knowledge First እውቀት ይቅደም
243 subscribers
1.5K photos
252 videos
438 files
1.1K links
እውቀት ብርሀን ሲሆን አለማወቅ/ ጅህልና ጨለማ ነው።እንቅራ በጊዜአችን እንጠቀም ሰዎች መለወጥ ካልቻልን እራሳችን እንለውጥ።ከራሳችን ጀምረን ቤተሰባችን እንታደግ ከተለያዩ ከሱሶች;ከቢድአ ;ከሽርክ እንራቅ።ወደ ቻናላችን ለመግባት ከፈለጋቹ ከስር
https://t.me/MuradAhmede
ኢማሙ አዙኸይብይ እንድህ አሉ እውቀት ባለህ ነገር ተናገር አልያ ችለህ ዝም በል።(አላህ ይርኸማቸው)joi@
Download Telegram
ማሌዥያ እና ሳዑዲ በሐላል ኢንዱስትሪ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ፈጸሙ

ማሌዥያ እና ሳዑዲ ዐረቢያ በሐላል ኢንዱስትሪ ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት የፈጸሙት ትናንት ሰኞ ነው። ሁለቱ ሀገራት ሥምምነቱን የፈጸሙት በማሌዥያ ኳላላምፑር በባለሥልጣኖቻቸው በኩል ባካሄዱት ውይይት ነው።

የማሌዥያ እና የሳዑዲ ዐረቢያ የስምምነት ዜና የመጣው የሳዑዲ ምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሂሻም ቢን ሳዕድ ከማሌዥያ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሐመድ ናዒም ቢን ሙኽታር ጋር ከመከሩ በኋላ ነው። ሁለቱ ባለሥልጣናት ባካሄዱት ውይይት የሀገራቱን የሐላል መመዘኛ እንዴት ማስተሳሰር ይቻላል የሚሉ ጉዳዮችን ማንሳታቸውን የሳዑዲ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል።

በውይይቱ ላይ በተጨማሪም በሐላል ኢንዱስትሪ ለሚከናወኑ ሥራዎች ወጥ የሆነ ሕግ እና ቁጥጥር አስፈላጊ መሆኑንም ባለሥልጣናቱ መግባባት ላይ ደርሠዋል። በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ሙስሊሞች የሐላል ምርቶችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ አሠራሮችን መዘርጋትም የውይይቱ አካል ነበር።

ማሌዥያ እና ሳዑዲ ዐረቢያ የሚሰጧቸው የሐላል መመዘኛ ሠርተፊኬቶች በሁለቱም ሀገራት ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድም ተፈራርመዋል።

የሐላል ኢንዱስትሪ በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተጽዕኖው እየጎላ የመጣ ነው። ሰባት ዘርፎችን የሚያቅፈው ይህ ኢንዱስትሪ፤ በሥሩ እስላማዊ ፋይናንስ፣ ሐላል ምግብ፣ ሐላል ፋሽን፣ ሐላል ሚዲያ እና መዝናኛ፣ የመድኃኒት፣ ጉዞ እና ሐላል መዋቢያዎችን ያካትታል።

በኢትዮጵያም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዕውቅና እየሰጠ እንደሚገኝ “ሚንበር ቲቪ” ከተቋሙ ማረጋገጥ ችሏል። የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትም እንዲሁ ከእርድ ጋር በተገናኘ ለበርካታ ዓመታት እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል። በግሉ ዘርፍ “ኢትሴፍ” የተሰኘ ድርጅት ላለፉት አራት ዓመታት እውቅና እየሰጠ ይገኛል።
https://t.me/MuradAhmede
“አንድነት የሚገለጸው በአንድ ተቋም ዉስጥ በመሰብሰብ ብቻ አይደለም!”
”وليس بصحيح أن يكون معنى الوحدة هو الاجتماع تحت سقف مؤسسة واحدة"
በሱና ኢኒስቲትዩት ስር የሚገኘው ሱና ዩኒቨርስቲ በሰሞኑ ያዘጋጀዉ ምሩቃን ኮንፈረንስ የመዝጊያ ፕሮግራም ከኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ጋር የልምድ ልዉዉጥ ያደረጉ ሲሆን አብረዉ መሰራት የሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል።
የሱና ኢኒስቲትዩት መስራች እና ዋና ፕሬዝደንት ሸይኽ ሙሀመድ ሓሚዲን (ዶ/ር) እዉቀትን በማስፋፋት ዘርፍ ኢስለምን ለማገልገል እየሰራን እንደመሆኑ ይህን አላማችንን ከግብ ለማድረስ ከመሰል ተቋማት ጋር ህብረት እንደሚያሻ እናምናለን ብለዋል።
ሸይኽ ኢልያስ አህመድ በበኩላቸው የአንድነት መገለጫ በአንድ ተቋም ዉስጥ በመሰብሰብ ብቻ አለመሆኑን ገልፀው ከዚህ በፊት ኢስላምን በማገልገል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ እንደ ነበረዉ ሁሉ ወደፊት እንደ ተቋም ተጋግዘን የሰለፎችን ጎዳና ህያዉ እንደምናደርግ ተስፋ አለኝ ሲሉ ገልፀዋል።
ሚያዚያ 15/2016
@daewa_tv
ከፈጅር ከግማሽ ሰዓት በፊት ንቃ፣ ዊትርን ስገድ ዱዓ አብዛ!

ለፈጅር አዛን ሲል መስጊድ ሄደህ ሁለት ረከዓህ ስገድ።
(ሴት ከሆነች እቤት ውስጥ ትሰግዳለች።)

ከዚያም ሁለት መዳፎችህን ወደ ላይ ዘርጋና  ለሶላቱ ኢቃም እስኪደረግ ድረስ ዱዓውን አስረዝም፣ ከዚያም ከሶላት በኋላ  የጠዋት ዚክርዎችን አንብብ።

በአላህ እምላለሁ! የአላህ ውዴታ፣ ስኬት፣ ሲሳይ እና  ደስታ በሁሉም የሕይወትህ ዘርፍ ውስጥ ታያለህ።

ዶ/ር ያሲር አል ዒነዘይ


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/MuradAhmede