Seid Social
9.46K subscribers
2.38K photos
378 videos
6 files
1.52K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
ኢራን በቴህራን የሚገኘውን የቱርክ አየር መንገድ ቢሮ ዘጋች ።
ኢራን የቱርክ አየር መንገድ ሶስት ሴት ኢራናዊ ሰራተኞች ሂጃብ አንለብስም በማለታቸው የቱርክ አየር መንገድ ቢሮን ዘግታለች ። በቴህራን የነበረው የቱርክ አየር መንገድ ቢሮ ሴት ሰራተኞች በቴህራን ሀላፊዎች ሂጃብ እንዲለብሱ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል ። በመሆኑም በሂጃብ አልደራደርም ያለቺው ኢራን ግዙፉን የአለማችን አየር መንገድ የሆነውን የቱርክ አየር መንገድ ቢሮን ለመዝጋት ተገዳለች ።

ሂጃብ አንለብስም ያሉት የቱርክ አየር መንገድ ሰራተኞች ኢራናዊ ሲሆኑ ኢራን በሚገኘው ቢሮው የቀጠራቸው ናቸው። እነዚህ ኢራናዊ ሴቶች በቱርክ አየር መንገድ ውስጥ መቀጠራቸውን እንደ ማምለጫ በመጠቀም ነው ሂጃብ አንለብስም ብለው የነበሩት።

በኢራን ውስጥ ማንኛዋም ሴት ሂጃብ እንድትለብስ ትገደዳለች። ይህንን አለማድረግም የሚያስቀጣ ወንጀል ተደርጎ የተደነገገባት ሀገር ነች ። መረጃው የ ABC News ነው ።

👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያዊው መምህር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፖሰተው ፖስት የ 20 አመት እስራት ተፈረደበት ።

ሳኡዲ አረቢያዊው መምህር አሰድ አልጋምዲ የሳኡዲን ጉዞ የሚተችና ከኢስላም አስተምህሮ እየተንሸራተተች ነው የሚል ፖስት በመፖሰቱ ነው ሌሊት ላይ በሳኡዲ የደህንነት ሀይላት ታፍኖ ከተወሰደ በሗላ የ 20 አመታት እስራት የተፈረደበት።


አሰድ አልጋምዲ ላይ የተመሰረተው ክስም የሽብርተኝነት ክስ ሲሆን " የአልጋወራሽ ሙሀመድ ሰልማንን ሀይማኖት ጥርጥሬ ላይ እንዲወድቅ አድርገሀል የሳኡዲን ጉዞም ኢስላማዊ አይደለም ብለሀል ይህ ደግሞ የሙሀመድ ቢን ሰልማንን ክብር የሚነካ ነው " በሚል ነው በፖስቱ የ 20 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት ።

አሰድ አልጋምዲ የ 47 አመት እድሜ ያለው መምህር ሲሆን አላህ ካለ ከእስርቤት ከወጣ የ 67 አመት እድሜ ሆኖት ይሆናል ። ይሁን እንጅ የሳኡዲን ንጉስ በመተቼት የታሰሩ ኡለሞችና ተቆርቋሪዎች የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም የማይፈቱ በመሆናቸው የአሰድ አልጋምዲም እጣፈንታ ተመሳሳይ እንዳይሆን ያስፈራል።

👉 t.me/Seidsocial
ሂጅራ ባንክ ትልቅ አብዮት ላይ ነው !

በዘንድሮው እለት በታሪኩ ሪከርድ የሆነን ትልቅ ትርፍ ማግኘት የቻለው ባንኩ የቅርንጫፍ ብዛቶቹን ከ 100 በላይ አድርሶ ሌሎች በርካታ ቅርንጫፎችን አዘጋጅቶ ጨርሶ ወደ ትልቅነት ምእራፍ ያደረገውን ጉዞ በታላቅ እመርታ ያጠናቀቀበት አመት ሆኖ አልፏል።
ያሉትን ክፍተቶች አርሞ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ብቁ ባለሙያዎችን ወደ ተቋሙ በመሳብ አብዮት ላይ ያለው ሂጅራ ባንክ Omni channel የተሰኘውን በሀገራችን ምናልባት ከሂጅራ ውጭ አንድ ወይንም ሁለት ባንክ ብቻ ያለውን የባንክ ኮር ቴክኖሎጂም ባለቤት ለመሆን ችሏል።

