Ministry of Revenues of Ethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር
25.7K subscribers
3.86K photos
93 videos
13 files
674 links
የገቢዎች ሚኒስቴር ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ እንዲሰበስብ ኃላፊነት የተሰጠው የፌዴራል ተቋም ነው፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን በስሩ ይዞ ተደራጅቷል፡፡
Download Telegram
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤታማ ተግባራት ስለመከናወናቸው ተገለጸ

ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በተቋሙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት መካከል 9,869 አዳዲስ የፌዴራል ግብር ከፋዮች ወደ ታክስ ስርዓት እንዲካተቱ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ገለጹ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://www.facebook.com/photo.php?fbid=745695217734878&set=a.231967245774347&type=3&ref=embed_post
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 11.81 ቢልዮን ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ ተችሏል

ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወነ የኮንትሮባንድ መከላከል ስራ ግምታዊ ዋጋቸው ብር 8.0 ቢሊዮን የሆነ የገቢ ኮንትሮባንድ እና ብር 3.82 ቢሊዮን የወጪ ኮንትሮባንድ በድምሩ ብር 11.81 የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎችና ህገ ወጥ ገንዘብ መያዝ መቻሉ ተግልጿል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://www.facebook.com/ERCA.info/posts/745697464401320?ref=embed_post
የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች በቻይና ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች (AEO) አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ

ግንቦት 01/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

6ተኛው የአለም የጉምሩክ ድርጅት ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች(AEO) አለም አቀፍ ኮንፈረንስ በቻይና፤ ሼንዘን ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮች በኮንፈረንሱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኮንፈረንሱ የ"AEO ፕሮግራሞችን ለአካታች እና ዘላቂ ዓለም አቀፋዊ ንግድ ማዋል" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን እኤአ ከግንቦት 8-10/2024 ይቆያል፡፡ በተጨማሪም ሴቶችን በአለም አቀፍ ንግድ የማብቃት እና ቴክኖሎጂን ለአለም አቀፍ ንግድ ስጋት ስራ አመራር ጥቅም ላይ ማዋልን የተመለከቱ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/56nv42
ተርን ኦቨር ታክስ

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡

ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ

ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም ዓመታዊ የንግድ አንቅስቃሴው ከብር 1 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ሰብስቦ ለሚመለከተው የታክስ መስሪያ ቤት/ሚኒስቴር ገቢ ያደርጋል፡፡
ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው ወይም ድርጅት በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው ሰብስቦ ለሚስቴሩ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ሻጩ ለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡- https://rb.gy/y45jqo
በሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተካሄደው የእውቅና እና ሽልማት መርሃ-ግብር

ግንቦት 02/2016 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅርንጫፋ ጽ/ቤት በ2015በጀት ዓመት ለታክስ ህግ ተገዥ ለሆኑ እንዲሁም የሞጁላር ስልጠና ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሰጠ::


በመርሀ ግብሩ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ እና በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ዘርፋ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ ባስተላለፋት መልዕክት ታክስ የአንድ ሀገር አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ሲሆን እንደ አገር አገራዊ ወጪን በራስ ገቢ ለመሸፈን እየተሰራ ቢሆንም ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ያክል ገቢ እየተሰበሰበ አለመሆኑንን ገልፀዋል::

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡-https://www.facebook.com/ERCA.info/posts/750722443898822?ref=embed_post