knowledge First እውቀት ይቅደም
241 subscribers
1.49K photos
252 videos
438 files
1.1K links
እውቀት ብርሀን ሲሆን አለማወቅ/ ጅህልና ጨለማ ነው።እንቅራ በጊዜአችን እንጠቀም ሰዎች መለወጥ ካልቻልን እራሳችን እንለውጥ።ከራሳችን ጀምረን ቤተሰባችን እንታደግ ከተለያዩ ከሱሶች;ከቢድአ ;ከሽርክ እንራቅ።ወደ ቻናላችን ለመግባት ከፈለጋቹ ከስር
https://t.me/MuradAhmede
ኢማሙ አዙኸይብይ እንድህ አሉ እውቀት ባለህ ነገር ተናገር አልያ ችለህ ዝም በል።(አላህ ይርኸማቸው)joi@
Download Telegram
ቢቢሲ አማርኛ ሀጅ ላይ ስለሞቱት ስንት ጊዜ ደጋግሞ እንደ ፖሰተ ... እህ ሚሊየኖችን ለቀናት በሚስተናገዱበት ታላቅ ስርዓት አንዳንዴ እንዲህ ያለ ነገር ማጋጠሙ የማይቀር ነው :: በዚያ ላይ ይህንን እድል እና አጋጣሚ ቢሊየኖች የሚቀኑበት ነው :: ምእራባዊያን ሚዲያዎች በዚሁ ዘገባ ተጠምደዋል ::

ይልቅ ሰብአዊነት ከተሰማቸው በፅዮናዊቷ እየተጨፈጨፈ ስላሉ ፍልስጤማዊያን ደጋግመው በዘገቡ
በደቡብ ክልል መጅሊስ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ወንድም ቢላል ማይዶ እና ኡስታዝ ሙስጠፋ መታሰራቸው ተሰማ

ጄይሉ ቲቪ ሰኔ 19/2016

ጄይሉ ቲቪወንድም ቢላል ሜይዶ በደቡብ ኦሞ ዞን ላይ ኢስላምን በማስተማር ለብዙ ወገኖቻችን መስለም ሰበብ መሆኑ ይታወቃል።ሰዎች ወደ ተፈጠሩለት እምነት መመለሳቸውን ያላስደሰታቸው አካሎች ቀይ አፈር ከተማ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነን ያሉ ሰዎች ጁመአ እለት የሀይማኖት ትምህርት  ለመማር ኡስታዝ ቢላል ያመጡዋቸውን ተማሪዎች መንገድ ላይ በማባበል ወደ ቤተክርስቲያን ወስደው በግድ እንዳሰለሙዋቸውና ማህተባቸውን እንዳስቆረጡባቸው በማስመሰል የመድረሳውን አስተምሪ ኡስታዝ ሙስጠፋ አስታጥቄን ማሳሰራቸው ተገልጿል።

ልጆቹን ወደ መድረሳ ሲያመጡ ህጋዊ አካሄድ ተከትለው ከቀበሌ ደብዳቤ አጽፈው በልጆቹ እና በወላጆቻቸው ሙሉ ፈቃድ መሆኑን ለማስረዳት እና እንዲለቀቁ ለማስደረግ በቦታው ላይ የተገኙትን የክልሉ መጅሊስ የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑትን ወንድም ቢላል ማይዶን አንተም ትፈለጋለህ በሚል ጨምረው ያሳሰሩ ሲሆን በተጨማሪም ከዳሰነች ወረዳ አንድ የሰለሙ አባትን መታሰራቸው ተሰምቷል።የተማሪዎቹ ወላጆች በአካል ቀርበው ልጆቻቸውን እንዲማሩላቸው ፈቅደውና ወደው የሰጡ መሆናቸውን ለማስረዳት ቀይ አፈር ከተማ ላይም እንዲሁም ኦሞራቴ ከተማ ላይ  ለማስረዳት ቢሞክሩም ሰሚ አላገኙም ተብሏል።

ተማሪዎቹ ከወላጆቻቸው ጋር እንዳይገናኙ በማድረግ በቤተክርስቲያን እንዲቆዩ ተደርጓል ተብሏል።ኡስታዞቹ ከተያዙ ዛሬ ስድስት ቀን ሁኖዋቸዋል እስከ አሁን ፍርድ ቤትም አልቀረቡም የዋስ መብትም ተከልክለዋል ።የክልሉ መጅሊስ ከወረዳ እስክ ክልል ስለጉዳዩ ሲጠየቅ የቻልኩትን ያህል ጥረት እያደረኩ ነው ቢልም ሚሰማቸው የመንግስት አካል አልተገኘም ብለዋል።


አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት
ድህረ ገጽ፡-   https://jeilumedia.com
  ዩትዩብ:-   https://www.youtube.com/c/JeiluTube/videos
ፌስቡክ:-   https://www.facebook.com/jeilutv
ኢሜል :-   jeilumedia@gmail.com
ቴሌግራም :-  https://t.me/Jeilumedia
ጄይሉ ቲቪ ዛሬን ለተሻለ ነገ
አስጨናቂው የክረምት ወቅት መጥቷል ‼️

ፖስቱ ቫይራል መሆኑ ለእናቶች ይጠቅማቸዋል። ላይክ አርግ። ኮፒ አርጋችሁም በየፔጃችሁ ፖስቱት 🙏

ክረምቱ በዝናብ ታጅቦ መጥቷል ይህም ደግሞ ያለ መከለያ ጎዳና ላይ ጉሊት ለሚሸጡ እናቶች መከራ ሆኗል። የሚሸጧቸውን አትክልትና ፍራፍሬ ከማከፋፈያ ቦታ ከማምጣት ጀምሮ ቸርችሮ እስከመሸጥ ድረስ ያለውን ሂደት ክረምቱ ይበጠብጠዋል። አብዛኞቹ እናቶች በጋ ላይ ያገኙት የነበረውን ገቢ ግማሹንም አሁን ላይ አያገኙትም።

በእንቅርት ላይ ... እንዲሉ ገቢያቸው ሲቀንስ ወጪያቸውን ደግሞ ክረምቱ ያንረዋል። አብዛኞቹ እናቶች ልጆቻቸውን መንግስት ትምህርት ቤት ያስተምራሉ። በጋውን ልጆቻቸውን መንግስት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ይመግብላቸው ነበረ። ክረምቱ ግን የልጆቻቸውን ፊት ከባዶ ሌማታቸው ጋር ያፋጥጠዋል።

አስቤዛ ስትገዙ እስቲ ጉሊት ግዙ። ዋጋ አትከራከሩ ። ቲፕም ስጡ 🙏

አቅሙ ያላችሁ ሰዎች ደግሞ ጉሊት ጋ መኪና አቁሙና አንዱን መደብ በሺዎች ግዙ። አስደስቷቸው። ተመረቁ🙏

#ጉሊት #ጉሊት_challenge Tesfa G Neda
ወራሪዎቹ የሰው ጭራቆች ለዓለም በገሃድ የሚያሳዩት ጭራቃዊ ተግባር ይህ ነው። "ከገርቀድ" ዛፍ በስተቀር ለመደበቂያ ዋስ የሚሆናቸው አጥተው በድንጋዩም በዛፉም እክ ትፍ እየተባሉ ሌጣቸውን የሚቀሩበት ቀን ለመምጣቱ ከዚህ ምስል በላይ ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ አይደለም። የሰዎቹ የፀነነ ግፍ ከጣሳው በላይ ሞልቶ ከፈሰሰ ሰንብቷል። ዕድሜ በሸበሸበው የአዛውንቶች ቆዳ ላይ እነሱን መሳይ አውሬዎች የሚያሰፍሩት ወራሪዎቹ የግፍ ዘመን ሰዓታቸው ሊገባደድ ከወትሮው በተለየ ፍጥነት እየቆጠረ ነው። ያኔ ሰንኮፉ ከሥር ሲነቀል ዓለም አዲስ ቅርፅ መያዟን በችግሮች የተበተበው የሰው ዘር በሙሉ መመልከቱ አይቀሬ ይሆናል። መቼ ...