ሆኖም የባንኩ ባለቤትነትን የሚፈልጉ በርካታ ማህበረሰቦች በመኖራቸውና ባንኩም ባለቤትን ማብዛትና ካፒታሉን የበለጠ ማግዘፍ ለታላቅነት ለሚያደርገው ግስጋሴ አንዱ ስትራቴጂ አድርጎ በመውሰዱ የዚህን የባለቤትነት እድል ዳግም በውጭና በሀገር ውስጥ ለሚኖረው ማህበረሰባችን እንካችሁ ብሏል።
በመሆኑም የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ የሂጅራ ባንክ ባለቤት መሆን  የሚትችሉበትን እጅግ ቀላል አማራጭ አቅርቦላችሗል። በቴሌግራም መተግበሪያ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ብቻ አክሲዮን የመግዛት ጉዟችሁን መጀመር ትችላላችሁ ፡፡
https://t.me/hijra_share_bot?start=DIEISOC በመጠቀም ጥያቄዎቹን በመሙላት እና ደረሰኙን በመጫን የሂጅራ ባንክ አክሲዮኖችን ከ15 ሺህ ጀምሮ እስከ 300 ሚሊዮን ድረስ በማንኛውም ጊዜ ከየትኛውም ቦታ መግዛት ትችላላችሁ።

ኢትዮጵያ ለባንኩ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከውጭ ሀገር ሳይቀር ባንኮች ወደ ሀገራችን እንዲገቡ የፈቀደች በመሆኑ እናንተም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደዚህ ዘርፍ መቀላቀልና ኢስላማዊ ባንኮችን ፈርጣማ እንድታደርጉ መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ።
https://t.me/hijra_share_bot?start=DIEISOC በመጠቀም አሁኑኑ የሂጅራ ባንክ ባለቤት ይሁኑ !
ጋዛ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት ። ከዚህ ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከ 200 ሺህ እስከ 300 ሺህ የሚጠጉት ቁርአን ሀፊዞች ናቸው ። ያ ማለት ከመቶ የጋዛ ሰው 15ቱ ሀፊዝ ናቸው ማለት ነው ።
በእያንዳንዱ የጋዛ ቤትም አንዳንድ የቁርአን ሀፊዝ አለ ። ይህም በአለም ጋዛን በቁርአን ቀዳሚ ያደርጋታል።

ስለዚህ እስራኤል 100 ጋዛዊያንን በገደለች ቁጥር 15 የቁርአን ሀፊዞችን አብራ ትገድላለች። እስካሁን ኦፊሴላዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የተገደሉት ፍልስጤማዊያን ንፁሀን 39,000 ገደማ እንደሆኑ ቢነገርም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግን ከ 180,000 በላይ ንፁሀን ጋዛዊያን በጦርነቱ ሙተዋል ። ከጋዛ ህዝብ 10% ገደማ እንደማለት ነው። እጅግ ልብ አይሰብርም ???

ወደ ቁርአን ሀፊዞቹ ስንመጣ በቅድሙ ስሌት በእስካሁኑ ጦርነት ወደ 27,000 ቁርአን ሀፊዞች ተገድለዋል ማለት ነው ። ይህ ህይወት ባለው ኡማ ውስጥ ቢደረግ አንድ ሙስሊም እንኳ ተኝቶ ያድር ነበር ወይ?

በየማማ ጦርነት ጊዜ 360 የቁርአን ሀፊዞች ሲገደሉ በአቡበክር ሲዲቅና በሶሀቦቻቼው ላይ የደረሰው ድንጋጤና ስብራትን ሲራን የሚያውቅ ያውቀዋል ። ዛሬ ላይ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሀፊዞች ጋዛ ላይ በጅምላ ሲጨፈጨፉ እንኳንስ ሊያስደነግጠን ሊያሳስበንም አልቻለም !
ዛሬ ላይ በዚያች ጋዛ ምድር ብቻ ከ 1,000 በላይ ጥንታዊ መስጅዶች በመሰቀል ጦረኞቹና በፅዮናዊያኑ ጥምረት ሲወድም ሊያመን አልቻለም ። የራሳቼው ጉዳይ ብለን ጋዛዊያንን ክደናቸዋል !!

