላችሁ እና ጉራችሁን መና ያስቀረባችሁ አላህ ምስጋና ይገባው!›› ብሎ አፌዘባቸው አስተዳዳሪው (ክ.ግዛት ገዥ)

‹‹ይልቁኑ ያ በነቢ ዐሰ ያከበረን እና መጥራራትን ያጎናፀፈን አላህ ምስጋና ይገባው። ውርደት ለአመፀኛ እና ለዋሾ ሁላ ይሁን›› ብላ በስሜት መለሰችለት።

አስተዳዳሪውም፦‹‹አላህ በቤተሰባችሁ የሰራውን ውርደት እንዴት አየሽው?›› አላት እያላገጠ።

‹‹አላህ መሞትን ፃፈባቸውና ሞቱ። በመጨረሻም አላህ አንተንም እነሱንም አቁሞ ያሟግታችኋል›› ስትል መለሰችለት።

ሊማታ ተገባበዘ። ከዙርያው ያሉ ሰዎች ገላገሉ።

እሷን ትቶ ወደ አንድ ህፃን እየተመለከተ፦‹‹እስቲ ተመልከቱት አድጓል እንዴ?›› ብሎ ወታደሮቹን አዘዘ። ወታደሮቹም ሽርጡን አስወልቀው ሀፍረተ ገላዩን ካዩ በኋላ፦‹‹አዎን አድጓል›› አሉት።

‹‹ውሰዱት'ና አንገቱን ቁረጡት›› አላቸው።

ይቀጥላል...

Sefwan Sheik Ahmedin

እጅግ ዘግናኝ ክስተት በመሆነ በብዙ አሳጥሬ ክፍል አንዱን እዚህ ጋ አብቅቻለሁ። በሁለት ክፍል ይጠናቀቃል።

t.me/Seidsocial
እኔ ስለነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለምና ስለቤተሰቦቻቼው ሳወራ እርሱ ስለ ሺአነት ከሚያወራኝ ዘገምተኛ ጋር እንደት ልንግባባ እንችላለን ?

እነዚህ ሰዎች ቀስ በቀስ ስለ ነብያችንም ስለቤተሰቦቻቼውም ስለደረሰባቸው ግፍ ውጣ ውረድ ስለሀቅ ስለተከፈለው መስዋዕትነትም እንዳይወራ ያለ የሌለ ሀይላቸውን ተጠቅመው እየለፉ ነው።

እነዚህ ሰዎች ስለ ነብዬችንና ቤተሰቦቻቼው ማውራት ሺአነት ነው ብለው በተቆጣጠሯቸው መሳጅዶች ባላቸው ፕላትፎርም ሁሉ እየሰበኩ ነው ለትውልድ አደገኛ የሆነ ነገር እያወረሱ ነው።

እኔ እንግዲህ የሚጠላ ይጠላኛል የሚወድ ይወዳል ስለነዚህ ቅዱሳን ቤተሰቦች እስከመጨረሻው መፃፌን ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ መናገሬን እቀጥላለሁ።

t.me/Seidsocial
#አሹራ አላህ ነብዩላህ ሙሳን ከፊርአውን ነፃ ያወጣበትን የአሹራን ፆም እንድንፆም ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ማዘዛቸው የሚያስተምረን ነገር እጅግ ትልቅ ነው።
የመጀመሪያው መቼምና የትም ቢሆን ከተገፊዎች ጋር መቆም ገፊዎችን ማውገዝ ኢስላማዊ ግደታ መሆኑን ያስተምረናል ። ነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ተበዳይን ሲያዩ ወይንም ስለተበዳይ ሲሰሙ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጎኑ ይቆማሉ። ሙስሊም ባይሆን እንኳ ከተበዳይ ጎን ይቆማሉ።

