Soccer Ethiopia
83.5K subscribers
68.3K photos
213 videos
6 files
21.9K links
The voice of Ethiopian football

For business enquiries ONLY

Tell: +251940018801
Email: ads@soccerethiopia.net
Download Telegram
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ ክፍያ ፈፀመ።
===============================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየጊዜው ለደንበኞቹ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማቅረብ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማስተናገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።

በዚህም መሰረት በዛሬው ዕለት ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ለባንኩ የቀረቡ የውጭ ምንዛሪ የደንበኞቻችን ማመልከቻዎችን ሁሉንም በማጽደቅ የ420.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ዓይነቶች ለተለያዩ ፍላጎቶች ፈቅዷል።

የዛሬው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከተፈቀደው ጋር ተደምሮ በአጠቃላይ በባንካችን ለ1,140 ደንበኞች 541.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ተፈቅዷል።

ይህም የተሰጠው የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ከነዳጅ፣ ማዳበሪያ እና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎች ጋር በተያያዘ በየቀኑ ከሚሰጠው መደበኛ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተጨማሪ የተሰጠ ነው።

ባንካችን ከጁላይ 1 ቀን 2025 ጀምሮ ለገቢ ንግድና ለአገልግሎት ክፍያዎች በአጠቃላይ 1.034 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሪ ክፍያ ፈፅሟል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከውድ ደንበኞቻችን ፍላጎት እና ከአገራችን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ጋር በማጣጣም ለውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በመደበኛነት ምላሽ መስጠቱን ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#EthiopianBanking #ForeignCurrency #BankingServices #CurrencyExchange #CBE
21🔥1