ويقولون متى هو؟ قل عسى أن يكون قريبا !
Abx
በሃይማኖት አንድ አይደሉም።ነገር ግን በኢስላምና በሙስሊሞች  ላይ  ምንም ድንበር ሳይለያያቸው ይረዳዳሉ።

አላህ እንደሚተባበሩብን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፦

«እነዚያም የካዱት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ (ከምእምናን መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይኾናል፡፡»
(አል አንፋል 73)

  
Share share share

ይህ መኪና የወንድማችን ዘይኑ መኪና ነው ዛሬ 11:15 ላይ የስራ ቦታ ከሆነው አዲስ ሰፈር አስኮ አፍናን ካፌ በር ላይ በሌቦች ተወስዶበታል
የታርጋ ቁጥር አአ 29921 ኮድ 3

ሲልቨር ከለር ዶልፊን አይናማው

0911958452/0911715649
ሰበር ዜና ሄዝላህ የእስራኤልን ድንበር ጥሶ ገብቶ መመለሱ ተሰማ

በርካታ ሚሳኤሎችንና ሮኬቶችን የታጠቀዉ ባለ ግዙፍ ፈርጣማ ወታደራዊ ጉልበት ባለቤት የሖነዉና በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት ሄዝላህ የእስራኤል ከተሞችን ጥሶ ገብቶ ወሳኝ የሚባሉ የእስራኤል ወታደራዊ ስፍራዎችን ያለምንም እንከን በቪዲዮ ቀርፆ መዉጣቱ የአለም መነጋገሪያ ሁኗል፡፡

የህዘቦላህ የሖፕ ተልዕኮ ቡድን ያሰማራቸዉ ድሮኖች የእስራኤልን የአይረን ዱምን መከላከያን ጥሰዉ ገብተዉ ሀይፋ ወደብን ጨምሮ ወሳኝ የተባሉ የእስራኤል የጦር ካምፖችን እንዲሁም የአየር ስፍራዎችን የመከላከያ አይረን ዶምን ሽባ አድርገዉ ገብተዉ እስራኤል ሳታዉቅ ሰልለዉና ቪዲዮ ቀርፀዉ ወደ ሊባኖስ መመለሳቸዉ አለምን ጉድ አስብሏል፡፡

ጠንካራ የሚሳኤል፤ሮኬትና ድሮን መከላከያን ድንበር ላይ ተክላለች የምትባለዉ እስራኤል የሄዝቦላህ ድርጊት እጅጉን አስደንግጧታል፡፡

ከሄዝቦላህ ጋር ጦርነት ለመክፈት ጦሯን ወደ ድንበር ያስጠጋችዉና ከዉሳኔ የደረሰችዉ እስራኤል የሆነዉን ማመን አቅቷታል፡፡

አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉https://t.me/MuradAhmede
" እስራዔል ምዕራባውያንን ተማምና ጦርነቱን የምታሰፋ ከሆነ ቱርክ ሊባኖስን ለመደገፍ ትገደዳለች " - ቱርክ

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን፣ " እስራዔል የጦርነቱን አድማስ የማስፋት ፍላጎት አላት " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" እስራዔል ትኩረቷን ሊባኖስ ላይ አድርጋለች፤ የምዕራቡ ኃይሎች ከሁነቱ ጀርባ ሆነው እስራዔልን እየገፋፉ ነው " ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ጠ/ሚ ኒታንያሁ ግጭቱን አስፍተው አካባቢያዊ ቀውስ ለመፍጠር ተዘጋጅተዋል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

" እስራዔል ምዕራባውያንን ተማምና ጦርነቱን የምታሰፋ ከሆነ ቱርክ ሊባኖስን ለመደገፍ ትገደዳለች " ብለዋል።


አዳዲስ አለማቀፍ ሰበር ዜናዎችን ለማግኘት በነዚህ አማራጮች ይጠቀሙ 👇👇👇

👉👉Telegram https://t.me/MuradAhmede
ስለ ቢላል ዝም አንልም !

