Seid Social
9.14K subscribers
2.26K photos
332 videos
6 files
1.43K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
እኔና አባቴ

ለመጨረሻ ቤተሰብ ጋር የሄድኩ ግዜ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ረዥም ሰአት አወጋን። ያመው ስለነበር ትንሽ ሰውነቱ ቀንሷል። ቀን ሲከፋ ግዜ ከእድሜ ቀድሞ ያስረጅ የለ እርሱም ላይ የእርጅና ምልክቶቹ መታየት ጀምረው ነበር።

ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሯችንን ደግመን ደጋግመን እየቃኘን ብዙ ተጫወትን። አልፎ አልፎ ሁለታችንም በዝምታ በሀሳብ ባህር ውስጥ እንነጉዳለን። የቀዶ ህክምና ት/ቴን እና ውጭ ሀገር ህክምና ለማጥናት ፈቃድ የሚያስገኝልኝን ፈተና (USMLE) እኩል እያስኬድኳቸው እንደሆነና ሁሉም ጥሩ እየሄዱ እንደሆነ ነገርኩት።

"አንተ እያመለጥክ ነው። ህይወት አምርራ ብትታገልህም እያሸነፍካት ነው"አለኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሌም የሚለኝ ነገር "ተማር ልጄ" ነበር። "ተማር ልጄ ወገን ዘመድ የለኝ ሀብት የለኝም ከጄ "የሚለውን ይወደዋል ... ታዳ ዛሬም ድረስ ድምፁ ይሰማኛል።

እኔም "አንድ ቀን ሁሉም መልካም ይሆናል። ህይወት መስመር እየያዘችልኝ ይመስለኛል" ብየው ትንሽ ዘወርወር ማለት ስለፈለኩ ወጣ ብየ ልምጣና ኋላ እናወራለን ብየው ተነሳሁ።

"በቀጣይ ስትመጣ አንዲት መኪና ይዘህ መትህ አብረን ደግሞ እንዞራለን" አለኝ። ውስጤን ደስ አለው። እሱ በኔ ተስፋ ሲኖረው የኔ ደግሞ የጋራ ህልማችንን የማሳካት ፍላጎቴ ይጨምራል። መኖርህስ ትርጉም የሚኖረው የምትኖርለት አላማ የምታስደስተው ሰው ሲኖርህ አይደል።

ከቤት ወጥቼ ከቅዳሜ ገበያ ት/ቤት እስከ ፒያሳ በእግሬ አዘገምኩ።ፒያሳ ከሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ ብቻየን ገብቼ በረንዳ ላይ ቁጭ ብየ ማኪያቶ እየጠጣሁ በሀሳብ ከወጭ ወራጁ ጋር እየተመምኩ እኔም አንድ ቀን ከሱ ጋር ከላይ ከታች እንደምል በህሊናየ እያሰላሰልኩ አምሽቼ ምሽቱ አይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ወደ ቤቴ ተመለስኩ።

ከለታት በአንዱ ቀን በደረሰብኝ የመኪና አደጋ ከአርቲፊሻል መተንፈሻ መሳሪያው ተላቅቄ ትንሽ ማገገም ስጀምር ዘመድ አዝማድ በተሰበሰቡበት እንዳረፈ ነገሩኝ።

ስለ ሁኔታው ጠየኳቸው

እኔ አድስ አበባ ሆስፒታል ስገባ እርሱ በተመሳሳይ ቀን ደሴ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ነገሩኝ፤

ስለ እኔ ሰምቶ ነበር አልኳቸው?

"እኛ መናገር አልፈለግንም ነበር። መጀመሪያ የሰማው ሊጠይቁት ከሚመጡት ሰወች ነበር።" አሉኝ

"እና እሱ ጋር ማን ነበር። ሁላችሁም እኔ ጋር አድስ አበባ ከነበራችሁ?"