ሌላኛው ለተበዳዮች ለመዝሉሞች ማዘን ለነርሱ መቆርቆር እነርሱን ማሰብና ስለነርሱ ማውሳት ትልቅ ምንዳ የሚያስገኝ ከአላህ ዘንዳም ሽልማቱ እጅግ ትልቅ መሆኑን የአሹራ ፆም ትልቅ አስረጂ ነው። አላህ ፊርአውን በሙሳ ላይ ያደረሰውን ግፍና ከዚያ ግፍም ነፃ የወጡበትን ክስተት በማስታወሳችን የአመት ወንጀል እንደሚማርልን ለነብያችን ቃል የገባበት አስደናቂ ነገር ነው።

ሌላኛው ትምህር ክስተቶች በተከሰቱበት ቀን ማስታወሱ ደግሞ ሸሪአ መሆኑን አመላካች ነው ። አላህም በቁርአኑ " በአላህ ቀናቶች አስታውሳቸው " ይላልና። እናም ውዱ ነብይ ወደ ሗላ በርካታ አመታትን ተመልሰው ስለዚያ የሙሳና የፊርአውን የጨቀኝና የተጨቋኝ ታሪክ አወሱን ።

እንግድህ እንዳለመታደል ሆኖ በዚህቹ ቀን የዚድ ቢን ሙአዊያ የተባለ አረመኔ ከቤተሰቦች ሁሉ ከዘሮች ሁሉ ምርጥ የነበሩት የነብያችንን ቤተሰቦች በበቀል ተነሳስቶ ከርበላእ ላይ አግቶ የጨረሳቸው። እናም ይህንን በአለም ከተፈፀሙ ግፎች ሁሉ ወደር የሌለውን አሳዛኝ የውዱ ነብይ ቤተሰቦች የመከራና የሀዘን ጊዜ እንዘክራለን ።
ሁለቱንም ክስተቶች ማስታወስ አይጋጭብንም እንደውም በጣም የተያያዙ ናቸው።

ኡመውዮች በኢስላም ላይ ከፈፀሙት በደል ቀዳሚ በሆነው በዚህ የነብያችንን ዘር የማጥፋት ዘመቻ የደረሰውን አሳዛኝ የነብያችን ቤተሰቦች እልቂት ፅናት ሶብር የነብያችንን አደራ የጀነት ወጣቶች አለቃ የነ ኢማም ሁሰይንን ገድልና የኢማን ልቅና እያወሳን እንቀጥላለን !

👉 t.me/Seidsocial
አቡ ሱፍያን የነብያችን እጅግ ቀንደኛው ጠላት ነበረ !
ሙአዊያ ቢን አቢ ሱፍያን የአሊና የሀሰን ቀንደኛ ጠላት ነበረ !
የዚድ ቢን ሙአዊያ ደግሞ የሁሰይንና የተረፉት የነብያችን ቤተሰቦች ቀንደኛ ጠላት ነበረ !
የየዚድ ተከታዮችና ተወላጆች ከከርበላእ ጭፍጨፋ የተረፉትን ጥቂት ቤተሰቦች ማሳደድ ተያያዙት !
ከዚያ እነ ሀጃጅ ኢብኑ ዩሱፍን የመሳሰሉ አረመኔዎች ከነብያችን ቤተሰቦች አልፈው ኡለማኦችን እየለቀሙ መረሸን መጨፍጨፍ ቀጠሉ ። እነ ሰእድ ኢብኑ ጁበይር እና አብዱሏህ ኢብኑ ዙበይርን የመሳሰሉ ታቢኢዮችን ጨምሮ 125,000 ኡለማእና ሙስሊሞችን ጨፍጭፏል ። ለዚያም " ከሀጃጅ ዘንዳ ሰውን መግደል ልክ ዶሮ እንደ ማረድ ነው " የሚል ተቀፅላን ያገኘው !