ትላንት ሀበሻዊውን ቢላል እምነትህን ካልቀየርክ በሚል የቁረይሽ ሹማምንት እንዳሰቃዩት ዛሬም የቢላል ማይዶ ዳእዋ ለማሰናከል ሴራ
ጎንጉነው በማሰር እያሰቃዩት ነው::
ስለ ቢላል ዝም አንልም የቢላል መንገድ መንገዳችን ነው ቢላልን ፍቱት !
https://t.me/MuradAhmede
ለምን ዲኑል ኢሥላምን ለሌላ ሰው አስተማርክ ተብሎ ለታሰረው ለወንድም ቢላል "ፍትሕ ለቢላል! እኔም ቢላል ነኝ።" በሚል መርሕ ቃል ሁላችንም ለቢላል እንጩው!
በዘንድሮው የሐጅ ስነስርዓት 10 ኢትዮጵያዊያን ሐጃጆች ሕይታቸው ማለፉን የፌደራል መጅሊሱ ገለፀ!
...
(ሀሩን ሚዲያ፦ሰኔ 24/2016፣አዲስአበባ)
...
በ1445 ዓ.ሒ. ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ውስጥ በድምሩ 10 ሐጃጆች ሕይታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ አሺቢ ተናግረዋል
.
አሥሩ ኢትዮጵያውያን ሐጃጆች በሙሉ በመካ፣ መስጂደል ሀረም ላይ ሶላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው የቀብር ሥርዓታቸው እንደተፈፀመ ሸይኽ አል-መርዲ አብዱላሂ ተናግረዋል።የአምስቱ ሐጃጆች ሕይወት የሐጅ ሥርዓት ከመጀመሩ በፊት ማለፉን ያስታወሱት ሸይኽ አል-መርዲ የሌሎቹ ሕይወት ያለፈው በአረፋ ወቅት መኾኑን ተናግረዋል።
.
ከሟቾቹ መካከል በተለይ ሁለቱ እናቶች በሐጅ ሥርዓተ ክንዋኔ ወቅት ጠፍተው ከነበሩት አምስት ሰዎች መካከል መኾናቸውና 'ሚና' ላይ ሕይወታቸው ማለፉ እንደታወቀ ተነግሯል።በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የሐጃጆችን ደኅንነት ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ የሚከታተለው ኤጀንሲ፣ ስድስቱ ሐጃጆች በድንገተኛ ህመም፣ ሁለቱ በክፍላቸው ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲኾን፣ አንድ ሐጃጅ በመኪና አደጋ፣ አንድ በካንሰር፣ እንዲሁም ሌላ አንድ ሐጃጅ በህመም ምክንያት እንደሞቱ የሆስፒታሉን ውጤት አያይዞ ይፋዊ መረጃ ሰጥቷል።
.
የሐጃጆቹ የቀብር ሥርዓት የተፈፀመው በሀገሪቱ ደንብ መሠረት በሦስት ሰዓታት ውስጥ የሟች ቤተሰብ፣ የቅርብ ዘመድ አልያም ምስክር የሚኾን ጎረቤት በተገኘበት እንደኾነ ለማወቅ ተችሏል።በዚሁ መሠረት የዘጠኙ ሟቾች ሥርዓተ ቀብር የተፈፀመው በዚሁ ደንብ መሠረት ሲኾን፣ ሚና ላይ ሞተው ከተገኙት የአንዷ እህት በተባለው ጊዜ ውስጥ መገኘት ባለመቻሏ ሕይወቷ ማለፉን የሚያረጋግጥ ሰርተፊኬት ተሰጥቷል።
.
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚና የሐጃጆች የሕክምና ቡድን ዋና አስተባባሪ ሸይኽ አል መርዲ አብዱላሂ፣ የ1445 ዓ.ሒ. የአርረህማን እንግዶች ሆነው መጥተው ሞት ቢቀድማቸውም ኒያቸው ከፍ ያለ በመኾኑ፣ ሞታቸውን የሸሂድ (የሰማዕት) ደረጃ የሚያደርሱት አሉ ብለዋል።"ሞት የማይቀር ተፈጥሯዊ ሕግ በመኾኑ፣ በእንዲህ ዓይነት ሂደት መሞት ትልቅ ፀጋ ነው" ብለዋል ሸይኽ አል መርዲ ሲል የዘገበው የጠቅላይ ም/ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ነው።
.
©ሀሩን ሚዲያ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የድሬዳዋ ወንድሞች፤ አብሽር ታገሱ። ዱንያ እንዲህ ናት፤ ትናንት አረንጓዴ ሆና ዛሬ ትጠወልጋለች። ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባልተቻለው ሰልባጅ ተራ (አሸዋ) አካባቢ በተነሳው እሳት ከ500 በላይ የሚሆኑ ሱቆች መቃጠላቸውን ሰምተናል። አላህ ሶብሩን ይስጣችሁ፣ ኢንሻ አላህ እናንተ ደህና ሁኑ እንጂ ንብረት ይተካል።

||https://t.me/MuradAhmede
✍️የሰላተል ጀናዛ አሰጋገድ‼️
     ===============

    🔘ወደ ሰላት ከመገባቱ በፊት

💫እንደ የትኛውም ሰላት ሙሉ የሆነ ውዱእ ይደረጋል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ወደ ቂብላ ይቀጣጫል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ሰፍ ይስተካከላል።
💫እንደ የትኛውም ሰላት ማእሙኖች ኢማሙን ተከትለው ይቆማሉ።