"አንተን እንጅ እርሱ ይቀድማል ብሎ ያሰበ ሰው ማንም አልነበረም። ቢሆንም ግን ግማሻችን አንተ ጋ ግማሻችን ደግሞ እሱ ጋር ነበርን አሉኝ።

"ምን አለ መጎዳቴን ሲሰማ?"ብየ ስጠይቅ

ብዙ አያወራም ነበር። አልፎ አልፎ ብቻ "ልጄ ምንም አይሆንም። እርሱ ገና ልጅ ነው ፤ እኔ ለሱ ፊዳ እሆናለሁ ፣እኔ የርሱን ሞት እሞትለታለሁ" ይል ነበር አሉኝ።

በዛ በክረምት እኔም ቀን ሊወጣልኝ ነው ስል ሌላ ጨለማ ውስጥ ዳግም የገባሁበት አባቴም ከዚች አስከፊ የህይወት ውጣ ውረድ ለዘላለሙ ያረፈበት ክረምት ሆኖ አለፈ።

የለፋሁበት የደከምክምበት ድንገት እንደ ማለዳ ጤዛ በኖ ሲጠፋ በህልሜ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ሲቸለስበት፣ ጉልበት ሲከዳኝና አቅም ሳጣ፣ ፍራቻና ጭንቀት ቤታቸውን ሊሰሩብኝ ዱብዱብ ሲሉ በሰወች መሀል ተከበቤ ብቸኝነት ሲሰማኝ የመናር ትርጉሙ ሲጠፋብኝና የመኖር ጉጉት ሲለየኝ፣ በሀዘንና በደስታየ በከፍታና በዝቅታየ፣ ፍራቻየንና ጭንቀቴን የማዋየው ሰው ድንገት ሲለየኝ ስሜቱን መግለፅ ከባድ የነበረ ቢሆንም ከወደኩበት የጨለማ ዋሻ ወጥቼ ድጋሜ እንደ ንስር ለመብረር "ህይወትን ብቻህን ሁነህ ለመጋፈጥ እንዳትፈራ፣ ለራስህ ከራስህ በላይ ማንም የለህም፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ከምንም በላይ ወደ አላህ ራስህን አስጠጋ" ብሎ የመከረኝ ምክር ለመከራ ግዜ ስንቄ፣ የድካም ግዜ ምርኩዜ፣ የጨለማ ግዜ መብራቴ ከመሆኑም በላይ ነገሮችን ቀለል አድርጌ እንዳይ፣ መንፈሰ ጠንካራና የማይሰበር ማንነት እንዲኖረኝ በአለማዊም በመንፈሳዊም ህይወት ላለኝ የዛሬ ማንነት ትልቅ አሻራውን ጥሎ ያለፈ ለጀግና አባቴ ስል ምንም እንዳልተፈጠረ ነገሮችን ተቀብየ ጉዞየን ቀጥየ ዛሬ ላይ ደርሻለሁ... ስለ ነገ ነገ ራሱ ያውቃል እያልኩ በልቤ ውስጥ ህያው የሆነውን አባቴን ዛሬ በአደባባይ ላመሰግነው ወደድኩ!

እንዲሁም ለመላው የእስልምና ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Dr. Nuru Ahmed: MD, Surgeon

© Hakim

t.me/Seidsocial
አሜሪካ በቻይና ላይ የንግድ እቀባ ጥላለች። አሜሪካ ይህን እርምጃ የወሰደቺው ቻይና የኡይጉር ሙስሊሞችን የሰብአዊ መብት እየጣሰች ነው በማለት ነው።

በመሆኑም በኡይጉር ብዝበዛ የሚመረቱ የትኛውም ምርቶችን ቻይና ወደ አሜሪካ መላክ እንዳትችል ማእቀብ ጥላለች። አሜሪካ የኡይጉር ሙስሊሞችን መብት ቻይና እንድታከብርም አሳስባለች።