ይሄ ረሱላችን ፊት ስንቀርብ የሚያሳፍረን አይመስላችሁም ? ሸፈአቸውን ለመከጀል አንገታችንን ቀና ማድረግ ይቻለን ይሆን ??
ሲያዩን የሚያፍሩብን አይመስላችሁም ???

👉 t.me/Seidsocial
ከፍተኛ የጦር መሳሪያ እጥረት ስለገጠማትና ወታደሮቿም ካለ በርካታ የጦር መሳሪያ ውርጅብኝ ስኬታማ ውጊያ ስለማያደርጉ በጀኔራሎቿ ጉትጎታ እስራኤል ከሀማስ ጋር ተኩስ እንዳቆም ተባበሩኝ ስትል ጥሪ አቅርባ ነበር ። ይህንንም ኔታኒያሁ በአንደበቱ ተናግሮ ድርድርም ተጀምሮ ነበር ።

ይህ እስራኤልን ተሸናፊ የሚያስመስል የተኩስ አቁም ጥሪ ሲደረግ ታድያ አሜሪካን የሚዘውሩ አይሁዳውያን ፖለቲከኞች እና የእስራኤል ወዳጅ አሜሪካዊያን ፖለቲከኞች ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ በባይደን ላይ ወረዱበት ። ምክንያቱም የእስራኤል ጦር እየተፍረከረከ የመጣ አሜሪካ ወደ እስራኤል የምታጓጓዘውን መሳሪያ በጊዜያዊነት በማቆሟ ነበር።

በዚህ የተበሳጨው ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን " አስቀያሚ ፍልስጤማዊያ" በማለት ጭምር ሰደበው። እናም የባይደን አስተዳደር ይህን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ወደ እስራኤል የጦር መሳሪያዎችን ማጓጓዙን ቀጠለ።
በጥቂት ቀናት ብቻ አሜሪካ 500 ፓውንድ የሚመዝኑ በርካታ ሚሳኤሎችን ጅምላ ጨራሽ ቦንቦችን ጭና ወደ እስራኤል አጓጓዘች። እናም ኔታኒያሁ በዚህ የሀይል ሀይል ተሰማው ። አሜሪካ እያስታጠቀችኝ ከቀጠለችማ ለምን ተኩስ አቆማለሁ ወደሚል ሀሳብ ተቀየረ ። እናም አቅርቦት የነበረውን የተኩስ አቁም ጥሪ አጥፎት ተኩስ መቀጠልን መርጧል።

አዎ ጋዛን በቀጥታ እየተዋጋቻት ያለቺው አሜሪካ ነች ። እስራኤል የአሜሪካን ድጋፍ እስካገኘች ድረስ አሜሪካ ከተትረፈረፋት የጦር መሳሪያዋ በገፍ እስካስታጠቀቻት ድረስ እስራኤል ብዙ አመት እየተዋጋች ትቀጥላለች ። ምናሻት ከላይ የሚያዘንቡት የአሜሪካ F-16 እና F-35 የጦር ጄቶች ፤ የሚዘንበው የአሜሪካ ጅምላ ጨራሽ ሚሳኤልና ቦንቦች ስለዚህ ይህ ፍልስጤማዊያንን እስከጨረሰላት ድረስ በደስታ ትቀጥልበታለች ።


