"ግብር መክፈል ለመንግስት እና ለህዝብ የመታመን አርበኝነት ነው” - አቶ አስፋው አዶሬ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
ሚያዚያ 16/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ኃላፊው ይህንን ያሉት በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ የህግ ተገዢነትን አፈጻጸም ላሳዩ እና የሞጁላር ስልጠና አጠናቀው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ግብር ከፋዮችም የዕውቅና መርሃ-ግብር በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው አዶሬ በእለቱ እዉቅና እና ሽልማት ለተሰጣቸዉ ግብር ከፋዮች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ ፡- https://shorturl.at/sRAZr

የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከጉምሩክ አስተላላፊዎች ጋር ምክክር አደረገ
ሚያዚያ 16 /2017 ዓ. ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር )
ቅ/ጽ/ቤቱ ከተገልጋዮች ጋር ባደረገው ውይይት የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ ህገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል የማህበረሰቡን ደህንነት መጠበቅና ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ በሚቻልበት ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡ በጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ታየ በዚህ ዙሪያ የሚገጥሙ ችግሮችን መለየትና በቀጣይ በማይደገሙበት ሁኔታ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተገቢ መሆኑን በመናገር ለዚህም የሚረዳ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ሰነድ በቅ/ጽ/ቤቱ የደንበኞች ትምህርት ቡድን አስተባባሪ አቶ ተሰማ አቡየ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንዲህ ያሉ መድረኮች በሁለት ወገን ያሉ ግንኙነቶችን የሚያዳብርና ከውይይት በኋላም የሚገኝበት ግብረ መልስ ገንቢ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በህይወት ከበደ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የስፖርት ቡድኖች በ18ኛው የፌዴራል መስሪያ ቤት ሰራተኞች ስፓርት ለሁሉም ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ
ሚያዚያ 16 /2017 ዓ. ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር )
የመክፈቻ ስነስራዓቱ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፓርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር መክዪ መሐመድ ሰራተኛው ማህበራዊ ግንኙነቱን አጠናክሮ በአዕምሮም በአካልም የተገነባ እንዲሆን ከስፓርታዊ ውድድሮች ጎን ለጎን አንድነትን ወንድማማችነት እየገነባን የምንሄድበት መንገድ በመሆኑ ስፓርታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝነት አለው በማለት ገልፀዋል፡፡
በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሚያዝያ 16 እስከ ግንቦት 14/2017 ዓ,ም በሚካሄደው ስፖርታዊ ውድድር ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ እና በቼዝ ተሳታፊ መሆኑ ታውቋል፡፡
በታደሰ ኢብሳ

የታክስ አይነቶችና የማሳወቂያ ጊዜያት
ሚያዚያ 17/2017 ዓ. ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር )
#ከመቀጠር_የሚገኝ_ገቢን_በሚመለከት
👉ከራስ ገቢ ላይ የሚቀንስ በየ3 ወሩ፣
👉ድርጅቶች በየወሩ፡፡
#ከቤት_ኪራይ_እና_ንግድ_ሥራ_ገቢ_ግብርን_በሚመለከት፤
👉ደረጃ “ሀ” ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30፤
👉ደረጃ “ለ” ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 5/6፤
👉ደረጃ “ሐ” ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30፤
https://shorturl.at/cdjvf
ሚያዚያ 17/2017 ዓ. ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር )
#ከመቀጠር_የሚገኝ_ገቢን_በሚመለከት
👉ከራስ ገቢ ላይ የሚቀንስ በየ3 ወሩ፣
👉ድርጅቶች በየወሩ፡፡
#ከቤት_ኪራይ_እና_ንግድ_ሥራ_ገቢ_ግብርን_በሚመለከት፤
👉ደረጃ “ሀ” ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30፤
👉ደረጃ “ለ” ከሐምሌ 1 እስከ ጳጉሜን 5/6፤
👉ደረጃ “ሐ” ከሐምሌ 1 ቀን እስከ ሐምሌ 30፤
https://shorturl.at/cdjvf