መቼስ የሀያላኑ ቁማርና ንፍቅና ገርሞ ገርሞ ይገርማል።
ከፍልስጤም እስከ አፍጋሃኒስታን ለሚሊን ሙስሊሞች ጭፍጨፋ ዋነኛ ተጠያቂ የሆነቺዋ አሜሪካ ለፖለቲካ ትርፏ ስትል ቻይና የሀገሯን ሙስሊሞች መብት እንድታከብር መጠየቋ ይደንቃል።
የኡይጉር ሙስሊሞች በቻይና ከፍተኛ ሲስተማቲክ የዘር ማፅዳት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ይታወቃል

ንፍቅናቸውን ለመግለጽ ቃል ያጥራል!

t.me/Seidsocial
የኡይጉር ሙስሊሞች ማን ናቸው ?
ኢስላምን እንደት ተቀበሉ ?
የቻይና ኡይጉሮችን ወደ ቻይናነት የመቀየር በቴክኖሎጂ የተራቀቀ ዘር ማጥፋት ምን ይመስላል ?
ይሳካላትስ ይሆን ??

ብታዳምጡት ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ


https://youtu.be/6aQPRJh-6YA?si=YrWNtY-g9Lr-0EpI
የጫካ ፕሮጀክት ጫካ ሙሉ ጉዶች !

ብልፅግና የ 10 ቢሊዮን ዶላር ቤተመንግሥት እየገነባ ነው ወደ ብር ሲቀየር 600 ቢሊዮን ብር ገደማ ማለት ነው።። በዚህም የአብይ አህመድ ቤተመንግስት 10 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ በአለም እጅግ ውዱ እጅግ ቅንጡው ቤተመንግስት ያደርገዋል። ይህ ቤተመንግሥት በአለማችን ላይ እስከዛሬ ውድ ተብሎ የተመዘገበውን የእንግሊዙን ቡኪንግሀም ቤተመንግስት በውድነት በ 10 እጥፍ ይበልጠዋል። ቡኪግንሀም ተገንብቶ የተጠናቀቀው በ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነውና። ስሙንም የጫካ ፕሮጀክት ብሎታል።

የአብይ አህመድ ቤተመንግሥት በሰፊው የየካ ክፍለከማ እየተገነባ ሲሆን ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በዘንባባ ዛፎች የተዋቡ 3 ሰው ሰራሽ ሀይቆች ፤ ሰው ሰራሽ ፏፏቴዎችና ወንዞች ፤ ቅንጡ ሆቴሎች ፤ የሀገራት መሪዎችን መቀበያ በጣም የተቀናጡ ዘመናዊ እንግዳ ማረፊያወች፤ የእንሰሳት ፓርኮች ፤ ቅንጡ የባለስልጣናት መኖሪያ አፓርትመንቶች ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነቤተሰባቸው የሚኖሩባቸው የተለዩ እጅግ ውድ ቤቶችን አካቶ የሚሰራ በከተማ ውስጥ ሌላ ከተማ ፤ ኢትዮጵያዊያን ሳይሆኑ ኢትዮጵያን የሚገዙ ብቻ የሚኖሩበት ከተማ እየገነባ ነው።

ይህ ቤተመንግሥት ድንገት መፈንቅለ መንግስት ቢያጋጥም በምድር ውስጥ የሚያሾልክ ዋሻንም ከመሬት በታች እየተገነባለት ነው ። ቤተመንግሥቱ በአለም ላይ አለ በተባ የደህንነት ቴክኖሎጂ እጅግ በሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችም እንዲጠበቅ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ አመታዊ በጀት 17 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ብቻውን 10 ቢሊዮን ዶላር ቅርጥፍ አድርጎ ይበላል። ያ ማለት የሀገሪቱን አጠቃላይ በጀት 59% ያክልን ይወስዳል ማለት ነው።ብልፅግና ይህንን ፕሮጀክት በዋናነት ከኢማራት በሚገኝ ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን ለዚህም ኢትዮጵያን ለኢማራት ቀብድ አሲዟል።