👉 t.me/Seidsocial
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙጃሂዶቹ ጀብድ !
የማይሰበሩት ፅኑዎች ! የማይንበረከኩት ብርቱዎች!
የማይፍረከረኩት ባለኢማነኞች በዛሬው እለት የፈፀሙትን ጀብዱ እነሆ ተመልከቱ !
ለሙጃሂዶቱ ወዳጆችም ላኩላቸው
ዛሬ አንድ መስጅድ ውስጥ ጁሙአ እየሰገድኩ አንድ ዳኢ ነኝ ባይ ውሸታም " የአሹራ ቀን የሀዘን ቀን አይደለም አዝናችሁ እንዳትውሉ የደስታ ቀን ነው ። እከሌ ሞተ እያሉ በሀዘን የሚውሉት ጠማ**ማዎቹ ሺአዎች ናቸው እነርሱ ናቸው ገድለው መልሰው የሚያለቅሱት እና እንዳታዝኑ አላህ ሙሳን ነፃ ያወጣበት የደስታ ቀናችን ነው ። ሀገራችን ላይ ስለተገደሉት ሰዎች እናዝናለን የሚሉ ብቅ ብቅ እያሉ ነው እርሱ ሺአዎች ናቸው እንዳትታለሉ ተጠንቀቋቸው" ወዘተ እያለ አፉን ይከፍታል ።

ይህ ሰው የተገደሉት እያለ ስማቸውን ለመጥበስ እንኳ የተፀነፋቸው የነብያችን አደራ የሆኑትን የጀነት ወጣቶች አለቃ የውዱ ነብያችን ሽታና በውዱ ነብይ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት" ቁርአንና ቤተሰቦቼን ትቼላችሁ ሂጃለሁ የቤተሰቦቼን ነገር አደራ " የተባልነውን ውዶቹን የነብያችንን ቤተሰቦች ነው ። ስማቼውን መጥራት ተፀይፎ ስለነርሱ ማዘንንም አፈንጋጭነት አድርጎ ሲጮህ ነበረ።

ያው ከዚያም አልፎ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚፅፉ ሺአዎች በማለት እኛንም በነገር ሲያሽሟጥጥ ነበር ። አግኝቼ ለመሞገት ጊዜውም ሁኔታውም ስላልፈቀደልኝ ትቼዋለሁ።

ለማንኛውም እነዚህ ኡመውዮች አፋቸውን ስለከፈቱና ሰለነቢ ቤተሰቦች እልቂት አታውሩ አትናገሩ አትዘኑ ብለው ስለጮሁ የምንተወው ነገር የለም ።

የሙሳ ህዝቦች ወይንም እስራኤላውያን በመትረፋቸው ከምንደሰተው በላይ የውዱ ነብያችን ንፁህ ቅዱስ ብፁአን ቤተሰቦች በግፈኞችና ሙጅሪሞች በማለቃቸው እናዝናለንና ያንን እናስተጋባለን !
የነብያችን ቤተሰቦች ስለሀቅ የከፈሉትን መስዋዕትነትም አጉልተን እናሳያለን !
እንኳን በሺአነት መፈረጅ ቢያከፍሩኝ ደንታ የለኝም !

👉 t.me/Seidsocial
#ጋዛ_እንደ_ከርበላእ ! ታሪክ ራሱን ሲደግሞ !

በሙጅሪሙ በየዚድ ቢን ሙአዊያና በቅዱሱ በሁሰይን እና ቤተሰቦቻቼው መካከል የተደረገው ፍልሚያ የሀቅና የባጢል ፍልሚያ ነበረ ። በርግጥ ሁሰይን የነብያችንን 70 የሚጠጉ ቤተሰቦች ይዘው ነው በየዚድ ቢን ሙአዊያ በ አስር ሺህ የሚቅጠር ጦር ከርበላእ ምድር ላይ የተከበቡት ።
መቼስ የረሱሉ ትንፋሽ ናቸው ! የጀግኖቹ ጀግና የአሊ የአብራክ ክፋይ የቅድስቷ የጀነቱ ዋና የፋጢመቱ ፍሬ ተወዳጁ ነቢ የሚሳሱላቸው የአይኔ ማረፊያ የሚሏቸው ቅዱሱ የጀነቱ ሙሽራ ሁሰይን !!! እርሳቸው ከአያታቸው ከሙሀመድ ቢን ከብዱሏህ ከአባታቸው ከአሊ ቢን አቢጧሊብ ከእናታቸው ከፋጢመቱ ዘህራ ቢንት ሙሀመድ የተማሩት የወሰዱት በሀቅ ላይ መሰዋትን እንጅ በፍረሀት ከሀቅ ማፈግፈግን አይደለም ። ደግሞም ውዱ ነብይ ናፈቀዋቸው የለ በሞቱ ወደርሳቸው ነው የሚሄዱት ። ፋጢመቱ ያቺ የሴቶች ጀግና በመካ ምድር ላይ ያኔ ሁሰይንን ለመግደል የከበቡት ወላጆች የሆኑት ቁረይሾች በነብያችን ላይ የእንሰሳት ፈርስ በላያቸው ላይ ደፍተው ለመነሳት ቢሞክሩ ባቃታቸው ጊዜ ያንን የቁረይሽ ሙጅረም መሪ ሁሉ ሳትፈራ ሂዳ ያንን ቆሻሻ ነገር ከውዱ ነብይ ከቅዱሱ ነብይ ከአዛኙ ነብይ ከንፁሁ ነብይ ላይ ያነሳችላቸው እነዚያን ሙጅሪሞች የጋፈጠችው ጀግና በርግጥ ለሁሰይን የጡት ወተቷን ሳይሆን ጀግንነት ፅናቷንም ነው አስተላልፋላቸው የሄደቺው ።

እናም ልክ ዛሬ እስራኤልና አጋሮቿ ምእራባውያን እና አረቦች ጋዛን ከብበው እንደሚፈጩት ሁሉ ያኔም የሙጅሪሙ የየዚድ ቢን ሙአዊያ ጦር የነብያችንን ቤተሰቦች ከቦ ጨረሳቸው ።
ዛሬ ላይ ጋዛን ሁሉም ሙስሊም እንደካዳቸው ሁሉ የነብያችንም ቤተሰቦች ተካዱ ። አለን ያሏቸው ኩፋዎች ነበሩ ። የኩፋ ህዝቦችን የዚድ ጦሩን ልኮ ዋናዎቻቼውን ሁሉ ሲጨርስባቸው ለነብያችን ቤተሰቦች ማን ይድረስላቸው !!???

ያኔ የዚድ በነብያችን ቤተሰቦች ላይ ረሀብን ውሀ ማስጠማትን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ ነበር ልክ ዛሬ ጋዛ ላይ እንደሚሆነው!
ኢማም ሁሰይን ልጃቸውን ከፍ አድርገው " እባካችሁ ይህን ህፃን ልጄን አንዴ ብቻ ውሀ እንዳጠጣ ፍቀዱልኝ ብለው የሙጅሪሞቹን ጦር በጠየቁ ጊዜ ሙጅሪሞቹ በሁሰይን ህፃን ልጅ ላይ ቀስት ነበር ያርከፈከፉበት ! ልክ እንደ አሁኑ እንደ ጋዛ ያውም ከዚያም በላይ !

አዎ ዛሬ ጋዛ ላይ ከምናየው ግፍ በላይ በከርበላእ ሙሉ የነብያችን ቤተሰቦች ዘራቸው ተጠፋ ። የሁሰይን አንገት ተቆርጦ ለየዚድ ቢን ሙአዊያ ስጦታ ተላከለት !!

በርግጥ የነብያችን ቤተሰብ ገዳዮች ሁላቸውም የእጃቸውን እያገኙ ነው ። አላህ ይበቀላል !!
ዛሬ ጋዛን የከዱት የነዚያ የበኑ ኡመውዮች የመንፈስ ተጋሪዎች ናቸው !

ሁላቸውንም ለአላህ ብየ ለነብዩ ብየ ለቤተሰቦቻቼው ብየ እጥላቸዋለሁ ! ከነዚህ ጨካኞች ጋርም ለአንድት ቅፅበት እንኳ አብሮ እንዳያኖረኝ !!!

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀማስ ሙጃሂዶች ወደ ፍልሚያ ከመግባታቸው በፊት የተገኘቺውን ነገር ይቀማምሱና ይተጣጠባሉ ውዱእ ያደራርጉና ያላቸውን ንፁህ ልብ ይለብሳሉ። ከዚያም ሽቶ ይቀባባሉ ። ፀጉራቸውን ፂማቸውን ያስተካክላሉ።
ባላቸው ነገር ይዋቡና ሶላት ሰግደው ዱአ አድርገው ለሞት እንደሚከፈን ሬሳ ራሳቸውን አበጃጅተው ወደ ጅሀድ ይገባሉ ። ሸሂድ ለመሆን አላህ ለመገናኘት ናፍቀው !ይህ እንግድህ የኢኽላስ ጥግ ነው።

ሙጃሂዶቹ ሲናገሩ በጣም በጣም ይገርማል ።
በቃ በዚህ ህይወት ውስጥ በዚህ አሳዛኝ ትግል ውስጥ ሆነው ደስተኛ ናቸው። ደግሞ ያላቸው የቂን !
በነገራችን ላይ ይህ የቴሌግራም ግሩፕ አሁን ካለው የአባል ቁጥር እኩል የሆነ ሰው በብሎክ አሰናብቻለሁ። ይህን የምለው ብሎክ በማድረጌ ለመመፃደቅ አይደለም ። አብዛኛው ብሎክ ያደረኩት ሰው ተሳዳቢ ለማወቅ ምንም አይነት ፍላጎት ሳይኖረው ሳያነብ በጭፍን የሚሳደብ የሚያከፍር ፅንፍ የረገጠ ፊርቀኛ ነው። እንደዚህ አይነት ሰው ጋር መዳረቅ ስለማያስፈልግ አብሬ አላስቀጥልም።

እኔ follower ደንታየ አይደለም ። ሲጀመር ሶሻል ሚዲያ ለኔ Cost እንጅ Benefit አይደለም ። የሚጠቅመኝ አንዳች ነገርም የለም። እውነት ያልኩትን መረጃዎች አስተላልፋለሁ ለአንባቢ ሰው ከጠቀመ ። ከዚያ ውጭ እየተከፈለህ ተላላኪ ምናምን ቅብጥርሶ የምትሉ ክሳችሁን ከቁምነገርም አልቆጥረውም።
እና በሀሳብ ልዩነት ውስጥ በሀሳብ የሚሞግተኝ ብቻ ጋር አብሬ እቀጥላለሁ ። ተሳዳቢና አክፋሪን ግን ታግሼ ከማስቀጥል ቻናሉን ደልቼው ብወጣ እመርጣለሁ። ተሳዳቢን ሙስሊምን የሚያከፍርን መአሰላማ ብሎ ማሰናበት አስፈላጊ ነው
በዛሬው እለት እስራኤል በአል መዋሲ የስደተኞች ካምፕ በላይ በፈፀመቺው የሚሳኤል ውርጅብኝ በሰአታት ውስት ከ 100 በላይ ተፈናቃይ ፍልስጤማዊያን አልቀዋል።

ጥቃቱ ፍልስጤማዊያንን ከጋዛ ምድር በሙሉ ለማጥፋት የሚደረገው የዘር ማጥፋት አካል ነው ። ሰሞኑን ከአሜሪካ ለቁጥር የሚታክት የጦር መሳሪያ ያገኘቺው ጨካኟ ሀገር እስራኤል ያለ ምንም እርህራሄ የታጠቀቺውን መሳሪያ ንፁሀን ላይ አርከፍክፋዋለች።ንፁሀንና ህፃናትም በእሳት እየተቃጠሉ መሞት እጣፈንታቸው ሆኗል።

ምእራባውያንም በስራቸው ተደስተው የፍልስጤማውያን ንፁሀንን የሲቃ ድምፅ ልክ እንደ ሞዛርት ሙዚቃ እያጣጣሙት ነው። የንፁሀኑ ለቅሶ ሲቀንስ እስራኤልን ሀይል ይጨምሩላትና እንደገና ሌላ ለቅሶ እያዘጋጁ ይሄ በአለም ፊት አለም አይኑ እያየ አንድ ህዝብ በሀያላን ትብብር እየጠፋ ነው።

👉 t.me/Seidsocial
እነ እንትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ ወሎ ሂዶ ደሴ ላይ አቀባበል ስለተደረገለትና የሆኑ እናቶችም ስለ ደህንነቱ ስለጠየቁት የወሎን ህዝብ እየወረዱበት ነበር ። ጭራሽ በባንዳነት ሲከሱት ያው የተለመደውን የወሎ ጥላቻቼውንም ሲያራግቡ ነበር ።
በርግጥ ሰውየው ወሎ ከመሄዱ በፊት ጎጃም ሂዶ ነበር ። ያው እነርሱ ወሎን መስደቢያ ስለሆነ የሚፈልጉት ያንኛውን ባላየ ያልፉታል ።

ይሄው ሰውየው ዛሬ ጎንደር ይገኛል ጎንደር ሲገባም አዝማሪዎች ሳይቀር በማሲንቆ አጅበው ተቀብለውታል የፈረስና ጋሻ ስጦታም ተበርክቶለታል። አዳነች ጭምር እየተንጎማለለች ጎንደርን ዘንጣባታለች። ግና ያኔ በወሎ ህዝብ ላይ ሲሳለቁ የነበሩ ዛሬ ድምፃቸው የለም። ትንፍሽ አይሉም።

ለማንኛውም ይሄ ንፍቅናቸው ነው የትም እንዳይደርሱ አድርጎ መንደር ላይ ያስቀራቸው። ወሎን ንቆ ተፀይፎ ፈቀቅ የሚል ነገር አይኖርም ።
ወሎ ሚዛን ነው !
አንድ የማይረባ ተኳሽ ዶናልድ ትራምፕ ላይ ተኩሶ ጆሮውን በጥይት መቶታል ። ይህ የሆነው ዛሬ በነበረ የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው ።
እንደት አይነት ማለም የማይችል ከረፈፍ ቢሆን ነው ስንት ነገር እያለ ጆሮውን ጨርፎ የሚስተው።

ትራምፕ ለማንኛውም አሁን አሪፍ የመቀስቀሻ አንድ ነገር አገኘ። ከዚህ በሗላ ሞት የተደገሰልኝ ለአሜሪካ ስል ነው እያለ ይተረተራል ።

አሜሪካን አላህ ያዋርዳት !

ተቦርቡራ የምትወድቅበትን ጊዜ ቅርብ አላህ ያድርገው !
ለአንዲት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ በረሀብ ለሚማቅቁባት ፤ ህዝቦቿ በሰላም ወጥቶ መግባት ከሰማይ ለራቀባቸው ፤ የኑሮ ውድነቱ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎቿን አሸቀንጥሮ ወደ ድህነት ወለል የፈጠፈፈጣቸው ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቿ መጠለያ አልባ ሆነው ጎዳና ላይ ለሚኖሩባትና ስራ አጥነቱ እጅግ ተስፋፍቶ ሀገሪቱ ምርት አልባ እየሆነች ላለች ሀገር ቢሊዮኖች የሚከሰከሱባቸው የመዝናኛ ሪዞርቶች ምኗ ነው ???

የህዝባችን አንገብጋቢ ጥያቄ ሪዞርት ነው ? ሀብታሞችና ባለስልጣናቶች ብቻ እየገቡ አሸሸ ገዳሜ የሚሉበት ሪዞርት ነው ህዝባችንን የራበው ? መዝናኛ አጥቶ ነው ህዝባችን እየተሰቃየ ያለው ???

በእውነት እንደ ብልፅግና አይነት መንግስት ደንታ ቢስ የህዝብ ብሶት ለቅሶ ትንሽ የማይሰማውና የማይረብሸው አላየሁም !!
አብይ አህመድ ሀገሪቱን በኢኮኖሚም በፖለቲካም ሳያረጋጋ ሪዞርት ለሪዞርት እየዞረ ባማሩ መስኮች ውሰጥ ፎቶ እየተነሳ " የብልፅግናችን ቱርፋት " እያለ መቀደድ መዋሸት ከጀመረ ይሄው 6 አመታት አለፉት ነው። ኢትዮጵያ ግን ለዜጎቿ አሜካላ መሆኗን አጠናኬራ ቀጥላለች !

ይሄ የአምባገነኖች ቱርፋት ነውና !!!

t.me/Seidsocial