ታድያ ይህ ሁሉ ከዘመን ዘመን የተሸጋገረ ጥላቻ ምክንያቱ ምንድነው ከተባለ ጎሰኝነት ዋናውን ቦታ ይይዛል።

አቡሱፍያንን የመሳሰሉ የቁረይሽ ባላባቶች ኢስላምን አንቀበልም ብለው እስከመጨረሻው የተፋለሙት እንደት ከኛ ውጭ ነብይ ይላካል በሚልም ጭምር ነው ። ነብያችንን " አሁን አላህ ሰው አጥቶ ነው አንተን ነብይ አድርጎ የመረጠህ ?" እያሉ ይሳለቁባቸው ነበር ። ነብያችን የበድር ጦርነት ላይ በኑ ኡመያዎችን በነ አሊና ሀምዛ መሪነት ልክ እስኪያስገቧቸው ድረስ የነበራቸው ንቀት ንቀት አልነበረም ። መሳለቅ ፤ እብድ ብሎ መሳደብ ፤ ገጣሚ ጠንቋይ ብሎ ማንቋሸሽ ያልፈፀሙት የለም ።
አላህ ነብይ ካስነሳ ለምን ከኛ ወገን አያስነሳም እንደት ከበኑ ሀሽም ያስነሳል እያሉም ይሞግቱ ነበር ።

አቡሱፍያን ባለቤቱ ሂንድ ልጆቹ እነ ሙአዊያ ነብያችን መካን ከፍተው እስኪገቡባት ድረስ ያለመታአት እስከሠጨረሻ እኔጥፍጣፊያቸው ተዋግተዋቸዋል ። በሗላም ነብያችን መካ ሲገቡ እነ አቡሱፍያን መገደልን ሲጠብቁ አዛኙ ነብይ ግን " ሂዱ እናንተ ነፃ ናችሁ " በማለት የእዝነትና የይቅር ባይነት እጃቸውን ዘርግተውላቸዋል ። ከዚያም ኢስላምን ተቀብለናል ብለው ነብያችን ጋር መጡ ከተቀበላችሁ መልካም ብለው ነብያችንም ተቀበሏቸው። እዚህ መጨረሻ ላይ ሲሸነፉ ኢስላምን ተቀበልን ያሉት ሰዎችም ጡለቃእ ይባላሉ ። እንደ ሌሎቹ ሶሀቦችም አይታዩም በደረጃም ከነርሱ ጋር አይመደቡም ።

ግና በኑ ኡመያዎች ተሸንፈው ይቅርታ ተደርጎላቸውም በውስጣቸው ቂምን ከመያዝ በኑሀሽሞችንም መበቀልን ከማለም ቦዝነው አያውቁም ነበረ ።አቡሱፍያን ኢስላምን ከተቀበለ በሗላ ያደረገው ክፉ ነገር አልነበረም።
ሙአዊያ የመጀመሪያውን የበቀል ጅራፍ አስጀመረ ልጁ የዚድ ቀጠለ የልጅ ልጆቹ ከዚያም የጦር አመራሮቹ እነ ሀጃጅ ያን ሁሉ ፊርአውናዊ ግፍ በሙስሊሞች ላይ ፈፀሙ።

ለዚያም ነው የዚድ ቢን ሙአዊያ የሁሰይን የራስ ቅል ተቆርጦ ስጦታ በተላከለት ጊዜ " የበድርን ጦርነት ተበቀልን" በማለት ያኔ በድር ላይ በነ አሊና ሀምዛ የተገደሉትን ቅድመ አያቶቹን አስታውሶ የተደሰተው።

ይህ የአረቦች የጎሳ ፖለቲካ ቀጥሎ የነብያችንን ቤተሰቦች የሚጠሉ ጎራዎች እንዲፈጠሩ አደረገ ። እነዚህ የነቢ ቤተሰቦች ሲነሱ የማይወዱ ሰዎች ናሲቢያዎች ተብለው ይጠራሉ ።


አሁን ላይ ናሲቢያዎች ከአንደኛው የአለም ጦርነት በሗላና የኦቶማን ኺላፋ ከወደቀ በአረብ ነገስታት ስፖንሰር አድራጊነት መልሰው ቁጥራቸው አንሰራርቶ ተረኩን ለመቆጣጠር ችለዋል። እነዚህ አካላት ስለነብያችን ቤተሰብ የሚያወራን ሁሉ በሺአነትና ራፊዷነት እየፈረጁ ለማሸማቀቅ የማይሞክሩት ነገር የለም።

እኛ ግን የናሲቢያዎችን ስም ማጥፋት ፈርተን የ
ስነብያችንን አደራዎች ዝም አንልም !!!

