Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
23.5K subscribers
3.4K photos
86 videos
13 files
569 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች “የኢትዮጰያ ታምርት ” ኤግዚቢሽንን ጎበኙ

ግንቦት 02/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ኤግዚቢሽኑ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን በርካታ የመንግስት እና የግል ተቋማት እየጎበኙት ይገኛል:: በዛሬው እለትም የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ኤግዝብሽኑን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር ሠራተኞች እና አመራሮች የ2016 ዓ.ም “የኢትዮጰያ ታምርት” ኤግዚቢሽን ኢትዮጰያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር እያደረገች ያለችው መዋቅራዊ ሽግግር እውን ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://tinyurl.com/5n6awd55
የንግድ ተሽከርካሪን የባለቤትነት ስም፣ ሰሌዳ እና አድራሻ ለመቀየር የሚያስፈልግ ክሊራንስ


የንግድ ተሽከርካሪን ባለቤትነት ስም ለማዛወር ወይም ሰሌዳ ለመመለስ ወይም አድራሻ ለመቀየር የሚያስችል ክሊራንስ ለማግኘት፡-

— የጠየቁት አገልግሎት በሽያጭ ለማዛወር ከሆነ ተሽከርካሪው በተገዛበት ዋጋ መካከል ባለው ልዩነት ላይ ግብር የሚጠይቅ አንደመሆኑ መጠን ግብር ተወስኖ የሚከፈለው እስከተዛወረበት ጊዜ ድረስ ይሆናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/h2iua7
የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመላሽ ስርዓት

ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገበ ሰው በአንድ የሂሳብ ጊዜ ካከናወነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ዋጋ ውስጥ ቢያንስ 25 ፐርሰንት በዜሮ የማስከፈያ ልክ ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ የተመዘገበው ሰው በብልጫ የተከፈለውን ታክስ ከሚያሳይ የሰነድ ማስረጃ ጋር በማያያዝ ጥያቄውን ባቀረበ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የግብር አስገቢው ባለስልጣን በዚህ የሂሳብ ጊዜ ሊከፈል ከሚገባው ታክስ በላይ የተከፈለውን እንዲመልስ የተጠየቀውን ታክስ መመለስ አለበት::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/gcue0j
የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ለሁለንተናዊ ገቢ አስተዳደርና አሰባሰብ

ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅርንጫፍ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ቅንጅታዊ ስራ ለሁለንተናዊ የገቢ አስተዳደርና አሰባሰብ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ መንግሥት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖሊትካዊ እድገትን ለማፋጠን ከፍተኛ ኃላፊነት አለበት ጠቅሰው ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መንግሥት የራሱ ገቢ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/xmn6j3
ሁለተኛው የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄያችን ተጀምሯል።
1000623230248
ስራን ማክበር እራስን እንደማክበር ይቆጠራል

ግንቦት 07/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ለባለሙያዎች በሥነ-ምግባር እና ሙስና እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ እና በስብእና ግንባታ ዙሪያ የማነቃቂያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/unqzak