knowledge First እውቀት ይቅደም
241 subscribers
1.48K photos
252 videos
438 files
1.09K links
እውቀት ብርሀን ሲሆን አለማወቅ/ ጅህልና ጨለማ ነው።እንቅራ በጊዜአችን እንጠቀም ሰዎች መለወጥ ካልቻልን እራሳችን እንለውጥ።ከራሳችን ጀምረን ቤተሰባችን እንታደግ ከተለያዩ ከሱሶች;ከቢድአ ;ከሽርክ እንራቅ።ወደ ቻናላችን ለመግባት ከፈለጋቹ ከስር
https://t.me/MuradAhmede
ኢማሙ አዙኸይብይ እንድህ አሉ እውቀት ባለህ ነገር ተናገር አልያ ችለህ ዝም በል።(አላህ ይርኸማቸው)joi@
Download Telegram
በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጊድ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የመኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንዳሉት÷አደጋው የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በጀርባ በሚገኝ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ በማረፉ ነው የተከሰተው፡፡

ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በደረሰው አደጋም እስካሁን የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነው ሥራ አስፈጻሚዋ የተናገሩት ሲል ፋና ነው የዘገበው።
https://t.me/MuradAhmede
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰሐቦችን አትስደቡ

ኡስታዝ አማን ኢብራሂም

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
https://t.me/MuradAhmede
በአሜሪካ በሀርቫርድ እና ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲዎች የተቀሰቀሰው የአሜሪካ ተማሪዎችና ፕሮፌሰሮች ተቃውሞ በመላው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የያሌ ፤ ሚቺጋን ፤ ፕሪንስተን ፣ ኦሀዩ ፣ ካሊፎርኒያ ስቴት ፣ ዋሽንግተን ፣ ሚኒሶታ ፣ ብራውን ፣ ቴክሳስ ፣ ዳላስ በመሳሰሉት ዩኒቨርስቲዎች ስለፍልስጤማዊያን ነፃነት ተቃውሞ በሚያሰሙ ሰልፈኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ ፕሮፌሰሮች ፣ የካምፓስ ዲኖች ምክንያት በአብዛኛው የአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት መቆሙ ተሰምቷል።
...
በተጨማሪ በአውሮፖዊቷ ሀገር ፈረንሳይ በሺዎች የሚቆጠሩ የፓሪስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፍልስጤምን ሰንደቅ በመያዝ "ነፃ ፍልስጤም " በማለት ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።
...
የሀገራቱ መንግስታት የተማሪዎችን ሰልፍ ለመበተን በርካታ የፀጥታ ሀይሎችን በማሰማራት ተማሪዎችን የማሰርና ሰልፍ የመበተን ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
...
https://t.me/MuradAhmede
« قناة بوت الأذكار »:
يارب بقدر ما تحملت وتألمت وصبرت ، عوضني خير🤍

يا رب هب لنا نورًا نفرق به بين الحق والباطل..

يا رب ارزقنا اليقين وحسن الظن والعمل..

اللهم ارزقنا صفاء النفس وسلامة الروح..
🤙በሚድያ ከወንዶች ፈተና ራስሺን ለመጠበቅ፦

ያለ ሀጃ ወንዶች አትገናኚ ! ራቂ !

በሀጃ ከተገናኘሽ ከሀጃሽ ዉጭ ትርፍ ወሬ አትጨምሪ ሀጃሽ ብቻ ጨርሰሽ ላሽ በይ!

የሚፀፉልሽ ሁሉ መልስ አትስጪ! አስፈላጊ ነዉ ብለሽ ያሰብሺዉ ብቻ በአጭር ቃል መልስ ሰጥተሺ ዘወር በይ!

በተደጋጋሚ ደህና ነህ እንደት ነህ እያልሺ አትመላለሽ በመስመራቸዉ ይሄ ከብዛት ሌላ ኮተት ያመጣብሻል ተጠንቀቂ!

በፀሁፍ መመለስ እየቻልሺ በድምፀ አትመልሽ! አይረዳኝም ካልሽ ድምፀሽ ሳታለሰልሽ በኖርማል ድምፀ አስረጅ ከዛ ዘወር በይ አትደጋግሚ!

ቀልድ አታብዥ የቀልድ ብዛት ብዙ ነዉ መዘዙ ቀንሽ ! ደግሞ እያየሽ ቀልድ መጠቀሚያ ቦታ ዝም ብለሽ እንደመጣልሽ አትቀልጅ !ጠንቀቅ በይ!

ከሁሉም ዱዓ ይበልጣል !ሰበቦች እያደረሽ ጌታሺ ለምኚዉ ! እኔም በነሱ ከመፈተን እነሱም በኔ ከመፈተን ጠብቀኝ እያለሽ ሁለዬ ተማፀኚዉ!


መልካም ጊዜ...! ዉጤት በቦት ሹክ ትይኛለሽ!
https://t.me/MuradAhmede
=
የሐጅ ቪዛ ሳይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል የሳዑዲ የሐጅ ሚኒስቴር አስታወቀ!

(ሀሩን ሚድያ ሚያዝያ 21፣ 2016)

የሳዑዲ አረቢያ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር፣ የሐጅ ቪዛ ሳይይዙ ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል በመግለጽ ዘንድሮ ሐጅ የማድረግ ኒያ ያላቸው ምዕመናን "ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ የግል ኩባንያዎች እንዳይታለሉ በጥብቅ አስጠነቀቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ማስጠንቀቂያ ይፋ ያደረገው፣  በተለያዩ ሀገራት በማኅበራዊ ትስስር አውታሮች የሐጅ ቪዛ እንሰጣለን የሚሉ ሐሰተኛ ኩባንያዎች በስፋት የሚያሰራጩት ማስታወቂያ መበራከቱን ከተመለከተ በኋላ መኾኑን በመግለጫው ጠቅሷል።

ሐጅ ለማድረግ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በሥራ ቪዛ፣ በቱሪስት ቪዛ፣ በትራንዚት እና በመሳሰሉት ቪዛዎች ሳዑዲ አረቢያ በመግባት ሐጅ ማድረግ እንደማይቻል አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ አክሎም፣ ሐጅ ማድረግ የሚቻለው ጉዳዩ የሚመለከተው የሳዑዲ አረቢያ ሚኒስቴር በየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር በሚሰጠው የሐጅ ቪዛ እና፣ እነዚህ ተቋማት በሌሉባቸው ሀገራት ደግሞ "ኑሱክ ሐጅ" በሚሰኘው ፕላትፎርም አማካይነት ብቻ መኾኑን መረዳት ያስፈልጋል ብሏል።

ሐጅ ለማድረግ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከመገባቱ በፊት ራሱን የቻለ የሐጅ ቪዛ ማግኘት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ የጠቀሰው የሚኒስቴሩ መግለጫ፣ ከሳዑዲ የሐጅና ዑምራ ሚኒስቴር ጋር ግንኙነት ካላቸው የየሀገራቱ የሐጅና ዑምራ ተቋማት ውጪ የሐጅ ቪዛን ማግኘት እንደማይቻል በመግለጽ ምዕመናን ከመታለል እንዲጠነቀቁ አስጠንቅቋል።

"ሐጅ እናስደርጋለን" በሚሉ አጭበርባሪ ኩባንያዎች መታለል ከሚያስከትለው የገንዘብ ኪሳራ በተጨማሪ፣ የጓጉለትን ሐጅ ለማድረግ አለመቻልን በማስከተል ከባድ ሐዘን ላይ ሊጥል እንደሚችል ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
…መረጃው
©ሀሩን ሚድያ
https://t.me/MuradAhmede