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጋዛ ጋዛ ጋዛ 💔
አህ ዳግማዊቷ ከርበላእ !!

ሁለት ቢሊዮን ህዝብ ከዳችሁ ጠላት ደግሞ ተነባብሮ ጨረሳችሁ 💔
የኢቅና ኢራን ጦርነት !
የሰዳም ሁሰይን ትልቁ ፈተናና የአያቱሏህ ኹመይኒ መራር ትግል ሲታወስ ?

ኢራቅ ኢራንን ለምን ወረረቻት ? ውጤቱስ ምን ሆነ ?
https://youtu.be/fo3AUsNu55o?si=JJYk7aflfZikHbf_
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኑሰይራት ጭፍጨፋ ጋዛ 💔
ከዶናልድ ትራምፕ የግድያ ሙከራ ጀርባ ኢራን እንዳለችበት ተገለፀ።
ኢራን ዶናልድ ትራምፕን ለበቀል ግድያ እያሳደደች ትገኛለች።

ከቀናት በፊት በዶናልድ ትራምፕ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ሙከራ ያቀነባበረቺው ኢራን እንደሆነች CNN እና New york times ይዘው የወጡት መረጃያመለክታል። ትራምፕ በበተኮሰበት ጥይት ጆሮውን ተመቶ መትረፉ ይታወቃል።

በ 2020 በዶናልድ ትራምፕ ትእዛዝ የኢራን ኢስላማዊ አብዮት ጦር መሪ ጀኔራል ቃሲም ሱለይማኒ ከተገደለ በሗላ ኢራን በትራምፕ ላይ ቂም ቋጥራለች። እናም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ዶናልድ ትራምፕ እንዲገደል የኢራን ደህንት መስሪያ ቤት እንደሚሰራ ነው የሚነገረው።

ለረጅም ጊዜ ከተከታተሉ በሗላ የመጀመሪያውን ቃታ ከቀናት በፊት በትራምፕ ላይ መሳባቸውን ነው ሁለቱ ግዙፍ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሀን የጠቆሙት።

አሜሪካ በደህንነት መስሪያ ቤቷ በኩል በሰጠቺው መግለጫ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተልኩ ነው ብላለች። ኢራን ትራምን ለመበቀል እንደምትሰራም አሜሪካ አሳውቃለች ።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ሙሐመድ ይባላል።የኦቲዝም ተጠቂ ጋዛዊ ህፃን ነው።የወራሪው ሰራዊት ቤታቸውን በሐይል ሰብረው ገቡና ሁሉንም የቤተሰብ ክፍል ከቤቱ ውጭ እንዲወጡ አደረጉ።ሙሐመድ ከተቀመጠበት ወንበር መንቀሳቀስ ስለማይችል መውጣት አልቻለም ።እናት ልጇን ተሸክማ ለመውጣት ስትሄድ ከልክለዋት በኃይል ልጇን ጥላ እንድትወጣ አደረጉ።
ከዚያም በቤት ውስጥ ያሰለጠኗቸውን ውሻዎች ለቀቁባቸው።ውሻው አካሉን እየቀረጣጠፈ እየበላ፤ደሙን ሲያይ:-
"በቃህ የኔ ውድ በቃህ!" ይለው ነበር።
የሚያውቀው ቃላት፤የሚያውቀው ነገር ሁሉ መልካም ነበር።
ከጊዜያት ቆይታ በኃላ ቤተሰቦቹ ወደቤት ሲመለሱ ያገኙት አካላቱ በውሻ የተቦጫጨቀ የሙሐመድን ሬሳ ነበር።

© Ber Hum
ይህ ሆስፒታል ቱርክ ለፍልስጤማውያን በጋዛ የገነባቺው ትልቁና ብቸኛው የካንሰር ሆስፒታል ነበር ። ከሁለት ሚሊዮን በላይ ጋዛዊያን የከባድ ህመሞችና የካንሰር ህመምተኞች ብቸኛ መታከሚያ ይህ ሆስፒታል ነበር ። ሆስፒታሉም የቱርክ-ፍልስጤም ወዳጅነት ሆስፒታል ይባላል።