       🔘የሰላቱ አሰጋገድ

✍️የመጀመሪያው ተክቢራ ይባልና…
ሱረቱል ፋቲሃ ይቀራል።
          {بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ}
     {الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
                 الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ
                   مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
           إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
               اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ
              صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ
         غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ}
ይህንን ሲጨርስ ሁለተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከሁለተኛው ተክቢራ በኋላ……
በነብዩﷺ ላይ ሰለዋት ያወርዳል።
«اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد»
ይልና ሶስተኛው ተክቢራ ይላል

✍️ከሶስተኛው ተክቢራ በኋላ……
ለሟቹ ዱዓ ያደርግለታል። ለምሳሌ ከመጡ ዱዓዎች መሃል……
«اللهم اغفر له وارحمه، وعافه واعف عنه،
   وأكرم نزله، ووسع مدخله، واغسله بالماء والثلج والبرد، ونقه من الخطايا كما ينقى الثوب الأبيض من الدنس،
  اللهم أبدله دارًا خيرًا من داره، وأهلًا خيرًا من أهله،
  اللهم أدخله الجنة، وأعذه من عذاب القبر، ومن عذاب النار، ووسع له في قبره، ونور له فيه»
ከዚህም ውጪ ያሉ ዱዓዎች የቻለውን ያደርግለታል። ይህንን ሲጨርስ አራተኛው ተክቢራ ይላል።

✍️ከአራተኛው ተክቢራ በኋላ…
ቲንሽ ዝም ይልና እዛው በቆመበት ወደ ቀኝና ወደ ግራው ያሰላምታል።
«السلام عليكم ورحمة الله,
       السلام عليكم ورحمة الله»
ይላል።

  
        🔘አንዳንድ ነጥቦች

💫ጀናዛው ከኢማሙ ፊት ይቀመጣል።
ጀናዛው የወንድ ከሆነ;
   ኢማሙ ጭንቅላቱጋ ይቆማል።
ጀናዛው የሴት ከሆነ;
   ኢማሙ ወገቧ አካባቢ ይቆማል።

💫ባለው የሰጋጆች ብዛት ረዥም ሰፍ ከመስራት ይልቅ ሰፎቹ መብዛታቸው ይመረጣል።

💫አራቱንም ተክቢራዎች ሲባሉ እጅ ማንሳቱ የተሻለ የተወደደ ነው።

💫አንድ ሰው ኢማሙ የተወሰነ ከሰገደ በኋላ ደርሶ ወደ ሰላቱ ቢገባ የሚጀምረው ኢማሙ ከደረሰበት ቦታ ሳይሆን ከመጀመሪያው ቦታ ነው።
ለምሳሌ፦
ኢማሙ የሁለተኛው ተክቢራ ሲያደርግ ቢደርስ እሱ የሚያደርገው ሰለዋት ማውረድ ሳይሆን ፋቲሃን መቅራት ነው; በመጨረሻ ኢማሙ ሲያሰላምት ቶሎ ቶሎ ብሎ ይጨርስና ያሰላምታል።

💫ጀናዛው የሆነ ቦታ ተሰግዶበት የተቀበረ ከሆነ ሌላ ቦታ "ሰላተል غይብ" ተብሎ አይሰገድበትም።

💫አንድ ሰው ሰላተል ጀናዛ ቢያመልጠውና መስገድ ቢፈልግ ጀናዛው ቢቀበር እንኳ ቀብሩ አጠገብ ሄዶ ይሰግድበታል።

        🔘ማሳሰቢያ

✏️ቀላል ከመሆኑም ጋ ብዙሃኖች የሚከብድ መስሏቸው ብዙ ጊዜ ከመስገድ ሲቆጠቡ ይታያሉና ሼር አድርጉላቸው።

  🤲አላህ መጨረሻችን አሳምሮ ይውሰደን🤲
Credit : kurean ye lbe brhan.....

https://t.me/MuradAhmede