ከዚያ ውጭ ብልፅግና የተለያዩ ባለሀብቶችንና ድርጅቶችን በግድ እያስከፈለ ሲሆን ይህን በማያደርጉ ላይ ከገበያ የማስወጣት ስራም እየሰራ ይገኛል።
ቤተመንግስቱ ከሚያርፍበት ከየካ ክፍለከተማ የተፈናቀሉ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ብሔራቸው እየተለየ አማራ የሆኑት ወደ ደብረብርሃን ኦሮሞ የሆኑት ደግሞ ወደ ወለጋ እንዲሄዱ ተደርገዋል።
የአብይ አህመድ ጫካ ቤተመንግሥት በጀት 5 የህዳሴ ግድቦችን በመቶ የሚቆጠሩ ኢንዱስትሪዎችን መክፈት ይቻለዋል።
ኢትዮጵያ ከ IMF ለመበደር እየለመነች ያለቺው 3.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም አብይ አህመድ ለቤተመንግሥት እያወጣው ያለውን ውጪ 1/3ኛ ብቻ ነው የሚሆነው። ይሁንና IMF የብር ዋጋ ከዶላር አንፃር እንዲወርድ ካላደረግሽ አላበድርም በማለት ኢትዮጵያን እምቢ ብሏል።
በአብይ አህመድ አነሳሽነት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ አዲስ አበባ ቦሌ ላይ እየገነባው ያለው ቤተመንግሥት ብቻውን አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን በዚህም በአለም ላይ የሚበልጠው የእንግሊዙ ቡኪንግሀም ቤተመንግስት ብቻ ነው።

40 ሚሊዮን ዶላር እዳዋን መክፈል ያልቻለች ሀገር ፤ ከ 20 ሚሊዮን በላይ ህዝቦቿ በረሀብ ውስጥ እየኖሩ ባሉባት ሀገር ፤ ከአድስ አበባ ውጭ በሁሉም አቅጣጫ ሰቅጣጭ ጦርነትና የጅምላ ግድያ ባለባት ሀገር ፤ መንግስት ሰራተኞቿ በልተው ማደር በማይችሉባት ሀገር ፤ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ጎዳና ላይ በሚኖሩባት ሀገር ፤ የኑሮ ውድነቱ የስራ አጥነቱ ህዝቡን እያስለቀሰ ባለባት ሀገር ማንም ሀገር ያላደረገውን 10 ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ቤተመንግሥት እየገነባች ነው ብንባል እንደት አድርገን ልንቀበል እንችላለን ?? ያው ለነገሩ ባንቀበልስ ምን ምን ታመጣላችሁ ብሎን የለ !!

እንደዚህ መንግስት ህዝብ የናቀ በህዝቡ ሰቆቃ ያላገጠ ያፌዘ ጨካኝ መንግስት አይቼ አላውቅም።

ኢትዮጵያ የቁልቁለት ጉዞዋን ተያይዛዋለች።
መሪዎቿ ግን የራሳቸውን አለም እየገነቡ ነው።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
" ኑሮ የከበዳቸው የመንግስት ሰራተኞች የምሳ ሰአትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ ነው "
ይላል የሪፖርተር ዘገባ ። ዘገባው በንኡስ ርእሱም " የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉም ተደብቀው ቢሮ ውስጥ እያደሩ ነው " ይላል።

ብዙ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሲወጡ ማንነታቸውን ቀይረው ልመና ላይ ጭምር ተሰማርተዋል። የዩኒቨርስቲ መምህራኖች ራሳቸውን በምግብ መቻል ባለመቻላቸው ዩኑቨርስቲዎች ምገባ እየጀመሩ ነው ።

ከዚህ በላይ የአንድ ስርአት ውድቀት ማሳያ የለም። ይህንን መራር ውድቀት የውሀ ፎንቴንንና የሳር ፓርክ ስለሰራህ አትሸሽገውም።

የሀገሪቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የቁልቁለት ጉዞውን አፍጥነውታል። የትምህርት ስርአቱማ ሙቷል ማለት ይቻላል።

ብልፅግና ሀገሪቱን አሪፍ አድርጎ እያወላለቃት ነው !

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሞቱ የሀጂ ተጓዦች ከ 900 ማለፉ ተገለፀ።
ከ 46 ድግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሙቀት ያስተናገደቺው ሳኡዲ አረቢያ በሙቀቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል።
እስካሁን 922 ሁጃጆች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 600 ዎቹ ሁጃጆች ግብፅ ናቸው።
የሙቀቱ መጠን መካ ላይ ከ 51.8 ድግሪ በላይ እንደደረሰም ተገልጿል።

ከግብፅ በመቀጠል ኢንዶኔዥያ ፤ ህንድ ኢራን የመሳሰሉ ሀገራት ከፍተኛ ሁጃጆች የሞቱባቸው ናቸው።
ሳኡዲ አረቢያ ሙቀቱን ለመቆጣጠርና በሁጃጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ አሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ የተጠቀመች ቢሆን ከአቅም በሗላ በሆነ ሁኔታ የዚህ ሁሉ ተጓዦች ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

ሌሎች ሟቾችንም የመፈለግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

👉 t.me/Seidsocial
የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ቃልአቀባይ ዛሬ ለእስራኤል አስደንጋጭ የሆነ መግለጫ ሰጥተዋል ለመሆኑ ምን አሉ ? ኔታኒያሁ ብቻውን እየቀረ ይሆን ?
የሂዝቦላሁ መሪ ሀሰን ነስረላህ የጦርነት አዋጅና የሂዝቦላህ የደህንነት መረጃ ስለምን እስራኤልን አስደነገጠ ?
ቆጵሮስ ምን ነካት ?

ሁሉንም ስለጋዛ የተሰሙ አዳድስ መረጃዎችን ተከታተሉኝ

https://youtu.be/vQBB8r3klhU?si=B57xrWMUTbBx8aI-
ሲሪል ራማፎዛ በድጋሜ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለመሀላ ፈፅመዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ምንም እንኳ ፓርቲያቸው ANC መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘት ባይችልም ምርጫውን በአሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወቃል። እናም ከ DA ፓርቲ ጋር ጥምረት በመፍጠር በቀጣይ ደቡብ አፍሪካን የሚመራ ይሆናል።

ፕሬዚዳንት ራማፎዛ በቃለመሀላቸው ወቅት በገቡት ቃል አድስ የከፍታ ምእራፍ ለደቡብ አፍሪካ ለመክፈት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎዛ በፍልሥጤም ጠበቃነታቸው የሚታወቁ ሲሆኑ እስራኤልን በአለምአቀፉ ፍርድቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል Genocide ከሰው እየተሟገቱ ይገኛሉ።

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በሰሜን ኮሪያ የተደረገላቸው አቀባበል እጅግ ልዩ ነበር።
እንደዚህ አይነት ወታደራዊ ትርኢት አስፈሪ የወታደር ሰልፍ አንድን መሪ ለመቀበል ሲደረግ ምናልባትም ፑቲን የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም።

ፑቲን ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ባደረጉት የጦር ስምምነት ከሁለቱ ሀገራት አንደኛው ላይ ወታደራዊ ጥቃት ቢፈፀም ሁለቱም ላይ እንደተፈፀመ እንደሚቆጠርና ሁለቱም በጋራ ጦርነት እንደሚያውጁ የሚያትት የጦር ስምምነት ተፈራርመው ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን የሰሜን ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው የተመለሱት
እስራኤልና ሂዝቡሏህ ለሙሉ ጦርነት ተዘጋጅው የመሳሪያ አፈሙዛቸውን እየወለወሉ ነው።

አሰላሙአይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ እንደምን ሰነበታችሁ ። እኔ ደህና ነኝ አልሃምዱሊላህ ።

እስራኤል ከጋዛ ጦሯን እየቀነሰች ወደ ሰሜን እስራኤል ሊባኖስ ድንበር እያጓጓዘች ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ዛሬ የጋዛ ጦርነትን እንደሚቀንስ ተናግሯል። አሁን አድሱ ግንባር የሊባኖስ ግንባር ይሆናል።

ክንደ ፈርጣማውና እስራኤልን መቶ ማሳመም ገጥሞ ማሸነፍ የቻለው ብቸኛው ታጣቂ ቡድን ሂዝቡላህ የሮኬት አፈሙዞቹን ወደ እስራኤል ሰድሯል ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ሂዝቡላህን ተቀላቅሎ እስራኤል ለመዋጋት ከኢራቅ ከሶሪያ ወደ ሊባኖስ እየተመሙ ነው። እስካሁን ከተደረጉት ጦርነቶች ሁሉ አስፈሪው ጦርነት ሊለኮስ ክብሪት መጫር ቦቻ ቀርቶታል።

አሜሪካና ፈረንሳይ ጦርነቱ እንዳይከሰት ለማድረግ እያደረጉት ያለው ጥረት ውጤታማ እየሆነ አይመስልም። እናም አሜሪካ ጦርነቱ ካልቀረ ከእስራኤል ጎን እሰለፋለሁ ብላለች ። ኢራን ደግሞ ጦርነቱ ከተጀመረ እስራኤል ለአሳማሚ ሽንፈት ትዘጋጅ ብላለች ። ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እየወጡ ይሆን ??

ሂዝቡላህ እያንዳንዷን የእስራኤል ኢላማ በድሮኖቹ ቀርፆ የጥቃት ኢላማዎቹን ለይቶ ቀመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሚሳኤሎቹ የትና መቼ መምታት እንዳለባቸው አዘጋጅቶ ቀናት ይሁን ሰአታት እየተጠባበቀ ነው ።

የእስራኤል አየር መከላከያ IRone dome የሂዝቡላህነሰ የርኬትና ሚሳኤል ውርጅብኝ መመከት አይቻላቸውም ያለቺው አሜሪካ እስራኤል ከዚህ በተሻለ መልኩ ካልተዘጋጀች ከባድ ኪሳራ ነው ብላለች።
እስራኤል የአየር ሀይሏን ሊባኖስ ያነድ ዘንድ አዘጋጅታለች። ሂዝቡላህ የድሮንና የሚሳኤል ሀይሉን ሞትን ከማይፈሩ ወታደሮቹ ጋር በተጠንቀቅ አቁሟል።


👉 t.me/Seidsocial
በዘንድሮው የሀጂ ጉዞ የሞቱት ሁጃጅች ቁጥር 1,301 መድረሱን ዛሬ ሳኡዲ አረቢያ አሳውቃለች። ይህም በሙቀት ምክንያት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሁጃጅ የሞተበት ሆኖ ተመዝግቧል።

ሳኡዲ አረቢያ ዛሬ እንዳሳወቀቺው አብዛኛው የሞቱት ህገወጥ ሀጃጆች ናቸው ብላለች። ከሞት የተረፉ ሁጃጆች በበኩላቸው ከሳኡዲ መንግስት በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸውና በሙቀቱ ካለምንም ውሀና መጠለያ ብዙ ኪሎሜትሮችን ለመጓዝ መገደዳቸውን ገልፀዋል። ይህም በርካታ አጋሮቻቼው እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

ሳኡዲ አረቢያ ለሀጅ ፈቃድ የሌላቸው በሚል 330,000 ሁጃጆችን በፖሊስ ማሰሯና ማባረሯ ይታወቃል። ከዚህ የፖሊስ ማባረር የተረፉት ደግሞ የመጓጓዣ አገልግሎት የውሀና የማረፊያ ቦታ እንዳያገኙ በመደረጉ ብዙዎቹ መሞታቸውን ነው Middle east eye ያስነበበው። ይህም ከ 1,300 በላይ ሁጃጆች እንዲሞቱ አድርጓል።

ሳኡዲ አረቢያ በበኩሏ ዛሬ በሰጠቺው መግለጫ ከሞቱት ውስጥ 85% የሚሆኑት "ህገወጥ" ሁጃጆች ናቸው በማለት ጉዳዩን ለማስተባበል ሞክራለች።
የሳኡዲ የሀጂና ኡምራ ሚኒስትር እንዳሳወቀው " እኛ ያዘጋጀነው መጓጓዧና ሌሎች አቅርቦቶች ለህጋዊ ሁጃጆች ብቻ ነው በነርሱ ቁጥር ልክ ቦቻ ነው ያለ ሲሆን ሌሎቹ በእርዳታ እጥረትና የነፍስ አድነሰ ስራም ባለመሰራቱ ይህ ሁሉ ሁጃጅ ሊሞት ችሏል።


ከሟቾቹ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ግብፃውያን ናቸው። መረጃው የ Middle east eye ነው።
👉 t.me/Seidsocial
እስራኤል ዛሬ በፈፀመቺው የአየር ጥቃት 10 የኢስማኢል ሀኒያን ቤተሰቦች ገድላለች።
ወላሂ ይሄ ሰው ለካ ተፈተነ !!

ባለፈው በፈፀመቺው ጥቃት ሶስት ልጆቹና አራት የልጅ ልጆቹ የተገደሉበት የሀማሱ መሪ ኢስማኢል ሀኒያ በዛሬው እለትም 10 ቤተሰቦቹን በእስራኤል የአየር ጥቃት አጥቷል። ከተገደሉት የኢስማኢል ቤተሰቦች ውስጥ እህቱ ትገኝበታለች።

ይህንን የመርዶ ዜና እንደት እንደሚቋቋመው አላውቅም። ባለፈው ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ሸሂድ ሲሆኑበት ያሳየው ፅናት እጅግ አስገራሚ ነበር። ለአላህ ሸሂድ ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን አስቀደምኩኝ ነበር ያለው።
ብቻ በጣም ያማል ! ኢስማኢል እጅግ ተፈተነ!
ይህ ግፍ ግፍ ይከፈላል !! መቼም ለማይሽረው ጠባሳ ፂዮናዊያኑ ዋጋ ይከፍላሉ !

👉 t.me/Seidsocial
ካናዳ በሀማስ ላይ ማእቀብ ጣለች።

የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በዛሬው እለት እንደገለፀው ሀማስ በእስራኤል ላይ ለፈፀመው ጥቃት ካናዳ በሀማስ ላይ ማእቀቦችን መጣሏን ገልፃለች።
ካናዳ ሀማስን በሰብአዊ መብት ጥሰት እገታ እና ሽብር በመወንጀል ነው ማእቀቡን የጣለቺው።

የካናዳ ውጭጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ በሰጠው መግለጫ
" ዛሬ ለሀማስና አጋሮቹ ግልፅ መልእክት አስተላልፈናል መልእክቱም ሽብርተኝነት በጭራሽ የምንታገሰው አለመሆኑን ነው። ከእስራኤል ህዝብ ጎን እንሰለፋለን የታገቱት ምርኮኞችም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን " ብሏል።

ንፍቅና ከነ ሙሉ ውርደቷ ምእራባውያን ላይ ተሰብሰባለች!
ሁሉም የሚገለባበጥበት ቀን ይመጣል !

👉 t.me/Seidsocial
ፌስቡክ የእስማኢል ሀኒያ ቤተሰቦች በእስራኤል ተገደሉ ብየ ስለፖሰትኩ ብቻ አካውንቴን መፖሰት እንዳልችል አግዶኛል።
መቼስ የምእራባውያን ቆሻሻነት ልክ የለውም።
ስለዚህ ከቻልኩ በዚህች የቴሌግራም ቻናል ብቻ ለመፃፍ እሞክራለሁ ።
መረጃዎቹ ይጠቅማል ካላችሁ ተደራሽ እንዲሆን የበኩላችሁን ብታደርጉ ደስ ይለኛል። ካልሆነም ላለው ጥቂትም ሰው ቢሆን የቻልኳትን ለማስተላለፍ እሞክራለሁ ።
ሳኡዲ ባትደርስላት ልንትኮታኮት የነበረቺው አሜሪካ እንደት በሳኡዲ እርዳታ ተረፈች ?
ለመሆኑ አሜሪካን ያተረፈው ያ ስምምነት ምን ነበር ?
ሳኡዲ ምን ለማግኘት ብላ ሙስሊሙንና አረቡን አለም ከድታ የአሜሪካ ጀርባ አጥንት ሆነች ?
ታሪክን የሗሊት ተመልሰን ያን ምስጢራዊ ስምምነት እንዳስሳለን


https://youtu.be/zUPCY-zXh9g?si=80av97xSy5HzSKxF
Seid Mohammed Alhabeshiy የሚለው ዋናው አካውንቴ እግድ ላይ ስለሆነ በአድሱ የፌስቡክ አካውንቴ ጓደኛ መሆን የምትሹ በቀጣዩ ሊን Friend request ልትልኩልኝ ትችላላችሁ ።

ከዚህ በሗላ ፌስቡክ ላይ በዚህኛው አድሱ አካውንት ነው የምጠቀሙው። ስሙም ከቀድሞው ጋር ተመሳሳይ ነው ።
የአካውንቱ ሊንክ

https://www.facebook.com/profile.php?id=61551466234124
የእስራኤል ወታደሮች እኝህን ፍልስጤማዊት አዜውንት እናት በወታደራዊ ውሻቸው ሲያስነክሱ የሚያሳየው እጅግ ሰቅጣጭ ልብ ሰባሪ ምስል መውጣቱን ተከትሎ የእስራኤል ወዳጆችን ጭምር ማስቆጣቱ እስራኤልን አስደንግጧል።

እናም የእስራኤል ጦር ዛሬ በሰጠው አስቂኝ ማስተባበያ "ውሻው በሀማስ ተማርኮብን ነበር ውሻው በሀማስ እጅ ነበረ ከዚያም ሴትዮዋን ያስነከሳቸው ራሱ ሀማስ ነው ። ሀማስ ውሻውን ከማረከ በሗላ ወጥመድ ሰርቶበት ወታደሮቻችንም ውሻውንም ገድሎታል "የሚል አይን ያወጣ የቅጥፈት መግለጫ አውጥቷል። መቼስ ህፃናትን አሸባሪ ናቸው እያለ ለሚገድል አረመኔ ሀይል ይህንን ቢል አይገርም ይሆናል።

የሚደንቀው ግን ውሻውን ከሗላ ይዞት ፓውዛ አብርቶ የሚያስነክሰው የእስራኤል አረመኔያዊ ወታደር እዚያው ፎቶው ላይ እያለ ለማስተባበል መሞከራቸው ነው !

ኢንሻአላህ አንድት የምታስጠልላቸው ዛፍ እንኳ የሚያጡባት ጊዜ ትመጣለች ።

t.me/Seidsocial
Seid Social pinned «Seid Mohammed Alhabeshiy የሚለው ዋናው አካውንቴ እግድ ላይ ስለሆነ በአድሱ የፌስቡክ አካውንቴ ጓደኛ መሆን የምትሹ በቀጣዩ ሊን Friend request ልትልኩልኝ ትችላላችሁ ። ከዚህ በሗላ ፌስቡክ ላይ በዚህኛው አድሱ አካውንት ነው የምጠቀሙው። ስሙም ከቀድሞው ጋር ተመሳሳይ ነው ። የአካውንቱ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61551466234124»