እስራኤል ጋዛን ስትወር ሆስፒታሉ ውስጥ ይታከሙ የተነበሩ ታካሚዎች አብዛኞቹ እዚያው ሆስፒታል ውስጥ የሞቱ ሲሆን የተረፉትን ቱርክ ሀገሯ ወስዳ ለማሳካም ሞክራለች ።

በአሁኑ ሰአት ይህ ሆስፒታል የእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ ሆኖአል።
ቱርክ በእስራኤል ድርጊት ቁጣዋን የገለፀች ሲሆን እስራኤልን በአለምአቀፉ ፍርድቤት እንደምትገትራትም አሳውቃለች። እስራኤል ሆስፒታሉ ላይ በርካታ የሚሳኤል ጥቃቶችን በመፈፀም በርካታ ንፁሀንንና ዶክተሮችን መግደሏ ይታወሳል።

ያው ቱርክ እከሳለሁ ከማለት ውጭ በአሜሪካና አጋሮቿ ጥበቃ ውስጥ ያለችን ሀገር ምንም ማድረግ አይቻላትም።

እስራኤልን መክሰስም ከስሻለሁ ከሚል የፖለቲካ ፍጆታ የዘለለ ለውጥ የለውም ።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
" ፍልስጤማዊያን እንደዚህ ከሚያልቁና ከሚጨፈጨፉ ለምን አይሰደዱም ? ለምን ተሰደው እንደገና ራሳቸውን አደራጅተው አይመለሱም ? ከማለቅ አይሻላቸውም ወይ ? የነብያችንም ሱናኮ ይህ ነው ! " ብለው የሚጠይቁ ወይንም የሚሞግቱ ብዙ ወንድሞች አሉ ።

የኔ ምላሽ " ወዴት ይሰደዱ ? " የሚል ነው ። ማን ይቀበላቸዋል ? በየት መውጣት ይችላሉ ? ማን ያስጠጋቸዋል ? ማንም ! እና ተጨፍልቆ በአሜሪካ ጅምላሽ ጨራሽ መሳሪያ ማለቅን መርጠው ነው ? አይደለም ! ግና ማምለጫም መጠጊያም መሸሸጊያም የላቸውም። ተከበው ያሉት በሁለት ክፉ ሀገራት ማለትም በግብፅና በእስራኤል ነው ። ሁለቱም ዙሪናውን አፍነው ይዘዋቸዋል ። ወደየትም መውጣት አይችሉም።

ሲጀመር ጋዛኮ የስደተኞች ካምፕ ናት ። በአንድ ከተማ በምታክል ግዛት ውስጥ ይሄ ሁሉ ህዝብ ተፋፍጎ የሚኖረውኮ ከነ ቴልአቪቭ ሀይፋ ኢየሩሳሌም ከመሳሰሉ ከተሞች የመጡ ስደተኞች ናቸው ። እስራኤል ከሀይፋም ከኢየሩሳሌምም ከቴል አቪቭም ከሌሎችም የፍልስጤም ከተሞች የገደለቺውን ገድላ የተረፉት ናቸው ጋዛ ላይ የከተሙት ። አብዛኛው የጋዛ ነዋሪ ጋዛ ላይ አይደለም የተወለደው ። አሁን እስራኤል ከተሞቿ ባደረገቻቼው የቀድሞ የፍልስጤም ከተሞች ነው ። እና ከዚህ በሗላ ወዴት ይሂዱ !

ለምን አላቅማቸው ይዋጋሉም የሚሉ አሉ ? ጋዛዊያን ኑክሌየር የታጠቀን ሀገር መዋጋት የሚያስችል አቅሕ አለን ብለው ነው እንዴ የሚዋጉት ? በጭራሽ ! ቢዋጉም ባይዋጉም ሞት ስለማይቀርላቸው እስከ መጨረሻዋ እንጥፍጣፊ እየታገሉ የሚገኙት !

ለፍርድ አትቸኩሉ !

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial